Get Mystery Box with random crypto!

አሚነ ፅድቅ✨

የቴሌግራም ቻናል አርማ lesanegeez — አሚነ ፅድቅ✨
የቴሌግራም ቻናል አርማ lesanegeez — አሚነ ፅድቅ✨
የሰርጥ አድራሻ: @lesanegeez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 138
የሰርጥ መግለጫ

የእውነት እምነት ። group :- @lesanegeez2

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-12 13:25:01 ‹‹ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም›› /ዮሐ. 14፥18/

#ጰራቅሊጦስ በመንፈስ ቅዱስ ለምትመራው የሐዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን የልደት ቀኗ ነው፡፡
ቤተክርስቲያን ለሁሉም በየቋንቋው ሃይማኖትን ማስተማር እንዳለባት ከመንፈስ ቅዱስ በላይ ምስክር አያስፈልግም፡፡
በየሀገሩ ቋንቋ ወንጌልን ማስተማር እንጂ የየሀገሩን ቋንቋ ለህዝብ ማስተማር የቤተክርስቲያን ኃላፊነት አይደለም፡፡
ለቅዱሳን ሐዋርያት የተገለጡላቸው ልሳናት (ቋንቋዎች) የታወቁ፣ ሰዎችም የሚግባቡባቸው ቋንቋዎች ናቸው፡፡
ለቅዱሳን ሐዋርያት የየሀገሩ ቋንቋ መገለጡ ሁሉም የዓለማችን ቋንቋዎች የሐዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ልሳናት መሆናቸውንና የትኛውም ቋንቋ በተለየ ሁኔታ ብቸኛ የቤተክርስቲያን ልሳን እንዳልሆነ ያረጋግጥልናል፡፡
የልሳናት (ቋንቋዎች) መገለጥ ዓላማ ደቀመዛሙርቱ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወንጌልን ለማስተማር ሲዘዋወሩ ሁሉንም በየቋንቋው ማስተማር እንዲችሉ ነው፡፡
የሐዋርያትን ፈለግ በምትከተል ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከሚከበሩ ዘጠኝ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ በዓለ ጰራቅሊጦስ ነው፡፡ ይህም በዓል በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 በተገለጸው መልኩ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ለ120ው ቤተሰብ የወረደበትን ዕለት የምናስብበት ነው፡፡ በዚህች የአስተምህሮ ጦማር ስለ መንፈስ ቅዱስ ጸጋ፣ ስለ በዓለ ጰራቅሊጦስ የብሉይ ኪዳን ምሣሌዎች፣ ለሐዋርያት ስለተገለጠው ልሳን (ቋንቋ) እንዲሁም ስለተያያዥ ጉዳዮች እንዳስሳለን፡፡


#ጰራቅሊጦስ ማለት ምን ማለት ነው?

ጰራቅሊጦስ ማለት የግሪክ ቃል ሲሆን ከሦስቱ አካላት አንዱን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን የሚገልጥ ነው፣ ትርጉሙም መንጽኢ (የሚያጸና)፣ መንጽሒ (የሚያነጻ)፣ ናዛዚ (የሚያጽናና፣ የሚያረጋጋ) ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም ጰራቅሊጦስ ማለት ከሣቲ (ምስጢር ገላጭ)፣ መስተሥርዪ (ይቅር ባይ) እና መስተፍሥሒ (ደስታን የሚሰጥ) ማለት ነው፡፡ ከቅዱሳን ሐዋርያት የሚበዙት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ሞት በኋላ አይሁድን ፈርተው ይሸሹ ነበር፡፡ ከአይሁድ ፍርሃት ሙሉ በሙሉ መላቀቅ ያልቻሉ ደቀመዛሙርቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእነርሱ ተለይቶ እንደሚያርግ ሲነግራቸው አዘኑ፡፡ ለተልዕኮ የጠራቸው፣ ዓለምን በወንጌል ብርሃን እንዲያበሩ የመረጣቸው ጌታ ግን ለድካማቸው አሳልፎ አልሰጣቸውም፡፡ ከትንሣኤው በኋላ እስከ ዕርገቱ ድረስ ለ40 ቀናት እየተገለጠላቸው እምነታቸውን አጸናላቸው፣ ቅዱስ ቃሉን አስተማራቸው፣ ለሐዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያንም መሰረት የሆነ መንፈሳዊ ሥርዓትን አሳያቸው፡፡ ሰብሳቢ፣ ጠባቂ እንደሌላቸው የሙት ልጆች የሚሆኑ መስሏቸው ነበርና “የሙት ልጆች ትሆኑ ዘንድ አልተዋችሁም” (ዮሐ. 14፡18) አላቸው፡፡ ስለ ስሙ መከራን ለመቀበል እንዲጸኑ መንጽኢ (የሚያጸና) መንፈስ ቅዱስ ያስፈልጋቸው ነበርና “እኔ የአባቴን ተስፋ ለእናንተ እልካለሁ፤ እናንተ ግን ከአርያም ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ተቀመጡ፡፡” (ሉቃስ. 24፡49) በማለት ተስፋ ሰጣቸው፡፡ ይህም ተስፋ አስቀድሞ በነቢያት የተነገረ ነው (ትንቢተ ኢዩ. 2፡15)፡፡


#ጰራቅሊጦስ ስለምን #ኀምሳው ቀን በተፈጸመ ጊዜ ወረደ?

የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በግልጥ ለሐዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን የተገለጠው ቅዱሳን ሐዋርያት፣ አርድእትና ቅዱሳት አንስት ከእመቤታችን ጋር በአንድነት ለጸሎት ለምስጋና ተሰብስበው እያለ ነው ፡፡ “ኀምሳው ቀን በተፈጸመ ጊዜ፣ ሁሉም በአንድነት በአንድ ቦታ ተሰብስበው ነበር” (ሐዋ 2፡1-47)ሐዋ 2:1) እንዲል፡፡ በነቢያትና በሐዋርያት መሰረትነት የቆመች ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን (ኤፌ. 2፡20) በዓለ ጰራቅሊጦስን በሐዋርያት ዘመን እንደነበረው ከጌታችን ትንሣኤ በኋላ በኀምሳኛው ቀን ታከብራለች፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በዓለ ጰራቅሊጦስን “የቤተክርስቲያን የልደት ቀን” ሲል ጠርቶታል፡፡ በመንፈስ ቅዱስ የምትመራው የሐዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተመልታ ለሰው ልጆች ሁሉ እውነተኛ የክርስቶስን ወንጌል መስበክ የጀመረችበት ቀን ነውና፡፡

በዘመነ ሐዲስ ከሚከበሩ በዓላት ብዙዎቹ በዘመነ ብሉይ የነበሩ ምሣሌዎች አሏቸው፡፡ ከእነዚህ አንዱ በዓለ ጰራቅሊጦስ ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ሙሴ በኦሪት መጻሕፍት እንደገለጠልን እስራኤል ዘሥጋ በዓለ ፋሲካን (እስራኤል ዘሥጋ ከግብጽ ባርነት ነፃ የወጡበት) ካከበሩ በኋላ ሰባት ሣምንታትን ቆጥረው በኀምሳኛው ቀን በዓለ ሰዊት (የእሸት በዓል) ያከብሩ ነበር (ዘሌ 23፡15-22፣ ዘጸ 34፡22፣ ዘኁ 28፡26)፡፡ ይህ የብሉይ ዘመን ታሪክ ሊመጣ ላለው ለክርስቶስ ቤዛነት ምሣሌ ነበር፡፡ መቶ ሃያ ቤተሰብ (12ቱ ሐዋርያት፣ 72ቱ አርድእትና 36ቱ ቅዱሳት አንስት) ከጌታችን ትንሣኤ በኋላ ሞገሳቸውን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በመካከል አድርገው በፍፁም አንድነት በጸሎት እየተጉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጣቸው የተስፋ ቃል የሚፈምበትን ዕለት በእምነትና በተስፋ ይጠብቁ ነበር (ሉቃ. 24፡49፣ ዮሐ. 14፡15-18፣ ዮሐ. 16፡7-15፣ ሐዋ. 1፡8)፡፡

አባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምስጢር የበዓለ ኀምሳ ምንባብ እንደገለፀልን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ “የመንፈስ ቅዱስን መውረድ ተስፋ በሰጣቸው በኀምሳ ሦስተኛው ቀን፣ ከሙታንም ተለይቶ በተነሣ በኀምሳኛው ቀን፣ በዕለተ እሁድ ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ደቀመዛሙርቱ በጽርሐ ጽዮን ተሰብስበው ሳሉ” የሚያጸና፣ የሚያነፃ፣ የሚያረጋጋ የእግዚአብሔር መንፈስ በእሳትና በነፋስ አምሳል ተገለፀላቸው፡፡ በዕለተ እሁድ በመገለፁም የሰንበተ ክርስቲያንን ክብር አስረዳን፡፡ ነገረ ምጽዓቱ (ደብረ ዘይት)፣ የትንሣኤው ብርሃን፣ የመንፈስ ቅዱስም መውረድ ዘላለማዊት በሆነች (ዓለማት በሚያልፉባት ስለዚህም ጊዜ በሚጠፋባት)፣ የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ በሆነች በሰንበተ ክርስቲያን ነውና መንፈስ ቅዱስ በዕለተ እሁድ በእሳትና በነፋስ አምሳል ተገለፀ፡፡

እንግዲህ እናስተውል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ግን ከቅዱሳን ሁሉ በላይ ናትና ቁጥሯ (ክብሯ) ከ120ው በቤተሰብ ጋር አንድ አይደለም፤ የመንፈስቅዱስን ጸጋ ለመቀበል እንደ ሌሎች ቅዱሳን በዓለ ኀምሳን መጠበቅም አላስፈለጋትም፡፡ ከአበው አብራክ ከፍሎ የጠበቃት፣ በማኅፀነ ሐና ያከበራት፣ በቅዱስ ገብርኤል ብስራት ክብሯን የገለጠ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በተለየ ክብር ቀድሷታልና (ሉቃስ 1፡35)፡፡

#የእሳትና #የነፋስ ምሳሌነቱ ምንድን ነው?

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በፍፁም አንድነት በልዩ ሦስትነት የሚመሰገን የራሱ ፍፁም መልክ፣ ፍፁም ገፅ፣ ፍፁም አካል ያለው፣ ከአብና ከወልድ ጋር ህልው ሆኖ የሚኖር፣ ዓለማትን የፈጠረ፣ የፍጥረታት ሁሉ መጋቢ፣ ዓለምንም አሳልፎ ለዘለዓለም የሚኖር አምላክ ነው፡፡ አባታችን አባ ሕርያቆስ መንፈስ ቅዱስ በገለጠለት የቅዳሴ ማርያም ምስጋናው እንዳስተማረን መለኮት (እግዚአብሔር) ግን ይህን ያህላል፣ ይህንንም ይመስላል ሊባል አይቻልም (ቅዳሴ ማርያም ቁጥር 47)፡፡ ይሁንና በዓለም ሁሉ በምልዓት የሚኖር አምላክ በፈቃዱ ለፍጥረታት ይገለጣል፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም ዓለምን የፈጠረ፣ የሚጠብቅ፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም ህልው ሆኖ (በህልውና ተገናዝቦ) ደቀመዛሙርቱን ለሐዲስ ኪዳን አገልግሎት የጠራቸው፣ በትምህርትም በተዓምራትም ከአብ ከወልድ ጋር የማይለይ ነው፡፡
26 views10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 20:10:08 ✞እኛ ግን ስላንቺ✞

የነገስታት ንጉሥ ፈጣሪን ወልደሽ
እንዴትስ መመስገን ይነስሽ
ዓለም ለማመስገን እውነቱ ቢከብደው
እኛ ግን ስላንቺ ምንለው ብዙ ነው(2x)

ከሰማያት መጣ የሚደነቅ ክብር
ሰማን ከገብርኤል ላንቺ ሲነገር
እውነትን ለማወቅ ዓለምን ጋረደው
የህይወትን ምግብ ከማን ነው ያገኘው
እኛስ ስለገባን ፀጋና ክብርሽ
እጅጉን አብዝተን ማርያም ወደድንሽ
አዝ= = = = =
ማንም ሰው ለእናቱ ክብርን እንደሚሻ
ላንቺ ያለን ፍቅር የለው መጨረሻ
ስንዘምር ስንጠራሽ ዓለም ብዙ ቢለን
የገባንን እውነት እንዲያየው ወደድን
አዝ= = = = =
ዝም የሚል አንደበት የለንም ለክብርሽ
በደማችን ሰርጿል ስምሽ ና ፍቅርሽ
ፀሀይን ስላየ ዓለም ደስ ካለው
አንቺን ለማመስገን ስለምን ከበደው
አዝ= = = = =
ከቶ በሰው ልማድ ፍጹም ያላየነው
እናት ሆኖ ድንግል አንቺን ነው ያየነው
ገና ብዙ ብዙ ቃላት አለኝ
አንቺን ከማመስገን ማነው የሚያስተወን
እኛስ ስለገባን ፀጋና ክብርሽ
እጅጉን አብዝተን ማርያም ወደድንሽ

መዝሙር
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
➢➢➢
➧ ቀራንዮ
➧ ድንግል እናታችን
➧ ምልክቴ ነሽ
➧ እኛ ግን ስላንቺ ...ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮችን በድምፅ እና በግጥም ለማግኘት


➮ከወደዱት ያጋሩ
JOIN US
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘  
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር
ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ በPDF
ኦርቶዶክሳዊ ግጥም
የግእዝ ትምህርት
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 ‌‌
36 views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 17:35:19 Art of kidus
https://t.me/art_of_kidus
58 views14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 12:29:51 #መፆረ_ንጉሥ_ዘሊባኖስ
†⊙…◆⇝✧⇜◆…⊙†

"መፆረ ገብረ ንጉሥ … ለርእሱ እምዕፀወ ሊባኖስ
ንጉሡ ከሊባኖስ እንጨቶች ለራሱ ዙፋን ሠራ" (መኃ ፫፥፱)

ይህች ዕለት ለዕለታቱም ዕለታቸው ናት!

✧ ሰንበተ ሰንበታት ፣ ምዕራፈ ነፍሳት፣ ክብረ ኩሉ ፍጥረት፣ ከጨለማ ግዞት ሕዝቡን ወደብርሃን ለማሻገር ማዕዶት የምትሆን ተስፋ እመብርሃን የተገኘችባት ዕለትናትና የዕለታት ዕለት፤

✧ ድኅነተ ነፍስ "ለሰብአ ዓለም የጎሰቆለ ባህሪ" ካሳ ሊሆን የተወጠነባት ዕለትናትና የዕለታት ዕለት፤

✧ ለቤዛ ኩሉ ዓለም እናት፣ መሠረተ መሠረቱ ለሕይወት ፣ ለዕጓለ አንበሳ ወላዲት፣ ታዕካ በምድር ወታዕካ በሰማይ ማርያም (እመ አርያም) የተወለደችበት ዕለት ናትና የዕለታት ዕለት!

ከአንዱ አዳም ጥፋት የተነሳ በዓለም የወደቀው ኀጢአት እና ደሞዙ (ኀጢኦት ፣ ኀጥአ ⇥ ከሚለው እግዚአብሔርን ማጣት በሚል አገባብ ይወሰድ 'እስመ ተግባራሰ ለኃጢአት ወረባሐ ዚአሃ ሞት' እንዳለው እንዲሁም የማጣቱ ውጤት መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ) ከባህርየ ሰብእ የተወገደባት ህፃን፣ "ትምክህተ ዘመድነ" የምትሰኝ ዘርዕ-እቅብት ፣ ቡርክት የሆነች እናት ፣ ኃጥእት ያለሆነች ቅድስት ፣ ታትማ የኖረች ድንግል፣ ወላዲቱ ለአምላክ ማርያም፦ ዛሬ ከአምላክ ኅሊና ወደ አዳም ተስፋ ተሻግራ በነቢያቱ ትንቢትና በአበው ኅብረ ምሳሌ ስትጠበቅ ቆይታ በሥጋ የተገለጠችበት የከበረ ዕለት ነው!

በቀደመው መልክአ ማርያም (ሣልሲት) እንዲህ የሚል ይገኛል ፦

☞ "ሰላም ለተፈጥሮኪ እለ ፈጠሩኪ በተአቅቦ:
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በተናብቦ:
ንዒ ንዒ ንዒ ማርያም ፀምረ ጌድዮን ህቦ:
አመ ኃሠሠ ኅሊናየ እምፍጥረተ ዓለም ዘቦ:
ከማኪ በምሳሌ ዘይመስል አልቦ። "

↳ አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ተገናዝበው በተአቅቦ ለፈጠሩት ባህሪሽ (ተፈጥሮሽ) ሰላምታ ይገባል የጌድዮን የፀምሩ ጠል ማርያም ነዪ ነዪ ነዪ (ብዬ እምጠራሽ ነኝ) ከአለም መፈጠር አንስቶ ያለውን ኅሊናየ ቢፈልግም አንቺን የሚመስልበት አምሳል ግን ከወደየትም አላገኘም!

ይኼንኑ ጠቢቡ በምስጋናው ምስጋና ፣ ከሁሉ በላቀው ማኅሌት፣ በመኃልየ መኃልይ እየዘመረ በገዛ ስሙ ሰሎሞን እያለ መስተሳልም ክርስቶስን ሲያወድስ በምሥጢርም የንጉሡን እናት ያነሳና (እኅትየ መርዓት ፣ እኅቴ ሙሽራዬ እያለ) ሲቀኝላት ቆይቶ ከተነሳንበት ሦስተኛው ምዕራፍ አሻግሮን እንዲህ ሲል ይጠይቃል ፦

∽†∽ "መኑ ይእቲ ዛቲ እንተ ተአርግ እምገዳም ከመ ደመና ? እንደ ደመና አቅንታ ከምድረበዳ የምትትወጣ ይች ማናት? " (ቁ ፮)

ከምድረ በዳው ዓለምና ኀጢአት ይቡስ ካደረገው ኅላዌ የተገኘች እውነተኛው ዝናመ ምሕረት ክርስቶስ አምላካችን ለፍጥረቱ ከተገኘባት አማናዊት ደመና ከድንግል በቀር ማናት … ቅዱስ ያሬድ "ደመናሰ ዘይቤ ይእቲኬ ማርያም እንተ ፆረቶ ዲበ ዘባና" ይላታልና።

አስጠግቶ ይመልሳል መፍቀሬ ጥበብ ፦

∽†∽ "ናሁ ዓራቱ ለሰሎሞን …የሰሎሞን አልጋ ይች ናት" (ቁ ፰)

የመስተሳልም ሰሎሞን የተባለ የክርስቶስ አልጋው ይኽችው ድንግል ማርያም ናት !

አባቱ ዳዊትም በትንቢቱ አስቀድሞ ጽዮን ድንግል ማርያምን ንጉሡ ክርስቶስ
⇛ "ከመ ትኩኖ ማኅደሮ" ብሎ ለክብሩ ዙፋንነት እንዳዘጋጃት፣
⇛ "ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም" ብሎ ለዘልዓለም መኖርያነት እንዳከበራት እና
⇛ "ዝየ አኀድር እስመ ኃረይክዋ" ብሎ ወድዶ ሊወለድባት እንደመረጣት ተናግሮላት ነበርና (መዝ ፻፴፩)

ልጁም ያንኑ ምሥጢር ስቦ የተገለጠለትን በኅሊናው ሲያወጣና ሲወርድ ቆይቶ
⇛ ለቃል መውረድ ዙፋን የሆነ የንጽሕናዋን መደብ ፣
⇛ ለሥጋ ማረግ መሰላል የሆነ የቅድስናዋን እርካብ ከእኛ እንዲህ ሲል አደረሰው ፦

"መፆረ ገብረ ንጉሥ … ለርእሱ እምዕፀወ ሊባኖስ
ንጉሡ ከሊባኖስ እንጨቶች ለራሱ ዙፋን ሠራ" (ቁ ፱)

#የሊባኖስ_እንጨቶች (ዕፀወ ሊባኖስ) ቅድስት ሃናና ቅዱስ ኢያቄም

ሊባኖስ ተራራማ እንጨት የበዛባት መልካም ሀገር ናት። ሊቀ ነቢያት ሙሴ ምኞቱን ከመሞቱ በፊት እንዲህ ሲል አውስቷል "እኔ ልሻገር በዮርዳኖስም ማዶ ያለችውን መልካሚቱን ምድር ያንም መልካሙን ተራራማውን አገር ሊባኖስንም ልይ።" (ዘዳ ፫፥፳፭)

በዚያም ያሉ ዕፀው እንደ ዝግባ ያሉቱ በረዥም ዘመን ቆይታቸው ለዐይን ርእይ ባላቸው ልምላሜና ለአፍንጫ ሽታ ባላቸው ግሩም መዓዛ የበጎ ነገር ማጌጫና የመልካም ምሳሌ መገለጫ ሆነው በቅዱስ መጽሐፍ ተዘግበዋል።

ለቤተ እስራኤል ስለተሰጠችው ብዕለ አሕዛብ ለምዕመንም ስለተገለጠችው ሕገ ወንጌል መልካምነት ለማጠየቅ ቅዱስ ኢሳይያስ በትንቢቱ "ወክብረ ሊባኖስ ተውኅበ ላቲ " (፴፭፥፪) ብሏል።

የዛሬዋ ሊባኖስም በቅዱስ መጽሐፍ ከ፸፯ ጊዜ በላይ ስለተጠቀሰላት መልካም ዝግባዋ ቦታ ሰጥታ ከ1943(እ.አ.አ.) ጀምሮ የሰንደቋ መገለጫ ሆኖ በመኖር ዛሬም በቀይ በታጠረ ሁለት እጅ ነጩ የባንዲራ መደቧ ላይ (1:2:1) ያንን ዝግባ በኩራት የቅድስና አርማ የዘልዓለማዊ ሕይወት ማሳያና የሰላም ምልክት እንደሆነ በማመን ትጠቀምበታለች። (The Cedar is a symbol of holiness, eternity and peace. As an emblem of longevity, the cedar of Lebanon has its origin in many biblical references.)

♛ንጉሥ ዳዊት ቤተመንግሥቱን ለማነጽ (፪ሳሙ ፭፥፲፩፣ ፩ዜና ፲፯፥፩)
♚ ንጉሥ ሰሎሞን እቃ ቤቱን ፣አልጋ ዙፋኑን ፣ ቤተ መንግስቱንና የከበረ የታቦቱ ማደሪያ መቅደሱን ለማነጽ (፩ነገ ፯፥፪ ፣ ፪ዜና ፩፥፲፭ ፣ ፪፥፫―፰)
♜ በዕዝራም መቅደሱ ዳግመኛ ሲታነፅ (ዕዝ ፫፥፯) ለእግዚአብሔር የክብሩ መገለጫ የሊባኖስ እንጨቶች እንደተመረጡ ቅዱስ መጽሐፋችን ደጋግሞ ያስረዳናል።

ዕፀዋት በለመለመ ቅጠላቸው ርቱዕ እምነት ፣ ባማረ ፍሬአቸው ምግባር ትሩፋት እያስተማሩ በቅድስና ለደመቁ ቅዱሳን በምሳሌነት ያገለግላሉ።
ንኡዳን ክቡራኑን "ይከውኑ ከመዕፅ " እንዲላቸው (መዝ ፩፥፫)

መጽሐፍ ቅዱሳችን በምሥጢርና በዘይቤ የተመላ የክርስትናው ፍኖት ማንጸሪያ ነው ( full of metaphors that compare the Christian journey)

በአብነቱ አባታችን፣ በአርያነቱ ፍኖታችን ክርስቶስም ከዕፀው ባንዱ ራሱን እንዲህ መስሏል
"አነ ውእቱ ሐረገ ወይን ዘጽድቅ እኔ የወይን ግንድ ነኝ! " (ዮሐ ፲፭፥፩) በኅርያቆስ ቅዳሴም "አብ ጕንደ ወይን ፤ ወልድ ጕንደ ወይን ፤ ወመንፈስ ቅዱስ ጕንደ ወይን ፩ዱ ውእቱ ወይነ ሕይወት ዘቦቱ ጥዕመ ኵሉ ዓለም ።… አብ የወይን ግንድ ነው፣ ወልድ የወይን ግንድ ነው፣ መንፈስ ቅዱስም የወይን ግንድ ነው፣ ዓለሙ ሁሉ የጣፈጠበት አንዱ የሕይወት ወይን እርሱ ነው " ያለው ይህን የበለጠ ያጎላል።

ከእርሱ ተጠግተው ልምላሜን ከፍረከፍሬ አስተባብረው የኖሩ ቅዱሳንም በዚሁ ተመስለው ይኖራሉ! በተለይ “the king of trees” የተሰኘው እስከ ፻፳ ጫማ ከፍታ የሚረዝም ሰፋፊ ቅጠሎቹ እስከ ፶ ጫማ ወደ ጎን ከግንዱ የሚሳቡ በረዥም ቆይታው በሚያውድ መዓዛው የሚታወቀው የሊባኖሱ ዛፍ (ዝግባ ) ለደጋጎቹ አበው ተደጋግሞ ተመስሏል
ልበ አምላክ ዳዊት ፃድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል እንዳለ (መዝ ፺፩፥፲፪)

✧ ወደ ሊባኖስ ተራራ ተሻግረው ድንግልን ያስገኙ ቅድስት ሃና ቅዱስ ኢያቄምአማናዊው የንጉሥ መፃር የተሠራባቸው ዕፀወ ሊባኖስ ናቸው!
39 views09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 14:15:53
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤ በሰላም አደረሰን
በፍቅር ተስቦ የወረደው ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የፍቅሩን ፍፃሜ በመስቀል ላይ ገልፆልን ሀያል ጌታ በመሆኑ ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል ረድኤት በረከቱ በእያለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን

ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም ተነስቷል በዚህ የለም #መድኃኔዓለም

@Eftah_bemaleda
25 views11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 09:27:15
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤ በሰላም አደረሰን
በፍቅር ተስቦ የወረደው ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የፍቅሩን ፍፃሜ በመስቀል ላይ ገልፆልን ሀያል ጌታ በመሆኑ ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል ረድኤት በረከቱ በእያለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን

ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም ተነስቷል በዚህ የለም #መድኃኔዓለም

@Eftah_bemaleda
27 views06:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 19:43:46 ☞ “ጐየ ፀሓይ ወጸልመ ወርኅ ወከዋክብትኒ ተኀብኡ ከመ ኢያብርሁ ለምእመናን በጊዜ ስቅለቱ ቅዱስ እንዘ ፍጹም በገሃሁ ወርኅ ኢያብርሀ…” (ፀሓይ ብርሃኑን ነሣ ጨረ

ቃም ጨለመ፤ ከዋክብትም በከበረ ስቅለቱ ጊዜ ለምእመናን እንዳያበሩ ብርሃናቸውን ነሡ፤ ጨረቃም በምልአቱ ሳለ አላበራም፤ ፀሓይ ብርሃኑን በነሣ ጊዜ ፍጡራን ኹሉ በጨለማ ተያዙ፤ የፈጠራቸው ፈጣሪያቸው እንደ ሌባ እንደ ወንበዴ በዕንጨት ላይ ተሰቅሎ እንዳያዩ ቀኑ ጨለመ፤ ባለሟሉ መልአክም ከሓድያንን ያጠፋቸው ዘንድ ሰይፉን በእጁ መዝዞ ይዞ ከመላእክት መኻከል ወጣ፤ የክርስቶስም ቸርነት በከለከለችው ጊዜ ያ መልአክ የቤተ መቅደሱን መጋረጃ በሰይፉ መታው ቀደደውም፤ ከላይ እስከ ታችም ወደ ኹለት አደረገው (ማቴ ፳፯፥፶፩፤ ማር ፲፭፥፴፰፤ ሉቃ ፳፫፥፵፭)።

መላእክትም ኹሉ በሰማይ ኹነው ርሱን አይተው በአንድነት ሲቈጡ የአብ ምሕረቱ፣ የወልድ ትዕግሥቱ፣ የመንፈስ ቅዱስ ቸርነቱ ከለከለቻቸው፤ ፀሓይ ብርሃኑን ነሣ፤ በጨለማ ተይዞ ሲድበሰበስ ዓለምንም ተወው፤ ይኽ ኹሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ከሥጋው ከመለየቱ አስቀድሞ ተደረገ) (ቅዱስ አትናቴዎስ)

☞ “እስመ ሶበ ተሰቅለ ክርስቶስ ጸልመ ሰማይ አሜሃ ወፀሓይኒ ሰወረ ብርሃኖ ወወርኅኒ ደመ ኮነ…” (ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ ያን ጊዜ ሰማይ ጨለማ ኾነ፤ ፀሓይም ብርሃኑን ነሣ፤ ጨረቃም ደም ኾነ፤ ምድርም ተነዋወጠች ደንጊያውም ተከፈለ፤ መቃብራትም ተከፈቱ፤ ስለዚኽም ለፍጡራን ከፈጣሪያቸው ጋር ሊታመሙ ተገባቸው (ማቴ ፳፯፥፵፭-፶፩) (ቅዱስ ሱኑትዩ)

☞ “ፀሓይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ ወከዋክብት ወድቁ ፍጡነ ከመ ኢይርአዩ ዕርቃኖ ለዘአልበሶሙ ብርሃነ” (ፀሓይ ጨለመ፤ ጨረቃም ደም ኾነ፤ ከዋክብትም ፈጥነው ወደቁ፤ ብርሃንን ያጐናጸፋቸውን የጌታን ዕርቃን እንዳያሳዩ) (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ)

ሊቁ አባ ጊዮርጊስም ምስጢሩን በመጠቅለል በሕማማት ሰላምታው ላይም፡-
“ፀሓይ ብሩህ አሜሃ ጊዜ ቀትር ጸልመ
ወወርኅኒ ጽዱል ተመሰለ ደመ
ትንቢት ከመ ቀደመ፤ ስብሐት ለከ”
(ብሩህ የኾነ ፀሓይ ያን ጊዜ በቀትር (በስድስት ሰዓት) ጨለመ፤ ጽዱል የኾነ ጨረቃም ደምን መሰለ፤ አስቀድሞ ትንቢት እንደተነገረ፤ ጌታ ሆይ ምስጋና ይገባኻል) በማለት ከትንቢተ ነቢያት በመነሣት በዚኽ በስድስት ሰዓት ምስጋናው ላይ በሰዓቱ ከተከናወነው ምስጢር በመነሣት አስተምሯል፡፡

በመስቀል የተሰቀለው የክብር ባለቤት ሰማይን የፈጠረ ነውና በሰማይ ከላይ የተጠቀሱት ተአምራት ሲደረጉ ምድርንም የፈጠረ ነውና በምድር ደግሞ አራት ተአምራት ማለት የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለኹለት ተቀደደ፤ ምድር ተናውጣ ዐለቶች ተሠንጥቀዋል፤ መቃብራት ተከፍተዋል፤ ከ፭፻ በላይ ሙታን ተነሥተዋል (ማቴ ፳፯፥፵፭፤ ፳፯፥፶፩፤ ፳፯፥፶፪-፶፫)፡፡

አንድያ ልጇን በመስቀል ተሰቅሎ አካሉ ደም ለብሶ ስታየው ኹሉ ሲሸሽ በታማኝነት ቀራንዮ ድረስ ከተገኘው ከሚወድደው ደቀ መዝሙር ከዮሐንስ ጋር መሪር ልቅሶን በምታለቅስበት ጊዜ ዮሐንስ ጌታን በእጅጉ ከመውደዱ የተነሣ ኹሉም ከቀራንዮ ሲሸሽ ርሱ ግን ሳይሸሽ በመቅረቱ ጌታም እንዲኽ ለሚወድደው ለዮሐንስ ፍቅሩን ሊገልጽለት ከስጦታ ኹሉ የላቀች ስጦታው እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን “እናትኽ እነኋት” በማለት ሲሰጠው፤ እናቱንም “እነሆ ልጅሽ” በማለት ዐደራ ሰጥቷታል፡፡

ይኽ የአደራ ቃል ሊፈጸም ጌታችን ካረገ በኋላ ዐሥራ ዐምስት ዓመት በዮሐንስ ቤት ኑራለች፤ በመኾኑም ዮሐንስን በሃይማኖት በምግባር ለምንመስል ለእኛ ለክርስትያኖች ያደራ እናታችን ያደራ ልጆቿ ነንና በልቡናችን ቤት ዘወትር ከብራ ትኖራለች (ዮሐ ፲፱፥፳፮-፳፯)፡፨
የመድኀኔ ዓለም ይቅርታ ከኹላችን ጋር ይኹን፨
ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

ዐርብ
ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ እንዲህ አለ ‹‹አውቀውስ ቢኾን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት" 1ኛ ቆሮ 1፥18

ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤
56 viewsedited  16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 19:43:29 [ዕለተ ዐርብ የመድኀኔ ዓለም ስቅለት]
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (በድጋሚ ፓስት የተደረገ]
(ነገረ ክርስቶስ ከሚለው መጽሐፌ በጥቂቱ የተወሰደ)
ጌታችን ዓለምን ለማዳን በቀራንዮ በመስቀል ላይ ከምድር ከፍ ከፍ ብሎ ስለምን ተሰቀለ? ቢሉ:-
“እምከመ ተለዐልኩ እምድር እስሕብ ኲሎ ኀቤየ” (ከምድር ከፍ ከፍ ባልኊ ጊዜ ኹሉን እስባለኊ) ብሎ ነበርና ይኽነን ሊፈጽም ነው (ዮሐ ፲፪፥፴፪)፡፡

ዳግመኛም ከምድር ከፍ ከሰማይ ዝቅ ብሎ መሰቀሉ “ኅሩይ ማእከለ እግዚአብሔር ወሰብእ” እንዲል አምላክ ወሰብእ ኾኖ እንዳስታረቀን ለማጠየቅ፡፡

በመጨረሻም ምድርን በኪደተ እግሩ እየተመላለሰ እንደ ቀደሳት፤ ዐየራትን ደግሞ ሥብ እያጤሱ አስተራኲሰውት ነበርና አየራትን ለመቀደስ ነው፡፡

ንጹሐ ባሕርይ ጌታችንን አይሁድ መስቀሉን አሸክመው ቀራንዮ ወደሚባል ቦታ ከወሰዱት በኋላ ኹለት ወንበዴዎችን በቀኝና በግራ አድርገው ጌታችንን በመኻከል ሰቅለውታል (ማቴ ፳፯፥፴፰)፡፡

በትርጓሜ ወንጌል እንደታተተው ክፉዎች አይሁድ ይኽነን ያደረጉበት ምክንያት በክፋት ነው፤ ይኸውም በቀኝ የሚመጡ ሰዎች በቀኝ የተሰቀለውን ወንበዴ አይተው “ይኽ ምንድነው?” ብለው ሲጠይቁ “ወንበዴ ነው” ይሏቸዋል፤ ከዚያም ጌታን “ይኽስ ምንድነው?” ብለው ሲጠይቁ “ይኽስ ከርሱ ልዩ ነውን አንድ ነው እንጂ” ብለው ሰዎችን ለማሳሳት፤ በግራ የሚመጡ ሰዎች በግራ የተሰቀለውን ወንበዴ አይተው “ይኽ ምንድነው?” ብለው ሲጠይቁ “ወንበዴ ነው” ይሏቸዋል፤ ከዚያም ጌታን “ይኽስ ምንድነው?” ብለው ሲጠይቁ “ይኽስ ከርሱ ልዩ ነውን አንድ ነው እንጂ” ብለው ሰዎችን ለማሳሳት ያደረጉት ነው፡፡

ዳግመኛም አነገሥንኽ ብለውታልና ቀኛዝማች ግራዝማች ሾምንልኽ ለማለት ለመዘበት፡-
በተጨማሪም ነቢዩ ኢሳይያስ በምዕ ፶፫፥፲፪ ላይ “ከዐመፀኞችም ጋር ተቈጥሯልና” የሚለው ትንቢቱን ሊፈጽም ሲኾን ምስጢሩ ግን እኛን ከጻድቃን ጋራ አንድ ያደርገን ዘንድ ርሱ ከበደለኞች ጋር ተቈጥሯል፤ ሌላውም በዕለተ ምጽአት እኛን ኃጥኣንን በግራ ጻድቃንን በቀኝ ታቆማለኽ ሲያሰኛቸው ነበር (ማቴ ፳፭፥፴፫፤ ራእ ፩፥፯)፡፡

ይኽነንም በሕማማት ድርሳኑ ላይ ሲገልጹ፡- “ወሰቀልዎ ለእግዚእ ኢየሱስ ዲበ ዕፀ መስቀል እንዘ ገጹ መንገለ ምሥራቅ ወእዴሁ ዘየማን መንገለ ደቡብ ወእዴሁ ዘፀጋም መንገለ ሰሜን…” (ጌታችን ኢየሱስንም በዕንጨት መስቀል ላይ ሰቀሉት፤ ፊቱን ወደ ምሥራቅ ቀኝ እጁን ወደ ደቡብ፤ ግራ እጁን ወደ ሰሜን አድርገው ሰቀሉት … ከርሱም ጋር ኹለቱን ወንበዴዎች አንዱን በቀኝ አንዱን በግራው በመኻከላቸው ጌታችን ኢየሱስን አድርገው ሰቀሉ፤ ሕዝቡም ርሱም እንደነርሱ ወንበዴ ነው ይሉት ዘንድ ሰቀሉት፤ ርሱ ግን ወድዶ ከወንበዴዎች ጋር በዕንጨት መስቀል ተሰቀለ፤ ልዑላን መላእክት ፈርተው በፊቱ ራሳቸውን ዝቅ ዝቅ የሚያደርጉለት ርሱ በሚሰቅሉት ፊት ራሱን ዝቅ አደረገ (ፊልጵ ፪፥፲፤ ራእ ፬፥፲-፲፩)።

በከሃሊነቱ ሰማይና ምድርን ያጸና ከግርማውም የተነሣ ሰማያትና ምድር የሚንቀጠቀጡለትን ርሱን ደካማ ዕንጨት ተሸከመው (ምሳ ፴፥፬፤ ኢሳ ፵፪፥፭)፤ ርሱ ግን ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ከራሱ ያስታርቀን ዘንድ ከሰማይ ዝቅ ብሎ ከምድር ከፍ ብሎ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ፤ ርሱም ስለእኛ በሥጋው በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ፤ ከኀጢአታችን ይለየን ዘንድ በቸርነቱ ያድነን ዘንድ ተሰቀለ (፩ጴጥ ፪፥፳፬)።

ርሱ ግን ሰማያትን ይቀድስ ዘንድ በአየር ያሉ አጋንንትን ያወርዳቸው ዘንድ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ፤ ሙሴ አርዌ ብርትን በገዳም እንደ ሰቀለው ርሱም በዕንጨት ላይ ተሰቀለ ፤ በርሱ ያመነ ኹሉ ይድናል እንጂ እንዳይጐዳ የክብር ባለቤት ርሱ ግን ስለ እኛ በዕንጨት ላይ ተሰቀለ (ዮሐ ፫፥፲፬-፲፭)፤

አውቀውስ ቢኾን የክብር ባለቤት ጌታን ባልሰቀሉት ነበር (፩ቆሮ ፪፥፰)፤ ሰማይ ዙፋኑ ሲኾን ምድርም በእግሮቹ የተረገጠች ስትኾን ስለኛ በዕንጨት ተሰቀለ (ኢሳ ፷፮፥፩)፤ ርሱ ግን ተጠብቆለት ስላለ ስለ ደስታው የመስቀልን መከራ ንቆ አቃልሎ ተቀበለ ኀፍረትንም ናቃት፤ ለተሰቀለው ለርሱ የማይሰግድ ቢኖር የተለየ የተወገዘ ይኹን (ፊልጵ ፪፥፰-፲፩)፤ ርሱ ግን ስለ ዓለሙ ደኅንነት በማእዝነ ምድር ወደ ላይ ወደ ታች ወደ ግራ ወደ ቀኝ ኾኖ እንደ መጋረጃ በዕንጨት ላይ ተሰቀለ፤ እኛን ከጻድቃን ጋራ አንድ ያደርገን ዘንድ ርሱ ከበደለኞች ጋር ተቈጠረ) በማለት በስፋት የነገረ ስቅለቱን ምስጢር አስተምረዋል፡፡

በመስቀል ሲሰቀልም በቀኙ የተሰቀለው ጥጦስ በግራ የተሰቀለው ዳክርስ ይባላል፤ በቀኝ የተሰቀለው ጥጦስ ፀሓይ ስትጨልም፣ ጨረቃ ደም ስትኾን፣ ከዋክብት ከብርሃናቸው ሲራቈቱ፣ ድንጋዮች ሲሠነጠቁ፣ መቃብራት ሲከፈቱ፣ ሙታን ሲነሡ፣ የምኩራቡ መጋረጃ ወደ ኹለት ወደ ሦስት ሲቀደድ ሰባቱ ተአምራት ሲደረጉ አይቶ አምላክነቱን ተረድቶ “አቤቱ በመንግሥት ዐስበኝ” እያለ ወደ ርሱ ሲለምን፤ በግራ የተሰቀለው ወንበዴ ሰምቶት እየተዘባበተ “አንተስ ክርስቶስ አይደለኽምን? ራስኽንም እኛንም አድን” ይል ዠመር (ሉቃ ፳፫፥፴፱)፡፡

ያን ጊዜ በቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ ጌታችን ለቤዛ ዓለም የተሰቀለ እውነተኛ የባሕርይ አምላክነቱን ስለተረዳ በግራ የተሰቀለውን “አንተ እንደዚኽ ባለ ፍርድ ሳለኽ እግዚአብሔርን ከቶ አትፈራውምን? ስለ አደረግነውም የሚገባንን እንቀበላለንና በእኛስ እውነተኛ ፍርድ ነው፤ ይኽ ግን ምንም ክፋት አላደረገም” ብሎ ከገሠጸው በኋላ ኀጢአት ሳይኖርበት የተሰቀለውን ንጹሐ ባሕርይ አምላኩን፡- “ተዘከረኒ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ” (ጌታ ሆይ በመንግሥትኽ በመጣኽ ጊዜ አስበኝ) እያለ ሲለምነው ጌታችንም “እውነት እልኻለኊ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኾናለኽ” ብሎት ተስፋውን ሰጥቶታል፡፡

በኹለት ወንበዴዎች መኻከል ከሰቀሉት በኋላ ጲላጦስም “የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ” የሚል ጽሕፈት በዕብራይስጥና በሮማይስጥ በግሪክም ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው፤ (ዮሐ ፲፱፥፲፰-፳፪)፤ የአይሁድ ካህናት አለቆች ጲላጦስን “ርሱ የአይሁድ ንጉሥ ነኝ እንዳለ እንጂ የአይሁድ ንጉሥ ብለኽ አትጻፍ” ሲሉት፤ ጲላጦስም “የጻፍኹትን ጽፌአለኊ” ብሎ መልሶላቸዋል።

ይኽነንም በሕማማት ድርሳኑ ላይ ሲተረጒሙት፡- “ወዝ መጽሐፈ ጌጋይ ዘጸሐፎ ጲላጦስ ወአንበሮ መልዕልተ ርእሱ ይደምስስ ለነ በኲሉ ጊዜ መጽሐፈ ዕዳነ ዘጸሐፉ አጋንንት” (ጲላጦስ ጽፎ ከራሱ በላይ ያኖረው በደሉን የሚናገር ይኽ መጽሐፍ ኹልጊዜ አጋንንት የጻፉትን የዕዳችንን መጽሐፍ ያጠፋልን ዘንድ ነው) በማለት አራቅቀው ገልጠዋል፡፡

ጌታችን በሚሰቀልበት ጊዜ ብርሃን ያለበሳቸውን አምላክ ዕርቃኑን ለመሰወር ከስድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ፀሓይና ጨረቃ ብርሃናቸውን ነሥተዋል (ማቴ ፳፯፥፵፭)፡፡

ይኽ በጌታ ስቅለት ዕለት እንደሚደረግ አስቀድሞ በነቢዩ አሞጽ ኹለት ጊዜ በትንቢት ተነግሯል፡- ይኸውም
☞ “የእግዚአብሔር ቀን ብርሃን ሳይኾን ጨለማ አይደለምን? ጸዳል የሌለውም ድቅድቅ ጨለማ አይደለምን?” (አሞ ፭፥፳)
☞ በዚያም ቀን ፀሐይ በቀትር እንድትገባ አደርጋለኊ ይላል ጌታ እግዚአብሔር በብርሃንም ቀን ምድሩን አጨልማለኊ” (አሞ ፰፥፱) ተብሎ

በዕለተ ዐርብ በጌታችን ስቅለት ዕለት ስለተደረገው ስለዚኽ ታላቅ ተአምር ሊቃውንት እንዲኽ ይገልጹታል፡-
63 views16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 12:06:30 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸዉ አምስቱ ችንካሮች (ሚስማሮች) ስም፦

#1ኛ ሳዶር
#2ኛ አላዶር
#3ኛ ዳናት
#4ኛ አዴራ
#5ኛ ሮዳስ

አምስቱ የእመቤታችን ኃዘናት፦

#1ኛ ከአምስቱ አንዱ አይሁድ እንዲገድሉክ በቤተ መቅደስ ስምዖን ትንቢት በተናገረ ጊዜ ነዉ።ሉቃ 2÷34
#2ኛ ሁለተኛዉም ሦስት ቀን በቤተ መቅደስ ባጣሁህ ጊዜ ነዉ።ሉቃ 2÷41
#3ኛ ሦስተኛዉም እጅህን እግርህን አስረዉ በጲላጦስ አደባባይ የገረፉህን ግርፋት ባሰብኩ ጊዜ ነዉ።ዮሐ19÷1
#4ኛ አራተኛዉም በዕለተ አርብ እራቆትህን ቸንክረዉ በሁለት ወንበዴዎች መካከል እንደሰቀልኩ ባሰብኩ ጊዜ ነዉ አለችዉ። ዮሐ19÷17
#5ኛ አምስተኛዉም ወደ ሐዲስ መቃብር ዉስጥ እንዳወረዱህ ባሰብኩ ጊዜ ነዉ።ዮሐ 19÷38

ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈፀሙ 7ቱ ተአምራት፦

#1ኛ ፀሐይ ጨልሟል
#2ኛ ጨረቃ ደም ሆነ
#3ኛ ከዋክብት እረገፉ
#4ኛ ዓለቶች ተሰነጠቁ
#5ኛ መቃብር ተከፈቱ
#6ኛ ሙታን ተነሱ
#7ኛ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለሁለት ተቀደደ

ሰባቱ የመስቀል ላይ ንግግሮች፦

#1ኛ አምላኬ አምላኬ ለምን ተዉከኝ።ማቴ 27÷46
#2ኛ አባት ሆይ የሚያደርጉት አያዉቁምና ይቅር በላቸዉ።
ሉቃ 23÷34
#3ኛ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእዉነት እነግረሃለሁ።
ሉቃ 23÷43
#4ኛ እነሆ ልጅሽ አነዃት እናትህ።ዮሐ 19÷26
#5ኛ ተጠማሁ።ዮሐ 19÷28
#6ኛ አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ።ሉቃ 23÷46
#7ኛ የተፃፈ ሁሉ ደረሰ ተፈፀመ አለ።ዮሐ19÷30

የአምላካችን ቸርነትና የእመቤታችን ምልጃ አይለየን አሜን ፫


@Eftah_bemaleda
30 views09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 12:02:33 " ሕማማት መስቀል" ተብለው የሚዘከሩት አሥራ ሦስት ሲሆኑ እነዚህም፦

1. በብረት ሐብለ መጋፊያና መጋፊያው እስኪጋጠም ድረስ የኋሊት መታሰሩ
2. ከአፍንጫው ደም እስኪውጣ ድረስ 25 ጊዜ በጡጫ መመታቱ
3. 65 ጊዜ ከግንድ ማጋጨታቸው
4. 120 ጊዜ በድንጋይ ፊቱን መመታቱ
5. 365 ጊዜ በሽመል መደብደቡ
6. 80 ጊዜ ጽህሙን መነጨቱ
7. 6666 ጊዜ መገረፉ
8. አክሊለ ሦክ በራሱ ላይ መደፋቱ
9. 136 ጊዜ በምድር ላይ መውደቁ
10. ሳዶር፡ አላዶር፡ ኤዴራ፡ ዳናትና ሮዳስ በሚባሉ 5ቱ ቅንዋተ መስቀልበችንካር መቸንከሩ
11. መራራ ሐሞትን መጠጣቱ
12. መስቀሉን ተሸክሞ መንገላታቱ
13. በመስቀል መሰቀሉ ናቸው።

@Eftah_bemaleda
32 views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ