Get Mystery Box with random crypto!

🔴 ምክረ አበው MEKRA ABAW™

የቴሌግራም ቻናል አርማ mekra_abaw — 🔴 ምክረ አበው MEKRA ABAW™ ም
የቴሌግራም ቻናል አርማ mekra_abaw — 🔴 ምክረ አበው MEKRA ABAW™
የሰርጥ አድራሻ: @mekra_abaw
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.32K
የሰርጥ መግለጫ

#አባቶችን_ጠይቅ_ይነግሩሃል
● ጠቢብ ከሰነፍ ጋር ቢጣላ፥ ሰነፍ ወይም ይቈጣል ወይም ይስቃል፥
ደምን ለማፍሰስ የሚሹ ሰዎች ፍጹሙን ሰው ይጠላሉ፥ ደግሞም የቅኑን ሰው ነፍስ ይሻሉ።
ሰነፍ ሰው ቍጣውን ሁሉ ያወጣል፤ ጠቢብ ግን በውስጡ ያስቀረዋል።
○ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕ. 29 ○
ሀሳብ ካላችሁ @habmisget

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-04-04 21:51:35 የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ያዕቆብ በበረሃ የታገለህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኢዮብ በደመና የታየህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሙሴ ስለ እርሱ ‹እንደእኔ ያለ ነቢይ ይነሣል› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዳዊት ‹‹እነሆ በኤፍራታ ሰማነው፣ በበረሃ ዛፍም አገኘነው›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኤርሚያስ ‹‹የክቡሩን ዋጋ ሠላሳ ብር ተቀበሉ›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡

ኢሳይያስ ‹‹ወልድ ሰው ለመሆን ተገለጠልን፣ ሕፃን ተወለደልን፣ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሕዝቅኤል ‹‹አምላክ ወደ ተዘጋች ደጃፍ ገባ፣ ከተዘጋች በርም ወጣ›› ብለህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዳንኤል ነጭ ሐር ለብሶ ያየኸውን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኤልያስ ከሞት በፊት የሰወረህ በእሳት ፈረሶች ያሳረገህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሕዝቅያስ የፀሐይ መግባቱን ያሳየህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ምናሴ ችንካሮችህን ከእግር ብረት የፈታ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኢዮስያስ ፋሲካውን ያደረግህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤል ከእሳት ምድጃ ያዳናች የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ አብያና ሲላ ፌንቶስ ከመወለዱ አስቀድሞ ያመናችሁበት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ የቀድሞ አባቶች ነቢያት ሁላችሁ ከፋራን ተራራና ከቴማን ይመጣል ያላችሁት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ አሞፅ በአድማስ ቅጥር ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዘካርያስ በተራራዎች መካከል ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዕዝራ በአርፋድ በረሃ ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡

ስምዖን በክንድህ የታቀፍከውን ሕፃን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዮሴፍ እንደ አንተ የተሸጠ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ጠራቢ ዮሴፍ በትከሻህ ያዘልከው በክንድህ የተሸከምከው ሕፃን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ከሕፃንነትህ ጀምሮ በበረሃ ያለ እናት ያለ አባት ያሳደገህ መንገዱንም እንድትጠርግለት ያዘጋጀህና መለኮትን እንድታጠምቅ የመረጠህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡

ኢያቄምና ሐና ሆይ የልጃችሁን ልቅሶዋን የልቧንም መዘንጋት ታዩ ዘንድ ኑ፡፡ ከሔዋን እስከ ፋኑኤል ልጅ እስከ ሐና ያላችሁ ሁላችሁ ቅዱሳት ሴቶች የድንግልን ልቅሶዋን ታዩ ዘንድ ኑ፣ አንድ ልጇ ሙቷልና፡፡ የለመለመ የሥጋ ሞት ሕንፃ የተጀመረበት የአቤል ተከታዩ፣ ከጎኑ የፈሰሰው ደም ሔዋንን ከጥፋት ያዳናት የተገደለ መድኃኒታችን ነው፡፡ የናቡቴ ጓደኛው የተገፋው መድኃኒታችን ነው፡፡ አቤል ስለሚስቱ ሞተ፡፡ ናቡቴም ስለ ወይኑ ቦታ ሞተ፡፡ መድኃኒታችን ግን በቀኙ ያነጻት ዘንድ ስለቤተክርስቲያን ሞተ፡፡ ነፍሳችሁን ይወስዷታልና መውረዱንም አላወቁምና ስለ ወገኖቹ ኃጢአት እስከ ሞት ደረሰ ብሎ ስለ እርሱ የተናገረ አባቱን እንስማው፡፡ ሙሴም እርሱን ያውቁት ዘንድ አላሰቡትም፣ በሚመጣበት ቀንም አላወቁትም አለ፡፡ ዕዝራ በባሕር ጥልቅ ያለውን ማወቅ እንዳይችሉ ወልድንም ማወቅ እንዲሁ ሆነባቸው አለ፡፡ ጳውሎስም ብታውቁትስ ኖሮ የክብርን ጌታ እግዚአብሔርን ባልሰቀላችሁት ነበር አለ፡፡

በመሰደድ፣ ያለምንም በደልም በፍርድ አደባባይ በመቆም መከራ መስቀልን በመሸከም አብነት የሆናችሁ ሰማዕታት ሁላችሁ ኑ የመድኃኔዓለምን የሞቱን ዕለት አስባችሁ በጋራ አልቅሱለት፡፡ ሁሉ የእርሱ ከእርሱ ለእርሱ ተፈጥሮ ሳለ በምድር ላይ ምንም ሳይኖረው ራሱን እንኳን የሚያስጠጋበት ቤት ሳይኖረው አብነት የሆናችሁ ባሕታውያንና መነኮሳት ሁላችሁ ኑ በዛሬዋ ዕለት ስለሞተው አምላካችሁ መሪር ዕንባን አልቅሱለት፡፡ ሕግ ጠብቆ፣ ሥርዓት አክብሮ፣ ነዳያንን በመመገብና ያዘኑትን በማጽናናት 33 ዓመት በምድር ላይ ኖሮ አብነት የሆናችሁ እናንት በዓለም ሆናችሁ ሕግ ጠብቃችሁ፣ አሥራት በኩራቱን አውጥታችሁ፣ ድሆችን በመርዳት የምትኖሩ ክርስቲያኖች ሁላችሁ የመድኃኔዓለምን የሞቱን ዕለት ታስቡ ኑ፡፡

‹‹የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና›› ብሎ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደጻፈልን (1ኛ ጴጥ 2፡21) እርሱ ንጹሕ ባሕርይ ሲሆን ወደ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ወደ ዮርዳኖስ በመሄድ ለተጠመቅን ለእኛ ለተነሣሕያን ለሁላችን አብነት የሆነን መድኃኒታችን ስለእኛ ሞቷልና ሞቱን እናስብ ዘንድ ኑ በቤቱ ተሰብስበን እናልቅስለት፡፡ መታሰያውንም እናድርግለት፡፡ ጌታችን ሞቶ ተቀብሮ ካረገ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለቅዱሳን አባቶቻችን ለእነ አቡነ መባዓ ጽዮን፣ ለእነ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ እንደነገራቸው የሞቱን መታሰቢያ የሚያደርግ ኃጠአተኛ እንኳ ቢሆን ሲኦልን አያያትም፡፡ የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ የሚያድርግ ቢኖር ሲኦል ራሷ አፍ አውጥታ ‹‹ይህችን ነፍስ ወደኔ አታምጡብኝ›› ብላ ትጮሃለች እንጂ ችላ አትቀበለውም፡፡

የጌታችን ወዳጆቹ ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በድርብ በፍታና በመቶ ወቄት ሽቱ ገንዘው በሐዲስ መቃብር ሊቀብሩት ቢሉ ጌታችን ያን ጊዜ ዐይኑን ክፍቶ ‹‹በሰውነቴ መዋቲ ብሆን በመለኮቴ ሕያው ነኝ እንጂ ምነው እንደ እሩቅ ብእሲ ዝም ብላችሁ ትገንዙኛላችሁን?›› አላቸው፡፡ ይህን ጊዜም ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በታላቅ ድንዳጤ ሆነው ‹‹አቤቱ ጌታችን ሆይ! እንግዲያስ ምን እያልን እንገንዝህ?›› አሉት፡፡ መድኃኒታችንም እንዲህ እያላችሁ ገንዙኝ አላቸው፡- ‹‹ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተጠምቀ በዮርዳኖስ ወተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት ዕለት ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ ዳግመ ይመጽእ በስብሐት ይኰንን ሕያዋነ ወሙታነ ተሣሃለነ እግዚኦ› እያላችሁ ገንዛችሁ ቅበሩኝ አላቸው፡፡›› ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን ለወዳጆቹ ለ12ቱ ሐዋርያት፣ ለ72ቱ አርድእት፣ ለ36ቱ ቅዱሳት አንስት ‹‹እስከ ሦስት ቀን እነሣላችኋለሁ እዘኑ አልቅሱ፣ እህል ውኃ አትቅመሱ በሏቸው›› ብሎ ለዮሴፍና ለኒቆዲሞስ አክፍሎት አስተማራቸው፡፡

ዳግመኛም መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከዕርገቱ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያት የሞቱን መታሰቢያ እንዲያደርጉ ነግሯቸዋልና፡፡ ሕማሙንና ሞቱንም እንዲዘክሩ አዟቸዋልና አሁንም ያንን ሁሉ የመድኃኔዓለምን ሞቱን ያላሰበና የሞቱን መታሰቢያ በዓል ያላከበረና እርሱንም የማይወደው ቢኖር ዕድል ፈንታው ጽዋ ተርታው ከአይሁድ ጋር ነው፡፡

የአምላካችንን የመድኃኔዓለምን ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ተባብረን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ከእርሱ ለመተባበር ያብቃን!

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መጋቢት እና #ከገድላት_አንደበት)
476 views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 21:51:35 #መጋቢት_27

#መድኃኔዓለም (#ጥንተ_ስቅለት)

መጋቢት ሃያ ሰባት በዚችም ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ ተሰቀለ። ፈጣሪዋ በዕንጨት መስቀል ላይ ተዘርግቶ ተሰቅሎ በአየችው ጊዜ ፀሐይ ጨለመች እርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የነሣትን ለባዊት ነባቢት የሆነች ነፍሱን ከሥጋው ለያት ሐዋርያ ጴጥሮስ በሥጋ ምውት ሲሆን በመለኮት ሕያው ነው እንዳለ ነፍሱ ከመለኮት ሳትለይ ከሥጋ ተለየች በዚያ ጊዜ ሥጋ ከመለኮት ሳትለይ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ነበር። እንዲሁም ነፍስ ከመለኮት ጋራ አንድ ሁና እሥረኞች ነፍሳትን ትፈታቸው ዘንድ ወደሲኦል ወረደች።

መድኃኔዓለም ክርስቶስ ስለ ዓለም ሁሉ ድኅነት በሥጋ ተሰቅሏልና ሞቱን በአንክሮ እናዘክር ዘንድ የልቡናችን ዐይን ወደ ቀራንዮ እናንሳ! እነሆ ክፉዎች አይሁድ ሰይጣን ልባቸውን አስቶታልና እንደ ወረንጦና እንደ ወስፌ እንደመርፌም ያለ 300 እሾህ ያለው ስረወጽ አድርገው አክሊል ሠርተው ከፍላት አግብተው በጉጠት አንስተው ‹ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሥ ነህ ዘውድ ይገባሃል› ብለው በራሱ ላይ ደፉበት፡፡ ለአክሊለ ሦኩም 73 ስቁረት ነበረው፡፡ እራሳቸው እንደ መሮ፣ ወርዳቸው እንደ ሞረድ 4 ማዕዘን አሠርተው ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር፣ ስለታቸውን እንደ ወስፌ አድርገው 73 ችንካር ሠርተው በ73ቱ ስቁረት አግብተው በጌታችን በራሱ ላይ ቢመቱበት ሥጋ ለሥጋ ገብቶ መሐል ልቡን ወጋው፡፡ አክሊለ ሦኩን በራሱ ላይ አድርገው ሲያበቁ ከቤት ወደ አደባባይ እያመላለሱ ‹‹ንጉሥ ሆይ!...›› እያሉ ምራቃቸውን እየተፉበት ተዘባበቱበት፡፡ መስቀል አሸክመው ከሊቶስጥራ እስከ ቀራኒዮ ድረስ እያዳፉ ሲወስዱት 136 ጊዜ በምድር ላይ ጣሉት፡፡ ከኋላ ያሉት ‹‹ፍጠን›› እያሉ ገፍትረው ይጥሉታል፣ ከፊት ያሉት ደግሞ ‹‹ምን ያስቸኩልሃል?›› እያሉ መልሰው ገፍትረው ይጥሉታል፡፡ ከዚህ በኋላ ክፉዎች አይሁድ ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር ስለታቸው ደግሞ እንደ ወስፌ የሆኑ 5 ችንካሮችን ሠርተው ሳዶር በሚባለው ችንካር ቀኝ እጁን፣ በአላዶር ግራ እጁን፣ በዳናት ሁለት እግሮቹን፣ በአዴራ መሐል ልቡንና በሮዳስ ደረቱን ቸንክረው የአዳም ራስ ቅል ባለበት ቀራኒዮ አደባባይ ላይ ሰቅለውታል፡፡

ክፉዎች አይሁድ መድኃኔዓለም ክርስቶስን እንደያዙት የኋሊት አስረው አፍንጫውን 25 ጊዜ ቢመቱት ደሙ በመሬት ላይ እንደ ውኃ ፈሰሰ፡፡ ከጌቴሴማኒ እስከ ሐና ቤት ድረስ አስረው የፊተኞቹ ሲጎትቱት የኋለኞቹ እየለቀቁት የኋለኞቹም በተራቸው ሲጎትቱት የፊተኞቹ ይለቁታል፡፤ እንዲህ እያደረጉ 65 ጊዜ ከመሬት ጋር አጋጭተውታል፡፡ ሳውል በእግሩ ሲረግጠው ጌታችን ‹‹መመለስህ ላይቀር ለምን ትረግጠኛለህ?›› ቢለው ስለዚህ ንግግርህ ብሎ ሳውል 440 ጊዜ አስገረፈው፡፡

ክፉዎች አይሁድ መድኃኒታችንን በሁለት ግንዶች መካከል አድርገው 65 ጊዜ ከግንዱ ጋር አጋጩት፡፡ ቀያፋ በሚመረምረው ጊዜ ጌታችን ‹‹አምላነቴን አንተው ራስህ ተናገርኽ›› ቢለው አይሁድ በእጃቸው ሲመቱት እጃቸውን ቢያማቸው ድንጋይ ጨብጠው 120 ጊዜ ፊቱን ጸፉት፡፡ አይሁድ ወደ ጲላጦስ ዘንድ ሲወስዱት ‹‹ምናልባት ጲላጦስ ባይፈርድበት እንኳ እንዳይቆጨን›› ብለው 305 ጊዜ በሽመል ደብድበውታል፡፡ በአምላክነቱ ቻለው እንጂ የአንዱ ምት ብቻ በገደለው ነበር፡፡ በርባን የይሁዳ የሚስቱ ወንድም (አማቹ) ስለነበር እርሱ እንደፊታለትም ከዋጋው ከ30ው ብር ጋር አብሮ ተደራድሮበት ነበር፡፡
ሰይጣን ልባቸውን ለክፋት ያስጨከናቸው ክፉዎች አይሁድ በጲላጦስ አደባባይ የጌታችንን ፂሙን 80 ጊዜ ነጭተውታል፡፡ ጲላጦስ እንደ ሕጋቸው 41 ብቻ ገርፈው እንዲለቁት ቢያዝም ክፉዎች አይሁድ ግን ጌታችንን ሲገርፉት ‹‹አሠቃቂ ግርፋቱን አይተን ልባችን እንዳይራራ›› ብለው ሰንጠረዥ ገበጣ ሰርተው ሲጫወቱ አንዱ ተነስቶ እስከ 60 እና 70 ድረስ ይገርፍና ሲደክመው ‹‹ቆጠራችሁን?›› ብሎ ይጠይቃል፡፡ ‹‹አልቆጠርንም›› ሲሉት ከድካሙ የተነሣ ‹‹እኔው ልግረፍ እንደገና እኔው ልቁጠር›› ብሎ ትቶት ሲቀመጥ ሌላኛው ይነሣና እንደዛኛው ሁሉ በተራው 60 እና 70 ይገርፈዋል፡፡ ሁሉም እንዲህ እያሳሳቱ የራሳቸውን ሕግ እየተላለፉ አይሁድ ጌታችንን ሥጋው አልቆ አጥንቱ እንደበረዶ ነጭ ሆኖ እስኪታይ ድረስ 6666 ጊዜ ጽኑ ግርፋትን ገረፉት፡፡ በእነዚህ ሁሉ ግርፋቱ ወቅት 366 ጊዜ ሥጋው ተቆርሶ መሬት ላይ ወድቋል፡፡

የመድኃኔዓለም ወገኖች ሆይ! የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ መሆኑንና የትዕግሥቱን ብዛት አይተን እናደንቅ ዘንድ ከመጻሕፍት ጠቅሰን እንነግራችኋለን፡፡ አይሁድ ጌታችን አብርሃም ሳይወለድ በፊት እርሱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን አምላክ መሆኑን ቢነግራቸው ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፡፡ እሱ ግን ጊዜው ገና ነበርና ተሰውሮአቸው በመካከላቸው አልፎ ሲሄድ በፍጹም አላዩትም ነበር፡፡ በቅዱስ ወንጌል ላይ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- ‹‹አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው። አይሁድም:- ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት። ኢየሱስም:- እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው። ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ፡፡›› ዮሐ 8፡56-59፡፡

ዳግመኛም በዮሐንስ ወንጌል ላይ እንደተጻፈው አይሁድ መድኃኔዓለምን ሊይዙት የጦር መሣሪያቸውን ሰብስበው ወደ ጌቴሴማኒ በመጡ ጊዜ ‹‹ማንን ትፈለጋላችሁ?›› ቢላቸው ‹‹የናዝሬቱን ኢየሱስን እንፈልጋለን›› ሲሉት ‹‹እኔ ነኝ›› ቢላቸው ከአንደበቱ የወጣውን መለኮታዊ ቃል ብቻ መቋቋም አቅቷቸው መሬት ላይ ወድቀው ተዘርረዋል፡፡ ይህም ክስተት በተደጋጋሚ ተከስቷል፡፡ (ዮሐንስ ወንጌል ላይ ምዕራፍ 18 ከቁጥር አንድ ጀምሮ ይመለከቷል፡፡) እናም የጌታችን ሞቱ በፍጹም ፈቃዱ ባይሆን ኖሮ በጌቴሴማኒ ሊይዙት የመጡት ክፉዎች አይሁድን እንደመጀመሪያው ሁሉ በተሠወራቸው ነበር አሊያም ከአንደበቱ በሚወጣው አምላካዊ ቃሉ ብቻ ባጠፋቸው ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን ጌታችን ወደዚህች ምድር የመጣበትን ዓላማ ይፈጽም ዘንድ እንዲገድሉት በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ ቢሰጣቸው ያን ሁሉ እጅግ አሠቃቂ መከራ አደረሱበትና ለመስቀል ሞት አበቁት፡፡

ወዮ ለዚህ ለመድኃኒዓለም ፍጹም ትዕግስት አንክሮ ይገባል! ዓለምን በመዳፉ የያዘ አምላክ በአይሁድ እጅ እንደሌባ ተያዘ፡፡ ሠራዊተ መላእክት ለምሥጋና በፊቱ የሚቆሙለት መድኃኔዓለም እርሱ ሊፈረድበት በፍርድ አደባባይ ቆመ፡፡ በእስራት ያሉትን የሚፈታ እርሱ በብረት ችንካር ተቸነከረ፡፡ ሰማይን በከዋክብት ምድርም በአበባ ያስጌጠ እርሱ ግን የእሾህ አክሊል በራሱ ላይ ደፋ፡፡ ዓለሙን ሁሉ በቸርነቱ የሚመግብ እርሱ ተጠማሁ አለ፡፡ ወዮ የመድኃኔዓለም የማዳኑ ምሥጢር ምንኛ ድንቅ ነው!!! ለዚህ ባሕርይው አንክሮ ይገባል፡፡

በመድኃኔዓለም ክርስቶስ ሞት በአንድነት እናለቅስ ዘንድ ቅዱሳን ሁላችሁ ኑ! መድኃኒታችን ሙቷልና ፍጥረታት ሁሉ ያለቅሳሉ፤ መያዝንና መታሠርን የተቀበለ መድኃኒታችን ሙቷልና፡፡ ጥፊንና ግርፋትን የተቀበለ መድኃኒታችን ሞተ፡፡ መደብደብንና መመታትን የታገሰ መድኃኒታችን ሞተ፡፡ ሄኖክ እግዚአብሔር ‹‹በሴም ቤት ይደር›› ብሎ አብ ስለራሱ የተናገረለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ አብርሃም ቃልኪዳን የገባልህን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ይስሐቅ ከሰይፍ ቤዛ የሆነህን
436 views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 14:56:40
እንኳን አደረሳችሁ!

" እኔ ድኻ መስሎኝ፥ ተራቁቶ ባየው፤
ለካስ ጌታ ኖሯል፥ የተሰቀለው!

@mekra_abaw
845 views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, edited  11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 00:34:05 ኒቆዲሞስ

ኒቆዲሞስ ኒቆዲሞስ ክቡር
ሌቱን በብርሃን የሚማር መምህር

በጨለማው ግርማ ኮከብ የደመቀ
በመከራው ፅናት ይህን ዓለም ናቀ
መምህር ሆኖ ሳለ ከመማር ያልራቀ
የትዕቢትን ጅረት በትህትና ተዋርዶ አደረቀ

ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አዝ
ፍርሃትን በሚጥል ፍፁም ፍቅር ያደረ
ከመስቀል አውርዶ ጌታውን ቀበረ
የመግነዙን በፍታ በሽቶ አከበረ
ከመቅደሱ አንቀፅ ላይረሳ አምድ ሆኖ ታጠረ

ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አዝ
ለሊትም ለሊት ዕውቀትን ነገረች
ህጉን ለሚያስበው ምክር አለኝ እያለች
ከጨለማ ሀጢያት ነግታ ብርሃን ከአየች
እንደ ኒቆዲሞስ ነፍስህም ተምራ ተመለሰች

ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ

ዲያቆን ዘማሪ ቀዳሚፀጋ
በvideo ለማግኘት
https://www.youtube.com/channel/UCfWtKqb7qsxjXey4kN_tykg?sub_confirmation=1
ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@mekra_abaw
@mekra_abaw
@mekra_abaw
126 views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, edited  21:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 00:24:56 7. ኒቆዲሞስ
   ኒቆዲሞስ ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ የአይሁድ አለቃና መምህር ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናገኘው መምህር መሆኑን የሚከተለው ጽሑፍ ያስገነዝበናል፡፡ ‹‹ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ መምህር ሆይ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን›› አለው፡፡ ኢየሱስም መልሶ ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም›› አለው፡፡ ኒቆዲሞስም ‹‹ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል?›› አለው፡፡ ኢየሱስም ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካለተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፤ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው፤ ዳግመኛ ልትወለዱ ያስፈልጋችኋል ስላልሁ አታድንቅ፤ ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፤ ድምፁንም ትሰማለህ ነገር ግን ከወዴት እንደመጣ ወዴትም እንዲሔድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው›› አለው፤ (ዮሐ 3፥1-8)፡፡ ከውኃና ከመንፈስ ዳግም መወለድ የእግዚአብሔር ልጆች ለሆኑት ልዩ መገለጫ ነው፡፡
  
ኒቆዲሞስ በሌሊት እየመጣ ከኢየሱስ ክርስቶስ እግር ሥር ቁጭ ብሎ ወንጌልን ይማር ነበር፡፡ ሰንበቱ በእርሱ ስም የተሰየመው ሥራውን ለመዘከር ነው፡፡ በሌሊት መጣ የሚለው በምሥጢር ሲተረጎም አንደኛ ወደፊት በቀን ይመጣልና ከዚያ አስቀድሞ መጣ ለማለት ነው፤ አንድም በኋላ በዕለተ ዓርብ የጌታን ሥጋ ከመስቀሉ አውርዶ ገንዞ ለመቅበር ይመጣልና ከዚያ አስቀድሞ ለመማር መጣ ለማለት ነው፡፡ አንድም ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስን ሳያምን በፊት በኦሪት ጨለማ እያለ መጣ ለማለት በሌሊት መምጣቱን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን አመሥጥረው ያስተምራሉ፡፡
ኒቆዲሞስ ከመዓልት ይልቅ በሌሊት መማር የመረጠበት ምክንያቶች
ሀ. ውዳሴ ከንቱ ሽቶ፦ እርሱ ራሱ የአይሁድ አለቃና መምህር ስለነበር ከሌላ መምህር (ከኢየሱስ ክርስቶስ) እግር ሥር ተቀምጦ ሲማር አይሁድ ቢያዩት ሳይገባው ነው መምህር ያልነው ብለው ይነቅፉት ነበር፡፡ በሌላ አገላለጽ ኒቆዲሞስ መማርን ይፈልጋል ደቀ መዝሙር መባልን ግን አይፈልግም፡፡ በአንጻሩም ምሁረ ኦሪት ነበረና መምህር መባልን ይፈልጋል፡፡

ለ. የአይሁድን ዛቻና ማስጠንቀቂያ ፈርቶ፦ አይሁድ በክርስቶስ የሚያምንና ትምህርቱንም የሚሰማ ቢገኝ ከማኅበራችን ይለይ ቤቱም የጉድፍ መጣያ ይሁን ብለው ተስማምተው ሕግ አውጥተው ነበርና ቅጣቱን ፈርቶ ላለመታየት ሌሊት መማርን መርጧል፡፡

ሐ. አእምሮ ልቡናውን ሰብስቦ ለመማር ፈልጎ፦ መዓልት ዓይንን፣ ጆሮንና አእምሮን የሚሰርቅ ነገር ብዙ ነውና ከቀን ይልቅ ሌሊትን መረጠ፡፡ አንድም አለቃ እንደመሆኑ ቀን ቀን የራሱ ሥራ ይበዛበት ነበረና ሌሊትን መረጠ፡፡
   በዚህ ሳምንት ቤተ ክርስቲያን ስለ ምሥጢረ ጥምቀት ታስተምራለች፡፡ ጥምቀት ሰው ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ዳግመኛ ተወልዶ የክርስቶስ አካል የማኅበረ ምእመናንም አባል የሚሆንበት ምሥጢር ነው፡፡ በጥምቀት ኃጢአት ይሰረያል፤ የእግዚአብሔር ልጅነት ይሰጣል፤ ልጅ ለሆነው ሁሉ ርስት ገነትና መንግሥተ ሰማያትም ይወረሳል፡፡
   በዚህ ሰንበት የሚሰበከው ምስባክ ‹‹ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጎበኘኸኝ ፈተንኸኝ ምንም አላገኘኽብኝም፤ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው››፤ (መዝ 16፥3-4) የሚለው የቅዱስ ዳዊት መዝሙር ነው፡፡
   ዛሬ ብዙዎቻችን ባለሥልጣን ስለሆንን በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ውስጥ ባለው መሬት ላይ ቁጭ ብለን መማር ያሳፍረናል፤ ሌሎቻችንም ባለሀብት ስለሆንን ለገንዘባችን እንጂ ለእግዚአብሔር የሚሆን ጊዜ አጥተናል፤ ሌሎች ደግሞ መምህር ነኝ አለቃ ነኝ በቅቻለሁ ነቅቻለሁ ትምህርት አያስፈልገኝም በማለት ከቤቱ ርቀናል፡፡ ቀሪዎቻችን ደግሞ የየራሳችን ምክንያት አበጅተናል፡፡ ኒቆዲሞስ ግን ከጌታ እግር ሥር ቁጭ ብሎ ለመማር እነዚህ ሁሉ ምክንያቶች አልከለከሉትም፡፡ እነዚህን ሁሉ ተጋፍጦ በመማሩ ከዮሴፍ ጋር የክርስቶስን ሥጋ ገንዞ ለመቅበርና በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝግቦ በታሪክ ለመዘከር በቅቷል፤ (ዮሐ 19፥38-42)፡፡ የእኛንም ሕይወት መቃኘት እንደሚገባን ቤተ ክርስቲያን በዚህ ሳምንት ከኒቆዲሞስ ሕይወት ጋር በማነጻጸር ታስተምረናለች፡፡
           ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ጾምና ምጽዋት፣ ሰባቱ አጽዋማት
 በvideo ለማግኘት
https://www.youtube.com/channel/UCfWtKqb7qsxjXey4kN_tykg?sub_confirmation=1
ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@mekra_abaw
@mekra_abaw
@mekra_abaw
135 views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 21:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 16:03:53 ምክረ አበው MEKRA ABAW pinned « አመ ፳፯ቱ ለመጋቢት መድኃኔዓለም  ስርዓተ ማህሌት የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ" ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ…»
13:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 08:17:58
በዓቢይ ፆም የማንን የንስሐ መዝሙር ማዳመጥ ትፈልጋላችሁ የፈለጉትን መርጠው ያዳምጡ
https://t.me/+Qvj8Ost1xjwKbP2J
174 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 05:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 08:01:20
የርዕሰ ሊቃውንት መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረኪዳን ትምህርቶች

ድንቅ፣ኃያል፣ርትዕት፣ጥንታዊት የሆነች የኦርቶዶክስን ሃይማኖት ከሚሰብኩ እናም ዕንቁ ከሚባሉት መካከል ቀዳሚው አባት ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳንን ትምህርት የሚያገኙት ብቸኛው ቻናል ነው ይግቡ።


@abagebrekidan
@abagebrekidan
@abagebrekidan
128 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 05:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 08:37:45 የምስራች አሁን online ላላችሁ ብቻ 56,000 member ባለው ቻናላችን ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው

ለወጣ 500 ብር ካርድ
ለወጣ 250 ብር ካርድ
ለወጣ 100 ብር ካርድ

ዝግጁ ከሆናችሁ START የሚለውን ይጫኑ
            
https://t.me/+ULytP9NXh6o2ZDdk
451 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 05:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 13:38:12 "ጾምህና ምጽዋትህ ሁለት ዋጋ አላቸው፡፡ ከሰው ክብርን ሽተህ የምትጾም ከሆነ ኃጢአት በአንተ ላይ እንድትበረታ ደንቁርናህም እጅግ ጽኑ እንዲሆን እወቅ፡፡ ነገር ግን እጆችህን ለተቸገረ ሰው የምትዘረጋ ሕሊናህን ግን ወደ አምላክ የምታነሣ ከሆነ፣ እንዲሁም ስትጾም ጾምህን በእግዚአብሔር ፊት ያደረግህ እንደሆነ ከፈጣሪህ ዘንድ መልካምን ዋጋ ትቀበላለህ፡፡ ይህ ኃይለ ቃል “ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና፡፡” (ማቴ.6፥21) ብሎ ጌታችን ካስተማረው ትምህርት ጋር አንድ ዓይነት ትርጉም ያለው ነው፡፡

ጾምና ምጽዋታችን በከንቱ ፈቃዳችን ምክንያት ለኃጢአት አሳልፎ እንዳይሰጠንና በደላችንንም እጥፍ ድርብ እንዳያደርግብን አምላካችን ይህን ማስተዋል ዘወትር ይሰጠን ዘንድ በዚህ የጦም ወቅት እንለምነው፡፡

ለወደደንና በእኛ ጥቂት ድካም ዘለዓለማዊ ዋጋን ለሚሰጠን ለእርሱ ምስጋና ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

#ቅዱስ_ኤፍሬም
በvideo ለማግኘት
https://www.youtube.com/channel/UCfWtKqb7qsxjXey4kN_tykg?sub_confirmation=1
ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@mekra_abaw
@mekra_abaw
@mekra_abaw
864 views▂▃▄▅▆░ Hab mis ░▆▅▄▃▂, 10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ