Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙር ዘ ተዋህዶ

የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmur_z_tewahdo — መዝሙር ዘ ተዋህዶ
የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmur_z_tewahdo — መዝሙር ዘ ተዋህዶ
የሰርጥ አድራሻ: @mezmur_z_tewahdo
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.88K
የሰርጥ መግለጫ

እናመስግነው በአንድነት መሰዋትም ነውና
በመዝሙር እናወድሰው ይገባዋልምና
ከመላክት ጋር ባንድነት ከፃድቃን ጋር ሆነን
ቅዱስ ቅዱስ እንበል እናመስግን ስሙን
@GlorytoGod_Bot
. 🔷
🔷
🔶🔸🔶
🔷
🔷
🔷
https://telegram.me/https:/mezmur_z_tewahdo

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 17:44:53 ​​እንኳን ለታላቁ ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

#ልደት

መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ ጸጋ ዘአብ ካህኑና እግዚእ ኃረያ ናቸው። እርሱ በክህነቱ እርሷ በደግነቷ በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል።

በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው ቅዱስ ሚካኤል ጸጋ ዘአብን ከሞት እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል። በሁዋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል።

ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የጸነሱት መጋቢት 24 ቀን በ1206 ዓ/ም ሲሆን የተወለዱት ደግሞ ታሕሳስ 24 ቀን በ1207 ዓ/ም ነው። በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል። ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል።

#ዕድገት

የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው "ፍሥሃ ጽዮን" ይሰኛል። ይሕንን ስም ይዘው አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል። በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት: ሐዲሳትን) ተምረዋል። በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል። ዲቁናም ከወቅቱ ዻዻስ አባ ጌርሎስ ተቀብለዋል።

#መጠራት

አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮስ ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክት እያመሰገኑ በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ።

የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ። "ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን። ከዚህ በሁዋላ አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ። ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ። ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በሁዋላ ሰዓትን አላጠፉም። ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ።

#አገልግሎት

ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዻዻሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ። በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ (ጽላልሽ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ። ያን ጊዜ ኢትዮዽያ 2 መልክ ነበራት።

1ኛ. ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል።

2ኛው. ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር።

ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ። ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን (ጠንቁዋዮችን) አጥፍተዋል::

#ገዳማዊ ሕይወት

ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮዽያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል። እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል።

እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ12 ዓመታት: በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26 ዓመታት አገልግለዋል።

በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በሁዋላም ወደ ምድረ ሽዋ (ዞረሬ) ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ22 ዓመታት ቆመው ጸልየዋል። በተሰበረ እግራቸውም 6 ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል።

#ስድስት_ክንፍ

ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል። ጻድቁ ምድረ እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር::

የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል። ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በሁዋላ ነው ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር።

ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም። በገሃድ:-
-በቤተ መቅደስ ብስራቱን
-በቤተ ልሔም ልደቱን
-በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
-በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
-በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር።

የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ። በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ ተክልየን ወደ ሰማይ አሳረገቻቸው።

#በዚያም :-
-የብርሃን ዐይን ተቀብለው
-6 ክንፍ አብቅለው
-የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
-ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
-ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
-ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
-"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል።

#ተአምራት

የተክልየ ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው።
ሙት አንስተዋል
ድውያንን ፈውሰዋል
አጋንንትን አሳደዋል
እሳትን ጨብጠዋል
በክንፍ በረዋል
ደመናን ዙፋን አድርገዋል።

ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል። በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት አብረው ኑረዋል። በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና::

#ዕረፍት

ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው: እልፍ አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ99 ዓመት: ከ8 ወር: ከ1 ቀናቸው ነሐሴ 24 ቀን በ1306 ዓ/ም ዐርፈዋል።

ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል። 10 ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል።
374 views14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 07:03:57 ወር በገባ በ 21
★★★እሳታዊው ሀያል አባት አቡነ ቀውስጦስ★★★
#አቡነ_ተክለ ሃይማኖት_ጋር_አብረው_አንድ_ቤት_ያደጉ
#470300_አጋንንትን_ከሰማይ_እሳት_በፀሎት_አውርደው_አቃጥለው_ህዝቡን_ያዳኑ
#በጦር_በተወጋው_ጎናቸው_በፈሰሰው_ደም_እኩለ_ሌሊቱን_ከፀሀይ_ሰባት_እጅ_በሚበልጥ_ብርሃን_የቀየሩት
#ዳዊታቸው_ክንፍ_አውጥታ_የበረረች
#በበትረ_መስቀላቸው_ፀበል_ያፈለቁ
#ሰባት_አክሊላትን_የተቸሩ
★ታላቁ ፃድቁ ሀያሉ እጅግ የከበረው የመሐግሉ ንቡረ እድ አቡነ ቀውስጦስ ከነገስታት ዘር ከሆኑት ከደጋጎቹ ገላውዴዎስ እና እምነ ፅዮን በሸዋ ክፍለ ሀገር ተወለዱ። ገላውዴዎስ እና እምነ ፅዮን ልጅ በማጣት ለእመቤታችን ብዙ ጊዜ ፀልየዋል ታድያ አንድ ቀን በታህሳስ 12 በሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ቀን ከእመቤታችን ስእለ አድኖ ስር ተደፍተው ሲፀልዩ ስእሏ አፍ አውጥታ « አንድ ልጅ አስቀድማችሁ ትወልዳላችሁ የሚወለደውም እኔ በተወለድኩበት ቀን ግንቦት 1 የሚያርፈውም እኔ ባረፍኩበት ቀን ጥር 21 ነው። እሱም የሰማያዊ ንጉስ ጭፍራ ይሆናል። ሁለተኛውም ለአስራት ሀገሬ ኢትዮጵያ ንጉስ ይሆናል ይህን ደግሞ ስሙን ይኩኖ አምላክ ይባላል ከእርሱም ጋር መልካም ሴት ትወልዳላችሁ» አለቻቸው። ከዚያም ግንቦት 1 1207 ዓም የኛ ውድ እና እንቁ የሆኑ አባት አቡነ ቀውስጦስ ተወለዱ።
★ አባታችን ገና ከመወለዳቸው አፋቸውን ፈትተው ሥላሴን አመስግነዋል እንዲሁም በህፃነነታቸው በእናታቸው ጀርባ ታዝለው ሳለ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም እንደዚሁ በእናታቸው ጀርባ ታዝለው ሲገናኙ ሁለቱ ፃድቆች እጃቸውን ተጨባበጡ ሆኖም ግን እጃቸውን እርስ በርስ ተጣብቆ ቀረ። የአቡነ ተክለ ሃይማኖት አባት ካህኑ ፀጋዘአብ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ በፀሎት ቢጠይቅ ሊቀ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ «የኔ ወታደር ነው ከልጅህ ጋር ይደግ ቤት ውሰደው፤ ከንፅህናው የተነሳ ቁጥሩ ከመላእክት የተደመረ ነው ክብሩ ታላቅ ነውና» አለው ከዚያም በአንድ ቤት አብረው አደጉ።
★ ፃድቁ አባታችን አቡነ ቀውስጦስ የዚህን አለም ደስታና ተድላ ጣዕም ንቀው ፈለገ ሀዋርያትን ተከትለው በሸዋ በከፋ በጅማ ተዘዋውረው የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በመስበክ ከአረማዋያን ንጉሶችና ባላባቶች የሚደርስባቸውን በደሎች ተቋቁመው ብዙ ህዝብን ከአምልኮተ ጣኦት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር መልሰዋቸዋል።
★ አባታችን በተለይ በሸዋ አርሲ ፈንታሌ ላይ ሠርቲ ለምትባል ጠንቋይ እየተላላኩ ህዝቡን የሚያስቱና የሚያሰቃዩ አራት መቶ ሰባ ሺህ ሦስት መቶ 470,300 አጋንንትን እንደ ነብዩ ኤልያስ በፀሎታቸው ከሰማይ እሳት አውርደው ተራራ ደምስሰው አቃጥለዋቸዋል። ታላላቆቹ እነ አቡነ ዜና ማርቆስና አቡነ መብአ ፅዮን የአባታችን ረዳኢ ነበሩ።
★ አቡነ ቀውስጦስ በብዙ ተጋድሎ ሲኖሩ በሰማእትነት ያርፉ ዘንድ ስለ እግዚአብሔር መንግስትና ዘላለማዊ ህይወት የሚተጉ እንጂ የዚህ አለም ሀብትና ስልጣን የማይሹ እውነተኛ መናኝ ነበሩና የታናሽ ወንድማቸው የአፄ ይኩኖ አምላክ ልጅ አፄ አምደ ፅዮን የአባቱን እቁባት በማግባቱ «ይህንን ልታደርግ አይገባህም» ብለው እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ቢገስፁት በሌሊት 11 ወታደሮቹን ልኮ ከበዮ ወደ እንሳሮ ሀገር ካስወሰዳቸው በኋላ ከበዩ ተራራ ላይ ኮሶ አረህ ከሚባለው አፋፍ ላይ እጅ እና እግራቸውን አስረው ቢገድሏቸው (ሰማእት ቢያደርጓቸው) ደማቸው ሲፈስ ጀማ ድረስ ሆነ።
★በእኩለ ሌሊት ጎናቸው በጦር ሲወጋ ደማቸው ቀይ ብርሃናማ ሆኖ ሌሊቱን ቀይሮት ከፀሀይ 7 እጅ የሚያበራ ብርሃን ሆኖ እስከ ታላቁ ወንዝ ደረሰ። በደማቸው ሌሊቱ ወደ ብርሃናማ ቀን ስለተለወጠ ቦታው አሁን ድረስ ቀን እየተባለ ይጠራል።
★ ደማቸው ከወንዙ ጋር ተቀላቅሎ እርሳቸው ከገደሙት ገዳም ደረሰ ድንበሩ ጋር ሲደርስም ቆመ ከዚያም እንደ እሳት ፈላ ቦታውም ደም እሳት እየተባለ መጠራት ጀመረ።
★ ዳዊታቸውን በስተቀኝ በኩል ቢወረውሯት እየበረረች አሁን ደብረ ዳዊት እየተባለ በሚጠራው ስፍራ አርፎ ተሰውሯል እስከ አሁን የት እንደደረሰ አይታወቅም።
★ በግራ የያዙትን በትረ መስቀላቸውን ቢወረውሩት መሬት ላይ ቢሰካ ዛሬ አለም ሁሉ የሚድንበት ፀበል ፈልቆልናል።
★ በዚህም ጥር 21 1332 ዓም በ125 አመታቸው አረፉ። ጌታችን እመቤታችንንና መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ 7 የብርሃን አክሊላትን አጎናፅፏቸዋል።
★ቃልኪዳናቸው
፩ ደጅህን ለረገጠ 84 ትውልድ እምርልሃለሁ
፪ ቤተ መቅደስህን የሰራ ብቻ አይደለም፣ ሲሰራ ያየ፣ ቦታህን የጠቆመ ያመላከተ 64 ትውልድ እምርልሃለሁ
፫ ገድልህን የሰማ ያሰማ፣ ስምህን የጠራ፣ ስለአንተም የተነጋገረ 26 ትውልድ እምርልሃለሁ
፬ በሰንበት ቀን በስምህ የሚዘክረውን፣ ከመቃብርህ ጭብጥ አፈር ወስዶ በቤቱ የሚያኖረውን ከክፉ ሰው ከድንገተኛ አደጋ እጠብቀዋለሁ፣ እባብም አይነድፈውም።
፭ የመቃብርህን አፈር ዘግኖ ወስዶ ከሞተ ቤተሰቡ መቃብር ቢበትነው የሞተው ቤተሰቡ የሞተው ሰው ሲኦል ቢሆን ከመቅስፈት ገነት አስገባልሀለሁ።
፮ ለቁርባን ያልበቃ ቢሆን በተወለድክበት ቀን ባረፍክበት ቀን እጣን፣ ዘቢብ፣ ጧፍ ይዞ ለመጣው ስጋወ ደሙ እንደተቀበለ አደርግለታለሁ።
፯ ደጅህን መጥቷ የረገጠውን የሲኦልን ደጅ አያየውም፤ ላልምረው ደጅህን አላስረግጠውም
፰ ስለ እኔ ሰማእት የሆንክባት ምድር እንደ ዳዊት ሀገር ኢየሩሳሌም ትሁንልህ ወደ እርሷ የሄደውን ሁሉ ወደ መቃብሬ ጎለጎታ እንደሄደ እቆጥርለታለሁ። ብዙ ሀጢያት የሰራ ሰው ንሰሀ ገብቶ በዚች ቦታ ጥቂት ምፅዋት ቢሰጥ ሀጢያቱን እደመስስለታለሁ፣ በጠበልህም ቢጠመቅ በደሉን አጠፋለታለሁ ብሎ ጌታችን የማይታበይ ቃልኪዳኑን ሰጥቷቸዋል
ዛሬም ድረስ ልዩ ልዩ ተአምራትን የሚያደርጉት አባታችን በገዳማቶቻቸው አእላፍ ደዌ በሽታ ችግርን አባረዋል። በተጨማሪም እኛም ሼር በማድረግ የበረከቱ ተሳታፊ እንሁን እላለሁ።
የፃድቁ የሰማእቱ የቅዱሱ አባታችን አቡነ ቀውስጦስ በረከታቸው ረድኤታቸው ፀሎታቸው ይደርብን አሜን።
★★★ገዳማቸው 2ቱም ወደ ደብረ ሊባኖስ መንገድ ከአዲስ አበባ 120 ኪሜ ወደ ጅሩ አርሴማ መንገድ ሙከጠሪ ከተማ ሚጤና በዩ ልዩ ስሙ መገንጠያ ሌላኛው መንገዱ በዚያው ሆኖ በእግር 1 ሰአት ገደማ "ቀን ማርያም" (የእረፍት ቦታቸውና መቃብር ስፍራቸው ያለበት)★★★
በጎደለ አቡነ ቀውስጦስ ይሙሉ
በጠፋ አቡነ ቀውስጦስ ይማሩን
1.2K views04:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 23:11:08 ሃሌ-ሉያ አንተ ሰው ሆይ

ሃሌሉያ አንተ ሰው ሆይ (4)
ቡሄ መድረሱን ሰምተሃል ወይ
ሀሌሉያ አንተ ሰው ሆይ
መስማቱንማ ሰምቼ ነበር
ሀሌሉያ አንተ ሰው ሆይ
ከዚያ ቢያደርሰኝ ልዑል እግዚአብሔር
ሃሌሉያ አንተ ሰው ሆይ

እናቴ ሆይ.......... ሆ
ይህን ባየሻ ........ሆ
በቁርማ ዳቦ .......ሆ
ሲጥለኝ ውሻ........ሆ
ደጓ ጫማዋን ......ሆ
አውልቃዋለች.......ሆ
ውሃ ሲጠማ.........ሆ
አጠጥታዋለች......ሆ
የስዋ ውዳሴ .......ሆ
ሆኖኛል ውይን ......ሆ
ዘሬም ብዘምር ......ሆ
እኖራለሁኝ ...........ሆ
ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (4)

በእምነት እንውጣ .ሆ
ከተራራው ላይ......ሆ
ይታይ ብርሃኑ........ሆ
ክብሩ ኤልሻዳይ....ሆ
ሙሴን እንጠይቅ...ሆ
የጥንቱን ነገር .......ሆ
ምን እንደሚለው ...ሆ
ጌታን ሲያናግር......ሆ
ድምጹን እንስማ ....ሆ
እንደ ትሁትነቱ.......ሆ
እንቀበለው ..........ሳ
እኛም በትሩን .......ሆ
ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (2)
ተቁኙለት በልልታ ላዳኙ ጌታ(2)

ተራራውማ ..........ሆ
ነውና አምሳል.......ሆ
ለቤተ ክርስቲያን...ሆ
መንበረ ልዑል........ሆ
ወጥተን እንጠይቅ .....ሆ
ኤልያስን.............ሆ
እንድንዳስሰው.....ሆ
ጸጓራር ክንዱን....ሆ
ሰማይ በትለጉም...ሆ
ባህር ቢከፍል.......ሆ
እሳት ብታወርድ.....ሆ
ጠላትም ቢርድ......ሆ
በሰረገላ ..............ሆ
የተነጠከው...........ሆ
ይህ ሁሉ ክብር .....ሆ
በማን ስልጣን ነው....ሆ
ለሁላችን መልካም ነው በዚህ መኖር(4)

የእመብርሃን .........ሆ
የምዬ ልጅ............ሆ
ተጥሎ ላይቀር .....ሆ
ተረስቶ ደጅ...........ሆ
ሰአሊ ለነ .............ሆ
ባለበት አፉ...........ሆ
የጭንቁን እለት.....ሆ
ተሰብሮ ሰልፉ......ሆ
እንዳባቶቹ ............ሆ
ቅኔን ተቀኘ.............ሆ
ድንግል ስትረዳው....ሆ
አይኑ ስላየ..............ሆ
ተፈስሂ ደብረ ታቦር(2)
ተፈስሂ አርሙኒየም (2)
ባንቺ ላይ ታየ እግዚአብሔር
ተፈስሂ አርሙንየም

ሙሴ ስላለ ............ሆ
መና ያውርዳል........ሆ
ቅዱስ ኤልያስ.........ሆ
ስጋ ያመጣል..........ሆ
ዮሃንስንም............ሆ
ጌታ ይወዳል.........ሆ
መድኃኒታችን........ሆ
ፈውስ ይሆነናል.....ሆ
በዚህ እንድንኖር ...ሆ
ዳሱን ጥለናል .....ሆ
ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (4)

አባቴም ቤት..........ሆ
አለኝ ለከት.............ሆ
እናቴም ቤት ...........ሆሆ
አለኝ ለከት...,..........ሆ
ፍልሰታ ስትሆን.......ሆ
የቆምኩባት............ሆ
በድብረ ታቦር .........ሆ
ያጌጥኩባት...........ሆ
ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ(2)
ተቀኙለት በልልታ ላዳኙ ጌታ(2)

አመት አውዳመት "ድገምና" አመት "ድገምና"
ያባብዬን ቤት "ድገምና" አመት "ድገምና"
ይግባ በረከት "ድገምና" አመት "ድገምና"
የማምዬ ቤት "ድገምና" አመት "ድገምና"
ይትረፍረፍ በእውነት "ድገምና" አመት "ድገምና"
ነሩ በሀይማኖት
ጽኑ በጸሎት
በተዋህዶ ቤት(4)

የሰማይ ሰራዊት "በእምነት" ያድርጋችሁ "አሜን"
አማኑኤል በጸጋ "በእምነት" ያኑራችሁ "አሜን"
ከስጋ ወደሙ "በእምነት"
ያድላችሁ "አሜን"
ዘርን እደ አብርሃም "በእምነት"
ያብዛላችሁ "አሜን"
ይባረክ በእግዚአብሔር በእምነት ዘመናችሁ "አሜን"/2/
እድሜና ጤናውን በእምነት ያድላችሁ "አሜን" (2)
2.0K views20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 22:29:58 በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱአምላክ አሜን
በክርስቶስ ክርስቲያን ለተሰኛችሁና በደሙ የዋጃችሁ በኢትዮጵያ
የምትገኙ ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ በቤታችሁም ያላችሁ
በህመም ምክንያት በሆስፒታል ያላችሁ በማረሚያ ቤት ያላችሁ
በጦር ሜዳም ያለችሁ እንዲሁም በተለያየ ስፍራ የምትገኙ
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የከበረ ሰላምታችንን
በያላችሁበት ይድረሳችሁ፡፡እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ነገ ማለትም በ7 በ ብርሃናተ አለም ጴጥሮስ ወ ጳዉሎስ ተገኝተን ከረድኤት በረከቱ እንድንሳተፍ አምላካችን ልኡል እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜን ሰላም ያገናኘን
2.2K views19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 12:35:03

2.5K views09:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 20:57:55 ፍልሰታ የህጻናት ደስታ እንሂድ ከ ቅዱሱ ቦታ እያሉ በልጅነት አንደበታቸው እናታችን ንጺተ ንጹሃን የያእቆብ እመቤት የኖህ ድንቅ መርከብ አኩራሪተ መአት መራገ ጸሎት ተብላ ምትጠራ ድንግል ማርያምን ሲያወድሷት

ከድንግል ማርያም ረድኤት በረከቷን ታሳትፈን ለሀዋርያው ቶማስ የታየች እመ አምላክ እኛንም ከልጇ ከወዳጅዋ አማልዳ ታስታርቀን በዘርፋፋዋ ቀሚሷ የመጣብንን መቅሰፍት ከልላ ትንሳዔዋን ያሳየን
መልካም ፍልሰታ


2.2K views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 20:53:14 የሰኞ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን
1.9K views17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 22:02:30
† ወፌ ሰንብታ †

ወፌ ሰንብታ መጣች ለፍልሰታ
አግርሽ የት ነው ኤፍራታ
አሳድሪኝ ማታ
ይናፍቀኛል ሌሊት
የሰማዩ እልፍኝ መብራት
ወፌ የኔ እመቤት
በክንፍሽ ጥላጋርደሽ
ከልጅሽ ሥፍራ ወስደሽ
እንዳልቆምበሽ በግራ
እንዳያሰቃየኝ መከራ
ወፌ ነፍሴን አደራ
አንቺን ስለምን ስለምን
ደግሞም በልጅሽ ሳምን
ሲኦል ይብላኝ ወይ እኔን?
እሳት አዝላ እሳት አዝላ
ወዴት ባከነች ከገሊላ?
ባረፍሽበት ከዚያ ሥፍራ
ሽፍቶች ጠበቁሽ በዚያ ቆላ
ዓይኖችሽ ፈርተው ስለነሱ
እንባዎችንም አፈሰሱ
የኔ ይጥፋልሽ ሁለት ዐይኔ
ባንቺ ፋንታ ባንቺ ፋንታ
እኔ በስደት ልንገላታ
እኔን ይጭነቀኝ ይጥበበኝ
እንደጠበበሽ ግራ ቀኝ
ሽፍቶች ከበውሽ ሲማከሩ
ዐይኖችሽ ፈርተው እንባን ዘሩ
2.2K views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 21:17:17 ​​*ድንግል ትንሳኤሽን*

ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ
ገብተናል ሱባኤ በአንድነት በመንፈስ
ለእኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት
አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነ ምህረት (፪)

ሞትን የረገጠ ልጅሽ ካንቺ ጋር ነው
ውጦ የሚያስቀርሽ የቱ መቃብር ነው
የዕርገትሽን ዜና ከቶማስ ሰምተናል
ትንሳኤሽ እውነት ነው ሰበንሽን አይተናል

ሞትማ በሞት ተሽንፏል
ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል (፪)

አዝ = = = = = =

ልናየው ወደድን የቶማስን ክብር
ለምን ተስወረን የትንሳኤሽ ምስጢር
በራችንን ዘግተን በፀሎት ወድቀናል
ተገልጠሽ አብሪልን ልጆችሽ ናፍቀናል

ሞትማ በሞት ተሽንፏል
ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል (፪)

አዝ = = = = = =

መዝሙረኛ አባትሽ ዳዊት ጽፎልናል
ሞትን የማያይ ስው ማን አለ ብሎናል
ይህ እውነት በዘመን አንቺ ላይ ቢደርስም
በሞት ተሽንፏል መቃብር አይኖርም

ሞትማ በሞት ተሽንፏል
ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል (፪)

አዝ = = = = = =

ቶማስ ከደመናው ወርዶ ሲያናግረን
ስለ ሆነው ነገር እጅጉን ተመሰጥን
እኛም ይህን ክብር ተመኘን ለማየት
ድንግል አሳስቢልን ኪዳነ ምህረት

ሞትማ በሞት ተሽንፏል
ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል(፪)

መዝሙር
በሊቀ መዘምራን ዲ/ን ቴድሮስ ዮሴፍ

<< እነሆ በፆማችሁ ቀን…>>
ኢሳ ፶፰ ፥ ፩-፲፬
1.9K views18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ