Get Mystery Box with random crypto!

🔴 ምክረ አበው MEKRA ABAW™

የቴሌግራም ቻናል አርማ mekra_abaw — 🔴 ምክረ አበው MEKRA ABAW™ ም
የቴሌግራም ቻናል አርማ mekra_abaw — 🔴 ምክረ አበው MEKRA ABAW™
የሰርጥ አድራሻ: @mekra_abaw
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.32K
የሰርጥ መግለጫ

#አባቶችን_ጠይቅ_ይነግሩሃል
● ጠቢብ ከሰነፍ ጋር ቢጣላ፥ ሰነፍ ወይም ይቈጣል ወይም ይስቃል፥
ደምን ለማፍሰስ የሚሹ ሰዎች ፍጹሙን ሰው ይጠላሉ፥ ደግሞም የቅኑን ሰው ነፍስ ይሻሉ።
ሰነፍ ሰው ቍጣውን ሁሉ ያወጣል፤ ጠቢብ ግን በውስጡ ያስቀረዋል።
○ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕ. 29 ○
ሀሳብ ካላችሁ @habmisget

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-02-24 09:19:44 እየጦሙ አለመጦም

ተወዳጆች ሆይ! እየጦሙ የጦምን ፍሬ ፃማ የማያገኙበት ሁኔታ እንዳለ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያላችሁኝ እንደሆነም፦

➛ ከምግበ ሥጋ ተከልክለን ከምግበ ኃጢአት ያልተከለከልን እንደ ሆነ፣
➛ ከጥሉላት ርቀን ነዳያንን ያልጎበኘን እንደ ሆነ፣
➛ ወይን ከመጠጣት ታቅበን በክፉ መሻት ከመስከር ያልራቅን እንደ ሆነ፣
➛ ጀምበር እስክትጠልቅ ድረስ ከእህል ከውኃ ርቀን በዓይናችን መልካም ያልሆኑ ትዕይንቶችን ከማየት ያልጦምን እንደሆነ ነው ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እመልስላችኋለሁ፡፡ ስለዚህ እየጦሙ እንዲህ አለመጦም እንዳለ ዕወቁ፤ ተረዱም፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

      አምላከ ቅዱሳን እየጦሙ ካለመጦም ይሰውረን!

በvideo ለማግኘት
https://www.youtube.com/channel/UCfWtKqb7qsxjXey4kN_tykg?sub_confirmation=1
ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@mekra_abaw
@mekra_abaw
@mekra_abaw
✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ     ⎙ㅤ    ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
471 views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 09:14:27
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በቦረና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ።

ብፁዕነታቸው በማኅበራዊ የትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በቦረና እና አካባቢው በተከሰተው ድርቅ በርካታ ኢትዮጵያውያን በችግር ውስጥ እንደሚገኙ ከአካባቢው የተገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ ያሉ ሲሆን የተከሰተው ድርቅ ወደ ረሀብ ተለውጦ ከዚህ በላይ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት እንዳያልፍ መላው ኢትዮጵያውያን ድጋፋቸውን ሊያደርጉ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

መንግስትም በአካባቢው ላሉ ወገኖች የሚያደርገውን ድጋፍ በማጠናከር የተቀናጀ የነፍስ አድን ተግባራትን በማከናወን ሊደግፋቸው ይገባል ሲሉም አክለዋል።

በመጨረሻም መላው ኢትዮጵያውያን በአካባቢው ለተከሰተው ድርቅ ትኩረት በመስጠት የወገኖቻችንን ሕይወት ለመታደግ ከጸሎት ጎን ለጎን የተቻላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ አባታዊ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
468 views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 20:44:14
ከ60 second በኋላ ሰለሚጠፋ አሁኑኑ JOIN በማድረግ ተቀላቀሉ በቴሌግራም ምርጥ ከ200 በላይ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት በpdf የተለቀቀበት ብቸኛው ከ54,400member በላይ አንባቢ ኦርቶዶክሳዊያን ያለው ቻናል ነው በእርግጠኝነት ይወዱታል።
ይ ላ ሉን

https://t.me/+qqK-A9uE2dZkNjRk
268 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 12:49:27 የተወለዱበትን ወር በመመረጥ በዓቢይ ፆም መንፈሳዊ መጽሐፍትን በpdf ያንብቡ
ወጣቶችን ያማከሉ ትምህርቶችን በየዕለቱ ይማሩ
#የሚፈልጉትን ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ በpdf ያገኛሉ በተለይ በዚህ በፆም ወቅት ጠቃሚ ቻናል ነው!

መስከረም   ጥቅምት   ህዳር
 
ታህሳስ       ጥር           የካቲት

መጋቢት    ሚያዝያ    ግንቦት

ሰኔ           ሐምሌ      ነሐሴ
                  
                    ጷጉሜ

ከ54,400member በላይ አንባቢ ኦርቶዶክሳዊያን አሉበት የፈለጉትን ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ የቻናሉን ባለቤትም ሆነ ግሩፕ ውስጥ ያሉትን አባላት መጠየቅ ትችላላችሁ
        አሁኑኑ ይ ላ ሉ
            
https://t.me/+qqK-A9uE2dZkNjRk
https://t.me/+qqK-A9uE2dZkNjRk
758 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 08:20:26 ሥርዓተ ማኅሌት ዘኪዳነ ምሕረት 'የካቲት ፲፮'

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፣ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣህል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፣ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።

ዚቅ
ወታስተሥርዪ ኃጢአተ ሕዝብኪ ተበውሐ ለኪ፤ እምአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ ከመ ትኩኒ ተንከተመ ለውልደ ስብእ፤ ለሕይወት ዘለዓለም፤ ለኪ ይደሉ ከመ ትኩኒ መድኃኒቶሙ ለመሐይምናን ሕዝብኪ፤ ኦ መድኃኒተ ኵሉ ዓለም፤ ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰአሊ ለነ ቅድስት።

ነግሥ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
ቅንዑ ለእንተ ተዓቢ ጸጋ መድኃኒት ለነፍስ ወሥጋ፤ እስመ ርቱዓት ፍናዊሃ ጻድቃን የሐውርዎን ወኃጥአን ይስዕንዎን፤ ዘእንበለ ትብጻሕ ግብተ አሠንዶ ፍኖተ፤ ይፈኑ ለክሙ እመቅደሱ ረድኤተ፤ መድኃኒተ መቤዛዊተ እሞ ቅድስተ።

ወረብ
ቅንዑ ለእንተ ተዓቢ ጸጋ መድኃኒት ለነፍስ ወሥጋ ማርያም ድንግል/፪/
እስመ ርቱዓት ፍናዊሃ ጻድቃን የሐውርዎን ወኃጥአን ይስዕንዎን/፪/

መልክአ ኪዳነ ምሕረት
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘአስተማሰልዎ በኮከብ፤ ሶበ ብርሃኖ ተከድኑ ጽልሙታነ ራእይ ሕዝብ፤ ኪዳነ አምላክ ማርያም ወተስፋ መድኃኒት ዘዐርብ፤ ተናዘዘ ብኪ አኮኑ ኅሊና ቀዳማይ አብ፤ አመ እምገነቱ ተሰደ በኀዘን ዕፁብ።

ዚቅ
አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም፤ አመ ይሰደድ እምገነት።

ወረብ
አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አንቲ ውእቱ/፪/
አመ ይሰደድ እምገነት/፬/

መልክአ ኪዳነ ምሕረት
ሰላም ለአዕዛንኪ እለ ተበስራ ኪዳነ፤ እምአፈ ፈጣሪ ወልድኪ ዘባሕርየኪ ተከድነ፤ አምሕለኪ ማርያም ከመ ኢታርእይኒ ደይነ፤ እንበለ ምግባር ባሕቱ እመ ኢይጸድቅ አነ፤ ቦኑ ለከንቱ ኪዳንኪ ኮነ።

ዚቅ
ኪዳንኪ ኮነ ለኃጥአን ቤዛነ፤ ኪዳንኪ ኮነ ኪዳንኪ ኮነ፤ ለኃጥአን ቤዛነ ኪዳንኪ ኮነ።

ወረብ
ኪዳንኪ ኮነ/፮/
ለኃጥአን ቤዛነ ኪዳንኪ ኮነ/፬/

መልክአ ኪዳነ ምሕረት
ሰላም ለመዛርዕኪ ወለኲርናዕኪ ምፅንጋዕ፤ እለ ሐቀፋሁ ለክርስቶስ ባሕርየ መለኮት ኅቡዕ፤ ማርያም ኅሪት እምነ መላእክት ወሰብእ፤ ተዝካረኪ ለእመ ገብረ በተአምኖ ጽኑዕ፤ በመንግሥት ሰማይ ምስሌኪ ይነግሥ ኃጥእ።

ዚቅ
አመ ይነግሥ ወልድ በደብረ ጽዮን፤ ክፍልኒ ድንግል ዕቁም በየማን፤ ምስለ አባግዕ ቡሩካን።

ወረብ
ይነግሥ ወልድ በደብረ ጽዮን አመ ይነግሥ ወልድ/፪/
ክፍልኒ ድንግል ዕቁም በየማን/፪/

ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
መፍትው እንከ ንወድሳ ወንግበር ተዝካራ፤ ለቅድስት ድንግል ዓፀደ ወይን፤ መሶበ ወርቅ እንተ መና።

መልክአ ኪዳነ ምሕረት

ሰላም ለድንግልናኪ መክብበ ሕዋሳት ኅምስ። ወለአቀያጽኪ ክልኤ አዕማደ ነባቢት መቅደስ። ማርያም ታቦት ወጽላተ ኪዳን ሐዲስ። ቅብዕኒ ርጢነ ደም እስከ ሰኮና እግር ወርእስ እስመ ጾም ትፌውስ ሕማማ ለነፍስ።

ዚቅ ፆም ትፌውስ ቁስለ ነፍስ ወታፀምም ኩሎ ፍትወታ ዘሥጋ ትሜኅሮሙ ለወራዙት ፅሙና  እስመ ሙሴኒ ጾመ በደብረ ሲና

ወረብ

ጾም ትፌውስ ቁስለ ነፍስ ወታጸምም ኵሎ ዘሥጋ ፍትወታ×2
ትሜሕሮሙ ጽሙና ጽሙና ለወራዙት×2

መልክአ ኪዳነ ምሕረት
ሰላም ለመልክዕኪ እመልክዐ ሐና ወኤልሳቤጥ፤ ዘብዑድ ስኑ ወልምላሜሁ ፍሉጥ፤ ማርያም ድንግል ድንግልተ አፍአ ወውስጥ፤ ቤዛ ይኩነኒ ኪዳንኪ በገጸ ፈጣሪ ሥሉጥ፤ አመ ወርኀ ነጊድ የኃልቅ ወይጸራዕ ሤጥ።

ዚቅ
ቃለ እግዚአብሔር እምድንግል አስተርአየ፤ ኤልሳቤጥ ኮነት ዓባየ፤ እስመ ወለደት ነቢየ።

ወረብ
እምድንግል አስተርአየ ቃለ እግዚአብሔር/፪/
ኤልሳቤጥ ኮነት ዓባየ እስመ ወለደት ነቢየ/፪/

እስመ ለዓለም ዘወረደ

ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት ምድር ሠናይት ወአኮ ከመ ምድረ ግብፅ ምድር ሠናይት እንዘ ዘልፈ ይሄውፃ እግዚአብሔር እምዓመት እስከ ርዕሰ ዓውደ ዓመት ምድር ሠናይት ወአኮ ከመ ምድረ ግብፅ ያዕቆብኒ ይቤ ርኢኩ ሰዋስወ ዘሰማይ ዝየ ይትሐነፅ ቤተ እግዚአብሔር ሐነፀ መቅደሶ በአርያም ዳዊትኒ ይቤ ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ዘዓለም ዝየ የኃድር እስመ ኃረይክዋ ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ ሥርጉት አረፋቲሃ ለቤተ ክርስቲያን በእንቊ ሰንፔር ወበጳዝዮን ሥርጉት በከርከዴን ወበመረግድ (ሥ )በአስማተ ፲ ወ ፭ቱ ነቢያት (ሥ) በአስማተ ፲ ወ፪ ሐዋርያት (ሥ ዓረ ለቤ ክር) ሐጹር የዓውዳ ወጽጌረዳ ብእሲ ተወልደ በውስቴታ ንጉሠ ፳ኤል አልቦ ማኅለቅት ለመንግስቱ  ን ህየ ማኅደሩ ለልዑል  ን መድኃኔዓለም እግዚአብሔር ኃደረ ላዕሌሃ ኪያሃ ዘሠምረ ሀገረ::

አንገርጋሪ
ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር፤ ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ፤ አንቲ ምስራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ፤ አማን፤ ኪዳንኪ ኢየኃልቅ።

አመላለስ
'አማን በአማን'/፪/ ኪዳንኪ 'አማን በአማን'/፪//፩/
ኪዳንኪ ኢየኃልቅ/፬/

ወረብ
ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ/፪/
አንቲ ምሥራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ ምሥራቅ ደብረ ሕይወት/፪/

ቅንዋት
ዕፎኑ ንዜኑ ዕፎ ዕንጋ ንዜኑ፤ እንበለ ይትመሰው ማኅፀነ ድንግል ኢማሰነ፤ ዕፎ ዕንጋ ማኅፀነ ድንግል ፆሮ፤ ዘኲለሄ ሀሎ ወአልቦ አመ ኢሀሎ፤ ዕፎ ዕንጋ ማኅፀነ ድንግል ፆሮ፤ ሰማይ ወምድር ዘኢያገምሮ፤ ዕፎ ዕንጋ ማኅፀነ ድንግል ፆሮ፤ ነቢያት ቀደሙ አእምሮ፤ ዕፎ ዕንጋ ማኅፀነ ድንግል ፆሮ፤ ሐዋርያት ተለዉ አሠሮ፤ ዕፎ ዕንጋ ማኅፀነ ድንግል ፆሮ፤ ዕንባቆም ነቢይ ዘአንከረ ግብሮ፤ ዕፎ ዕንጋ ማኅፀነ ድንግል ፆሮ፤ ዕሌኒ ንግሥት ሐሠሠት መስቀሎ፤ ዕፎ ዕንጋ ማኅፀነ ድንግል ፆሮ፤ ወለዕውርኒ ዘከሠተ ዓይኖ፤ ዕፎ ዕንጋ ማኅፀነ ድንግል ፆሮ፤ ወለሰይጣንኒ ዘቀጥቀጠ ኃይሎ፤ ዕፎ ዕንጋ ማኅፀነ ድንግል ፆሮ፤ ፆረቶ እግዝእቱ ለአዳም ወአግመረቶ ማርያም።
Share
በvideo ለማግኘት
https://www.youtube.com/channel/UCfWtKqb7qsxjXey4kN_tykg?sub_confirmation=1
ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@mekra_abaw
@mekra_abaw
@mekra_abaw
957 views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 08:55:25 በዓቢይ ፆም የማንን የንስሐ መዝሙር ማዳመጥ ትፈልጋላችሁ የፈለጉትን መርጠው ያዳምጡ
                     
t.me/ethiopian_Orthodox_Mezmur

በዚህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ የቸብቸቦ እና የንስሐ መዝሙር የሚያገኙበት ቻናል ነው።
                   ይ ላ ሉን
የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር
  
➯የቴዎድሮስ ዮሴፍ መዝሙር
➯የዳግማዊ ደርቤ መዝሙር
➯የቀዳሜጸጋ መዝሙር
➯የዘማሪት ለምለም ከበደ መዝሙር
➯የኪነጥበብ መዝሙር
➯የይልማ ኃይሉ መዝሙር
➯የዘማሪ አቤል መክብብ መዝሙር
➯የዘማሪት ትንቢት ቦጋለ

እነዚህንና የተለያዩ መዝሙር ያገኙበታል ይቀላቀሉ።
645 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 05:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 08:55:25 እድሜህ/ሽ ስንት ነው?

የእርሶ እድሜ ከታች ካሉት ምርጫዎች በየትኛው ይመደባል?
የራስዎን ዕድሜ በመምረጥ የእርሶን ዕድሜ ያማከሉ ትምህርቶችን በየዕለቱ ይማሩ
#የሚፈልጉትን ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ በpdf ያገኛሉ በተለይ በዚህ በፆም ወቅት ጠቃሚ ቻናል ነው!

ከ53,400member በላይ አሉበት የፈለጉትን ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ የቻናሉን ባለቤት መጠየቅ ትችላላችሁ
        አሁኑኑ ይ ላ ሉ

https://t.me/+qqK-A9uE2dZkNjRk
https://t.me/+qqK-A9uE2dZkNjRk
583 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 05:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 08:41:57 ዘወረደ (የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት )

የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ይባላል፡፡
‹‹ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ›› የሚልና ይህንን የመሳሰለ ጌታ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ ሌላም ስም አለው #ጾመ_ሕርቃል ይባላል፡፡ ይህ ጾም የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን #ሕርቃል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

#ሕርቃል ማን ነው? ለምንስ በስሙ ተሰየመ?
በ614 ዓ.ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም ቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲየኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል። እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉን ያለበትን አጥቶ ሲቸገር መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቁስጥንጥንያ ተመለሰ፡፡ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ ይህን ለማሰብ ለማስታወስ በተጨማሪ በኃጢአት ላይ ድል እንድናገኝ መንፈሳዊ ጦር በውስጣችን እንዲበዛልን መስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን ለሕርቃል ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳት መንፈሳዊ ኃይልን ስጠን እያልን እንጾመዋለን፡፡

በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ እዚህ ላይ በዚያን ጊዜ ለሕርቃል ሕዝቡ ሱባኤ ይዞለታል፡፡ ዛሬም እኛ ለቤተክርስቲያን ያደረግነውን በማሰብ እግዚአብሔር አምላክ ለሕርቃል የሰጠውን በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትን ለእኛም እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ስለሆነ የመጀመሪያውን ሳምንት በሕርቃል ሰይመን ጾሙን እንጾማለን፡፡ የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡

«ዘወረደ» ማለትም በቀጥታ፣ ቃል በቃል ሲተረጐም «የወረደ» ማለት ነው፡፡ ይህም በምስጢሩ አምላክ ወልደ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም በቅዱስ ፈቃዱ ሰው ሆኖ ከሰማየ ሰማያት፣ ከባሕርይ ልዕልናው በትሕትና ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ ይህም የሚታወስበት፣ የሚወሳበት የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት ነው፡፡ ዮሐ.3፥13፡፡

ሳምንቱ ሙሴኒ የተባለበትም ምክንያት በዚሁ ሳምንት መጀመሪያ የሰኞ ዕዝል «ከመዝ ይቤ ሙሴ ፀዓቱ እምትእይንት» «ሙሴ ከከተማ መውጣቱ እንደዚህ ነው አለ» ስለሚል እንደዚሁም የዚሁ ዕለት ማለት የሰኞ አቡን «ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት ምድር ሰናይት» እያለ የሙሴን ታሪክ ስለሚያጠቃቅስ ሳምንቱ ሙሴኒ ተባለ፡፡ነቢያትም አርባ አርባ ቀን ጾመው ከአለፉ በኋላ የሙሴ ሕግና ትንቢተ ነቢያት ፈጻሚ የሆነው ምላካችን እንደ እነሱ 40 ቀንና 40 ሌሊት መጾሙን የሚያስታውስ ነው፡፡ /ዘፀ.24፥18፤ 1ኛ.ነገ.19፥8፤ ማቴ. 4፥1-4/፡፡
524 views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 08:41:41 ዘወረደ (የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት )

567 views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 21:35:31 እድሜህ/ሽ ስንት ነው?

የእርሶ እድሜ ከታች ካሉት ምርጫዎች በየትኛው ይመደባል?
የራስዎን ዕድሜ በመምረጥ የእርሶን ዕድሜ ያማከሉ ትምህርቶችን በየዕለቱ ይማሩ
#የሚፈልጉትን ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ በpdf ያገኛሉ በተለይ በዚህ በፆም ወቅት ጠቃሚ ቻናል ነው!

ከ53,400member በላይ አሉበት የፈለጉትን ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ የቻናሉን ባለቤት መጠየቅ ትችላላችሁ
        አሁኑኑ ይ ላ ሉ

https://t.me/+qqK-A9uE2dZkNjRk
https://t.me/+qqK-A9uE2dZkNjRk
271 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ