Get Mystery Box with random crypto!

Seyoum Teshome

የቴሌግራም ቻናል አርማ realseyoum — Seyoum Teshome S
የቴሌግራም ቻናል አርማ realseyoum — Seyoum Teshome
የሰርጥ አድራሻ: @realseyoum
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.99K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የስዩም ተሾመ ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ነው🇪🇹

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-04-22 21:48:50 ይሄ ያራዳ ልጅ በቀጣዩ እሁድ ወንጪ ሃይቅን እንጎብኝ እያለ ነው! ለበለጠ መረጃ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ! አሁኑኑ ይመዝገቡ
https://utentic.app/trip/d56285d0-615d-43ef-b0c2-fa151212a7c6
4.6K viewsSeyoum Teshome, 18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 18:07:26 ሱዳኖች የኢትዮጵያን መሬት የያዙት ሀገራችን አጣብቂኝ ውስጥ መግባቷን አውቀውና ጠብቀው ነው። በአንፃሩ ሱዳን አጣብቂኝ ውስጥ በገባችበት ወቅት የተወሰደብንን መሬት የማንስመልስበት ምክንያት ምንድነው? እነሱ ሰላምና መረጋጋት ውስጥ ከገቡ በኋላ በሃይል የያዙትን የኢትዮጵያ ግዛት ይመልሳሉ ብሎ መጠበቅ የዋህነት አሊያም ጅልነት ነው። ችግር ላይ ባሉበት ወቅት የሱዳንን ሉዓላዊ ግዛት መያዝ ተገቢ አይደለም። ነገር ግን ችግር ላይ መሆናችንን አውቀው የያዙትን የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ማስመለስ ግን መብትና ተገቢ ነው። በእርግጥ ሃሳቤ ምክንያታዊ ቢሆንም ቀናነት የጎደለው ሊመስል ይችላል። ይሁን እንጂ እነሱም ቀናነት ቢኖራቸው ኖሮ ኢትዮጵያ ራሷን መከላከል የማትችልበትን አጋጣሚ ጠብቀው፣ ከቅርብና ከሩቅ ጠላቶቻችን ጋር ተመሳጥረው መሬታችንን አይዙም ነበር። ከያዙ ደግሞ አሁን ያለውን አጋጣሚ በመጠቀም መሬታችንን ማስመለስ ይኖርብናል። ይህን አለማድረግ ግን ከጅልነት አልፎ እንደ ክህደት ይቆጠራል!


6.5K viewsSeyoum Teshome, 15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 20:04:31
የዐቃቤ ሕጉ ሹሙ የቅርብ ቤተሰብ የሆኑት አቶ ፍቅረ ሥላሴን ፖሊስ ሀሙስ ሚያዝያ 5 ቀን 2015 ዓ/ም ፖሊስ በሙስና ጠርጥሪያቸዋለሁ በሚል በቁጥጥር ሥር እንዳዋላቸው ማረጋገጥ ተችሏል። እንደ ታማኝ ምንጮቻችን ጥቆማ ከሆነ በሙስና (በሌብነት) የተጠረጠሩት የዐቃቤ ሕግ ሹሙ አቶ ፍቃዱ፤ የባለቤታቸውን ወንድም ለማስፈታት ከፍተኛ ገንዘብ ለመክፈል ያደረጉት ሙከራና የድርድር ጥረት ያልተሳካ መሆኑን ገልጸው፤ ከፍተኛ ባለሥልጣኑም በቅርቡ ከሓላፊነታቸው እንደሚነሱና በቁጥጥር ሥር ውለው ለሕግ እንደሚቀርቡ አረጋግጠዋል።

ፍትህ ሚኒስቴር ሐሙስ ዕለት ባወጣው መግለጫ ከምርጫ ጋር በተያያዘ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ለሙስና መጋለጡንና በዚህ ድርጊት ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ ሓላፊዎችና ግለሰቦች በቅርቡ ተጠያቂ እንደሚሆኑ መግለጹ አይዘነጋም።

6.1K viewsSeyoum Teshome, 17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 22:35:33 አምና እና ካቻምና ብለነው ብለነው የተውነው ነገር ዘንድሮ ለምን የግጭት መንስኤ እንደሆነ አልገባኝም።

6.5K viewsSeyoum Teshome, 19:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 20:24:50 ከረጅም ፅሞና በኋላ እንሆ ተመልሰን መጥተናል! እንዴት ከረማችሁ?

11.9K viewsSeyoum Teshome, 17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 22:59:19
ደህንነቴ አሳስቧችሁ ደጋግማችሁ ለጠየቃችሁ ወዳጆቼ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ከሚዲያ ላይ የጠፋሁት መፅሐፍ እየፃፍኩ ስለሆነ ነው። እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ በቅርብ ቀን ጨርሼ ወደ ሚዲያ እመለሳለሁ!
6.4K viewsSeyoum Teshome, 19:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 18:02:56
እጅግ ቅንና መልካም የሆነችው እህቴ Hani Konjo ተወልጄ ባደኩበትና ክርስትና ለተነሳሁበት የአቦ ቤተክርስቲያን ማሰሪያ ይሆን ዘንድ በልጄ እሸቴ ስም 10,000.00 ብር ድጋፍ አድርጋለች። በእግዚአብሔር እና በልጄ ስም እጅግ በጣም አመሰግናለሁ።

እስካሁን ድረስ ለቤተክርስቲያኑ ማሰሪያ 330ሺህ ብር ተሰብስቧል። ከዚህ ውስጥ 300ሺህ ብሩ ወጪ ሆኖ በቀጣዩ ማክሰኞ መጋቢት 5 በሚከበረው የንግስ በዓል ላይ ርክክብ ይደረጋል። በተመሣሣይ በቀጣይ ስድስት ወራት የሚሰበሰበው ገንዘብ ደግሞ ጥቅምት 5 ለሚከበረው ንግስ በዓል ላይ ርክክብ እንደሚደረግ ለማሳወቅ እንወዳለን።

በዚህ የተቀደሰ ተግባር መሳተፍ የምትሹ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000521800918 ድጋፍ በማድረግ፣ እንዲሁም መልዕክቱን ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ በማጋራት የበረከቱ ተቋዳሽ መሆን ትችላላችሁ
4.3K viewsSeyoum Teshome, 15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 21:48:15
ለመቄዶንያ የሚሰበሰበውን ድጋፍ $2 ሚሊዮን ዶላር ለማድረስ የቀረው ጥቂት ነው። እስኪ በቀጥታ ድጋፍ በማድረግ እና መረጃውን ለወዳጅ ዘመድ በማድረስ ዛሬውኑ $2,000,000 ዶላር እናድርሰው? https://gofund.me/216b39ce
5.8K viewsSeyoum Teshome, 18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 23:05:22
በሁለተኛው ዙር $2,000,000 ዶላር ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን ከዚህ ውስጥ $1,515,120 ዶላር (75%) መሰብሰብ ተችሏል። ቀናነት ካለ የማይችል ነገር የለም #መቄዶንያ https://gofund.me/216b39ce
5.7K viewsSeyoum Teshome, 20:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 20:41:44
ለመቄዶንያ $1.4 ሚሊዮን ዶላር በመሰብሰብ መጀመሪያ ላይ የተቀመጠውን $1,000,000 ዶላር ግብ አሳክቷል። አሁን ላይ ግባችን ወደ $2,000,000 ዶላር ከፍ ብሏል። በመጀመሪያው ዙር ያረጋገጥነው ነገር የመቄዶንያን መልካም ሥራና ተግባር የሚደግፉ እልፍ ኢትዮጵያዊያን መኖራቸውን ነው። በዚህ በጎ ምግባር ለመሳተፍ ያላቸውን ተነሳሽነት ከገመትነው በላይ ነው። በመሆኑም በሁለተኛው ዙር የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ከእኛ የሚጠበቀው በዚህ በጎ ምግባር እንዲሳተፉ ማስታወስ ብቻ ነው። #መቄዶንያ
http://gofund.me/216b39ce
7.2K viewsSeyoum Teshome, 17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ