Get Mystery Box with random crypto!

የአንድ ባራያ ወንጀል የቱንም ያህል ቢገዝፍ የአሏህ መሃርታ ከባሪያው ወንጀል የበለጠ ግዙፍ ነው ! | አል አዝካር AL AZKAR



የአንድ ባራያ ወንጀል የቱንም ያህል ቢገዝፍ
የአሏህ መሃርታ ከባሪያው ወንጀል የበለጠ ግዙፍ ነው !
[ ኢብን ረጀብ ]
°
ወዳጄ ከሰራኸው ወንጀል በላይ
በአሏህ ላይ ተስፋ መቁረጥህ
የበለጠ ዋጋ ያስከፍልሃል ፡፡
°
ምክንያቱም ተስፋ መቁረጥ የሚመነጨው
የአሏህን መሃሪነት ከማስተባበል አልያም
የአሏህን መሃሪነት ካለማወቅ ነውና !
°
ለዚህም ነበረ አባታችን ኢብራሂም ( ዐለይሂ ሰላም ) ከሸበቱና ከጃጁ ወዲያ መላዕክቶች በልጅ ሲያበስሯቸው ...
" قَالَ أَبَشَّرْتُمُونِى عَلَىٰٓ أَن مَّسَّنِىَ ٱلْكِبَرُ فَبِمَ تُبَشِّرُونَ "
« እርጅና የደረሰብኝ ከመኾኔ ጋር አበሰራችሁኝን በምን ታበስሩኛላችሁ » አለ ፡፡
[ ሱረቱል ሂጅር 54 ]

የዚህኔ መላዒካዎችም ቀበል አደረጉና
" قَالُوا۟ بَشَّرْنَٰكَ بِٱلْحَقِّ فَلَا تَكُن مِّنَ ٱلْقَٰنِطِينَ "
« በእውነት አበሰርንህ ፡፡ ከተሰፋ ቆራጮችም አትኹን » አሉ ፡፡
[ ሱረቱል ሂጅር 55 ]
ከዚያም ደጉ አባታችን ኢብራሂም ( ዐለይሂ ሰላምም ) መለስ አሉና ....

" قَالَ وَمَن يَقْنَطُ مِن رَّحْمَةِ رَبِّهِۦٓ إِلَّا #ٱلضَّآلُّونَ "
« #ከጠማማዎችም በስተቀር ከጌታው እዝነት ተስፋን የሚቆርጥ ማነው» አለ ፡፡
°
ተመለከታችሁ ....?
አባታችን ኢብራሂም ( ዐለይሂ ሰላም ) ተስፋ የሚቆርጥ አካል " መንገድ የሳተ ጠማማ ነው " እያሉን ነው ፡፡ ምክንያቱም ይህ አካል የአሏህን ትክክለኛ ማንነትን ( መሃሪነትን ) አላወቀምና ፡፡ የአሏህን ማንነት ያላወቀና አውቆም ያላመነ " መንገድ የሳተ " ይባላል !
°
እናም ............. ተስፋ አትቁረጡ !!
..