Get Mystery Box with random crypto!

​​*ድንግል ትንሳኤሽን* ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ ገብተናል ሱባኤ በአንድነት በመንፈስ | መዝሙር ዘ ተዋህዶ

​​*ድንግል ትንሳኤሽን*

ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ
ገብተናል ሱባኤ በአንድነት በመንፈስ
ለእኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት
አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነ ምህረት (፪)

ሞትን የረገጠ ልጅሽ ካንቺ ጋር ነው
ውጦ የሚያስቀርሽ የቱ መቃብር ነው
የዕርገትሽን ዜና ከቶማስ ሰምተናል
ትንሳኤሽ እውነት ነው ሰበንሽን አይተናል

ሞትማ በሞት ተሽንፏል
ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል (፪)

አዝ = = = = = =

ልናየው ወደድን የቶማስን ክብር
ለምን ተስወረን የትንሳኤሽ ምስጢር
በራችንን ዘግተን በፀሎት ወድቀናል
ተገልጠሽ አብሪልን ልጆችሽ ናፍቀናል

ሞትማ በሞት ተሽንፏል
ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል (፪)

አዝ = = = = = =

መዝሙረኛ አባትሽ ዳዊት ጽፎልናል
ሞትን የማያይ ስው ማን አለ ብሎናል
ይህ እውነት በዘመን አንቺ ላይ ቢደርስም
በሞት ተሽንፏል መቃብር አይኖርም

ሞትማ በሞት ተሽንፏል
ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል (፪)

አዝ = = = = = =

ቶማስ ከደመናው ወርዶ ሲያናግረን
ስለ ሆነው ነገር እጅጉን ተመሰጥን
እኛም ይህን ክብር ተመኘን ለማየት
ድንግል አሳስቢልን ኪዳነ ምህረት

ሞትማ በሞት ተሽንፏል
ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል(፪)

መዝሙር
በሊቀ መዘምራን ዲ/ን ቴድሮስ ዮሴፍ

<< እነሆ በፆማችሁ ቀን…>>
ኢሳ ፶፰ ፥ ፩-፲፬