Get Mystery Box with random crypto!

#መፆረ_ንጉሥ_ዘሊባኖስ †⊙…◆⇝✧⇜◆…⊙† 'መፆረ ገብረ ንጉሥ … ለርእሱ እምዕፀወ ሊባኖስ ንጉ | አሚነ ፅድቅ✨

#መፆረ_ንጉሥ_ዘሊባኖስ
†⊙…◆⇝✧⇜◆…⊙†

"መፆረ ገብረ ንጉሥ … ለርእሱ እምዕፀወ ሊባኖስ
ንጉሡ ከሊባኖስ እንጨቶች ለራሱ ዙፋን ሠራ" (መኃ ፫፥፱)

ይህች ዕለት ለዕለታቱም ዕለታቸው ናት!

✧ ሰንበተ ሰንበታት ፣ ምዕራፈ ነፍሳት፣ ክብረ ኩሉ ፍጥረት፣ ከጨለማ ግዞት ሕዝቡን ወደብርሃን ለማሻገር ማዕዶት የምትሆን ተስፋ እመብርሃን የተገኘችባት ዕለትናትና የዕለታት ዕለት፤

✧ ድኅነተ ነፍስ "ለሰብአ ዓለም የጎሰቆለ ባህሪ" ካሳ ሊሆን የተወጠነባት ዕለትናትና የዕለታት ዕለት፤

✧ ለቤዛ ኩሉ ዓለም እናት፣ መሠረተ መሠረቱ ለሕይወት ፣ ለዕጓለ አንበሳ ወላዲት፣ ታዕካ በምድር ወታዕካ በሰማይ ማርያም (እመ አርያም) የተወለደችበት ዕለት ናትና የዕለታት ዕለት!

ከአንዱ አዳም ጥፋት የተነሳ በዓለም የወደቀው ኀጢአት እና ደሞዙ (ኀጢኦት ፣ ኀጥአ ⇥ ከሚለው እግዚአብሔርን ማጣት በሚል አገባብ ይወሰድ 'እስመ ተግባራሰ ለኃጢአት ወረባሐ ዚአሃ ሞት' እንዳለው እንዲሁም የማጣቱ ውጤት መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ) ከባህርየ ሰብእ የተወገደባት ህፃን፣ "ትምክህተ ዘመድነ" የምትሰኝ ዘርዕ-እቅብት ፣ ቡርክት የሆነች እናት ፣ ኃጥእት ያለሆነች ቅድስት ፣ ታትማ የኖረች ድንግል፣ ወላዲቱ ለአምላክ ማርያም፦ ዛሬ ከአምላክ ኅሊና ወደ አዳም ተስፋ ተሻግራ በነቢያቱ ትንቢትና በአበው ኅብረ ምሳሌ ስትጠበቅ ቆይታ በሥጋ የተገለጠችበት የከበረ ዕለት ነው!

በቀደመው መልክአ ማርያም (ሣልሲት) እንዲህ የሚል ይገኛል ፦

☞ "ሰላም ለተፈጥሮኪ እለ ፈጠሩኪ በተአቅቦ:
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በተናብቦ:
ንዒ ንዒ ንዒ ማርያም ፀምረ ጌድዮን ህቦ:
አመ ኃሠሠ ኅሊናየ እምፍጥረተ ዓለም ዘቦ:
ከማኪ በምሳሌ ዘይመስል አልቦ። "

↳ አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ተገናዝበው በተአቅቦ ለፈጠሩት ባህሪሽ (ተፈጥሮሽ) ሰላምታ ይገባል የጌድዮን የፀምሩ ጠል ማርያም ነዪ ነዪ ነዪ (ብዬ እምጠራሽ ነኝ) ከአለም መፈጠር አንስቶ ያለውን ኅሊናየ ቢፈልግም አንቺን የሚመስልበት አምሳል ግን ከወደየትም አላገኘም!

ይኼንኑ ጠቢቡ በምስጋናው ምስጋና ፣ ከሁሉ በላቀው ማኅሌት፣ በመኃልየ መኃልይ እየዘመረ በገዛ ስሙ ሰሎሞን እያለ መስተሳልም ክርስቶስን ሲያወድስ በምሥጢርም የንጉሡን እናት ያነሳና (እኅትየ መርዓት ፣ እኅቴ ሙሽራዬ እያለ) ሲቀኝላት ቆይቶ ከተነሳንበት ሦስተኛው ምዕራፍ አሻግሮን እንዲህ ሲል ይጠይቃል ፦

∽†∽ "መኑ ይእቲ ዛቲ እንተ ተአርግ እምገዳም ከመ ደመና ? እንደ ደመና አቅንታ ከምድረበዳ የምትትወጣ ይች ማናት? " (ቁ ፮)

ከምድረ በዳው ዓለምና ኀጢአት ይቡስ ካደረገው ኅላዌ የተገኘች እውነተኛው ዝናመ ምሕረት ክርስቶስ አምላካችን ለፍጥረቱ ከተገኘባት አማናዊት ደመና ከድንግል በቀር ማናት … ቅዱስ ያሬድ "ደመናሰ ዘይቤ ይእቲኬ ማርያም እንተ ፆረቶ ዲበ ዘባና" ይላታልና።

አስጠግቶ ይመልሳል መፍቀሬ ጥበብ ፦

∽†∽ "ናሁ ዓራቱ ለሰሎሞን …የሰሎሞን አልጋ ይች ናት" (ቁ ፰)

የመስተሳልም ሰሎሞን የተባለ የክርስቶስ አልጋው ይኽችው ድንግል ማርያም ናት !

አባቱ ዳዊትም በትንቢቱ አስቀድሞ ጽዮን ድንግል ማርያምን ንጉሡ ክርስቶስ
⇛ "ከመ ትኩኖ ማኅደሮ" ብሎ ለክብሩ ዙፋንነት እንዳዘጋጃት፣
⇛ "ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም" ብሎ ለዘልዓለም መኖርያነት እንዳከበራት እና
⇛ "ዝየ አኀድር እስመ ኃረይክዋ" ብሎ ወድዶ ሊወለድባት እንደመረጣት ተናግሮላት ነበርና (መዝ ፻፴፩)

ልጁም ያንኑ ምሥጢር ስቦ የተገለጠለትን በኅሊናው ሲያወጣና ሲወርድ ቆይቶ
⇛ ለቃል መውረድ ዙፋን የሆነ የንጽሕናዋን መደብ ፣
⇛ ለሥጋ ማረግ መሰላል የሆነ የቅድስናዋን እርካብ ከእኛ እንዲህ ሲል አደረሰው ፦

"መፆረ ገብረ ንጉሥ … ለርእሱ እምዕፀወ ሊባኖስ
ንጉሡ ከሊባኖስ እንጨቶች ለራሱ ዙፋን ሠራ" (ቁ ፱)

#የሊባኖስ_እንጨቶች (ዕፀወ ሊባኖስ) ቅድስት ሃናና ቅዱስ ኢያቄም

ሊባኖስ ተራራማ እንጨት የበዛባት መልካም ሀገር ናት። ሊቀ ነቢያት ሙሴ ምኞቱን ከመሞቱ በፊት እንዲህ ሲል አውስቷል "እኔ ልሻገር በዮርዳኖስም ማዶ ያለችውን መልካሚቱን ምድር ያንም መልካሙን ተራራማውን አገር ሊባኖስንም ልይ።" (ዘዳ ፫፥፳፭)

በዚያም ያሉ ዕፀው እንደ ዝግባ ያሉቱ በረዥም ዘመን ቆይታቸው ለዐይን ርእይ ባላቸው ልምላሜና ለአፍንጫ ሽታ ባላቸው ግሩም መዓዛ የበጎ ነገር ማጌጫና የመልካም ምሳሌ መገለጫ ሆነው በቅዱስ መጽሐፍ ተዘግበዋል።

ለቤተ እስራኤል ስለተሰጠችው ብዕለ አሕዛብ ለምዕመንም ስለተገለጠችው ሕገ ወንጌል መልካምነት ለማጠየቅ ቅዱስ ኢሳይያስ በትንቢቱ "ወክብረ ሊባኖስ ተውኅበ ላቲ " (፴፭፥፪) ብሏል።

የዛሬዋ ሊባኖስም በቅዱስ መጽሐፍ ከ፸፯ ጊዜ በላይ ስለተጠቀሰላት መልካም ዝግባዋ ቦታ ሰጥታ ከ1943(እ.አ.አ.) ጀምሮ የሰንደቋ መገለጫ ሆኖ በመኖር ዛሬም በቀይ በታጠረ ሁለት እጅ ነጩ የባንዲራ መደቧ ላይ (1:2:1) ያንን ዝግባ በኩራት የቅድስና አርማ የዘልዓለማዊ ሕይወት ማሳያና የሰላም ምልክት እንደሆነ በማመን ትጠቀምበታለች። (The Cedar is a symbol of holiness, eternity and peace. As an emblem of longevity, the cedar of Lebanon has its origin in many biblical references.)

♛ንጉሥ ዳዊት ቤተመንግሥቱን ለማነጽ (፪ሳሙ ፭፥፲፩፣ ፩ዜና ፲፯፥፩)
♚ ንጉሥ ሰሎሞን እቃ ቤቱን ፣አልጋ ዙፋኑን ፣ ቤተ መንግስቱንና የከበረ የታቦቱ ማደሪያ መቅደሱን ለማነጽ (፩ነገ ፯፥፪ ፣ ፪ዜና ፩፥፲፭ ፣ ፪፥፫―፰)
♜ በዕዝራም መቅደሱ ዳግመኛ ሲታነፅ (ዕዝ ፫፥፯) ለእግዚአብሔር የክብሩ መገለጫ የሊባኖስ እንጨቶች እንደተመረጡ ቅዱስ መጽሐፋችን ደጋግሞ ያስረዳናል።

ዕፀዋት በለመለመ ቅጠላቸው ርቱዕ እምነት ፣ ባማረ ፍሬአቸው ምግባር ትሩፋት እያስተማሩ በቅድስና ለደመቁ ቅዱሳን በምሳሌነት ያገለግላሉ።
ንኡዳን ክቡራኑን "ይከውኑ ከመዕፅ " እንዲላቸው (መዝ ፩፥፫)

መጽሐፍ ቅዱሳችን በምሥጢርና በዘይቤ የተመላ የክርስትናው ፍኖት ማንጸሪያ ነው ( full of metaphors that compare the Christian journey)

በአብነቱ አባታችን፣ በአርያነቱ ፍኖታችን ክርስቶስም ከዕፀው ባንዱ ራሱን እንዲህ መስሏል
"አነ ውእቱ ሐረገ ወይን ዘጽድቅ እኔ የወይን ግንድ ነኝ! " (ዮሐ ፲፭፥፩) በኅርያቆስ ቅዳሴም "አብ ጕንደ ወይን ፤ ወልድ ጕንደ ወይን ፤ ወመንፈስ ቅዱስ ጕንደ ወይን ፩ዱ ውእቱ ወይነ ሕይወት ዘቦቱ ጥዕመ ኵሉ ዓለም ።… አብ የወይን ግንድ ነው፣ ወልድ የወይን ግንድ ነው፣ መንፈስ ቅዱስም የወይን ግንድ ነው፣ ዓለሙ ሁሉ የጣፈጠበት አንዱ የሕይወት ወይን እርሱ ነው " ያለው ይህን የበለጠ ያጎላል።

ከእርሱ ተጠግተው ልምላሜን ከፍረከፍሬ አስተባብረው የኖሩ ቅዱሳንም በዚሁ ተመስለው ይኖራሉ! በተለይ “the king of trees” የተሰኘው እስከ ፻፳ ጫማ ከፍታ የሚረዝም ሰፋፊ ቅጠሎቹ እስከ ፶ ጫማ ወደ ጎን ከግንዱ የሚሳቡ በረዥም ቆይታው በሚያውድ መዓዛው የሚታወቀው የሊባኖሱ ዛፍ (ዝግባ ) ለደጋጎቹ አበው ተደጋግሞ ተመስሏል
ልበ አምላክ ዳዊት ፃድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል እንዳለ (መዝ ፺፩፥፲፪)

✧ ወደ ሊባኖስ ተራራ ተሻግረው ድንግልን ያስገኙ ቅድስት ሃና ቅዱስ ኢያቄምአማናዊው የንጉሥ መፃር የተሠራባቸው ዕፀወ ሊባኖስ ናቸው!