Get Mystery Box with random crypto!

† ወፌ ሰንብታ † ወፌ ሰንብታ መጣች ለፍልሰታ አግርሽ የ | መዝሙር ዘ ተዋህዶ


† ወፌ ሰንብታ †

ወፌ ሰንብታ መጣች ለፍልሰታ
አግርሽ የት ነው ኤፍራታ
አሳድሪኝ ማታ
ይናፍቀኛል ሌሊት
የሰማዩ እልፍኝ መብራት
ወፌ የኔ እመቤት
በክንፍሽ ጥላጋርደሽ
ከልጅሽ ሥፍራ ወስደሽ
እንዳልቆምበሽ በግራ
እንዳያሰቃየኝ መከራ
ወፌ ነፍሴን አደራ
አንቺን ስለምን ስለምን
ደግሞም በልጅሽ ሳምን
ሲኦል ይብላኝ ወይ እኔን?
እሳት አዝላ እሳት አዝላ
ወዴት ባከነች ከገሊላ?
ባረፍሽበት ከዚያ ሥፍራ
ሽፍቶች ጠበቁሽ በዚያ ቆላ
ዓይኖችሽ ፈርተው ስለነሱ
እንባዎችንም አፈሰሱ
የኔ ይጥፋልሽ ሁለት ዐይኔ
ባንቺ ፋንታ ባንቺ ፋንታ
እኔ በስደት ልንገላታ
እኔን ይጭነቀኝ ይጥበበኝ
እንደጠበበሽ ግራ ቀኝ
ሽፍቶች ከበውሽ ሲማከሩ
ዐይኖችሽ ፈርተው እንባን ዘሩ