Get Mystery Box with random crypto!

አሌክስ ነኝ ባለን ነገር በተሰጠን እንማማር

የቴሌግራም ቻናል አርማ alexnote1405 — አሌክስ ነኝ ባለን ነገር በተሰጠን እንማማር
የቴሌግራም ቻናል አርማ alexnote1405 — አሌክስ ነኝ ባለን ነገር በተሰጠን እንማማር
የሰርጥ አድራሻ: @alexnote1405
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 198
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ page የኔ የሆኑ በማህበራዊ ህይወቴ ዉስጥ ትስስር ያላቸው ወዳጆቼን ይብለጥ እዴዘልቅ የሚፈጥር የመማማሪያ ብሎም የመተዋወቂያመንገድ ስለሆነ የሚተላለፎትን በማበብ በመረዳት ለወዳጅኦ ያካፍሉበት።በተጨማሪም ያገባኛል ያገባናል የሚል ሀቅ እውነትን ይዘን እድንማማር ጭምር ነው ።።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-20 09:56:21 ሳቋን የተቀማች
ሳቋን የተቀማች ያቺ ምስኪኗ ሴት
በህይወቷ ለማደግ ብዙ እቅድ ቢኖራት
ጉልበተኞች መተው ሳቋን እየቀሟት
እንዴት ብላ ትደግ
እንዴት ብላ ትኑር
ጉልበተኛ ሳሰቃያት በጥላቻ ፍቅር
የኔ ካልሆንሽ ብሎ ሳቋን እያሰረ
በሰይጣናዊ ስራ አይምሮው የሰከረ
ለመኖር ብላ ዝምታን ብትመርጥ ሀዘናም ቢበረታ
አይሰለቸው እሱ ቀን ከሌት እሷን ሲያንገላታ
እስቲ እንዴት ትቻል ይህንን መከራ
በመንገዷ ሁሉ ልቧ እየፈራ
ደስታ ከሷ እርቆ በሀዘን ቢተካ
እንዴት ብላ ትኑር ሳይኖራት..............
ሳቋን የተቀማች ያቺ ምስኪን ደሃ
መመኪያ ባይኖራት ሚሰጣት ፍስሃ
ዘላለም በለቅሶ ዘላለም ፍራቻ
እስከመቼ የሷ ደስታ ቅፅበታዊ ብቻ
እስቲ ምን ትሁን ለጉልበተኞች ብላ
ትሙት ወይስ ታልቅስ ወይስ ሀዘን ቤቷን ይሙላ
ሳቋን የተቀማች ያቺ ምስኪን ልጅ
ፍቅር ናት እሳ ሰውንም ወዳጅ
አንገቷን ጠምዝዞ ሊገዛት ሲሞክር
በጩቤ አስፈራርቶ ሊያስገድዳት ሲጥር
ታዲያ ይቺ ሴት ምን አጥፍታ ነው ማንንስ በድላ
የህይወቷ መንገድ እንዲህ የሚጉላላ
ሳቋን የተቀማች ያቺ ምስኪን ፀሎተኛ
ፈጣሪዋን አክባሪ ሲበዛ ሀይማኖተኛ
ታዲያ ለሷ ይኼ ይገባታል(2)
እንኳንስ ሳቅ ቀርቶ ምነም ይገባታል
አቤት ህይወት ግን
ለአንዱ ቀኝ ለአንዱ ግራ
አይነ ስውር አርጋ እሷው የምትመራ
አንዱ ጉልበተኛ ሆኖ ህይወቷን ሲያሰቃይ
ያቺ ቀን መቼ ናት
ለሷ ብላ የምትወጣው ፀሀይ
ሳቋን የተቀማች ያቺ የኔ ውባ
እንዴት ላውርድላት የሀዘኗን ካባ
አቅም አጥሮኝ አንዳች ባልፈጥርላት
አላስብም እኔ አንድ ቀን ልለያት
ሳቋን የተቀማች ያቺ የኔ ውባ
መች ይሆን ማወርደው የሀዘናን ካባ
አቅም ኖሮኝ ሁሉን ባደርግላት
ሀዘናን አጥፍቼ ደስታን በሰጠኃት
ምንኛ ደስ ባለኝ ምንኛ በታደልኩ
ለእሷ ስል ሁሉንም ባደረኩ
እስቲ እናንት ሰዎች አንድ ነገር በሉ
መፍትሔ የሚሆን አንድ ነገር አውሩ
ሳቅ የተቀማችውን እስቲ ደስታ እንስጣት
እስቲ እንዴት ብለን ከእስራት እንፍታት?
መልሱን ለናንተ ነው ለምታነቡ ይኽን
አንድ ነገር ንገሩኝ መፍትሔ የሚሆን።


Share_and_join
51 viewsalex Prizu, 06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 09:56:21 ለማሸነፍ የተሽነፋ ሰዎች

የህይወት አላማው መኖር ነው። life is meant for living ይላል ታዋቂው አሸንቃኝ ፍራንክ ሲናትራ። መኖር ዘመቻ ነው ፣ ጦርነቱ ከህይወት ጋር ነው። ጦርነቱን ለማሸነፍ ብቃትና ታክቲክ ከተለያዩ አንጋፋ ሰዎች በጥቅስም ፣ በተረት፣ በስነልልቦና መነባንቦች አንግበን እንዘምታለን።

ለምሳሌ ሩድያርድ ኪፕሊን ''IF'' በምትባል ታዋቂ ግጥሙ ህይወትን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል በተዋቡ ቃላቶቹ ጠቅሶ ይነግረናል። ዶ/ር ከበደ ሚካኤል በታሪክና ምሳሌ መጽሐፋቸው ይኼንኑ ግጥም "ሰው ለመሆን ብትፈልግ'' ብለው ተርጉመው ያቀርቡታል። ግጥሙ ላይ ያለውን የህይወት ፈተና እና ውጣ ውረድ ማሸነፍ ይከብዳል።

ያሽነፈው ደግሞ የሚሰጠው ማፅረግ ከባድ ነው። '' ሰው'' ተብሎ ይጠራል። '' ባልጠራ ይቅርብኝ'' የሚለው ፈሪ ወይንም ከጂ ተብሎ ሊሰየም ይችላል። እሱም ግን መኖሩን ይቀጥል፣ ወደ ኋላ እያፈገፈገም ቢሆን።

ሄሚንግዊይ የሚባል ሰለ ሰው እና የህይወት ፈተና ቁልጭ አድርጎ በመግለጽ የሚታወቅ ከባድ ሚዛን ደራሲ...

ህይወት ሰውን ያጠፋው ይሆናል እንጂ አያሸንፈውም.. ይላል (a man may be destroyed but not defeated) ::

በሰውና ህይወት መሀል በሚደረገው ፍልሚያ ሰው ያሸንፋል።

ቢሸነፍ እንኳን ግን እጅ ሰጥቶ አይደለም ይለናል። ይኸው ደራሲ ጭንቅላቱን በራሱ እጅ በጥሶ ጥሏል። እንግዲህ እዚህ ላይ ማን አሸናፊ ማን ተሸናፊ እንደሆነ ያጠያይቃል።

ህይወትን ለመግደል ብሎ ራሱን ጥሎ ይሆን? ህይወት ሲታጨድ ሞት በህይወት ምትክ ተዘርቶ መብቀል ይቀጥላል።

ከደራሲው የተሰወረበት እውነት ምናልባት ፤ ህይወት የሚኖረው ሰው ላይ መሆኑ ሊሆን ይችላል። ህይወትን ማሸነፍ ማለት ራስን ማሸነፍ ነው። ህይወትን ማዳን ራስን ማዳን፤ ህይወትን ማጥፋትም ራስን ማጥፋት መሆኑ ነው።

ነገር ግን ሄሚንግዌይን የመሰለ ለብዙ ተከታታይ ዘመናት የድርስት ከባድ ሚዛን ቀበቶ የወሰደ ደራሲ ይኼንን ያጣዋል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው።

እንዲያውም ፤ በአንድ ታዋቂ አጭር ልብወለድ ድርሰቱ መግቢያ ላይ ይሄንኑ በሰው እና ህይወት መሀል የሚደረግ ፍለጋ እና አደን ላይ ተመርኩዞ በተለዋጭ ዘይቤ መልካ የሚለው ነገር አለ፦ ... በበረዶ የተሸፈነው የኪሊማንጅሮ ተራራ የምዕራቡ ጫፍ የእግዜር ቤት ተብሎ ይጠራል።

እዛው ጫፍ አቅራቢያ በቅዝቃዜ የደረቀ የነብር ሬሳ ይገኛል። ነብሩ ምን ፈልጎ ወደ ቀዝቃዛ ተራራ ጫፍ እንደወጣ ማንም ማስረዳት አልቻለም.. ይለናል። ነብሩን ሰው አድርገን ብንወስደው አዳኝና ታዳኝ ህይወትን ተመስለው ይታዩናል። ነብሩ መሬት ላይ ያሉትን አራዊት አድኖ ወይንም አሸንፎ ከፍ ያለ ነገር ፍለጋ ተራራው ላይ ወጥቷል። ነብር አዋቂ፣ ጠንቃቃ እና ብቸኛ አዳኝ ነው። እንደሚያገኘው እርግጠኛ ያልሆነውን ጠረን ተከትሎ ያን ያህል ርቀት አይጓዝም። ምናልባት ድሮውኑ አሽትቶ ለማደን የተከተለው የራሱን ጠረን ይሆን እንዴ? የህይወት ትርጉም ራስን መፈለግ የሚሆነው እዚህ ላይ ነው።

ልቀጥል ነበር መተኛት አለብኝ በቃ ነገ ይቀጥላል



መልካም መልካም ነገሮችን ሼር ማድረግ ጥሩ
ነው
42 viewsalex Prizu, 06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 23:28:29 ጥሩ ጸሐፊ ለመሆን ጥሩ አንባቢ መሆን ይጠይቃል

@ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ከፀሀፊነቱ ይልቅ አንባቢነቱ ይጎላብኛል። በስነፅሁፍ ፍልስፍና ስነልቡና በስነመለኮት በወታደራዊ ሳይንስ ብዙ አንብቧል። የMeet Etv ጋዜጠኛ ተፈራ ገዳሙ

"እስከአሁን ያነበብካቸው መፅሀፍቶች 7000 ይደርሳሉ ይባላል ብሎ ሲጠይቀው ጋሽ ስብሐት

"በእርግጥ ብዙ መፅሀፍት አንብቤያለሁ። ማን ቆጥሮ 7000 እንዳደረሳቸው ግን እንጃ። የኔ ስራ ማንበብ እንጂ መቁጠር አይደለም" ብሎ መልሶለታል።

ስብሐት ምን ያህል እንዳነበበ ግልፅ የሚሆነው እግረመንገድ አምዱን እና ማስታወሻን በተለይ ንባበ ስብሐት የሚለውን አምድ ስናነብ ነው። ጋሼ በታሪክ፣ በአፈታሪክ ፣ በስነልቡና ፣ በፍልስፍና ጠብሰቅ ያለ እውቀት ነበረው። ምክንያቶቹ ደግሞ መፅሀፍት ናቸው።

@ኃይለመለኮት መዋእል

ኃይለመለኮት ጎበዝ ደራሲ ብቻ ሳይሆን ጎበዝ ተናጋሪም ነው። አንደበተ ርቱእ ነው። ንግግሩ አፍ ያስከፍታል። ምናልባት የተፈጥሮ ስጦታ ሊሆን ይችላል። ምናልባት ከማንበብ ልምዱ ሊሆን ይችላል። አይታወቅም። ግን ኃይለመለኮት ብርቱ አንባቢ ነው። አይጠቅምም ብሎ የሚተወው ነገር የለም። የስምንተኛ ክፍል የኬሚስትሪ መፅሀፍ፣ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ወይም የዶስቶቭስኪ መፅሀፍ ሁሉንም ያነባል።

@አለማየሁ ገላጋይ

አለማየሁ ታላቅ ደራሲ ነው። ደራሲነት ተሰጥኦው ነው። ደግሞም በንባብ አዳብሮታል። አለማየሁ ስላነበብከው መፅሀፍ መልሶ ሲያወራልህ መስማት ድጋሚ እንደማንበብ ነው። የሚያይበት አይኑ ጥልቅ ነው። ነገሮችን ካልታዩበት አቅጣጫ ገላልጦ ያሳያል። ከመአዛ ብሩ ጋር በሸገር ካፌ ብዙ ጨዋታቸውን ተከታትያለሁ። መፅሀፍት የማእድን ጉድጓድ ቢሆኑ አለማየሁ ቆፍሮ አልማዝ አልማዙን የሚያወጣ ብርቱ አንባቢ ነው።

@ዘነበ ወላ

ዘነበ ወላ ቁምነገረኛ ፀሐፊ ነው። ዘኔ አይቀልድም ፤ ቧልት አይወድም። ታድያ ቁምነገረኝነቱን ያገኘው ከመፅሀፍ ነው። ዘኔ የሚያነበውን መፅሀፍ ይመርጣል። ታሪክ ግለ ታሪክ የመሳሰሉት ምርጫዎቹ ናቸው። በቀድሞው ህይወቱ ባህረኛ ነበር። የባህረኛ ህይወት ከባድ ነው። ለወራት መሬት ሳያዩ ውሃ ላይ መቆየት ይኖራል። ታድያ ይሄንን ከባድ ህይወት ለመክፈል መፅሀፍ ተተኪ የማይገኝላቸው ውድ ጓደኞች ናቸው።

@በእውቀቱ ስዩም

በእውቀቱ ስዩም ቧልተኛ ነው፤ በእውቀቱ ስዩም ቁምነገረኛ ነው። ይሄ ጠባዩ በጣም ይደንቀኛል። ሁለቱንም በእኩል የሚያስኬድ ጥራ ቢባል ከበእውቀቱ ሌላ አላውቅም። ታድያ በእውቀቱ ቧልቱን በተፈጥሮ፣ ቁምነገሩን ደግሞ በንባብ ያገኘው ይመስለኛል። በእውቀቱ የአገሩን ስነፅሁፍ ታሪክ ባህል በዝርዝር የሚያውቅ ደራሲ ነው። ባነበበው ላይ ቧልቱን ጠብ እያደረገ በሚያዝናና አቀራረብ የሚሰጠን ፀሐፊም ነው።

@አሌክስ አብርሃም

የንባብ ፕሮፓጋንዳ አይወድም።(ይሄንንም ፅሁፍ አይወደውም ) ዝም ብሎ ማንበብ ብቻ። ከሚፅፈው ተነስቶ ብዙ እንደሚያነብ መናገር ይቻላል―በተለይ ልብወለድ ግጥም እና ታሪክ። ማንበብ ሙሉ አያደርግም። ግን ማንበብ ጎበዝ ፀሐፊ እንደሚያደርግ አሌክስን አይቶ መናገር ይቻላል። ታድያ የተፈጥሮ ተሰጥኦው መኖር እንደተጠበቀ ሆኖ ነው።

@የሺጥላ ኮከብ

የሺጥላ የ"ወገግታ" እና "ዶሰኛው" ደራሲ ነው። ታድያ አሁን የሺጥላ ከሃገር ወጥቶ ከስነፅሁፍ ተቆራርጧል። ሃገር ቤት እያለ ግን ጎበዝ አንባቢ ነበር። ወመዘክር ቋሚ ደንበኛ ነበር። ግን ወመዘክር 12 ሰአት ላይ ይዘጋል። እሱ ደግሞ እያነበበ ማደር ይፈልጋል። ስለዚህ መዝጊያ ሰአት ሲደርስ አንዱ ክፍል ገብቶ ይደበቃል። ሰራተኞቹ ቆልፈው ሲወጡ ከተደበቀበት ወጥቶ ንባቡን ያጧጡፋል። አቤት የንባብ ፍቅር!!!

@ኄኖክ ስጦታው ናሁሰናይ

እዚህ ሰፈር የኄኖክን ያህል አንባቢ ያለ አይመስለኝም። ኄኖክ ያላመጠውን ዝም ብሎ የሚተፋ ያነበበውን ዝም ብሎ የሚዘረግፍ አንባቢ አይደለም። አላምጦ አሰላስሎ የራሱን ቀለም ጨምሮ የሚሰጥ እንጂ።

ይብቃኝ!!!

ምንጭ Tewodros
56 viewsalex Prizu, 20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 21:24:27
51 viewsalex Prizu, 18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 21:24:00
50 viewsalex Prizu, 18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 16:33:11 #ጎረቤት:- ስንት ልጆች አሉክ?

#አባት:- አራት ልጆች አሉኝ
አንዱ መሀንዲስ ነው!
ሁለትኛው ማስተርስ ዲግሪ አለው!
ሶስተኛው ዶክትሬት ዲግሪ አለው!
አራተኛው ሌባ ነው!

#ጎረቤት:- ለምን ታዲያ ሌባውን ከቤት አታባረውም?

#አባት:- እንዴ ምን ነካህ: እሱ እኮነው የቤቱን ወጪ ቀጥ አድርጎ የያዘው ሌሎቹ ስራ የላቸውም!

58 viewsalex Prizu, 13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 16:33:06 "ወዳጄ ሆይ በህይወት እስካለህ ፊልም ታያለህ፡፡ህይወት ግን ፊልም አይደለችም፡፡ አንድ የፊልም ተዋናይ በሰባት ፊልም ላይ ሰባት ሴት ሊወድ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ሰባት ፊልም ስለሰራ፡፡ አንተ ግን አንድ ህይወት ነው ያለክ፡፡ አንድ የመኖር እድል ደጋግመክ መኖር አትችልም፡፡ህይወት አንድ ግዜ ብቻ ነው፡፡ያለህን አንድ እድል በአግባቡ ተጠቀምበት፡፡"
share ur friends

መልካም ቀን
52 viewsalex Prizu, 13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 14:34:27 አስቸኳይ #የራስ_በራስ የስብሰባ ጥሪ


ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች፤ ዛሬ እስቲ ለራሳችሁ አንድ ውለታ ዋሉ። እራሳችሁን ለማድመጥ ጊዜ ስጡ።እስኪ ዛሬ ከራስችሁ ጋር አስቸኳይ ስብሰባ ያድርጉ። ከፖለቲካ ወሬ፣ ከፌስቡክ ጫጫታ እና ግርግር ይውጡና ልባችሁን አድምጡ።ብቻችሁን የምትሆኑበትን ቦታ ምረጡ። ትኩረታችሁን በሙሉ ሰብስቡ እስኪብርቶ እና ወረቀት ይዛችሁ ጥያቄውን ለመመለስ ሞኩሩ ይህ ጥያቄ አሁን መመለስ ባትችሉ እንኳን መልስ እስክታገኙ ድረስ መጠየቅ እንዳታቆሙ።እነዚህ ጥያቄዎች የህይወት ቁልፍ ጥያቄ ናቸው። ማንም ሊመልስላችሁ አይችልም ራሳችሁ እንጂ ስለማንም አይደለም ስለራሳችሁ እንጂ
በራስ..ለራስ..ሰለራስ የሚጠየቅ ጥያቄ ነው።

የላቀ ምላሽ ለማግኘት ቁልፉ የላቀ ጥያቄ ማቅረብ ነው። የምትጠየቁት ጥያቄ ልህቀት ለህይወት ያላችሁን ግንዛቤ ይወስናል። በደመነፍስ የምትኖሩትን ህይወት እንድትመረምሩ እና የህይወታችሁን አላማ እና ጉዞ እንድታውቁ ያደርጋችኋል። ዛሬ የላቀ ሕይወት መምራት የጀመራችሁበት እለት እንደሆነ አስቡ። ሕይወታችሁን በፈለጋችሁበት መልኩ ለመቅረፅ ሙሉ ነፃነት አላችሁ። ይህንንም ለማድረግ የሚያስችሏችሁ ጥያቄዎች ከዚህ በታች ቀርበዋል። ራሳችሁን ሳትሸውዱ፤ መልሳችሁን ጊዜ ወስዳችሁ ና አስተውላችሁ ፃፉ!!!!

#####################
እናንተም ሌላውንም ይጠቅማል ብለዉ ካሰቡ ሼር በማድረግ መልካምነትን እናስፋፋ !!!
58 viewsalex Prizu, 11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 14:34:12 ውየ ከመግባቴ: ተኝቸም ስነሳ፣
ምነው ክፉ ክፉ: ያሰማኛልሳ።
በሽታ እንዳለባት: የሳንባ ነቀርሳ፣
ሃገሬን አረጓት: አድራ የምትከሳ።
....
ዘለው እየገቡ: እዛም እዚም መንደር፣
ሥርዓት የለሾች: በጠበጡ ሃገር።
እንክርዳዱን ከተው: በምስጥር ጎታቸው፣
ስንዴውን በእሳት: ማቃጠል አሻቸው።
55 viewsalex Prizu, 11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 20:06:17 "ይህችን ዓመት ተወኝ!"

ከዓመት እስከ ዓመት - ፍሬን ሳላፈራ - ደረቅ እንደሆንኩኝ
በራድ ወይም ትኩስ - ሁለቱንም ሳልሆን - እንዲያው ለብ እንዳልኩኝ
አለሁኝ በቤትህ - ለሙን መሬትህን - እያጎሳቆልኩኝ
አውቃለሁ አምላኬ - ፍሬዬን ለመልቀም - እንዳመላለስኩህ
ዛሬም ሳላፈራ - እሾህን አብቅዬ - ደርቄ ጠበቅሁህ
ያልተደረገልኝ - ያላፈሰሰክብኝ - ያልሰጠኸኝ የለም
ነገር ግን ይህ ሁሉ - አላርምህ አለኝ - አልለየኝም ከዓለም
የማትሰለቸኝ ሆይ - ተነሥቼ እስክቆም - እባክህ ታገሠኝ
የእኔን ክፋት ተወው - መልአክህን ሰምተህ - ይህችን ዓመት ተወኝ!

አውቃለሁ ታውቃለህ - ቀጠሮን ሰጥቼ - እንደማላከብር
ብዙ ጊዜ አቅጄ - ብዙ ጊዜ ዝቼ - በወሬ እንደምቀር
‹ዘንድሮስ…!› እንዳልኩኝ - አምና ይሄን ጊዜ - ሰምተኸኝ ነበረ
ምንም ሳልለወጥ - ‹ዘንድሮዬ› አልፎ - በአዲስ ተቀየረ
ፍሬ የማይወጣኝ - እኔን በመኮትኮት - እጆችህ ደከሙ
እኔ ግን አለሁኝ - ዛሬም አልበቃኝም - በኃጢአት መታመሙ
የቃልህን ውኃ - በድንጋይ ልጅህ ላይ - ሳትታክት ስታፈስስ -
ዘመን ተቆጠረ
ወደ ልቤ ሳይሰርግ - ሕይወቴን ሳይለውጥ - እንዲያው ፈስሶ ቀረ
ቃልህን ጠግቤ - እያገሳሁት ነው - ሌሎች እስኪሰሙ
በቃልህ መኖር ግን - አልያዝህ አለኝ - ከበደኝ ቀለሙ
ብዙ ጥቅስ አገኘሁ - ከቅዱስ መጽሐፍህ - ገልጬ አይቼ
ከራሴ ላይ ብቻ - አንድ ጥቅስ አጣሁኝ - በበደል ተኝቼ
ውጤቴ ደካማ - ትምህርት የማይሠርጸኝ - ተማሪ ብሆንም
ይህችን ዓመት ተወኝ - ደግሞ ትንሽ ልማር - ታገሠኝ አሁንም!

እባክህ አልቆረጥ - በቅዱስ መሬትህ - ልቆይ ፍቀድልኝ
ያፈሩት ቅዱሳን - የፍሬያቸው ሽታ - መዓዛ እንዲደርሰኝ
የተሸከምከኝ ሆይ - ዛሬም ተሸከመኝ - አትሰልቸኝ አደራ
ማን ይታገሠኛል - ጠላት እየሆንኩት - አይሠሩ ስሠራ!
አታውጣኝ ከቤትህ - ብዙ ቦታ አልይዝም - ፍሬ ስለሌለኝ
ስፍራ የማያሻኝ - ቤት የማላጣብብ - ፍሬ አልባ በለስ ነኝ!
ቦታስ የሚይዙት - ባለ ምግባሮቹ - ቅዱሳንህ ናቸው
ልክ እንደ ዘንባባ - የተንዠረገገ - ተጋድሎ ጽድቃቸው!
ከሊባኖስ ዝግባ - እጅጉን የበዛ - ገድል ትሩፋታቸው!
እኔ አይደለሁም - ቦታስ የምትይዘው - የአንተው እናት ናት
ሥሮቿ በምድር - ጫፎቿ በሰማይ - ሲደርሱ ያየናት
ይሀችን ዓመት ተወኝ - ከሥርዋ እሆናለሁ - ባፈራ ምናልባት!..
ይህችን ዓመት ተወኝ - እባክህ አምላኬ - አንድ ዓመት ምንህ ናት
ሺህ ዓመት አንድ ቀን - አይደለም ወይ ለአንተ - ዓመት ኢምንት ናት!
ይሄ ዓመት አልፎ - ዳግም ‹ዓመት ሥጠኝ› - እስከምልህ ድረስ
እባክህን ጌታ - ይህችን ዓመት ተወኝ - የወጉን እንዳደርስ!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
61 viewsalex Prizu, 17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ