2022-10-09 19:23:32
እናታችን አዒሻ ረዲየላሁ ዐንሀ እንዲህ ትላለች፦
ከእለታት ባንዱ ቀን የረሱልን ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም መደሰት ባየሁ ጊዜ እንዲህ አልኳቸው
" አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ ! እስኪ ዱዐ አድርጉልኝ"? ከዚያም እንዲህ ብለው ዱዐ አደረጉልኝ: "ጌታዬ አላህ ሆይ! የአዒሻን ሀጢያት ማርላት ያሳለፈችውንም ወደፊት የሚመጣውን እንዲሁም በድብቅ የሰራችውንም በገሀድ በግልፅ የሰራችውንም ሁሉንም ማርላት"አሉ።
ከዚያም እናታችን አዒሻ ከደስታ ብዛት በጣም ሳቀች በጣም ከመሳቋ የተነሳ በጭንቅላቷ ከረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ታፋ ላይ እስክትወድቅም ድረስ ደረሰች።
ከዚያም የአላህ መልክተኛ -ምነው ዱዓዬ አስደሰተሽ አሏት:
ከዚያም የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፦ በአላህ ስም እምላለሁ ይህ ላንቺ ያደረኩልሽ ዱዐ በእያንዳንዱ ሶላቴ ላይ ለሁሉም ለዑመቴ ( ለሕዝቦቼ) የማደርግላቸው ዱዐ ነው።
የእዝነቱ ነብይ
325 views16:23