Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም እና አባባል

የቴሌግራም ቻናል አርማ poemandquote — ግጥም እና አባባል
የቴሌግራም ቻናል አርማ poemandquote — ግጥም እና አባባል
የሰርጥ አድራሻ: @poemandquote
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.47K
የሰርጥ መግለጫ

╭─┅─┅──┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅─╮
እንኳን
:¨·.·¨: ወደ
`·.🇪🇹ግጥም እና አባባል ቻናል መጡ
╰─┅─┅──┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅─╯
━ ━━━━━━•●✠ተ✠●•━━━━━━ ━
「❝ ዓለሙን፡ሁሉ፡ቢገዛ
ነፍሱን፡ግን፡ቢያጠፋ
ለሰው፡ምን፡ይጠቅመዋል?
ሰው፡ለነፍሱ፡ቤዛ፡ምን፡ይሰጣል? ❞」
━ ━━━━━━•●✠ተ✠●•━━━━━━ ━
ማር ፰፥፴፮።

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-02 08:30:00 አርብ ነሐሴ ፳፯ ፳፻፲፬ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#የግፈኞች_ፍርድ

ባራዊት መካከል ፥ በሽታ ተነስቶ
ሁሉም ተጨነቁ ፥ ሕመምተኛው በዝቶ
ሳይበሉ ሳይጠጡ ፥ ብዙ ቀን ሆናቸው
ሲወድቁ ሲነሡ ፥ ሕመም ተጭኗቸው
ከሁሉም ኀይለኛው አንበሳ ፥ እንደዚህ ሲል
ጮኾ ተናገረ ፥ ቆመና መካከል
ታሪኩ እንደሚለን ፥ ጥንትም የእግዜር ቁጣ
ተልኮ ለቅጣት ፥ ባለም ላይ ሲመጣ
ዕጣ በመጣጣል ፥ ወይም በኑዛዜ
ዐመፅ የሠራ ሰው ፥ በተገኘ ጊዜ
ፍርዱን ተቀብሎ ፥ ባመፁ ሲቀጣ
ካለም ላይ ይጠፋል ፥ የወረደው ቁጣ።

ስለዚህ አሁንም ፥ በኛ ላይ መቅሠፍቱ
በኀጥአት ነው እንጂ ፥ አልመጣም በከንቱ
ከመካከላችን ክፉ ፥ ዐመፅ የሠራ
አይጠፋም እንፈልግ ፥ እናድርግ ምርመራ።
ክፉ ሥራችንን ፥ አንድ እንኳ ሳይቀር
ከራሴ ዠምሬ ፥ ሁሉን ልናገር።
ሁል ጊዜ ሲርበኝ ፥ የምበላው ሳጣ
በጉን ከነረኛው ፥ ጠብቄ ሲመጣ
ሥጋውን በልቼ ፥ ደሙን የምጠጣ
እንዲያ ሲጨነቁ ፥ የጨከንኩባቸው
አይቀርም ይደርሳል ፥ ከእግዜር ፊት ደማቸው
ይሄ ሁሉ ግፍ ነው ፥ መቅሠፍት የሚያመጣ
ምንም ቅር አይለም ፥ በፍርድ ብቀጣ።
እናንተም እንደ እኔ ፥ ሳትዋሹ ሳትፈሩ
ያጠፋችሁትን ፥ እስቲ ተናገሩ።
ቀበሮ መለሰች ፥ እንደዚህ ስትል
እርስዎ የሠሩትን ፥ ተመልካች ሲያስተውል
በጉን ከነረኛው ፥ ተርበው ቢበሉ
ኀጥያቱስ የት አለ ፥ ምንድነው በደሉ ?
ይልቅስ ተርበው ፥ እርስዎ ሲበሏቸው
ለበጉም ለረኛው ፥ ትልቅ ነው ክብራቸው።
ዝኆንና ነብር ፥ ዥብና አውራሪሥ
ቀጥለው በተራ ፥ ያጠፉትን ነብስ
ያፈሰሱትን ደም ፥ አንድም ሳይደብቁ
ይህንን ሠርተናል ፥ ብለው አስታወቁ።
ግን ካደባባዩ ፥ የነበሩት ሁሉ
ፈርተው በሚገባ ፥ መፍረድ ስላልቻሉ
ጥፋታችሁ ፥ በጣም ቀላል ነው እያሉ
ምንም ሳይወቅሷቸው ፥ እንኳንስ ሊቀጡ
ቀላል ነው አሏቸው ፥ ሁሉም ነጻ ወጡ።
አህያ ብቅ አለች ፥ ከሁሉም በኋላ
ትናዘዝ ዠመረ ፥ እሷም እንዲህ ብላ
አንድ ቀን ተጭኜ ፥ ደክሞኝ ስንገላታ
ጌታዬ ሲነዳኝ ፥ በዱላ እየመታ
ግጦሽ ሣር አይቼ ፥ የሚያምር በመስኩ
አንድ ጒርሻ በላሁ ፥ ሌላም አልደገምኩ
ርግጥ ነው ዐውቃለሁ ፥ መሆኑን የሌላ
ግን ሰይጣን ገፋፋኝ ፥ ሰርቄ እንድበላ።

ይሄንን ሲሰሙ ፥ ሁሉም በአንድነት
የስድብ የርግማን ፥ የቁጣ መዓት
እያከታተሉ አወረዱባት።
ቀበሮም ተነሥታ ፥ ያላንዳች ምሕረት
አንች አመዳም ርጉም ፥ እከካም ፍጥረት
ለካ ባንቺ ጦስ ነው ፥ ይህንን በሽታ
በሁላችንም ላይ ፥ ያመጣብን ጌታ።
እንዴት ትደፍሪያለሽ ፥ የሰው ሣር ለመብላት
ሞት ነው ሌላም አይደል ፥ የሚገባሽ ቅጣት
ብላ በሁሉም ስም ፥ ጨረሰች ተናግራ
ፍርዱም በዚህ ቆመ ፥ አለቀ ምርመራ።
እዚያ የነበሩት ፥ የምድር አራዊት
አዎን አዎን ብለው ፥ ይገባታል ሞት
ምስኪኗን አህያ ፥ ተከፋፈሏት።

እውን የሷ ዐመፅ ነው ፥ የፈጣሪን ቁጣ
ባራዊት ሁሉ ላይ ፥ ጎትቶ ያመጣ ?
ከተናዘዙትስ ፥ካራዊቶች ውስጥ
የሷ ዓመፅ ኗሯል ፥ ወይ በእውነት የሚበልጥ ?
ያም ሆነ ያም ሆነ ፥ አልዳነችም እሷ
ትቀጫለሽ አሏት ፥ በሥጋ በነፍሷ።

እንሆ ባለም ላይ ፥ በዳኝነት ሥራ
ጉባኤ ተደርጎ ፥ ሲጨረስ ምርመራ
ፍጻሜው እንዲህ ነው ፥ ስናየው በውነቱ
መሥዋዕት እየሆነ ፥ ደካማ ለብርቱ
ያልታደለው ደኻ ፥ ይጠፋል በከንቱ ።

​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
ከበደ ሚካኤል
╰══•••┈ የቅኔ ውበት
┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
፲፱፻፺፬ ዓ.ም

ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
67 viewsመከበር, 05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 06:00:03 አርብ ነሐሴ ፳፯ ፳፻፲፬ ዓ.ም
╭─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╮
「❝ ጀግናና፡ሚስማር
ሲመቱት
ይጠብቃል፡እንጂ፡አይላላም። ❞」
╰─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╯



ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
140 viewsመከበር, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 17:00:02 ኀሙስ ነሐሴ ፳፮ ፳፻፲፬ ዓ.ም
╭─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╮
「❝ ፍቅር
ፍፁም፡ዲሞክራሲ
በሆነ፡መንገድ፡የሚመረጥ
አምባገነን፡መሪ፡ነው። ❞」
╰─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╯



ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
340 viewsመከበር, 14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 08:30:00 ኀሙስ ነሐሴ ፳፮ ፳፻፲፬ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#መኖር_ኋላ_ቀረ_ሞት_እየዘመነ
#በአፍሪካ_መሬት_ላይ
#ክስተት_ያሉት_ሁሉ_ክፍተት_እየሆነ

በመርከብ አናት ላይ
የሚኖር ባንዲራ ፥ መኖሩ እንዲወሳ
ንፋስን ያስሳል
እርሱ እንዲውለበለብ ፥ መርከብ እየረሳ።
ውኃ ላይ እያሉ...
ለመውለብለብ ብቻ
ንፋስን መለመን ፥ ንፋስን ማባበል
መጣራት ምዕበል !
ውኃ ላይ ያለ ነፍስ
አይጠይቅም ንፋስ ፥ ለመታየት ብሎ
መታየት ይመጣል ፥ ከመኖር ቀጥሎ።
ይልቅ...
ዓላማህ እንዲታይ ፥ በዓለም ተረጋግቶ
የእኔና የአንተን ጀልባ
ማጋጠም እንያዝ ፥ መጋጠሙን ትቶ።
ያኔ...
ጻማ ቢሆን ቀኑ
አብረን እስከሆንን ፥ ንፋስ ቢንቀለቀል
የአመንከውን ሰንደቅ
እንኳን ጀልባዬ ላይ ፥ ጀርባዬም ላይ ስቀል።


በገጠምነው መርከብ ፥ ቢታገል ማዕበል
አንጋደደን እንጂ ፥ ገደለን አንበል።
ዳሩ እኔና አንተ
የባህር ላይ ሞቱን ፥ አንድ ላይ ተላልፈን
ምነው በየብሱ ላይ ፥ መቅዘፊያው ተርፈን ?
የመከራ ጊዜ ፥ እንዳላዋደደን
ከውኃው ላይ ቆመን
እመሬት ስንደርስ ፥ ምን አንገዳገደን ?
እንመካከር ዘንድ ፥ መከራ ምንሻ
እንከባበር ዘንድ ፥ ችግር እጅ መንሻ
ሆኖብን ነገሩ ፥ ሁሌ ማያግባባን
ከአሳ ጥርስ አምልጠን ፥ ቢላ ጥርስ የገባን።
እንተራረድ ዘንድ ፥ እጃችን ቀለለው
የገዳይን ትርክት ፥ ዕውቀት እያጀለው
ተዋከብን !
ተዳከምን !
አያውቁት አወቅና...
አይስሉት ሰላና...
ምራቅ መዋጫ እንኳን ፥ ጊዜ የት አለና ?
ኧረ ቀስ...
ኧረ ቀስ...
ኧረ ቀስ...
ኧረ ቀስ...
ኋላ ለመቅበዝበዝ ፥ እግዜርን መቀስቀስ።


ኧረ ሰከን! ፥ ሰከን!
በባከነ ሰዓት ፥ ደግሞ ለመባከን ?
ኧረ ማሰብ! ፥ መንቃት!
አሜን ሳያልቅብን ፥ የአባቶች ምርቃት።
ቅዱስ ፥ ቅድስና
ፍፁም ፥ ፍፅምና
ከቶ የለምና !
ደግሞ አይኖርምና።
እንደው እንኳን ቢያንስ...
ባንቀደስ እንኳን ፥ ባንቀድስ እንኳን
ባንባረክ እንኳን ፥ ባንባርክ እንኳን
ባናላቅስ እንኳን ፥ ባናለቅስም እንኳን
ምን ያሳልቀናል ፥ በእናቶች ድንኳን ?
ኧረ ቀስ...
ኧረ ቀስ...
ኧረ ቀስ ፥ ገመናው አይውጣ
እንችለው ይመስል ፥ እግዜርን እናውጣ ?


የጭካኔ ልኩ ፥ በአጥብቆ ቢጠማን
እንደስማዚያ ፥ ማልን ለእርግማን
የመጥፋት የመግፋት ፥ ለምዶብን ታሪኩ
ደምግባት ጠፍቶብን
ደም ግብዓት ሆነ ፥ የመሠልጠን መልኩ
እንጂ ታውቀው የለ
በቂ ስለት እንጂ ፥ በቂ ሰበብ የለ።
እንጂ ታውቀው የለ
ምን ቢለን ቃሉ
ዓለም ትጠፋለች ፥ ትጠፋለች ዓለም
በትዕቢት ነው እንጂ ፥ በትንቢት አይደለም።
ትንቢት የሚያስቀይር ፥ ትህትና ስላጣን
ሀገራችን ሁሉ
እንዳይጥም አድርጎ ፥ ነገራችን ቀጣን።
መኖር ኋላ ቀረ ፥ ሞት እየዘመነ
በአፍሪካ ሰማይ ሥር...
ክስተት ያሉት ሁሉ ፥ ክፍተት እየሆነ !
ክስተት እና ክፍተት
መለየት ካቃተው ፥ ሕዝብ ይሉት ፍጡር
ራሱን ይመርመር
ቢያንስ ለሁለቱም ፥ እንዳይሆን ደንገጡር።

እንደሰው ሳንስቅ
ዕንባችን የማይቆም ፥ ሞቱን የሚያፈጥነው
መርከብ እየረሱ
ንፋስ ሚለምኑ ፥ ሰንደቆች መብዛት ነው።

ኧረ ቀስ !

​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
ኤልያስ ሽታኹን
╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈


ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
427 viewsመከበር, 05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 06:00:01 ኀሙስ ነሐሴ ፳፮ ፳፻፲፬ ዓ.ም
╭─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╮
「❝ ኢትዮጵያ፡ዳሯ፡እሳት
ማሀሏ፡ገነት።
╰─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╯

አማረ አፈለ ብሻው
የሁለት ሺህ ዓመታት
ውጣ ውረድ በኢትዮጵያ
፲፱፻፺፱ ዓ.ም

ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
422 viewsመከበር, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 17:00:01 ረቡዕ ነሐሴ ፳፭ ፳፻፲፬ ዓ.ም
╭─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╮
「❝ መንደዱ፡ላይቀር
ጭሱ፡ገደለኝ። ❞」
╰─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╯


ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
512 viewsመከበር, 14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:00:11 ረቡዕ ነሐሴ ፳፭ ፳፻፲፬ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#ቀለም_አልባ_ምስል

የሚበር አህያ ፥ ቀንድ ያለው ዝንጀሮ
ሳር የሚግጥ ድመት ፥ የሚራገጥ ዶሮ
እንቁላል ጣይ በሬ ፥ የሚያገሳ ጉንዳን
መልዕክት አድራሽ ቁራ ፥ የሚታዘል ዝሆን
የጃርት ጎረቤት ፥ የሚጥሚጣ ንፍሮ
ቀለም አልባ ምስል ፥ ይህ ነው የኛ ኑሮ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
​​

ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
544 viewsመከበር, 07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 08:30:00 ረቡዕ ነሐሴ ፳፭ ፳፻፲፬ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#ሁለቱ_መላጦች

ሁለት በራ ሰዎች ፥ ሲያልፉ በጎዳና
ዕቃ መሬት ወድቆ ፥ ብልጭ ሲል አዩና
ተሽቀዳድመው ሄደው ፥ ከቦታው ሲደርሱ
ተፎካከሩበት ፥ ሁለቱም ሊያነሱ።
በኋላም ተማተው ፥ በጥፊ በጡጫ
አንደኛው ነጠቀ ፥ በጉልበቱ ብልጫ።
አገላበጠና ፥ ቢመላከት ፈጥኖ
ዕቃውን አገኘው ፥ ማበጠሪያ ሆኖ።
እስኪ ሁላችሁም ፥ በሉ ፍረዱት
እሱ ራሱ በራ ፥ ጠጒር የለበት
ሮጦ ተማቶ ፥ ቀምቶ ቢያመጣ
ምን ያደርግለታል ፥ ሚዶ ለመላጣ ?

ሰዎች ይፋጃሉ ፥ አስበው ሳይፈርዱ
የተጣሉበትን ፥ ጥቅሙን ሳይረዱ
ከመጣላት በፊት ፥ ከመቀያየም
የነገሩን ፍሬ ፥ መረዳት መልካም፡፡

​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
ከበደ ሚካኤል
╰══•••┈ የቅኔ ውበት
┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
፲፱፻፺፬ ዓ.ም

ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
516 viewsመከበር, 05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 06:00:03 ረቡዕ ነሐሴ ፳፭ ፳፻፲፬ ዓ.ም
╭─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╮
「❝ የሰው፡ልጅ
ከመቀበል፡በላይ
መስጠትን፡ካወቀ
የራሱን፡ሰጥቶ
የብዙዎችን፡ያተርፋል። ❞」
╰─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╯


ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
511 viewsመከበር, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:00:04 ማክሰኞ ነሐሴ ፳፬ ፳፻፲፬ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━


ምሽቴን ማን ተኝቷት ?
በሬዬን ማን አርሶት ?
አይሉም አይሉም
ቀን የከፋ ለታ ፥ ይደረጋል ሁሉም።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
​​

ምንጭ ➸ የግጥም አብዮት
ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
606 viewsመከበር, 18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ