Get Mystery Box with random crypto!

ሰኞ ነሐሴ ፲፮ ፳፻፲፬ ዓ.ም ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ | ግጥም እና አባባል

ሰኞ ነሐሴ ፲፮ ፳፻፲፬ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━


መልክሽ ፥ ከመልኮች ይልቃል
አቅጣጫ ነው እንጂ
ውበት እንዳልሆነ ፥ አሳምሮ ያውቃል
የጠፋበትን ቦታ
እንደሚጠቁም ካርታ
ግራ ሲገባኝ አካሄዴ
ሲፋለስብኝ መንገዴ
መልክሽን ፥ አምጡ ስል
ግልፅ ነው ፥ የዕድሌ ምስል
ወደፍቅር መንገድ
ወደናፍቆት መንገድ
ወደራስሽ መንገድ ፥ ወደራሴ መውደድ።

መንገዴን ፥ መልክሽ መራኝ
መች እመለሳለሁ ፥ ሞት እንኳን ቢጠራኝ
አልቆጥርም እርምጃ
በአንቺ የሄድኩትንም ፥ አላውቀውም እንጃ
መንገድን ፍለጋ ፥ የሚኳትን ከንቱ
አላደረግሽኝም እቱ
ቆሜያለሁ ከአውደምህረቱ
ደርሻለሁ ፥ ከህይወት ሰገነት
ወደው የሄዱት መንገድ ፥ በምን ያንሳል ከገነት።

​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
ኤልያስ ሽታኹን
╰══•••┈ ርእስ የለውም
┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
፳፻፲፫ ዓ.ም

ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛