Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም እና አባባል

የቴሌግራም ቻናል አርማ poemandquote — ግጥም እና አባባል
የቴሌግራም ቻናል አርማ poemandquote — ግጥም እና አባባል
የሰርጥ አድራሻ: @poemandquote
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.47K
የሰርጥ መግለጫ

╭─┅─┅──┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅─╮
እንኳን
:¨·.·¨: ወደ
`·.🇪🇹ግጥም እና አባባል ቻናል መጡ
╰─┅─┅──┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅─╯
━ ━━━━━━•●✠ተ✠●•━━━━━━ ━
「❝ ዓለሙን፡ሁሉ፡ቢገዛ
ነፍሱን፡ግን፡ቢያጠፋ
ለሰው፡ምን፡ይጠቅመዋል?
ሰው፡ለነፍሱ፡ቤዛ፡ምን፡ይሰጣል? ❞」
━ ━━━━━━•●✠ተ✠●•━━━━━━ ━
ማር ፰፥፴፮።

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-24 05:59:00 ረቡዕ ነሐሴ ፲፰ ፳፻፲፬ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━


ሀገሬ ላይ ሆኜ
ሀገሬ ላይ ሆኜ ፥ ናፈቀኝ ሀገሬ
ከማን ጋር ይኖራል? ፥ ሁሉም ሆኗል አውሬ።

ለከፋው ወገኔ ለተፈናቀለዉ ፥ ፀሐይ እስኪወጣ
አምላክ "በቃው" በለው ፥ የባሰ እንዳይመጣ።

የማይበሉት እህል ፥ ከአፈር እኩል ነው
የማይበላ እህል ፥ ከአፈር እኩል ነው
ኢትዮጵያ ሀገሬ ፥ ትንሳኤሽ ቅርብ ነው።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
​​
ምንጭ ➸ መሰንቆ
ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
651 viewsመከበር, 02:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 06:00:01 ማክሰኞ ነሐሴ ፲፯ ፳፻፲፬ ዓ.ም
╭─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╮
「❝ ዶፍ፡ያሳለፈ
ለካፊያ፡አይጨነቅም። ❞」
╰─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╯



ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
732 viewsመከበር, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 06:00:01 ሰኞ ነሐሴ ፲፮ ፳፻፲፬ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━


መልክሽ ፥ ከመልኮች ይልቃል
አቅጣጫ ነው እንጂ
ውበት እንዳልሆነ ፥ አሳምሮ ያውቃል
የጠፋበትን ቦታ
እንደሚጠቁም ካርታ
ግራ ሲገባኝ አካሄዴ
ሲፋለስብኝ መንገዴ
መልክሽን ፥ አምጡ ስል
ግልፅ ነው ፥ የዕድሌ ምስል
ወደፍቅር መንገድ
ወደናፍቆት መንገድ
ወደራስሽ መንገድ ፥ ወደራሴ መውደድ።

መንገዴን ፥ መልክሽ መራኝ
መች እመለሳለሁ ፥ ሞት እንኳን ቢጠራኝ
አልቆጥርም እርምጃ
በአንቺ የሄድኩትንም ፥ አላውቀውም እንጃ
መንገድን ፍለጋ ፥ የሚኳትን ከንቱ
አላደረግሽኝም እቱ
ቆሜያለሁ ከአውደምህረቱ
ደርሻለሁ ፥ ከህይወት ሰገነት
ወደው የሄዱት መንገድ ፥ በምን ያንሳል ከገነት።

​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
ኤልያስ ሽታኹን
╰══•••┈ ርእስ የለውም
┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
፳፻፲፫ ዓ.ም

ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
814 viewsመከበር, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 03:00:00 ሰኞ ነሐሴ ፲፮ ፳፻፲፬ ዓ.ም
╭─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╮
「❝ አምላክ
ከንጉሥ፡ሔሮድስ፡ሴት፡ልጅ
ቢወለድ፡ኖሮ
አልጋ፡ወራሽ፡በሆነና
ባልተሰደደ፡ነበር።
እርሱ፡ግን
የድሆች፡ልጅ፡የሆነችውን
ድንግል፡መረጠ።
ሔሮድስ፡የማይያዘውን
ይይዝ፡ዘንድ፡ተነሣ፣
ዓውሎ፡ነፋስንም
በቤቱ፡አስገብቶ፡ሊዘጋ፡ታገለ። ❞」
╰─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╯
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ምንጭ ➸ የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች
ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
702 viewsመከበር, 00:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 07:00:01 እሁድ ነሐሴ ፲፭ ፳፻፲፬ ዓ.ም
╭─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╮
「❝ በእርሱ፡ፊት
ንጹሕ፡ነኝ፡አትበል።
በንጉሥ፡ፊትም
ብልህ፡ነኝ፡አትበል፤
የብልሃት፡ሥራ
ሠርተህ፡አሳየኝ
ያለህ፡እንደ፡ሆነ
ታፍራለህና። ❞」
╰─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╯

ኅሩይ ወልደ ሥላሴ
ለልጅ ምክር ለአባት መታሰቢያ
፲፱፻፲ ዓ.ም

ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
794 viewsመከበር, 04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 07:00:01 እሁድ ነሐሴ ፲፭ ፳፻፲፬ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#ጥላ

በበርሃ ይሄድ የነበረ ሰው ወደ ኋላው ዞሮ ሲያይ ከእርሱ ሌላ አንድ ጥላ ይመለከታል፤ የዚህም ጥላ ነገር አሳስቦት የማን እንደ ሆነ ያመለክተው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። እግዚአብሔርም "ከኋላህ የተመለከትከው ጥላ የእኔ ነው፤ አንተን እየጠበኩህ እንደሆነ ታውቅ ዘንድ ይህን ምልክት አሳየውህ" አለው።

ያም ሰው ፈጣሪው ከእርሱ ጋር እንዳለ በመስማቱ እጅግ ደስ እያለው ጉዞውን ቀጠለ፤ ጥቂትም እንደተጓዘ ወጣ ገባ የሆነ በጣም አስቸጋሪ መንገድ አጋጠመው፤ ሰውየውም ያን አስቸጋሪ መንገድ እንደ ምንም ብሎ ለመውጣት ታገለ፤ በትግሉ መካከል ግን ወደ ኋላው ዞር ብሎ ቢመለከት እንደ ቀድሞው ሁለት ጥላዎች ሳይሆን አንድ ጥላ ብቻ ቀርቶ ታየው።

ከዚያ ፈታኝ መንገድ እንደ ምንም ብሎ ከወጣ በኋላም፣ በታላቅ ኃዘን ሆኖ እየተበሳጨ ፈጣሪውን እንዲህ ሲል ጠየቀው "ምንም ችግር ባልገጠመኝ በሰላሙ ጊዜ 'ከአንተ ጋር ነኝ' ስትል ጥላህን አሳየኸኝ፣ የአንተ እርዳታ በሚያስፈልገኝ ጊዜ ግን ራስህን ሰወርክብኝ፤ ይከተለኝ የነበረውን ጥላም ዘወር ብዬ ባየው አጣኹት፤ ለምን ተውከኝ?"
እግዚአብሔርም "በመከራህ ጊዜ ጥላዬን ያጣኸው ትቼህ እኮ አይደለም፤ ተሸክሜህ ነው!" ብሎ መለሰለት።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ዲያቆን አቤል ካሳሁን


ምንጭ ➸ ተዋሕዶ
ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
749 viewsመከበር, 04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 06:00:04 እሁድ ነሐሴ ፲፭ ፳፻፲፬ ዓ.ም
╭─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╮
「❝ መካሪ፡አያስፈልገኝም
የማለትን፡ያህል
ታላቅ፡ትዕቢት፡የለም። ❞」
╰─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╯
ቅዱስ ባስልዮስ



ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ምንጭ ➸ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
እንወቃት እንኑራት
ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
691 viewsመከበር, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 09:00:05 ቅዳሜ ነሐሴ ፲፬ ፳፻፲፬ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#የሐዘን_እንጉርጉሮ_ከያዙ_ቅንጫቢ_ኢትዮጵያዊ_ቅኔዎች


"ትግራይ" አይደለም ወይ ፥ መለስ አገርህ፣
"አክሱም" አይደለም ወይ ፥ መለስ ትውልድህ፣
የጁ ነው በማለት ፥ የደበደቡህ፡፡

"መለስ ዜናዊ" ፥ ታላቅ መስፍን፣
ነበሩ ሲሉ ፥ ባገራችን፣
እንዲያ ሳያጡ ፥ ሰገነት፣
ምነው አደሩ ፥ ፈረስ ቤት፣
ሞከሩት እንጂ ፥ አልኖሩም፣
ከዳሞት ፥ አልቀሩም፡፡
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
​​

ምንጭ ➸ ዘጦቢያ
ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
827 viewsመከበር, 06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 06:00:01 አርብ ነሐሴ ፲፫ ፳፻፲፬ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#ሰው_ለሰው

ሆድ ሆድን ሲብሰው ፥ ሆድ በሆድ ሲከፋ
ቀኑ ዘንበል ሲል ፥ ዘንበል ሲል ደፋ
የሰው ልጅ ለሰው ልጅ ፥ ነው አለኝታ ተስፋ

ጠጋኝ ድጋፍ ሰጪ ፥ ወገን አጋር ሲሻ
ቅስሙ ስብር ሲል ፥ አለሁ ባይ ወጌሻ
ከሕይወት ውዝግብ ፥ ከውጣ ውረዱ
ከማጣት ከማግኘት ፥ ከመጥላት መውደዱ
ከትርምስ ኑሮው ፥ ንፋስ ከሚንጠው
በማዕበል እንግልት ፥ ከሚብጠለጠለው
ጥግ ከለላ ሆኖ ፥ ትንፋሽ የሚያስጥለው
ማረፊያ ወደቡ ለሰው ልጅ ፥ ያው ሰው ነው።

አቋራጭ ሲፈትሽ ፥ ኑሮን ለማሸነፍ
ጠጠር ቋጥኝ ሆኖ ፥ ከእግሩ ሥር ሲወተፍ
ማፍቀር መውደድ ሲሻ ፥ ተፈቅሮ ተወዶ
ከአፍቃሪ ከወዳጅ ፥ ሲደርስ የጥል መርዶ
ቀኑ ጭልም ሲል ፥ ፀሐይ በጧት ወጥታ
ሊስም የቀረበ ፥ በጥፊ ሲመታ
ልብን ሲቃ ይዟት ፥ ዓይን እንባ ሲያዘራ
ከሰው ወዲያ ለሰው ፥ ማን አለ እሚራራ?

ማን አለው ለሰው ልጅ ፥ ከሰው ወዲያ ለሰው
በሀዘን በደስታ ፥ በሁሉ ሚደርሰው
ሲስቅ አብሮት ስቆ ፥ አንባ አባሹ ለሰው
ነው ውሉ ሰው ለሰው ፥ ሰው ከሰው
ሰው በሰው ፥ አቻ አጋርም የለው
ከሰው ወዲያ ለሰው።

ሰው ለሰው ነው ጌጡ ፥
ሰው ለሰው ነው ክብሩ
ሰው ለሰው ነው ተስፋው ፥
ሰው ለሰው ነው ፍቅሩ
የኑሮው ዋስትና ፥ ዋልታና ማገሩ።

​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
ትዕግስት ህሩይ
╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈


ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
907 viewsመከበር, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 05:59:00 አርብ ነሐሴ ፲፫ ፳፻፲፬ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#ተዓምር_አይደለም ?

ፍቅር እንደሸቀጥ
ገበያ ከዋለ ፥ ሲለካ ሲሰፈር
ስንት ገባ ገላ?? ፥ ስንት ገባ ከንፈር?
የገላ ተመኑ
የከንፈር ተመኑ
የናፍቆት ተመኑ
እንደየጊዜው ነው ፥ እንደየዘመኑ፡፡
(አሉ ነጋዴዎች)

ሲሸቀጥ ሲነገድ ፥ ፍቅር ጉልት ዋለ
ከራሱ ቀይ ደም ፥ እንጨት ላይ ተሳለ!
ተዘባበቱበት
ያን ሁሉ ዓለንጋ ፥ መቻሉ ረሱ።
"እስቲ ይውረድ" አሉ ፥ ከመስቀል በራሱ
እስቲ ተዓምር አድርግ? ፥ ይሉታል በዓለም
በታናሽ መገረፍ ፥ ተዓምር አየደለም?

ድንቅን አድርግ ይሉታል ፥ አይፈሩምና ጡር
ተዓምር አይደለም? ፥ መቸንከር በፍጡር?
ልፍስፍስ ነው አሉት
ደካማ ነው አሉት
ወከባ ነው አሉት ፥ አይችልም ማስገረም
እናትን እያዩ...
መመታት በራሱ ፥ ተዓምር አይደለም?

ተዘባበቱበት
ገላ ስንት ገባ? ፥ እንደራቆተ ዋለ ባደባባይ
ምድርን ያለበሰ ፥ በደመና ሰማይ።
ከንፈር ስንት ገባ? ፥ ተጠምቶ አደረ
ውኃ ለሁለት ከፍሎ ፥ እንዳላሻገረ፡፡
ማቀፍ ስንት ገባ ?
መሳም ስንት ገባ ?
ዋጋው ተወደደ ፥ ወይስ ቀዘቀዘ
ዓለምን የያዘ ፥ በዓለም ተያዘ፡፡
(ነፍስ ይማር ፍቅር)

​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
ኤልያስ ሽታኹን
╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈


ምንጭ ➸ @getnetsi
ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
769 viewsመከበር, 02:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ