Get Mystery Box with random crypto!

ባለህ ጊዜ፣ ቦታ፣ ጉልበትና ገንዘብ ምን ትሠራበታለህ? ሰዎች 'ጊዜ አጥቼ ነው እንጂ!' ቢሉም ሁ | ኦፍቲ ቲዩብ-ልበ ጥሞና

ባለህ ጊዜ፣ ቦታ፣ ጉልበትና ገንዘብ ምን ትሠራበታለህ?

ሰዎች "ጊዜ አጥቼ ነው እንጂ!" ቢሉም ሁላችንም እኩል ጊዜ አለን። እኩል 24:00 ሰዓት በየቀኑ። የጊዜ አጠቃቀማችን ግን የየዕለቱን ውሎ በትርፍ ወይም በኪሳራ ይደመድማል።

ብዙ የበሰቃ ሰዎች 250 ካሬ ሜትር ቦታ አላቸው። እነዚህ ሰዎች ይህንን ቦታ ምን የሚያደርጉት፣ እንዴት የሚጠቀሙበት ይመስልሃል? በርካታው እንኳን ቤት ሊሠራበት ጎመንም አይተክልበት። ቦታው ይባክናል።

ቁጥሩ ቀላል የማይባል ወጣት ተራራ የሚንድ ጉልበት አለው። ወይ እንደ ምባፔ ሮጦ፣ ጠርምሶ፣ ትርምስ ፈጥሮ የሚያገባ የኳስ ጎል አግቢ ሆኖ ራሱንና ወገኑን አይጠቅምም። "ሥራ አጣሁ" ብሎ ቁጭ ብሎ ይውላል። ከባሰበት ደግሞ ሱስ ውስጥ ይዘፈቃል።

ገንዘብ ይዞ ቁጭ ያለ ብዙ ነው። ከባንክ፣ እኩል ገንዘብ ተበድሮ አንዱ መሥሪያ ማሽን ሲገዛ፣ ሌላው መዘነጫ መኪና ይገዛል። እውነት ነው እንደ አዋዋል መድረሻም ለየቅል ይሆናል።

እንግዲህ ልዩነት ፈጣሪው ምንድን ነው?

ችግራችን የጊዜ አይደለም፣ የጉልበትም አይደለም፣ የቦታ ማጣትም አይደለም፣ የገንዘብም አይደለም።

ችግራችን የእይታ፣ የሃሳብና የራዕይ ማጣት ነው። ችግራችን የመንገድ አለማወቅ ነው። ችግራችን የህይወት ሹፍርናን አለማወቅ ነው።

ለዚያ ሰልጥነህ መንጃ ፈቃድ ማውጣት ያስፈልግሃል? አሰልጣኞቹ እየመጡ ነው!

ዐይን ካልተከፈተ፣ አእምሮ ካልተለኮሰ፣ የውስጥህ ብርሃን ካልበራ እንኳን ሃሳብ አቧራም አይገባም። ድፍንን ማን ይመርጣል? በራሱ የማይተማመን እንጂ!

"የሰዎችን ዐይን እከፍት ዘንድ" ያለው ማን ነበር?

ሰው ከሰው የሚለየው አስቦ በሚከውነው ድርጊት ነውና የሃሳብ ችቦህን ለኩስና ወደ ድርጊት ተጓዝ! ታድያ ዝም ብለህ ውርውር አትበል፤ ዝም ብለህ ጫማና ጎማ አትጨርስ።

አስብና ሂድ! አትፍራ! ፍርሃትን የምታሸንፈው በድርጊት ነው - ታስቦ በሚከወን ጥንቁቅ ድርጊት።

ኢንጅነር ጌቱ