Get Mystery Box with random crypto!

🔴 ምክረ አበው MEKRA ABAW™

የቴሌግራም ቻናል አርማ mekra_abaw — 🔴 ምክረ አበው MEKRA ABAW™ ም
የቴሌግራም ቻናል አርማ mekra_abaw — 🔴 ምክረ አበው MEKRA ABAW™
የሰርጥ አድራሻ: @mekra_abaw
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.32K
የሰርጥ መግለጫ

#አባቶችን_ጠይቅ_ይነግሩሃል
● ጠቢብ ከሰነፍ ጋር ቢጣላ፥ ሰነፍ ወይም ይቈጣል ወይም ይስቃል፥
ደምን ለማፍሰስ የሚሹ ሰዎች ፍጹሙን ሰው ይጠላሉ፥ ደግሞም የቅኑን ሰው ነፍስ ይሻሉ።
ሰነፍ ሰው ቍጣውን ሁሉ ያወጣል፤ ጠቢብ ግን በውስጡ ያስቀረዋል።
○ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕ. 29 ○
ሀሳብ ካላችሁ @habmisget

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 40

2022-07-10 15:18:42 በማርያም ይሄን ቻናል ሳታዩ እንዳታልፉት JOIN የምትለውን ብቻ ይንኳት።
ለጥበብ አፍቃርያን በሙሉ
ስለ ጥበብ ሲነሳ ተዋነይን ልንዘነጋው አንችልም

የተዋነይን ጥበብ ለማወቅ ሐሽማልን ያንቡ
ሞትን ለሰባት አመት ያስቀረ ጠቢብ

ለካህናትና ለዲያቆናት እንዲሁም ለጥበብ ፈላጊዎች በሙሉ የተከፈተ ቻናል ሁላችሁም ተቀላቀሉ

@Tibebe_Tewaney
@Tibebe_Tewaney
@Tibebe_Tewaney

https://t.me/+ieH42z8ELW40ODdk
2.8K viewsሚኤል አናንኤል, 12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 02:47:50 እውነተኛ ወዳጅ፥ ወዳጅ መኾኑ የሚታወቀው ጓደኛውን መገሠጽ ሲችል ነው፡፡ ኹላችንም በየጊዜው ኃጢአት እንሠራለን፡፡ አብዛኞቻችን ደግሞ ኃጢአታችንን እንዳላየነው ኾነን ለማለፍ እንጥራለን፡፡ ለራሳችን ይቅርታ እንቸራለን፡፡ ወይም ምንም እንዳላጠፋ ሰው ለመምሰል እንሞክራለን፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሰዓት እውነታውን በትክክል እናይ ዘንድ ዓይናችንን የሚከፍት እውነተኛ ወዳጅ ያስፈልገናል፡፡

አንተ ሆይ! እስኪ ራስህን መርምር፡፡ ጓደኛህ እውነታውን እንዲያይ ታደርጋለህ? ጓደኛህ ኃጢአት ሠርቶ ሲያበቃ ለራሱ ይቅርታ ሲያደርግ ይቅርታው ያደረገው ይቅርታ ትክክለኛ እንዳልኾነ እንዲያውቅ ታደርጓለህን? እንዲህ እውነታውን ስትነግረው ምናልባት ጓደኛህ አለአግባብ ሊቈጣህ ይችላል፡፡ ታዲያ ሲቈጣህ ለመታገሥ ዝግጁ ነህን? ወይስ ከዚህ በተቃራኒ የጓደኛህን ኃጢአት አይተህ እንዳላየህ ነው የምትኾነው?

ጓደኛ ስንመርጥ ከእኛ ጋር እውነተኛ ወዳጅ ሊኾን የሚገባውን መኾን አለበት፤ ስንቈጣው እንኳን ቁጣችንን ታግሦ ስናጠፋ የሚያርመን ሊኾን ይገባል፡፡ እንደዚህ ካልኾነ ጓደኝነት ጥልቀት አይኖረውምና፤ ጓደኞች ነን መባባላችን ጥቅም የለውምና፡፡

ልናውቀው የሚገባን ነገር ግን አለ፡፡ ጓደኛችን በሚያጠፋበት ሰዓት ተግሣጽ አስመስለን እንዲሁ ክብሩን በሚነካ መልኩ ልንናገረው አይገባንም፡፡ ተግሣጻችን ኹልጊዜ እውነቱን ብቻ እንጂ የተጋነነና ሌላውን መልካምነቱን የሚክድ መኾን የለበትም፡፡ ጥፋቱን ስንነግረው ኹልጊዜ በቀና ልብ እንደምንነግረው እርግጠኛ እንዲኾን ማድረግ አለብን፡፡ ይህን የምናደርገው ከፍቅራችን የተነሣ እንጂ ከቅናት ወይም ከንቀት እንዳልኾነ እንዲያውቅ ማድረግ አለብን፡፡ እውነተኛ ወዳጅነት ማለት ይህ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@mekra_abaw
@mekra_abaw
@mekra_abaw
3.0K views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 23:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 13:49:19 "አንተ ራስህ ለገዛ ወንድምህ ጨካኝና ይቅር የማትል ኾነህ ሳለስ እግዚአብሔር እንዲራራልህና እንዲምርህ እንዴት መለመን ይቻልሃል?

"ባልንጀራህ ምናልባት ንቆህ ሊኾን ይችላል፡፡ አዎ! አንተ ግን እግዚአብሔርን ኹልጊዜ እንደናቅኸው ነው፡፡ በባልንጀራና በእግዚአብሔር መካከልስ ምን ንጽጽር አለ? ባልንጀራህ ምናልባት ጉዳት ሲደርስበት ሰድቦህ ይኾናል፤ አንተም በዚህ ተበሳጭተህ ይኾናል፡፡ አንተ ግን ምንም ሳይጎዳህና በአንተ ላይ ክፉ ሳያስብ ይልቁንም ዕለት ዕለት በረከቱን እየተቀበልክ እያለ እግዚአብሔርን ሰድበኸዋል፡፡ እንግዲህ ተመልከት! ነቢዩ፡- “እመሰ ኃጢአተኑ ትትዐቀብ እግዚኦ መኑ ይቀውም - አቤቱ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ ማን ይቆማል?” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የምንፈጽመውን በደል ቢመረምር ኖሮ አንዲት ቀንስ እንኳን በሕይወት መቆየት አንችልም ነበር (መዝ.129፡3)፡፡

እያንዳንዱ በደለኛ ሰው ለራሱ የሚያውቀውንና ሌላ ሰው የማይመሰክርበትን እግዚአብሔር ብቻዉን ግን የሚያውቀውንስ ይቅርና የተገለጠውና ሰው ኹሉ የሚያውቀው ኃጢአታችንን እንኳን እግዚአብሔር ቢቈጣጠር ኖሮ ከእነዚህ ኃጢአቶች በኋላ የምንጠብቀው ምንድን ነው? እግዚአብሔር ንዝህላልነታችንንና ጸሎት ስናደርስ የምናሳየው ግድየለሽነታችንን፣ ሠራተኞች ለአሠሪዎቻቸው ወታደሮችም ለአለቆቻቸው ጓደኛሞች ለጓደኞቻቸው የሚያሳዩትን ፍርሐትና ክብር ያህልስ እንኳን ለጸሎትና ለልመና በፊቱ በቆምን ጊዜ አለማሳየታችንን ቢቈጣጠር ኖሮ ምን ነበር የምንኾነው?

አንተ ከጓደኛህ ጋር ስትነጋገር ለምታደርገው ማንኛውም ነገር ትጠነቀቃለህ፡፡ ስለ በደሎችህ እግዚአብሔርን ስትጠብቀው፣ ለብዙ መተላለፎችህ ይቅርታን ስትጠይቀው፣ ሥርየትን ለማግኘት ስታሳስበው ግን [በፊቱ ላይ] ኹልጊዜ ግድየለሽ ትኾናለህ፡፡ ጉልበትህ በምድር ላይ ተንበርክኮ ሳለ ልቡናህ ግን እዚህም እዚያም፣ በገበያ ሥፍራም፣ በቤት ውስጥም ይዋልላል፤ ከንፈርህ በከንቱና እንዲሁ ያነበንባል፤ ይህን የምንፈጽመው ደግሞ አንዴ ወይም ኹለቴ ሳይኾን ኹልጊዜ ነው።

እንግዲህ እግዚአብሔር ይህን ብቻ እንኳን ቢመረምር ይቅርታን ወይም ምሕረትን እንደምናገኝ ታስባለህን? በእውነት አይመስለኝም!"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
#ትምህርት_በእንተ_ሐውልታት_መጽሐፍ
ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው
ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@mekra_abaw
@mekra_abaw
@mekra_abaw
3.2K views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 20:16:31 “ለድሃው ልብሶቹ ቢያድፉበት በውሃ እጠብለት አዲስም ልብስ ገዝተህ አልብሰው፤ ደሃው ወደ ቤትህ የገባ እንደሆነ
እግዚአብሔር ወደቤትህ ይገባል፤ በመኖሪያህም ያድራል፡፡
ከመከራ ከስቃይ ላላቀቅኅው ለዚያ ድሃ እግዚአብሄርም አንተን ከሚመጣብህ መከራና ስቃይ ያላቅቅሃል፡፡

የእንግዳውን እግር አጠብክን? የበዛ ሃጢአትህን አጥበህ
አስወገድከው፡፡ ለድሃው ይመገብ ዘንድ ማዕድን አቀረብክለትን? እነሆ እግዚአብሄር አብ ከማዕድህ በላ፤ ክርስቶስም ለደሃው ካቀረብክለት ውሃ ጠጥቶ ረካ ፤ መንፈስ ቅዱስም ማደሪያ ቤቱ አደረገህ፡፡

ደሃው ባቀረብክለት ማዕድ በልቶና ጠጥቶ ደስ አለውን? ጌታ
ክርስቶስን ደስ አሰኘኅው፤ እርሱ ያደረክለትን መልካም ችሮታ የሚረሳ አይደለምና በመላእክትና በሰወች ፊት ያከብርሃል፡፡ ከረሃቡ እንዳሳረፍከው በመጨረሻው ቀን ይመሰክርልሃል ለጥማቱ የሚጠጣ ስላቀረብክለት በመላእክቱ ፊት ያመሰግንሃል፡፡

ልጄ ሆይ ፦ መልካም ዘርን በደስታና እግዚአብሄርን ተስፋ
በማድረግ ዝራ ፡ ልፋትህም ፍሬ ይስጥህ”

(ስብከት ወተግሳጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ መጽሐፍ የተወሰደ)

ቻናሉን ይቀላቀሉ፦
ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@mekra_abaw
@mekra_abaw
@mekra_abaw
3.7K views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 06:25:31 «ለመተኛት ወደ አልጋህ ባመራህ በቀረብህ ጊዜ አልጋዬ፡ ምን አልባት በዚህ ሌሊት ለእኔ መቃብሬ ልትኾኚ ይኾን ይኾናል፤ በጊዜአዊው ዕንቅልፍ ፈንታ በዚህ ሌሊት ያኛው እንቅልፍ (ሞት) ይመጣብኝም እንደ ኾነ አላውቀውም በላት ።ስለዚህ ነጻ እግሮች እያሉህ ከመልካም ሥራ በኋላ ሩጥ፤ ከታሠሩ መፈታት በማይችሉበት ማሰሪያ ከመታሠራቸው በፊት፡፡ የእጆችህ ጣቶችም እስካሉህ ድረስ ሞት ከመምጣቱ በፊት በጸሎት ፊትህንና መላ ሰውነትህን በተእምርተ መስቀል አማትብ፡፡ ዐይኖች እስካሉህ ድረስ በአቧራ ከመሽፈናቸው በፊት በእንብዕ(በእንባ) ምላቸው።ሰው ሆይ ከዚህ ዓለም መለየትህን አስብ፣ እንዲህም በል፡- እነሆ የታዘዘ መልአክ ከበር ቆሞአል (ደርሶአል)፣ እኔንም ይከተለኛል። ለምን ሊል ዘሊል እኾናለሁ? መመለሻ የሌለው ዘለዓለማዊ መንገድ አለ፡፡መለኮት ደግነት የተነሣ የሰውን ልብ የሚገዛውና ነፍስን ወደ ሕይወት የሚመራት የመጀመሪያው ትምህርት ተዘክሮተ ሞት ነው።.ተዘክሮተ ሞት በሰይጣን እጅግ በብዙ ይጠላል፡፡ እርሱም ከሰው ተዘክሮን ለመንቀል በሙሉ ኃይሉ መሞከርን አይተዉም፡፡ የሚቻለውስ ቢኾን በምድራዊ ሕይወት አሳብ ተብትቦ ተዘክሮተ ሞትን ከሰው ልብ (አእምሮ) ለማስወገድ ምድራዊ መንግሥታትን ለሰው በሰጠው ነበር፡፡ አታላዩ ሰይጣን ተዘክሮተ ሞት በሰው ሁልጊዜም ካለ፣ አሳቡ ለአሁኑ ሕይወት መታለሎች የተጣበቀ ኾኖ እንደማይቀር አልያም የሰይጣን ማታለሎች ሰውን ሊቀርቡት እንደማይችሉ ያውቃል፡፡"

#ማር_ይስሐቅ_ሶርያዊ

ቻናሉን ይቀላቀሉ፦
ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@mekra_abaw
@mekra_abaw
@mekra_abaw
4.5K views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 03:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 23:23:31 #ቤተክርስቲያን_እና_መጽሐፍ_ቅዱስ

መጽሐፍ ቅዱስ የቤተ ክርስቲያን የዶግማዋ፤ የቀኖናዋ፤ የትውፊቷ፤ የባህሏ እንዲሁም የዝማሬዋ ወዘተ መገኛ ነው፡፡
በጥቅሉ መጽሐፍ ቅዱስ ፡-
1ኛ.የመሰረተ እምነትዋ(ዶግማ) ምንጭ እና መገኛ ነው
2ኛ.የሥርዓትዋ ምንጭ ነው
3ኛ የባህልዋ ምንጭ ነው
4ኛ የዝማሬዋ ምንጭ ነው
5ኛ የጸሎትዋ ምንጭ ነው፡፡

1ኛ #የመሰረተ_እምነትዋ_ምንጭ_ነው፡-
ይህንን ስንል የቤተክርስቲያን መሠረተ እምነት የምንለው አምስቱን አዕማደ ምስጢር እና ሰባቱን ምስጢራተ ቤተክርስቲያን ራሱን መጽሐፍ ቅዱስንም ጨምሮ ነው፡፤ ቅዱስ ጳውሎስም አምስቱ አዕማደ ምስጢራት የቤተክርስቲያን መሰረታዊ የእምነት ትምህርተ እንደሆኑ ለማስረዳት‹‹በማኅበር እልፍ ቃላት ከምናገር ይልቅ በአእምሮዬ አምስት ቃላትን ብናገር እወዳለሁ›› ብሎ ያስተማረው 1ቆሮ14÷19፡፡ እነዚህም በጥቂቱ ሲዘረዘሩ፤ ስለ ምስጢረ ሥላሴ ዘፍ1÷26 ዘፍጥ18÷1 ማቴ 28÷19 ቆሮ13÷13 እና በመሳሰሉት ተዘርዝሯል፡፡ ምስጢረ ሥጋዌ የአምላክ ሰው መሆን ምስጢር ነው ይህንንም የተማርነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው መዝ. 8÷2 መዝ.113÷3 መዝ131÷6 ሉቃ2÷10 ዮሐ1÷14፤ የምስጢረ ጥምቀትንም ትምህርት የተማርነው ከመጽሐፍ ቅዱስ መሆኑን ለማየት እነዚህንና የመሳሰሉትን ጥቅሶች ማየት ጠቃሚ ነው ማቴ. 3÷16 ዮሐ 3÷5 ማቴ 28÷19 ምስጢረ ቁርባንንም የተማርነው እንዲሁም የምንማረው እና የምናስተምረው ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው ዘጸ12÷1 ማቴ. 26÷26 1ኛቆሮ. 11÷26 ምስጢረ ትንሳኤ ሙታንንም የተማርነው የምንማር እና ምናስተምረው በመጽሐፍ ቅዱስ ነው 1ተሰ. 4÷13-17 2ኛተሰ.2÷1 የምስጢራተ ቤተክርስቲያን መገኛ ምንጭ መሰረትም መጽሐፍ ቅዱስ ነው ይህንንም በምሳሌ እንይ ምሳሌ የምስጢረ ጥምቀት ሥርዓትን በተመለከተ ማቴ 28÷19 ሮሜ 6÷3 የምስጢረ ሜሮንን ሥርዓት በተመለከተ ደግሞ ዘፍ 28÷18 ያዕቆብ ተንተርሶት የነበረውን ድንጋይ ዘይት መቀባቱ አዲስ ቤተክርስቲያን ሲመረቅ በሊቃነ ጳጳሳቱ አማካይነት በሜሮን ለመክበሩ፤ ምዕመናን በሜሮን አማካኝነት ጸጋ መንፈስ ቅዱስን እንደሚያገኙ የሚያስረዳ ትምህርት ነው፡፡ የምስጢረ ቁርባንን ሥርዓት በተመለከተ ዮሐ. 6÷53 መዝ 4÷7 1ኛቆሮ.11÷27 ላይ ተጽፏል፡፡ የምስጢረ ክህነት ትምህርትንም ያገኘነው ከሊቀ ካህናት ክርስቶስ ነው፡፡ ማቴ16÷19 በምድር የምታስረው በሰማይ የታሰረ ይሆናል በምድር የምትፈታው በሰማይ የተፈታ ይሆና በማለት ዮሐ. 20÷22 ስለ ሥርዓተ ክህነት ሲመተ ክህነት 1ኛጢሞ.3÷8 ምስጢረ ንስሐን በተመለከተ ደግሞ በማቴ 9÷13 ሕዝ.18÷27 ሉቃ.15÷4 ማቴ.8÷4 ራስህን ለካህን አሳይ በማለት ሊቀ ካህናት መምህራችን እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡ የምስጢረ ተክሊልን ሥርዓት በተመለከተ ማቴ.19÷5 ሁልጊዜ በሥርዓተ ተክሊል ላይ የሚነበበብ ነው፡፡ኤፌ.5÷28-32 የምስጢረ ቀንዲልን ሥርዓት በተመለከተ ኢሳ.1÷6 ያዕ.5÷14 ተጽፎ እናገኛለን፡፡

2ኛ- #የቤተክርስቲያን_የሥርዓትዋ_ምንጭ_ነው፡-
የሥርዓተ ቅዳሴው መገኛ ምንጩ በሥርዓተ ቅዳሴ ሚከናወነው ሚነበበው ሚዜመው ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ በቅዳሴ መግቢያ ላይ ምዕመናኑ ከካህናቱ ጋር በኅብረት ‹‹በቅዳሴ ወቅት ከምዕመናን መካከል ወደ ቤተ ክርስቲያን የገባ ቢኖር ሥርዓተ ቅዳሴው እስኪያልቅ የማይታገስ ቅዱሳት መጻህፍትን የማይሰማ ቅዱስ ቁርባንን የማይቀበል ቢኖር ከቤተ ክርስቲያን ይውጣ ሐዋርያት አብጥሊስ በተባለ መጽሐፋቸው እንዲህ እንዳስተማሩን›› እያልን ምንዘምረው ከሰማንያ አንዱ በመጽሐፈ አብጥሊስ ቅዱሳት መጻሕፍት በአንዱ እንዲህ ስለተጻፈ ነው፡፡ ስለዚህ መጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ መሐሉ መጽሐፍ ቅዱስ ማጠናቀቂያው መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ በሥርዓተ ቅዳሴ መጽሐፍ ቅዱስ የማይነበብበት ክፍል የለም፡፡ የሐዲስ ኪዳንን ቅዳሴ የጀመረውም ጌታ ነው፤ ‹‹አመስግኖም ይህ ሥጋዬ ነው ብሎ ሰጣቸው›› እንዲል ማቴ 26÷26፡፡ መንበሩን እየዞሩ የሚያጥኑት ሲያጥኑም የሚናገሩት በመጽሐፈ ኢያሱ ምዕራፍ 6÷13-15 የተጻፈውን እየደገሙ ነው፡፡ የዕጣኑም ሥርዓት በራእ8÷3-4 ካህናት የሚለብሱት ልብስ፤ ሲካኑ የሚፈጸመው ሥርዓት መሠረቱ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ ዘጸ 39÷1 ዮሐ 20÷22

3ኛ- #የቤተክርስቲያን_የባህሏ_ምንጭ_ነው፡-
የለቅሶ ባህል ምንጩ መጽሐፍ ቅዱስ ነው ሰው ሲሞት ፍትሐት ምንፈታው ከእናንተ ያዘነ ቢኖር ይጸልይ መጽሐፍ ቅዱስ ስላስተማረን ነው ያዕ5÷13 ሥርዓተ ታቦት ዘንግስ፤ ታቦታቱን ካህናቱ አክብረው ሲወጡ ምዕመኑ እልል እያለ እየተከተለ የሚሄደው ለታቦቱ የሚሰግደው በታቦቱ ላይ ስመ እግዚአብሔር ስለሚጻፍ ለሱም መስገድ እንደሚገባን መጽሐፍ ቅዱስ ስላስተማረን ነው ፊል2፤10 ታቦታቱን ተከትለን የምንዞረው ተከተሉ ተብለን መበጽሐፍ ቅዱስ ስለታዘዝን ነው ኢያሱ3፤3 የምግብ ሥርዓታችን ምንጩ መጽሐፍ ቅዱስ ነው ይህን ብሉ ይህን አትብሉ ተብለን ታዘናልና ዘሌ11፤1ጀምሮ፡፡ የበዓላቶቻችን ምንጭ መገኛ መሰረቱ መጽሐፍ ቅዱስ ነው ዘሌ 23÷1

4ኛ. #የጸሎትዋ_ምንጭ_መገኛው_ነው፡-
ከጸሎት መጻህፍት አንዱና ዋነኛው መዝሙረ ዳዊት ሲሆን መዝሙረ ዳዊት በቤተክርስቲያን የማይጸለይበት አንድም ቀን የለም አይኖርምም፡፡ ሌላው በሁሉም ምዕመናን የሚወደድ ጸሎት እና የጸሎት መጽሐፍ ውዳሴ ማርያም ምንጩ መጽሐፍ ቅዱስ ነው ለምሳሌ የሐሙስ ውዳሴ ማርያም ለእስራኤል የነገሠ ዳዊት ከቤተልሔም ምንጭ ውሃ ሊጠጣ ወደደ 2ኛ ሳሙ 23÷15-17፤ 1ኛዜና.11÷17-19

5ኛ- #የዝማሬዋ_ምንጭ_መሰረት_ነው፡-
በቤተክርስቲያናችን ትምህርት የዜማ ቤት ትምህርት ከውዳሴ ማርያም ቀጥሎ የሚሰጠው የዜማ ትምህርት መዝሙረ ዳዊት ነው የቅዱስ ያሬድ አምስቱ የዜማ መጻህፍቶቹ ምንጭ መገኛቸው መጽሐፍ ቅዱስ ነው ለዚያውም የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ለምሳሌ ማቴ24 ላይ ጌታችን ምሳሌውን ከበለስ ተማሩ ያለውን ቅዱስ ያሬድ በድጓዋው በለስ ያላት ቤተ እስራኤልን ነው ብሎ ተርጉሞታል፡፡
የሰዓታት ዜማ ምንጭ መገኛው መጽሐፍ ቅዱስ ነው ‹‹ኢሰማዕነ ወኢርኢነ ወኢነገሩነ አበዊነ ከመቦ ባዕድ አምላክ ዘእንበሌከ አልሰማንም አላየንም አባቶቻችንም አልነገሩንም ካንተ በቀር ሌላ ባእድ አምላክ አናመልክም›› ይህም በዘዳ. 4÷35 ተጽፏል፡፡

(በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ዋና ክፍል የተዘጋጀ፡፡)
ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@mekra_abaw
@mekra_abaw
@mekra_abaw
5.6K views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 20:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 14:51:56 አንድ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ቆመና "ጌታ ሆይ ተመልከት እጆቼ ንፁሃን ናቸው። ደም አላፈሰሱም የሰው ገንዘብ አልቀሙም" አለ እግዚአብሔርም መለሰለት "ልጄ ሆይ! አዎ እጆችህ ንፁሃን ናቸው ግን ባዶዎች ናቸው" አለው ይባላል።

ያልገደለ እጅ ግን ያላዳነ፣ ያልሰረቀ አጅ ግን ያልመፀወተ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ የለውም። እውነተኛው መልካምነት ክፋ አለማድረግ ብቻ ሳይሆን መልካም ማድረግም ነው። የሚጎዳንን መተው ብቻ ሳይሆን ስለ ሌሎች ጥቅም መድከምም ነው።
ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@mekra_abaw
@mekra_abaw
@mekra_abaw
5.3K views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 14:00:34 #ጾም መድኃኒት ናት፡፡ አወሳሰድዋን በትክክል ላላወቁ ግን ጥቅም የላትም፡፡ ይህችን መድኃኒት የሚወስድ ሰው በየስንት ሰዓቱና በምን ያህል መጠን እንደምትወሰድ፣ ለምን ዓይነት በሽታ እንደምትጠቅም፣ በየትኛው አከባቢና የአየር ኹናቴ እንደምትወሰድ፣ ከእርሷ ጋር የሚኼዱና የማይኼዱ ምግቦችን እንዲሁም ከእርሷ ጋር የማይስማሙ ሌሎች ነገሮችን ለይቶ ማወቅ አለበት፡፡

እነዚህን ግምት ውስጥ አስገብቶ የማይወስዳት ሰው ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ታመዝንበታለች፡፡ አንድ በሐኪም የታዘዘልንን የደዌ ዘሥጋ መድኃኒት እንዲያሽለን ስንፈልግ በጥንቃቄ ልንወስደው ያስፈልጋል፤ የነፍሳችንን ደዌና በአእምሮአችን ውስጥ ያሉ ቁስሎችን ለመፈወስ ብለን በምንወስደው መድኃኒት ደግሞ ከዚህ የበለጠ መጠንቀቅ ይገባናል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
በእንተ ሐውልታት መጽሐፍ፣ ድርሳን 3፥8
ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@mekra_abaw
@mekra_abaw
@mekra_abaw
5.2K views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 10:06:44 “እንደ እባብ ልባሞች ኹኑ” /ማቴ.10፡16/

እባብ ራሱን (ጭንቅላቱን) ለማዳን ሲል ሌላው ሰውነቱን ለአደጋ እንደሚያጋልጥ ኹሉ አንተም እንዲህ አድርግ፡፡ ሃይማኖትህን ለመጠበቅ ስትል ሀብትህን ወይም ሰውነትህን ወይም የዚህ ዓለም ሕይወትህን ወይም ያለህን ኹሉ እንኳን መስጠት ካለብህ ይህን በማድረግህ በፍጹም አትዘን! አንተ ሃይማኖትህን ይዘህ ወደ ወዲያኛው ዓለም ስትሔድ እግዚአብሔር ደግሞ ኹሉም ነገር እጅግ ውብ አድርጎ ይመልስልሃል፤ ሰውነትህን በታላቅ ክብር ያስነሣልሃል፤ ከሀብት ከንብረት ይልቅም ከመግለጽ ኃይል በላይ የኾኑ በጎ በጎ ነገሮችን ይሰጥሃል፡፡ ኢዮብ ዕራቁቱን ኾኖ በአመድ ላይ ከሞት እልፍ ጊዜ የሚከፋ ሕይወትን እየመራ የተቀመጠ አይደለምን? ነገር ግን ሃይማኖቱን ስላልጣለ አስቀድሞ የነበረው ኹሉ እጅግ በዝቶ ተመልሶለታል፤ ጤናውና ውብ የኾነ ሰውነቱ፣ ልጆችን፣ ሀብቱን፣ ከዚህ ኹሉ የሚበልጥ ደግሞ አክሊለ ትዕግሥትን አግኝቷል፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - #ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ)
ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@mekra_abaw
@mekra_abaw
@mekra_abaw
5.0K views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 08:46:34 ትምክህተ ዘመድነ

ትምክተ ዘመድነ ፪× ማርያም ዕምነ
ማርያም ትምክህተ ዘመድነ

የድነታችን አርማ የነፃነታችን
የህይወት መሰረት ነሽ ድንግል እናታችን
አንቺን ለኛ ዘርን ባያስቀር
እንደጥንቱ እንደ ሰዶም ምድር
ሁላችን በጠፋን ነበር

የአብርሀም ድንኮን ነሽ አምላክ ያደረብሽ
የጌድዮንም ፀምር ለይቶ ያከበረሽ
የኛ ቤዛ በጉ የተያዘብሽ
የዋህ ርግብ  ከ አበውስር የተገኘሽ
እፀሳቤቅ የህይወት ሀረገ ነሽ

አምላክ ከሰማይ ሆኖ ይችን አለም ሲቃኝ
ንፅህይት ቅድስት ሁነሽ ማርያም አንቺን ቢያገኝ
ትህትናሽን ሂወትሽንም ወዶ
ቃል ሰው ሆነ ከሰማያት ወርዶ
አከበረሽ በፋፁም ተዋህዶ

የመዳናችን ምክንያት የሰው ልጆች ሰላም ከሀጢያት ከመርገም የዳነብሽ አለም
አምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን
በሲኦል ውስጥ ተግዘን የኖርን
ድንግል ባንቺ ነፃነት አገኘን

ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ

@mekra_abaw
@mekra_abaw
@mekra_abaw
5.9K views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, edited  05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ