Get Mystery Box with random crypto!

ኦፍቲ ቲዩብ-ልበ ጥሞና

የቴሌግራም ቻናል አርማ lebtemona — ኦፍቲ ቲዩብ-ልበ ጥሞና
የቴሌግራም ቻናል አርማ lebtemona — ኦፍቲ ቲዩብ-ልበ ጥሞና
የሰርጥ አድራሻ: @lebtemona
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 195

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-02-28 00:59:36 https://www.facebook.com/100069795433607/posts/pfbid0BXhgTZw46G9K4uhcT2PcHYcgLvPXWiTwAAnWXxEREuKxWx1zSAeFd6hTaocyAkvAl/?app=fbl
13 viewsጌቱ በቀለ, 21:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 07:46:51 Watch "እንታደግ ራሣችንን?" on YouTube


154 viewsጌቱ በቀለ, 04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 20:48:03 ባለህ ጊዜ፣ ቦታ፣ ጉልበትና ገንዘብ ምን ትሠራበታለህ?

ሰዎች "ጊዜ አጥቼ ነው እንጂ!" ቢሉም ሁላችንም እኩል ጊዜ አለን። እኩል 24:00 ሰዓት በየቀኑ። የጊዜ አጠቃቀማችን ግን የየዕለቱን ውሎ በትርፍ ወይም በኪሳራ ይደመድማል።

ብዙ የበሰቃ ሰዎች 250 ካሬ ሜትር ቦታ አላቸው። እነዚህ ሰዎች ይህንን ቦታ ምን የሚያደርጉት፣ እንዴት የሚጠቀሙበት ይመስልሃል? በርካታው እንኳን ቤት ሊሠራበት ጎመንም አይተክልበት። ቦታው ይባክናል።

ቁጥሩ ቀላል የማይባል ወጣት ተራራ የሚንድ ጉልበት አለው። ወይ እንደ ምባፔ ሮጦ፣ ጠርምሶ፣ ትርምስ ፈጥሮ የሚያገባ የኳስ ጎል አግቢ ሆኖ ራሱንና ወገኑን አይጠቅምም። "ሥራ አጣሁ" ብሎ ቁጭ ብሎ ይውላል። ከባሰበት ደግሞ ሱስ ውስጥ ይዘፈቃል።

ገንዘብ ይዞ ቁጭ ያለ ብዙ ነው። ከባንክ፣ እኩል ገንዘብ ተበድሮ አንዱ መሥሪያ ማሽን ሲገዛ፣ ሌላው መዘነጫ መኪና ይገዛል። እውነት ነው እንደ አዋዋል መድረሻም ለየቅል ይሆናል።

እንግዲህ ልዩነት ፈጣሪው ምንድን ነው?

ችግራችን የጊዜ አይደለም፣ የጉልበትም አይደለም፣ የቦታ ማጣትም አይደለም፣ የገንዘብም አይደለም።

ችግራችን የእይታ፣ የሃሳብና የራዕይ ማጣት ነው። ችግራችን የመንገድ አለማወቅ ነው። ችግራችን የህይወት ሹፍርናን አለማወቅ ነው።

ለዚያ ሰልጥነህ መንጃ ፈቃድ ማውጣት ያስፈልግሃል? አሰልጣኞቹ እየመጡ ነው!

ዐይን ካልተከፈተ፣ አእምሮ ካልተለኮሰ፣ የውስጥህ ብርሃን ካልበራ እንኳን ሃሳብ አቧራም አይገባም። ድፍንን ማን ይመርጣል? በራሱ የማይተማመን እንጂ!

"የሰዎችን ዐይን እከፍት ዘንድ" ያለው ማን ነበር?

ሰው ከሰው የሚለየው አስቦ በሚከውነው ድርጊት ነውና የሃሳብ ችቦህን ለኩስና ወደ ድርጊት ተጓዝ! ታድያ ዝም ብለህ ውርውር አትበል፤ ዝም ብለህ ጫማና ጎማ አትጨርስ።

አስብና ሂድ! አትፍራ! ፍርሃትን የምታሸንፈው በድርጊት ነው - ታስቦ በሚከወን ጥንቁቅ ድርጊት።

ኢንጅነር ጌቱ
18 viewsጌቱ በቀለ, 17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 08:46:56 የኢ ጌቱ ሀሳብ ነው
20 viewsጌቱ በቀለ, 05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 08:46:03 "The best investment you can make is an investment in yourself.

The more you learn, the more you earn."

~ Warren Buffett

ዋረን በፌት ስመ-ጥር፣ ዘመን ጠገብ አሜሪካዊ ቱጃር ናቸው። ከላይ ያለውን አባባል እሳቸውም፣ ሌላው ጎምቱ ሰው ጂም ሮህን ደጋግመው ይናገሩታል።

"ራስህን አብቃ፣ ራስህን አልማ፣ ራስህን ለማሳደግ ስልጠናን ቸል አትበል፣..." ይላሉ።

በዚህ ዘመን የምታደርገው ትልቁ ኢንቨስትመንት ራስህን ለማሰልጠን የምታደርገው ጥረት ነው።

መረጃዎች፣ ግንኙነቶች፣ ሃሳቦች፣ የአሠራር መንገዶች፣ የገበያ ፍላጎቶች በየጊዜው ይለዋወጣሉ። ከለውጥ ጋር መራመድ መቻል ትልቅ ችሎታ ነው። ይህ ችሎታ ደግሞ ዝም ብሎ አይገኝም። በመርህ ላይ የተመሠረተ ዕይታን ማስተካከል፣ ልምምድና አዳዲስ ግን ደግሞ ጠንካራ ኔትወርክ ይፈልጋል።

ለዚህ የሚሆን ስልጠና አግኝተሃል? ወይንስ ትፈልጋለህ?

ይህንን ዘመን በአንድ መንገድ፣ በአንድ ሃሳብ እና በጥቂት ግንኙነት ብቻ አትቋቋመውም።

የቀድሞዎቹ እስከዛሬ የወሰድካቸው ስልጠናዎች ምን አገዙህ? ምንስ አጎደሉብህ? ምን ፈልገህ ምን አጣህ? የት አደረሱህ?

በቅርቡ በቢዝነስ ላይ ያተኮረ ልዩ ስልጠና በአዲስ አበባ ውስጥ ለመስጠት ምዝገባ እያደረግን ነው። ለምዝገባው ሙሉ ስምና የሞባይል ስልክ ቁጥራችሁን በውስጥ ላኩልን።

እስካሁን ብዙዎች ተመዝግበዋል። ምዝገባው ቀጥሏል።

የስልጠና ቦታው፣ የስልጠናው ርዕሶች፣ የአሰልጣኞች ዝርዝርና የስልጠና ዋጋው ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል።

Registration is on progress >>>>>
23 viewsጌቱ በቀለ, 05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 08:30:12 ላይክና ሼር ሰብስክራይብ እፈልጋለሁ። ለልበ ቅኖች ብቻ ነው መልዕክቱ።
22 viewsጌቱ በቀለ, 05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 08:30:12
23 viewsጌቱ በቀለ, 05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-30 02:10:11 Watch "ዓለምገናን በወፍ በረር። ወቅታዊ ጉዳዮችንም አንሰተናል።" on YouTube


321 viewsጌቱ በቀለ, 23:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-30 02:10:07 -አለምገና የቀድሞ መንደር
-ስለ ነገረ-ሲኖዶስ
-ማትሪክ ውጤት
-ስለ አለምገና ባለውለተኞች
-ስለ ጣሊያን ወቶአደሮች ቀብር ጉዳይ
-የቀድሞውን ቤተክርስቲያን መልሶ ግንባታ ወይስ?
-ስለ ሀውልታችን

እጅግ ብዙ ሀሣቦች ተነስተዋል።

ሰብስክራይብ ሼርና ላይክ ከናነተ ይጠበቃል።

ለለውጥ መጥቻለሁ።
መረጃን በማሥረጃ። ኦፍቲ ትዮብ።
38 viewsጌቱ በቀለ, 23:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 09:56:56 ይህ ለርስዎ ነው። ይገባዎታል።

በርግጥም የማይቆጭ ግዜን እንሰጣጣለን

ናፖሊዮን ድሎቹን ከመቀዳጀቱ በፊት መጀመሪያ አአምሮው ወስጥ ለአሸናፊነቱ እውቅና ሰጥቶ ያጨበጭብ ነበር። እያንዳንዱ ታላላቅ የፈጠራ ሥራ ተጨባጭ ቅርጽን ይዞ ገሀድ ከመውጣቱ በፊት በፈጣሪያቸው አአምሮ ውስጥ የሚኖር ነበር።
እናም በመልካም መጻሕፍት ሞግዚትነት የብዙ ታዋቂ ሰዎች አምሳሎች ዓለም ስለ እነርሱ ፈጽሞ ከመስማቱ በፊት በአእምሮአቸው ቅርጽን የያዙ ናቸው። እኛም እንዲሁ የዓለማችንን ታላላቅ እሳቤዎች የራሳችን መካር አሰልጣኞች ልናደርጋቸው እንችላለን። በእነርሱ እገዛ በመንገዳችን ላይ እንቅፋቶች ከሚመስሉ ከማንኛውም ነገሮችና ሁከቶች በላይ አልፈን ወደ ላይ መውጣት እንችላለን። ነገር ግን ፈጽሞ ከእነርሱ መሸሽ የለብንም። ጨከን ባለ ቁርጠኝነት ከተጋፈጥናቸው አብዛኞቹ በቀላሉና በፍጥነት ብትንትናቸው ይወጣል። "ሽሙጡን ከግምት ውስጥ አታስገባው÷ ሽንፈትንም አትቀበለው÷ የጥንቱ ልብ ሆይ ዳግም ተነስ! ለሁሉም ፍትህ ገናም ድል አይቀርምና።" ሲል ኤመርሰን ተናግሮአል።

በመጻሕፍት በኩል የሚጣሩትን እነዚህን ድምጾች "ለመሞት አሻፈረኝ ያሉትን የሙታን ሰዎች" ድምጾች ለመስማት የነፍሶቻችንን ጣቢያ ማስተካከል ይኖርብናል። ከእነርሱ ጋር መተዋወቅ ወዳጃዊ ጓደኝነትን መኮትኮት ልክ እንደ ገዛ ራሳችን የቤተሰብ አባላት ለእነርሱም ምላሽ ሰጪ መሆን ይገባናል።

ኦፍቲ ትዮብ
ተከተሉት ሰብስክራይብ ያድርጉ ላይክ ሼር አይርሱ።
ከትዩባችን የህይወት ምስጢራትን ይማራሉ። ግሩም ድንቅ የሚያስብሎትን የባህሪ ጥንካሬንና የአእምሮ ኃይልዎን ያጎለብታሉ። አዲስነት የሌላቸው ከፀሐይ በታች የሆኑ ከመጻሕፍት ገጾች ያገኘናቸውን ጉዳዮችን እናቀርብላችኋለን። ባጠቃላይ የማይነሱ ጉዳዮች አይኖሩም።

ይሄን ቪዲዬ ይመልከቱልኝ። እጅግ ድንቅ የእይታ ጥጎቼን ይተዋወቁበታል




240 viewsጌቱ በቀለ, 06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ