Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም እና አባባል

የቴሌግራም ቻናል አርማ poemandquote — ግጥም እና አባባል
የቴሌግራም ቻናል አርማ poemandquote — ግጥም እና አባባል
የሰርጥ አድራሻ: @poemandquote
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.47K
የሰርጥ መግለጫ

╭─┅─┅──┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅─╮
እንኳን
:¨·.·¨: ወደ
`·.🇪🇹ግጥም እና አባባል ቻናል መጡ
╰─┅─┅──┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅─╯
━ ━━━━━━•●✠ተ✠●•━━━━━━ ━
「❝ ዓለሙን፡ሁሉ፡ቢገዛ
ነፍሱን፡ግን፡ቢያጠፋ
ለሰው፡ምን፡ይጠቅመዋል?
ሰው፡ለነፍሱ፡ቤዛ፡ምን፡ይሰጣል? ❞」
━ ━━━━━━•●✠ተ✠●•━━━━━━ ━
ማር ፰፥፴፮።

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-30 07:00:01 ማክሰኞ ነሐሴ ፳፬ ፳፻፲፬ ዓ.ም
╭─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╮
「❝ አንዳንዴ
አልቅሰህ
የማትመልሰውን፡ነገር
እየሳቅህ
መሸኘት፡ልመድ። ❞」
╰─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╯



ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
636 viewsመከበር, 04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 08:30:00 ሰኞ ነሐሴ ፳፫ ፳፻፲፬ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━


ቁንጫና ቱሀን ፥ ፉክክር ገቡና
ያለከልካይ ሰፍረው ፥ ደሜን መጠጡና
በተለይ ቁንጫ ፥ ቱሀን መሆን አምሯት
ሲያዘልል ሲያፈርጣት
ሲያዘልል ሲያፈርጣት
መላ ሰውነቴን ፥ ስትነክስ እንዳሻት
መዥገር ነበር አሉ ፥ ታዛቢና ዳኛ
ግና ምን ያደርጋል ?
መዥገርም እንደዛው
ከደም መጣጭ ተራ ፥ ተሰልፎ ኖሮ
ማን ለማን ይፈርዳል? ፥ ፍርድ የለም ዘንድሮ ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
​​ፍራሽ አዳሽ
ተስፋሁን ከበደ

ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
709 viewsመከበር, 05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 06:00:01 ሰኞ ነሐሴ ፳፫ ፳፻፲፬ ዓ.ም
╭─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╮
「❝ በጋራ፡መሥራት፡እንጅ
በጋራ፡ማሰብ፡አይቻልም፤
ብቻችሁን፡ሁናችሁ፡አስቡ
ሥራ፡ላይ፡ግን፡ተባበሩ። ❞」
╰─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╯
ዓለማየሁ ዋሴ
ሰበዝ


ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
644 viewsመከበር, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 15:00:03 እሁድ ነሐሴ ፳፪ ፳፻፲፬ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#የንጉሡ_እንቆቅልሽ (የንግሥት ፉራ)

ንጉሡ ከሰጣቸው እንቆቅልሾቹ መካከልም "የእናቴን በሕይወት መኖሯን ወይም አለመኖሯን ሳትገልጡ ዜናዋን ላኩልኝ" በማለት በእናቱ አገር ለሚኖሩ ሰዎች ላከባቸው፡፡ እነሱም የሚኖሩት ፉራ በምትኖርበት መንደር ነበር፡፡ የሀገር ሽማግሌዎች የንጉሡ እንቆቅልሽ እንዴት እንደሚፈቱ ተሰብስበው መመካከር ጀመሩ፡፡ ዳሩ ግን "እናትህ ደኅና ናት" እንዳይሉት፡፡ "በሕይወት መኖሯን ገልጻችኋል"፤ "ሞታለች" እንዳይሉትም መሞቷን እንዳትነግሩኝ በማለት ስለከለከላቸው ይቀጣቸዋል፡፡ ስለዚህ ምን መባል እንዳለበት ለማወቅ መረጃ ሲያሰባስቡ ሰነበቱ፡፡

እንደሚባለው ከሆነ ምሥጢሩን ለማወቅ ያላረጉት ጥረት የለም፡፡ በመጨረሻም አንዲት ሕፃን ልጅ በዚህ እንቆቅልሽ መጨነቃቸውን ተረድታ "በሉ እንዲህ አድርጉ፡፡ ጸጉራችሁን በግማሽ ተላጭታችሁ ሂዱና እጅ ነስታችሁ እፊት ለፊቱ ቁሙ፡፡ ካልጠየቃችሁ በስተቀር እንዳትናገሩ፡፡ ሲጠይቃችሁ ግን እንዲህ በሉት" በማለት እንቆቅልሹን በእንቆቅልሽ እንዲመልሱ መከረቻቸው፡፡ ሰዎቹም ከንጉሡ ቤተ መንግሥት እንደደረሱ ለአጋፋሪው የእቆቅልሹን መልስ ይዘው እንደመጡ ገልጠው እንዲያስገባቸው ጠየቁት፡፡ አጋፋሪውም ወደ ንጉሡ ሄዶ የእናቱ አገር ሽማግሌዎች የእንቆቅልሽ መልስ ይዘው መምጣታቸውን ነገረው፡፡

ንጉሡ ፈቅዶላቸው እንደገቡም የራሳቸውን ክንንብ አውርደው እፊቱ ቆሙ፡፡ የራሳቸውንና የጺማቸውን ግማሽ ጎን የተላጩት ያገሩ ሽማግሌዎች ያየው ንጉሥም በሁኔታው በመደነቅ "ምነው እናቴ ምንሆነች?" በማለት ጠየቀ፡፡ የሽማግሌዎቹ መሪም "ምን የርሷ ነገር" አሉና ዝም አለ፡፡ ንጉሡም "ሞተች እንዴ?" ብሎ ሲጠይቅ "ብትሞት ኖሮ ጸጉራችንን እናሳድግ ነበር?" "እና በሕይወት አለች ማለት ነው?" አለ ንጉሡ፡፡እነሱም "በሕይወት ብትኖር እንደዚህ ጸጉራችንን እንላጭ ነበር?" በማለት መለሱ፡፡ በዚህ ጊዜ ንጉሡ እንቆቅልሹ በእንቆቅልሽ መመለሱን በማወቅ ከፍተኛ ድምፅ አሰምቶ
ሳቀና "ከፍተኛ ጠንቋይ ወይም ሽማግሌ መሆን አለበት፡፡ እንዴት ያለ ብልህ ሰው መከራችሁ?" በማለት ጠየቃቸው፡፡ እነሱም ከመጫወት በስተቀር ሌላ ምንም የማታውቅ ሕፃን መሆኗን ነገሩት፡፡ ንጉሡም "ይች ስታድግ አገር የምትመራ ናት" ብሎ ተናገረ፡፡
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ምንጭ ➸ ሪፖርተር
ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
729 viewsመከበር, 12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 08:30:00 እሑድ ነሐሴ ፳፪ ፳፻፲፬ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#የሐዘን_እንጉርጉሮ_ከያዙ_ቅንጫቢ_ኢትዮጵያዊ_ቅኔዎች


ውዳሴ ማርያም ደግሜ
ተቀምጬ አደርሁ ደክሜ፤
በመቁጠሪያዬ ሳንቀላፋ፣
ዋ! መቋሚያዬ ጠፋ፡፡

ከሚበልጠው ከሁሉ፣
ኧረ ተማሩ በሉ፤
እናንተ ሰዎች አስተውሉ፣
ከዳ ከዳ አትበሉ፡፡

መተኪያ እንኳን ሌላ የለኝ፣
ጥላዬ ተሠብሮ አዝናለሁኝ፡፡

ቤት ሥራልኝ ብንለው፣
እንጨት መረጠ አናጢው፤
ሰው ሲያነሣ ሣንቃውን፣
አንተም አትተው ማዘኑን፡፡

ሠሪው ፍጥረቱን አታለለ፣
በኖራ ሠራሁ እያለ፤
መች ይፈርስ ነበር ቤታችን
እውነት ኖራ ቢሆን፡፡

ቀፎ አለ አሉ ባገርህ፣
እረ ተው ማር እባክህ፡፡

መልካም ፈረስ ጭነህ፣
ስትወጣ ስትወርድ አየንህ፤
ከሜዳ ስትደርስ ዝግ አድርገው
መቼም ጊዜው ጣይ ነው፡፡

በምን ይበሏል ባዋዜ፣
ይህንን አልቦ ጊዜ፡፡

ስማኝ ልንገርህ አትስነፍ፣
ተው እየሠራህ እለፍ፡፡

ወደ አደባባይ ወጥተህ፣
ከባላጋራህ ተሟግተህ፣
ክርክር ገጥመህ ወደ ማታ፣
ዓለም አፈር ነው ስትረታ፡፡

እዚያ ላይ ሆነህ ብትጠራኝ፣
አቤት እንዳልል ድምጥ የለኝ፤
ኧረ ! የት ሆኜ ልጠብቅ
መምጫህ አይታወቅ፡፡

'ዋልድባ' ወርጄ ቀስሼ፣
ልብሰ ተክህኖ ለብሼ፣
ታዩኛላችሁ እኔን
ነገ ገብቼ ሣጥን፡፡
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
​​

ምንጭ ➸ ዘጦቢያ
ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
689 viewsመከበር, 05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 06:00:03 እሑድ ነሐሴ ፳፪ ፳፻፲፬ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━


አንድ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ቆመና
"ጌታ ሆይ ተመልከት እጆቼ ንፁሃን ናቸው።
ደም አላፈሰሱም የሰው ገንዘብ አልቀሙም"
አለ። እግዚአብሔርም መለሰለት "ልጄ ሆይ!
አዎ እጆችህ ንፁሃን ናቸው ግን ባዶዎች
ናቸው" አለው ይባላል።

ያልገደለ እጅ ግን ያላዳነ፣ ያልሰረቀ እጅ
ግን ያልመፀወተ በእግዚአብሔር ፊት
ሞገስ የለውም። እውነተኛው መልካምነት
ክፉ አለማድረግ ብቻ ሳይሆን መልካም
ማድረግም ነው። የሚጎዳንን መተው ብቻ
ሳይሆን ስለ ሌሎች ጥቅም መድከምም
ነው።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━

ምንጭ ➸ ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
671 viewsመከበር, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 05:00:01 ቅዳሜ ነሐሴ ፳፩ ፳፻፲፬ ዓ.ም
╭─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╮
「❝ ነገር፡ግን
ባንዱ፡ወገን፡እንቢ፡ቢልህ
በሌላው፡ወገን፡ፈትን ።
ለሥራው፡ሁሉ፡ዕድል፡አለውና
እግዚአብሔር
ድካምህን፡አይቶ
ባንዱ፡ወገን
ሳይረዳህ፡አይቀርም። ❞」
╰─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╯

ኅሩይ ወልደ ሥላሴ
ለልጅ ምክር ለአባት መታሰቢያ
፲፱፻፲ ዓ.ም

ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
333 viewsመከበር, 02:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 05:59:00 አርብ ነሐሴ ፳ ፳፻፲፬ ዓ.ም
╭─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╮
「❝ ልጄ፡ሆይ
ሰልፍ፡ለኀይለኞች
ሩጫም፡ለፈጣኖች
ባለጠግነትም፡ለሠራተኞች
አይደለም።
ነገር፡ግን
ሁሉንም፡ጊዜ፡ያጋጥማቸዋል።
ስለዚህ፡ሰውን፡ከመመልከትና
ሰውን፡ከመጠበቅ
ጊዜን፡መጠበቅ፡ይሻላል። ❞」
╰─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╯

ኅሩይ ወልደ ሥላሴ
ለልጅ ምክር ለአባት መታሰቢያ
፲፱፻፲ ዓ.ም

ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
518 viewsመከበር, 02:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 06:00:01 ኀሙስ ነሐሴ ፲፱ ፳፻፲፬ ዓ.ም
╭─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╮
「❝ እረኛውን፡በለው
ከብቶቹ፡ይበተናሉና። ❞」
╰─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╯
ዓለማየሁ ዋሴ
ሰበዝ


ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
625 viewsመከበር, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 22:00:03 ረቡዕ ነሐሴ ፲፰ ፳፻፲፬ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#አወይ_ጥይት_ማጣት!

እንደ ፀሀይ ንጣት
እንደ ቀለበት ጣት
እንደ እግዜር ቅጣት
እንደ እንትን ማጣት
ትኩረት ያልተሰጣት
አንዲት የዘር ቅንጣት
በየአሜኬላው ፥ በየጭንጫው መሬት
በተጣለች ቁጥር ፥ ስታሰማ ምሬት
እንዳ’ረጀ ምንጣፍ
ከቁብ የማትጣፍ
ወልጋዳ ‘ሚረግጣት
አንዲት የዘር ቅንጣት

እሮሮዋን በልታ
እንባዋን ጠጥታ
መ’ናቅ እያፋፋት
ችጋር እያሰፋት…
ዋርካ ሆና ሲያያት
አጎብድዶ ሊሾም ፥ የቋመጠ መንጋ
የኋሊት አጣምሮ
ዘሯን እየዳጠ ፥ ከስሯ ተጠጋ !

​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
አበረ አያሌው
╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈


ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
613 viewsመከበር, 19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ