Get Mystery Box with random crypto!

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

የቴሌግራም ቻናል አርማ memehirhenok — ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
የቴሌግራም ቻናል አርማ memehirhenok — ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
የሰርጥ አድራሻ: @memehirhenok
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 12.40K

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-05-16 13:26:55

1.2K views10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 19:30:40

1.6K views16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 18:32:13

2.0K views15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 12:54:34

2.3K views09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 15:48:23

1.1K views12:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 10:15:07

1.7K views07:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 16:57:53

2.0K views13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 20:15:10

2.3K views17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 07:52:11
3.0K views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 07:52:04 እግዚአብሔር ለራሱ ብቻ ፈጠራት፡፡ እርሱ ቅዱስ ነውና ለራሱ ቀደሳት፣ እርሱ ክቡር ነውና ለራሱ አከበራት እርሱ ንፁህ ነውና ለራሱ አነፃት፡፡ በንጽህና ከሰው ወገን እሷን የሚመስላት የለም፡፡ ከመላእክትም ዘንድ የእመቤታችን ንጹህ ነፍስ ከጌታ ነፍስ ጋር አንድ እንደምትሆን አውቆ ጠበቃት፡፡ ለሐናና ለፍጥረቱ መድኃኒት ትሆን ዘንድ ሰጣት፡፡:

የማይረቡ የማይጠቅሙ ልጆች ከመውለድ አለመውለድ ይሻላል፡፡ ልጅ ያልሰጣት እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን፡፡ ሴቶች እንደሚወልዱ ቶሎ ፈጥና ብትወልድ ኖሮ የማይረቡ የማይጠቅሙ ልጆችን በወለደች ነበር፡፡
እሱ ግን በሰው አንደበት ሥራው ይደነቅ ዘንድ እስከ ጊዜው የሐናን ማህጸን ዘግቶ አቆየው፡፡ በሁሉ ዘንድ የተወደደች የተመረጠች የከበረች ልጅን ትወልድ ዘንድ ጊዜው ሲደርስ የሐናን ማህጸን እግዚአብሔር ከፈተ፡፡

እመቤታችን ነሐሴ 7 /ሰባት/ ቀን ተፀነሰች። ሐናም ስለ ሐዘኗና ስለጭንቀቷ ስፍር ቁጥር የሌለው እርጋታን አገኘች፡፡ በመጠላት በመገፋት ፋንታ ክብርን ገናናነትን አገኘች፡፡

ከስድስት ወርም በኋላ የሐና ፅንሷ ታወቀ፡፡ የእሷም ዘመዶች የኢያቄምም ዘመዶች በሰሙ ጊዜ ወደ እሷ መጥተው የሕፃንነትሽ ዘመን ካለፈ በኋላ ላንቺ የተደረገ ይሄ ድንቅ የምንሰማው ነገር ምንድን ነው አሏት፡፡ መጽነሷንም ያረጋግጡ ዘንድ የሐናን ማህጸን ይዳስሱ ነበር፡፡

ዓይኗ የታወረ ከቅድስት ሐና ዘመዶች ወገን የነበረች የአርሳባን ልጅ የምትሆን አንዲት ሴት ምንም ሳታውቅ የሐናን ማሕጸን ዳሳ ዓይኗን ብትነካ ዓይኗ በራ፡፡ የዳነችውም ሐናን "ሐና ሆይ ብጽእና ይገባሻል። ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ በማሕጸኑ የእውራንን ዓይን ያበራ እንዳንቺ አላየሁም’’አለቻት፡፡ ዘመዶቿም ሰገዱላት አከበሯት፡፡

የሐና ዝና በየአገሩ ሁሉ ተሰማ፡፡ ድውያን ሁሉ እየመጡ ማሕጸኗን እየዳሰሱ ይፈወሱ ነበር፡፡ የተፈወሱትም ’’በማሕጸን ሳለ ህሙም የፈወሰ በተወለደ ጊዜ እንደምን ያለና የሚያደርግ ይሆን’’እያሉ ይገረሙ ነበር፡፡

እንዲሁም ሳምናስ ወልደ ጦሊቅ የሚባል የሐና የአጎቷ ልጅ ነበር፡፡ ይህ ሰው ሞተ። ሐና በጣም ትወደው ነበርና ስሙን እየጠራች በበድኑ ዙሪያ እየዞረች ስታለቅስ የሐና ጥላ ከበድኑ ላይ ቢያርፍበት ሟቹ ሳምናስ ብድግ ብሎ ’’የእውነተኛ ፀሐይ አያቱ፣ የጨረቃ እናቷ የምትሆኚ ቅድስት ሐና ሰላም ላንቺ ይሁን’’ ብሎ አወድሷት የራዕዩንም ትርጉም ገልጦላት ተመልሶ አርፏል፡፡

ከለቅሶ ላይ የነበሩት አይሁዶች ያዩትንና የሰሙትን ነገር ማመን ስላቃታቸው ሐና ላይ የክፋት ቂም ቋጠሩ፡፡ ሐና ከነገደ ሌዊ የተወለደች እንደሆነች ኢያቄምም ከነገደ ይሁዳ እንደተወለደ ስላወቁ "ይህ ከእነዚህ የሚወለደው በአባቱ በኩል ንጉስ ሆኖ እኛን ይገዛል። በእናቱ በኩል ደግሞ ሊቀ ካህናት መሆን ይችላል፡፡

ገና በማሕጸን ሳለ እንዲህ ድንቅ ነገር ተወልዶ ካደገማ ምን የማያደርገው ነገር ይኖራል? ስለዚህ ዞር ብሎ አያየንም፡፡ ቀደሞ የእነዚህ ወገኖች የነበሩ ዳዊት፣ ሰሎሞንና ኢዮስያስ በልዩ ዘመናት አስጨንቀው ገዝተውን ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ከእነዚህ የሚወለደው ምን ያደርገን ይሆን? ዝም ብለን መቀመጥ የለብንም የምናደርገውን እናድርግ’’ በማለት በክፋት ተማከሩ፡፡

የአይሁድን ክፋት ያወቀው ቅዱስ ገብርኤል በሌሊት በራዕይ መጥቶ "አይሁድ ሊገድሏችሁ መክረዋልና ከዚህ ውጡ ወደ ሊባኖስም ሂዱ’’ አላቸው፡፡ እነሱም ከሚኖሩበት ከገሊላ ተነስተው ወደ ለሊባኖስ ሄዱ፡፡

በሊባኖ ተራራ ኮረብታማ ቦታ ፈልገው በዚያ መኖር ጀመሩ፡፡ ሐናም የምትወልድበት ጊዜ ሲደርስ በ 5485 ዓ.ዓ ግንቦት 1 ቀን እመቤታችን እንደ ፀሐይ አብርታ እንደ መላእክት አስፈርታ ተወለደች፡፡ ሰሎሞንም ’"አንቺ የገነት ምንጭ፣ የሕይወት ውሃ ጉድጓድ ከሊባኖስ የሚፈስ ወንዝ ነሽ’’ ያለው ትትቢት ተፈጸመ፡፡
/መኃ 4÷15/

የገነት ምንጭ የሆነች የሕይወታችንን ውሃ ክርስቶስን የወለደች እመቤታችን ብርሃነ ልደቷ ከሊባኖስ ፈሰሰ፡፡ ለክርስቶስ መወለድ የእመቤታችን መወለድ መሠረት ነው። ስለዚህ ልደቷን እናከብራለን። የእመቤታችን ልደት የእኛም ልደት ነውና።

"ስለ እመቤታችን ክብር፣ ያላስተዋልነው ነገር" ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ።

ግንቦት 1-9-15 ዓ.ም
አዲስ አበባ
2.8K views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ