Get Mystery Box with random crypto!

እሁድ ነሐሴ ፳፪ ፳፻፲፬ ዓ.ም ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ #የንጉሡ | ግጥም እና አባባል

እሁድ ነሐሴ ፳፪ ፳፻፲፬ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#የንጉሡ_እንቆቅልሽ (የንግሥት ፉራ)

ንጉሡ ከሰጣቸው እንቆቅልሾቹ መካከልም "የእናቴን በሕይወት መኖሯን ወይም አለመኖሯን ሳትገልጡ ዜናዋን ላኩልኝ" በማለት በእናቱ አገር ለሚኖሩ ሰዎች ላከባቸው፡፡ እነሱም የሚኖሩት ፉራ በምትኖርበት መንደር ነበር፡፡ የሀገር ሽማግሌዎች የንጉሡ እንቆቅልሽ እንዴት እንደሚፈቱ ተሰብስበው መመካከር ጀመሩ፡፡ ዳሩ ግን "እናትህ ደኅና ናት" እንዳይሉት፡፡ "በሕይወት መኖሯን ገልጻችኋል"፤ "ሞታለች" እንዳይሉትም መሞቷን እንዳትነግሩኝ በማለት ስለከለከላቸው ይቀጣቸዋል፡፡ ስለዚህ ምን መባል እንዳለበት ለማወቅ መረጃ ሲያሰባስቡ ሰነበቱ፡፡

እንደሚባለው ከሆነ ምሥጢሩን ለማወቅ ያላረጉት ጥረት የለም፡፡ በመጨረሻም አንዲት ሕፃን ልጅ በዚህ እንቆቅልሽ መጨነቃቸውን ተረድታ "በሉ እንዲህ አድርጉ፡፡ ጸጉራችሁን በግማሽ ተላጭታችሁ ሂዱና እጅ ነስታችሁ እፊት ለፊቱ ቁሙ፡፡ ካልጠየቃችሁ በስተቀር እንዳትናገሩ፡፡ ሲጠይቃችሁ ግን እንዲህ በሉት" በማለት እንቆቅልሹን በእንቆቅልሽ እንዲመልሱ መከረቻቸው፡፡ ሰዎቹም ከንጉሡ ቤተ መንግሥት እንደደረሱ ለአጋፋሪው የእቆቅልሹን መልስ ይዘው እንደመጡ ገልጠው እንዲያስገባቸው ጠየቁት፡፡ አጋፋሪውም ወደ ንጉሡ ሄዶ የእናቱ አገር ሽማግሌዎች የእንቆቅልሽ መልስ ይዘው መምጣታቸውን ነገረው፡፡

ንጉሡ ፈቅዶላቸው እንደገቡም የራሳቸውን ክንንብ አውርደው እፊቱ ቆሙ፡፡ የራሳቸውንና የጺማቸውን ግማሽ ጎን የተላጩት ያገሩ ሽማግሌዎች ያየው ንጉሥም በሁኔታው በመደነቅ "ምነው እናቴ ምንሆነች?" በማለት ጠየቀ፡፡ የሽማግሌዎቹ መሪም "ምን የርሷ ነገር" አሉና ዝም አለ፡፡ ንጉሡም "ሞተች እንዴ?" ብሎ ሲጠይቅ "ብትሞት ኖሮ ጸጉራችንን እናሳድግ ነበር?" "እና በሕይወት አለች ማለት ነው?" አለ ንጉሡ፡፡እነሱም "በሕይወት ብትኖር እንደዚህ ጸጉራችንን እንላጭ ነበር?" በማለት መለሱ፡፡ በዚህ ጊዜ ንጉሡ እንቆቅልሹ በእንቆቅልሽ መመለሱን በማወቅ ከፍተኛ ድምፅ አሰምቶ
ሳቀና "ከፍተኛ ጠንቋይ ወይም ሽማግሌ መሆን አለበት፡፡ እንዴት ያለ ብልህ ሰው መከራችሁ?" በማለት ጠየቃቸው፡፡ እነሱም ከመጫወት በስተቀር ሌላ ምንም የማታውቅ ሕፃን መሆኗን ነገሩት፡፡ ንጉሡም "ይች ስታድግ አገር የምትመራ ናት" ብሎ ተናገረ፡፡
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ምንጭ ➸ ሪፖርተር
ለመቀላቀል @poemandquote
አስተያየት @poemandquotebot
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛