Get Mystery Box with random crypto!

🔴 ምክረ አበው MEKRA ABAW™

የቴሌግራም ቻናል አርማ mekra_abaw — 🔴 ምክረ አበው MEKRA ABAW™ ም
የቴሌግራም ቻናል አርማ mekra_abaw — 🔴 ምክረ አበው MEKRA ABAW™
የሰርጥ አድራሻ: @mekra_abaw
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.32K
የሰርጥ መግለጫ

#አባቶችን_ጠይቅ_ይነግሩሃል
● ጠቢብ ከሰነፍ ጋር ቢጣላ፥ ሰነፍ ወይም ይቈጣል ወይም ይስቃል፥
ደምን ለማፍሰስ የሚሹ ሰዎች ፍጹሙን ሰው ይጠላሉ፥ ደግሞም የቅኑን ሰው ነፍስ ይሻሉ።
ሰነፍ ሰው ቍጣውን ሁሉ ያወጣል፤ ጠቢብ ግን በውስጡ ያስቀረዋል።
○ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕ. 29 ○
ሀሳብ ካላችሁ @habmisget

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-03-27 22:41:03 + ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል +

ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶአል:: ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጠይቀው መጣ:: ሆኖም እንደ ልማዱ እግዚአብሔር ይማርህ አላለውም:: ለጆሮ የሚከብድ ቃል ጥሎበት ወጣ:: "ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!"

ነቢዩ ይህንን ብሎት ከወጣ በኁላ ሕዝቅያስ ወደ ግድግዳው ዞሮ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ:: አምላኩ በንግግር ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለምና ፊቱን ወደ መቅደሱ አቅጣጫ አዙሮ አለቀሰ::

ከጥቂት ደቂቃ በኁዋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ሌላ መልእክት ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔር እንዲህ ይላል :- ጸሎትህን ሰምቻለሁ ዕንባህን አይቻለሁ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ" (ኢሳ 38:5)

ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም:: ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው? ለባሪያዎችህ መመሪያ ሳትሠጥ የምታስተካክለው ቤትስ እንዴት ያለ ነው? በደቂቃዎች ውስጥ ትሞታለህ ከተባልክ በኁዋላ ዐሥራ አምስት ዓመት ያስጨመረልህ ምን ዓይነት ማስተካከያ አድርገህ ነው? ለእኛም ንገረንና ዕድሜ እናስጨምር::

ሕዝቅያስ ከአልጋው ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ ልቡ ነበር::
ልብህን ካስተካከልህ ቤትህ ይስተካከላል:: እግዚአብሔር እንደሆን ትሞታለህ ቢልህም መሞትህን አይፈልግም:: እርሱ ከኃጢአትህ እንጂ ካንተ ጋር ጸብ የለውም::

"በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን?" ይላል መሐሪው (ሕዝ 18:23)

እርሱ ትሞታለህ የሚልህ መኖርህን ፈልጎ ነው:: አንዴ ብያለሁ ብሎ አይጨክንብህም:: በንስሓ ተመለስ እንጂ ምሬሃለሁ ለማለት ይቸኩላል:: አሁን ትሞታለህ ብዬው አሁን ትድናለህ ብለው ይንቀኛል ሳይል ተመልሶ ይምርሃል:: ኃጢአትህንም ወደ ጥልቁ ይጥለዋል:: በጎ እንድትሠራም ዕድሜ ይጨምርልሃል:: አንተ ብቻ ተመለስና አሁኑኑ ንስሓ ግባ::
ከበደል አልጋ ጋር ያጣበቀህን ፈተናም ድል መንሻው ጊዜ አሁን ነው:: ሕዝቅያስ በደቂቃ ዕንባ ምሕረት አግኝቶ ዕድሜ ካስጨመረ በዐቢይ ጾም ሙሉ የሚያለቅስ ምን ያህል ዕድሜ ያገኝ ይሆን?
ወዳጄ አንተም ተነሣና በዚህ ወር ቤትህን አስተካክል::
እንደ ሕዝቅያስ ፈጣሪህ ይጠብቅሃል:: የተቀየምከውን ይቅር በል የበደልከውን ካስ የሚበቀልህን የማይተኛ ጠላትህን ዲያቢሎስ ተበቀለው::

የዐቢይ ጾም የወንጌል ምንባብ ስለ ዲያቢሎስ ፈተና ሦስቱ ወንጌላት የተናገሩትን ስናስተውል ሦስት ዓይነት ጥቅሶች እናገኛለን::

አርባ ቀን ከዲያብሎስ ተፈተነ። (ሉቃ 4:2)

በምድረ በዳም ከሰይጣን እየተፈተነ አርባ ቀን ሰነበተ (ማር 1:13)
የሚሉት ቃላት ጌታችን ዐርባውንም ቀን መፈተኑን ያሳያሉ::

አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ። ፈታኝም ቀርቦ እንዲህ አለው (ማቴ 4:2)

የሚለው ደግሞ ከጾሙ በኁዋላ የቀረቡለትን ሦስት ፈተናዎች የሚያሳይ ነው::
ሦስተኛው ጥቅስ ደግሞ ከተፈተነ በኁዋላ ያለው ሲሆን

ዲያቢሎስም ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ እስከ ጊዜው ከእርሱ ተለየ። (ሉቃ 4:13) ይላል:: ዲያቢሎስ ፈተናውን ቢጨርስም የሚተወው ለጊዜው እንጂ መፈተኑን አያቆምም:: የዲያቢሎስ ፈተና ስልቱ ይቀያየራል እንጂ ይቀጥላል::

ዐቢይ ጾም ዲያቢሎስ ድል የተደረገበት የጦር ዐውድማ ነው:: በዚህ ወራት ድል ያላደረግነውን ፈተና በሌላ ጊዜ አናደርገውም:: ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል እንደሚባለው በዐቢይ ጾም የተኛ ክርስቲያን መቼም አይነቃም:: ከነስሙ ሁዳዴ (ሰፊ እርሻዬ) የምንለው ይህ ጾም ለነፍሳችን ብዙ ዘር የምንዘራበት አጋንንት መድረሻ የሚያጡበት ጾም ነው:: በዐቢይ ጾም ያልተገራ አንደበት መቼም አይገራም:: በዐቢይ ጾም ያልተፈወሰ ቂም መቼም አይፈወስም::

ጌታችን በወንጌል አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥል ጋኔን ያለበትን ልጅ ሲፈውስ "ይህ ዓይነቱ ጋኔን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም" ብሎ ነበር:: ሀገራችንን አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥላት የጥላቻ ጋኔንም ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም::

ወዳጄ ከቁስልህ የምትፈወስበት ወር እንደደረሰ ዕወቅ:: አንተስ ብትሆን ልትላቀቀው እየፈለግህ ያቃተህ ክፉ ልማድ የለብህም:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "የምፈልገውን መልካም ነገር አላደርግም የማልፈልገውን ክፉ ነገር ግን አደርጋለሁ:: ምንኛ ጎስቋላ ለዚህ ለሞት ከተሠጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?" ብለህ ምርር እንድትል ያደረገህ ኃጢአት የለም? እንግዲያውስ እወቀው:: ይህ ዓይነቱ ወገን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም:: ይህ ጾም ቁስል የሚሽርበት ጾም ነው:: ይህ ጾም ሸክም ማራገፊያ ጾም ነው:: እንደ ሕዝቅያስ በዚህ ወር ቤትህን በንስሓ አስተካክል::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የካቲት 15 2012 ዓ ም
ዝዋይ ኢትዮጵያ

Deacon Henok Haile

ይህ ዓይነቱ ጽሑፍ ለእርስዎም ለሌሎችም እንዲደርስ

በvideo ለማግኘት
https://www.youtube.com/channel/UCfWtKqb7qsxjXey4kN_tykg?sub_confirmation=1
ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@mekra_abaw
@mekra_abaw
@mekra_abaw
196 views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 19:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 22:06:01 ልብን የሚመስጡ ቆየት ያሉ የመሰንቆ ዘለሰኛ መዝሙር


251 views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 14:53:43 "የራበው ሰው ለምግብ የጠማው ሰው ለመጠጥ እንደሚቸኩል ክርስቶስም ይቅር ለማለት ይቸኩላል።"

ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
710 views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 00:15:08
አመ ፳፯ቱ ለመጋቢት መድኃኔዓለም  ስርዓተ ማህሌት

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።
@mekra_abaw
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።
@mekra_abaw
ዚቅ
ሃሌ ሉያ ለአብ በመስቀሉ አተበነ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ በመስቀሉ ቤዘወነ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ በመስቀሉ ኮነ ሕይወትነ።

ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
@mekra_abaw
ዚቅ
መድኃኔዓለም ወልድኪ ሥጋ ዚአኪ ዘለብሰ፤ ሐፃውንተ መስቀል ተአገሰ፤ በዓውደ ጲላጦስ ተወቅሰ አማዑትኪ ተከወሰ።
@mekra_abaw
መልክአ መድኃኔዓለም
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢረከቡ ተፍጻሚተ፤ መላእክተ ሰማይ ወምድር እለ ለመዱ ስብሐተ፤ መድኃኔዓለም ተወከፍ እንተ አቅረብኩ ንስቲተ፤ ዘሰተይከ በእንቲአነ ከርቤ ወሐሞተ፤ በሞተ ዚአከ ከመ ትቅትል ሞተ።

ዚቅ
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ፤ ወአስተዩኒ ብሂዓ ለጽምዕየ፤ ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ።
@mekra_abaw
ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
ወአቅደምከ ጸግዎ መንፈሰከ ቅዱሰ ለሥርየተ ኃጢዓት፤ አክሊል ዘሦክ አስተቀጸሉከ ዘበሰማያት ለነ አክሊለ ጽድቅ አስተዳሎከ፤ ሰቀሉከ ዲበ ዕፅ፤ ብሂዓ ዘምስለ ሐሞት አስተዩከ፤ ከመ ለነ ታስትየነ ወይነ ትፍሥሕት ወሐሤት፤ ረገዙከ በኲናት ወተርኅወ ገቦከ፤ ከመ ለነ ተሀበነ ሥጋከ ቅዱሰ ወደምከ ክቡረ፤ ከመ ትጸግወነ።
@mekra_abaw
ወረብ
ወአቅደምከ 'ጸግዎ'/፪/ መንፈሰከ/፪/
አክሊለ ጽድቅ አስተዳሎከ በሰማያት አክሊለ ጽድቅ/፪/
@mekra_abaw
መልክአ መድኃኔዓለም
ሰላም ለጒርዔከ ክቡር ወልዑል፤ ወለክሣድከ ዓዲ ዘሰሐብዎ በሐብል፤ መድኃኔዓለም ክርስቶስ በቀራንዮ ስቁል፤ በለኒ መሐርኩከ በእንተ ማርያም ድንግል፤ እስመ ኄር አልቦ እንበሌከ ቃል።
@mekra_abaw
ወረብ
'በለኒ መሐርኩከ'/፪/ በእንተ ማርያም ድንግል/፪/
እስም ኄር አልቦ እንበሌከ ዘይሜሕር ቃል መድኃኔዓለም/፪/
@abenet_tmhert
ዚቅ@mekra_abaw
በእንተ ማርያም ወላዲትከ፤ ወበእንተ ዮሐንስ መጥምቅከ፤ ወበእንተ ኲሎሙ ቅዱሳኒከ፤ ርድአነ ወትረ በኃይለ መስቀልከ፤ ኢታስተኃፍረነ እግዚኦ በቅድሜከ።
@mekra_abaw
ወረብ
በእንተ ማርያም ወላዲትከ ወበእንተ ዮሐንስ መጥምቅከ/፪/
ርድአነ ወትረ በኃይለ መስቀልከ/፪/
@mekra_abaw
ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
በአማን ቃልከ አዳም፤ ዘተሰቀልከ በእንተ ኃጥዓን ከመ ትቤዙ ነፍሰ ጻድቃን፤ በአማን ቃልከ አዳም፤ በአማን ቃልከ አዳም።
@mekra_abaw
መልክአ መድኃኔዓለም
ሰላም ለልብከ እግዚአብሔር ናዝራዊ፤ ነቢይ ወመንፈሳዊ፤ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ህፃን ወአረጋዊ፤ እፎ ቀሰፉከ ካህናተ ይሁዳ ወሌዊ፤ በዓውደ ጲላጦስ መስፍን ከመ ገብር ዓላዊ።
@mekra_abaw
ዚቅ
ወጸሐፈ  ጲላጦስ መጽሐፈ፤ ወይብል መጽሐፉ ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ።
@mekra_abaw
ወረብ
ወጸሐፈ መጽሐፈ ጲላጦስ ወይብል መጽሐፉ ጲላጦስ ዘጸሐፈ/፪/
ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሥ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ/፪/
@mekra_abaw
መልክአ መድኃኔዓለም
ሰላም ለጸዓተ ነፍስከ አመ ዲበ መስቀል ቆመ፤ ወለበድነ ሥጋከ ምዑዝ እንተ ያጥዒ ሕሙመ፤ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከመ ትቤዙ ዓለመ፤ አሜሃ እግዚእየ ፀሐይ ጸልመ፤ ወወርኅኒ ተመሰለ ደመ።
@mekra_abaw
ዚቅ
ምድር አድለቅለቀት ወሰማይ ተሀውከ ሶበ ትወጽእ መንፈሱ ለኢየሱስ።
@mekra_abaw
ወረብ
ምድር አድለቅለቀት ወሰማይ ተሐውከ/፪/
ሶበ ትወጽእ መንፈሱ ለኢየሱስ/፪/
@mekra_abaw
ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
ሶበ ሰቀልዎ ሶበ ሰቀልዎ፤ ሶበ ሰቀልዎ ለእግዚእነ ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ፤ ዬ ዬ ዬ፤ አድለቅለቀት ምድር ወተከሥቱ መቃብራት።
@mekra_abaw
መልክአ መድኃኔዓለም
ሰላም ለግንዘተ ሥጋከ ዘመዓዛሁ ጽጌረዳ፤ ወለመቃብሪከ ዘኮነ ለኢየሩሳሌም በዓውዳ፤ መድኃኔዓለም ክርስቶስ በቅንዓተ ሰይጣን ዘይሁዳ፤ ሞተ ወተቀብረ በመቃብረ ሐዲስ እንግዳ፤ ኀበ ኢተቀብሩ ለሔዋን ውሉዳ።
@mekra_abaw
ዚቅ
አውረድዎ እምዕፅ ዕደው ጻድቃን፤ ወአምጽኡ አፈዋተ ከርቤ ሕውስ ወልብሰ ገርዜን ንጹሕ ለግንዘተ ሥጋሁ።

ወረብ
'አውረድዎ'/፫/ እምዕፅ/፬/
ወአምጽኡ አፈዋተ ከርቤ ሕውስ/፪/
@mekra_abaw
ምልጣን፦
መርሕ በፍኖት ሞገሶሙ ለጻድቃን፤ ዝንቱ ውእቱ መስቀል፤ ለአዳም ዘአግብዖ ውስተ ገነት፤ ወለፈያታዊ ኃረዮ በቅጽበት፤ መድኃኒት ዕፀ ሕይወት፤ ዝንቱ ውእቱ መስቀል።

አመላለስ፦
መድኃኒት ዕፀ ሕይወት፤
ዝንቱ ውእቱ መስቀል
@mekra_abaw
ወረብ፦
ሃሌሉያ መርሕ በፍኖት ሞገሶሙ ለጻድቃን ሞገሶሙ/፪
ዝንቱ ውእቱ መስቀል ለአዳም ዘአግብዖ ውስተ ገነት/፪
@mekra_abaw
እስመ ለዓለም
ብከ ንወግዖሙ ለኲሎሙ ፀርነ ይቤ ዳዊት በመንፈሰ ትንቢት፤ በእንተ ዕፀ መስቀል ዘተሰቅለ ዲቤሁ ቃለአብ፤ ወበስምከ ናኃሥሮሙ ለእለ ቆሙ ላዕሌነ፤ ወካዕበ ይቤ ወወሃብኮሙ ትዕምርተ ለእለ ይፈርሁከ፤ ከመ ያምሥጡ እምገጸ ቅስት፤ ወይድኃኑ ፍቁራኒከ፤ ወንሕነኒ ንትፈሣሕ ዮም ወንግበር በዓለ፤ በዛቲ ዕለት በዓለ እግዚእነ።
@mekra_abaw
ወረብ፦
ብከ ንወግዖሙ ለኲሎሙ ፀርነ ብከ ንወግዖሙ ለኲሎሙ ፀርነ ይቤ ዳዊት በመንፈሰ ትንቢት/ ፪/
በእንተ ዕፀ መስቀል ዘተሰቅለ ተሰቅለ ዲቤሁ ቃለአብ/፪/

በvideo ለማግኘት
https://www.youtube.com/channel/UCfWtKqb7qsxjXey4kN_tykg?sub_confirmation=1
ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@mekra_abaw
@mekra_abaw
@mekra_abaw
802 views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 21:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 22:09:01 "ላለማመን እንጂ ለማመን በዙሪያችን ብዙ ምስክሮች አሉልን!"
(ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ )
❖❖❖

ዐይነ ሥውሩ ቅዱስ ዲዲሞስ በአንድ ወቅት የእግዚአብሔርን መኖር የሚክዱ ተመራማሪዎች የራሳቸውን እውቀት መነሻ በማድረግ የእግዚአብሔርን አለመኖር ከነገሩት በኋላ <እስኪ አንተ እግዚአብሔር መኖሩን በተጨባጭ አስረዳን?> ሲሉ ጠየቁት። ቅዱስ ዲዲሞስ ተመራማሪዎቹ ጭልጥ ብለው መሳሳታቸውን ቢያውቅም በጥሞና ያዳምጣቸው ነበር እንጂ አልተበሳጨም። ለጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት "ምሽት ተመልሳችሁ ኑ" አላቸው።

እነርሱም የቀጠሮአቸውን ሰዓት አክብረው ምሽት ተመልሰው መጡ።ቅዱስ ዲዲሞስም "እስኪ ወደላይ አንጋጣችሁ የሰማዩን ገጽታ ተመልከቱ" አላቸው። እነርሱም እንዳላቸው ሰማዩን ተመለከቱ።እርሱም "በሰማይ ላይ ምን ምን ይታያችኋል?" አለ። እነርሱም "ከዋክብት" ብለው መለሱለት። እርሱም "በስጋዊ አይናችሁ የማየት ችሎታ እነዚህን ክዋክብት በቀን ማየት ትችላላችሁን?" አላቸው። እነርሱም "አንችልም" አሉት። እርሱም "ለምን ማየት ያቅታችኋል?" ሲል ጥያቄውን በጥያቄ ደገመላቸው። እነርሱም "ምክንያቱም ከዋክብትን ለማየት የግድ መምሸት አለበት" አሉት። እርሱም "በእርግጥ ትክክል ናችሁ የመለሳችሁት ምላሽ ትክክል ነው። ይሁን እንጂ በተፈጥሮ እንደምናውቀው የተሰወረውን ነገር ለማግኘት ብርሃን ያስፈልጋል እነዚህን የምታዩአቸው ከዋክብት ለማየት ግን ብርሃን ሳይሆን ጨለማ ሊኖር የግድ ነው። እንደዚሁ ሁሉ እግዚአብሔርንም ለማየት ቁሳዊ ነገርን ማየት በሚቻልበት በሳይንስ መሳሪያና ፍልስፍና ሳይሆን በእምነት ብቻ ማረጋገጥ እንደሚቻል ልነግራችሁ እወዳለሁ።" በማለት አስረዳቸው።

ከዚያም እርሱ በተራው "በሰማያት ገጽታ ላይ ከዋክብት እንደሚታዩ ነግራችሁኛል። ይሁን እንጂ እኔ አይነ ሥውር ስለሆንኩ በምን ታረጋግጥሉኛላችሁ?" ሲል አዲስ የጥያቄ ርእስ ከፈተላቸዉ። እነርሱም ግራ ተጋብተው ምላሽ አጡ እና ከመናገር ይልቅ ዝምታን ምረጡ። እርሱ ግን የእኔ አይነ ስውርነት የከዋክብቱን አለመኖር አያረጋግጥም፤ እኔ አየሁም አላየሁም ከዋክብቱ ዘወትር አሉ። እኔም ምንም ዐይነ ሥውር ብሆንም እንኳን ከዋክብቱን ሳልመለከት እናንተ አይታችሁ በነገራችሁኝ ምስክርነት ብቻ የከዋክብቱን መኖር አምኜ ተቀብየዋለሁ አላቸው። እኔ አንዳች ከዋክብት ሳልመለከት የከዋክብቱን መኖር እንዳመንኩ እናንተም በሥጋዊ አይናችሁ ባትመለከቱም እንኳን በእምነት እግዚአብሔር መኖሩን አታምኑምን? ብታምኑ መልካም ነው።" ሲል በትሕትና ጠየቃቸው። እነርሱም በጥያቄ መልክ ያቀረበላቸውን አስተሳሰቡን እና ምስክርነቱንም ተቀብለው የእግዚአብሔርን መኖር በእምነት አረጋገጥን አሉት። በዚህ የክርክርና የውይይት ሁኔታ ዐይነ ሥውሩ ቅዱስ ዲዲሞስ (በትሕትናውና በድክመቱ) የተናገሩትን አድምጦ የእነርሱን ዕውቀታቸውንና አስተሳሰባቸውን ተጠቅሞ ክብራቸውን ሳይጋፋ የእግዚአብሔርን መኖር በማሳመን ረታቸው። ክርክራቸውም በዚህ ተደመደመ።

ምንጭ ፦ በአቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ በእንግሊዝኛ "CALMNESS" በሚል ተጽፎ በመምሕር ሰለሞን በቀለ "የሕይወት መንገድ" በሚል በአማርኛ ከተተረጎመ መጽሐፍ የተወሰደ ነው።

በvideo ለማግኘት
https://www.youtube.com/channel/UCfWtKqb7qsxjXey4kN_tykg?sub_confirmation=1
ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@mekra_abaw
@mekra_abaw
@mekra_abaw
391 views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 16:37:47 ልብን የሚመስጡ ቆየት ያሉ የመሰንቆ ዘለሰኛ መዝሙር


268 views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 23:01:14 #ደብረ_ዘይት : የዐቢይ ጾም 5ኛ ሳምንት
※※※ ከዳግም ምጽአት በፊት የሚከሰቱተ ድርጊቶች ※※※

#ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ተራራ ማለት ነው፡፡ ይህም ቦታ ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ ካለው ከቄድሮስ ሸለቆ ራቅ ብሎ የሚገኝ፣ ርዝመቱ ፪ ኪሎ ሜትር፥ ከፍታው ደግሞ ከኢየሩሳሌም ከተማ በላይ 62 ሜትር ያህል ከፍታ ያለው ነው፤ቢታንያና ቤተ ፋጌ ከደ/ዘይት ተራራ ሥር የሚገኙ ቦታዎች ናቸው፡፡

በደብረ ዘይት ተራራ ላይ የተፈጸሙ ዋና ዋና ድጊቶች ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፡-
⊚ በደብረ ዘይት ተራራ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ የሚያድርበት፣ የሚያስተምርበት፣ ውሎ የሚያርፍበት ሥፍራ ነበር። ሉቃ ፳፩፥ ፴፯፣ ሉቃ ፳፪፥ ፴፱፣ ዮሐ ፰፥፩፡፡
⊚ የጌታችን በዳግም ምጽአት እንደሚመጣ አስተማሮበታል /ማቴ.24፥1-36/
⊚ 33 ዓመት ከ3 ወር በዚህ ምድር ተመላልሶ ሞቶ ከተነሳ በኋላ ያረገበት ተራራ ነው፤ ‹‹ሁለት ሰዎች ነጫጭ ልብስ ለብሰው በአጠገባቸው ቆመው ታዩአቸው ‹እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እያያችሁት ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ፥ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል› አሏቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ደብረ ዘይት ከሚባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤›› ሐዋ.1፥11-12፣ ሉቃ.24፥51-52/፡፡
⊚ ዳዊት ከልጁ ከአቤሴሎም በሸሸ ጊዜ ወደ ደብረ ዘይት አቀበት ወጥሮ ነበር /2ኛ ሳሙ.15፥30/፣
⊚ ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ሆሳዕና ከደብረ ዘይት ወደ ኢየሩሳሌም ሒዷል /ማር.11፥1/
⊚ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ግርጌ በምትገኘው ለምለም ስፍራ በጌቴ ሴማኒ በአይሁድ ጭፍሮች ተያዘ፡፡ ማር.26፥30-36፤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተቀበረችበት ቦታም በጌቴሴማኒ ነበር፡፡
⊚ በደብረ ዘይት ተራራ ወገብ ላይ በሰፊው ተንጣሎ የሚታይ የአይሁድ መቃብር አለ። ይህን ስፍራ ለመቃብርነት የመረጡበት ምክንያት ወደፊት መሢሑ መጥቶ እስራኤልን ነፃ አውጥቶ ወደ አባቱ ያርጋልና ኋላ ለፍርድ ሲመጣ በመጀመሪያ የሚፈርድበት ስፍራና ሙታንም የሚነሱበትና የሚሰበሰቡበት ስፍራ ይህ በመሆኑ እኛ መሢሐችንን ለማግኘትና ከሙታንም ለመነሳት የመጀመሪያዎቹ እንሆናለን ብለው በማመናቸው ነው። አይሁድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መሢሕ እርሱ ነው ብለው አያምኑም። በመሆኑም እስራኤል ወደፊት አንድ ታላቅ መሢሕ እግዚአብሔር እንደሚልክላቸው ባላቸው ተስፋ መሠረት ገና አሁንም ድረስ መሢሐችንን እንጠብቃለን ይላሉ፤ ነገር ግን አይሁድ በዚህ በትልቁ ነገር ላይ ወደኋላ ቀርተው ተበድለዋል። ቀመረ አዝማናትን ቀንሰዋል፥ ቈነጻጸለዋል፤ የኦሪት መጽሐፋቸው ኦሪተ ብጡል ተብላለች፤ ይመጣል ያሉበትም ዘመን ሳይመጣ ዓለም ከተፈጠረ፥ ዘመን ከተቈጠረ 8ኛ ሺህ ላይ ደርሰናል፡፡ ይሁንና እግዚአብሔር እስራኤልን ብቻ ሳይሆን ዓለሙን ሁሉ እንዲያድን አንድ ልጁን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ልኮልን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶልን በእርሱ ቁስል እኛ ተፈውሰናል፣ በእርሱ ሞት እኛ ሕይወትን አግኝተና/ኢሳ.፶፫፥፬-፮/። ከዚህ በኋላ ሌላ መሢሕ ሌላ አዳኝ ፈጽሞ የለም፡፡


※ #ከዳግም_ምጽአት በፊት የሚከሰቱተ ድርጊቶች /ማቴ. ፳፬፥ ፫-፴፮/ እንደተገለጸው፡-
⊚ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና ብዙዎችንም ያስታሉ
⊚ ጦርነትን የጦርነትንም ወሬ ትሰማላችሁ
⊚ ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣሉ
⊚ በየሀገሩም ረኃብ፣ ቸነፈርም፣ የምድር መናወጥም በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል
⊚ በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ ይገድሏችሁማል፤ ስለ ስሜም በሕዝብ ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ
⊚ በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በእርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ፣ እርስ በእርሳቸውም ይጣላሉ
⊚ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ
⊚ ከዐመፅም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች
⊚ የጥፋት ርኩሰት በተቀደሰችው ሥፍራ ቆሞ ታያላችሁ

⊚ በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናል ካለ በኋላ እስከመጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል በማለት ገልጾላቸዋል።
※የዐቢይ ጾም 5ኛ ሳምንት ደብረ ዘይት በመባል የሚታወቀው የደብረ ዘይት ሰንበት ምጽአት የተነገረበት ከመሆኑም በስተጀርባ በዚህ ዕለት ምጽአት እንደሚሆን ይታመናል፡፡ ከዐቢይ ጾም በ5ኛ ሳምንት መከበሩ #በ5,500 ዓመተ ዓለም የመጣው ጌታ ከዚህም በኋለ በዚሁ ዕለት የሚመጣ መሆኑን ለማመልከት ነው፡፡

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/
#share



በvideo ለማግኘት
https://www.youtube.com/channel/UCfWtKqb7qsxjXey4kN_tykg?sub_confirmation=1
ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@mekra_abaw
@mekra_abaw
@mekra_abaw
784 views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, edited  20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 04:42:23 ልብን የሚመስጡ ቆየት ያሉ የመሰንቆ ዘለሰኛ መዝሙር


702 views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 01:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 13:57:44 ምክረ አበው MEKRA ABAW pinned « መዝሙር ዘደብረ ዘይት እንዘ ይነብር እግዚእነ ውስተ ደብረ ዘይት ወይቤሎሙ ለአርዳኢሁ ዑቁኬ ኢያስሕቱክሙ ወንበሩ ድልዋኒክሙ ብዙኃን ይመጽኡ በስምየ እንዘ ይብሉ አነ ውእቱ ክርስቶስ ወዘአዝለፈ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን ወአመ ምጽአቱሰ ለወልደ እጓለ እመሕያው ይትከወስ ኲሉ ኃይለ ሰማያት ወምድር አሜሃ ይበክዩ ኲሎሙ ኃጥአነ ምድር ወይወርድ እግዚእነ እምሰማይ ዲበ ምድር በትእዛዙ ወበቃሉ ወበአዕላፍ መላእክቲሁ…»
10:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 13:53:10 መዝሙር ዘደብረ ዘይት

እንዘ ይነብር እግዚእነ ውስተ ደብረ ዘይት ወይቤሎሙ ለአርዳኢሁ ዑቁኬ ኢያስሕቱክሙ ወንበሩ ድልዋኒክሙ ብዙኃን ይመጽኡ በስምየ እንዘ ይብሉ አነ ውእቱ ክርስቶስ ወዘአዝለፈ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን ወአመ ምጽአቱሰ ለወልደ እጓለ እመሕያው ይትከወስ ኲሉ ኃይለ ሰማያት ወምድር አሜሃ ይበክዩ ኲሎሙ ኃጥአነ ምድር ወይወርድ እግዚእነ እምሰማይ ዲበ ምድር በትእዛዙ ወበቃሉ ወበአዕላፍ መላእክቲሁ በንፍሐተ ቀርን ዘእምኀበ እግዚአብሔር ይምሐረነ አብ በይእቲ ሰዓት እሞተ ኃጢአት እስመ ገባሬ ሕይወት ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት

ትርጒም፦

ጌታችን በደብረ ዘይት ተቀምጦ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው እወቁ እንዳያስቷችሁ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ ብዙዎች በስሜ ይመጣሉ ትዕግሥቱን ያዘወተረ እሱ ይድናል የሰው ልጅ በሚመጣ ጊዜ የሰማያትና የምድር ኃይል ይናወጣል ያንጊዜ የምድር ኃጥአን ሁሉ ያለቅሳሉ ከእግዚአብሔር ታዞ በሚደረግ የመለከት መነፋት፣ በአዕላፍ መላእክት አጀብ፣ በትእዛዝና በቃል ጌታችን ከሰማይ ወደምድር ይወርዳል በዚያች ሰዓት ከኃጢአት ሞት (በኃጢአት ከሚመጣ ፍርድ) ይማረን የሰንበት ጌታ እሱ ሕይወትን የሚሰጥ ነውና 

የዕለቱ ምስባክ

እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ 
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ መዝ ፵፱፥፫

ትርጒም፦

እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል
አምላካችን ዝም አይልም
እሳት በፊቱ ይነዳል

ምሥጢር፦

እግዚአብሔር በሰባ ዘመን በረድኤት ተገልጦ ይመጣል
መጥቶም ዝም አይልም በበጎዎቹ አድሮ ይፈርዳል አንድም በበጎዎቹ ካህናት አድሮ ክፉዎችን ካህናት ይዘልፋል
እሳት በፊቱ ይነዳል ማለት ክፉዎች የሚጠፉበትን መቅሠፍት መናገር ነው

አንድም እግዚአብሔር አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም በሥጋ ማርያም ይገለጣል 
መጥቶ ዝም አይልም ወንጌልን ያስተምራል አንድም አሌ ለክሙ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን - ጻፎችና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ እያለ ይዘልፋል
አይሁድ የሚጠፉበት መቅሠፍት በፊቱ ነው

አንድም በዕለተ ምጽአት የተወጋበትን ኲናት/ጦር የተቸነከረበትን ቀኖት አስይዞ ይመጣል
ጻድቃንን ንዑ ኀቤየ ብሎ ይጠራል ኃጥአንን ሑሩ እምኔየ ብሎ ያሰናብታል
ጻድቃን የሚድኑበት ሕይወት ኃጥአን የሚቀጡበት መቅሠፍት በፊቱ አለ

የዕለቱ ወንጌል፦

ማቴ ፳፬፥፩ -፴፮

ቅዳሴ፦ ዘአትናቴዎስ


ስለ ደብረ ዘይት በመጠኑ፦

አምስተኛው የዓቢይ ጾም ሰንበት ነው።
የዘይት ተራራ (የወይራ ዛፍ ያለበት) ማለት ነው።
ዳዊት መዝሙር ፳፩ን እየጸለየና እያዘነ ያለ ጫማ የወጣበት ተራራ ነው። ፪ሳሙ ፲፭፥፴፤
ምሥጢረ ምጽአቱ የተነገረበት ተራራ ነው። ማቴ ፳፬፥፫፤
ቅዱሳን ሐዋርያት ልዩ ምስጋና ያቅረቡበት ተራራ ነው። ሉቃ ፲፱፥፴፯፤

ጌታችን ያድርበት የነበረ ተራራ ነው። ሉቃ ፳፩፥፴፯፤
ምሥጢረ ዕርገቱ የታየበት ተራራ ነው። ግብ ፩፥፲3፤

በvideo ለማግኘት
https://www.youtube.com/channel/UCfWtKqb7qsxjXey4kN_tykg?sub_confirmation=1
ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@mekra_abaw
@mekra_abaw
@mekra_abaw
704 views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ