Get Mystery Box with random crypto!

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸዉ አምስቱ ችንካሮች (ሚስማሮች) ስም፦ #1ኛ ሳዶር #2ኛ | አሚነ ፅድቅ✨

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸዉ አምስቱ ችንካሮች (ሚስማሮች) ስም፦

#1ኛ ሳዶር
#2ኛ አላዶር
#3ኛ ዳናት
#4ኛ አዴራ
#5ኛ ሮዳስ

አምስቱ የእመቤታችን ኃዘናት፦

#1ኛ ከአምስቱ አንዱ አይሁድ እንዲገድሉክ በቤተ መቅደስ ስምዖን ትንቢት በተናገረ ጊዜ ነዉ።ሉቃ 2÷34
#2ኛ ሁለተኛዉም ሦስት ቀን በቤተ መቅደስ ባጣሁህ ጊዜ ነዉ።ሉቃ 2÷41
#3ኛ ሦስተኛዉም እጅህን እግርህን አስረዉ በጲላጦስ አደባባይ የገረፉህን ግርፋት ባሰብኩ ጊዜ ነዉ።ዮሐ19÷1
#4ኛ አራተኛዉም በዕለተ አርብ እራቆትህን ቸንክረዉ በሁለት ወንበዴዎች መካከል እንደሰቀልኩ ባሰብኩ ጊዜ ነዉ አለችዉ። ዮሐ19÷17
#5ኛ አምስተኛዉም ወደ ሐዲስ መቃብር ዉስጥ እንዳወረዱህ ባሰብኩ ጊዜ ነዉ።ዮሐ 19÷38

ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈፀሙ 7ቱ ተአምራት፦

#1ኛ ፀሐይ ጨልሟል
#2ኛ ጨረቃ ደም ሆነ
#3ኛ ከዋክብት እረገፉ
#4ኛ ዓለቶች ተሰነጠቁ
#5ኛ መቃብር ተከፈቱ
#6ኛ ሙታን ተነሱ
#7ኛ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለሁለት ተቀደደ

ሰባቱ የመስቀል ላይ ንግግሮች፦

#1ኛ አምላኬ አምላኬ ለምን ተዉከኝ።ማቴ 27÷46
#2ኛ አባት ሆይ የሚያደርጉት አያዉቁምና ይቅር በላቸዉ።
ሉቃ 23÷34
#3ኛ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእዉነት እነግረሃለሁ።
ሉቃ 23÷43
#4ኛ እነሆ ልጅሽ አነዃት እናትህ።ዮሐ 19÷26
#5ኛ ተጠማሁ።ዮሐ 19÷28
#6ኛ አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ።ሉቃ 23÷46
#7ኛ የተፃፈ ሁሉ ደረሰ ተፈፀመ አለ።ዮሐ19÷30

የአምላካችን ቸርነትና የእመቤታችን ምልጃ አይለየን አሜን ፫


@Eftah_bemaleda