2022-06-21 07:22:33
ዛሬ መዳን ለሁላችሁም ሆነ።
ይሄን ሀቅ ለማታውቁ ሁሉ
ለሌሎችም ይደርስ ዘንድ አጋሩት
ሁሉም በስራ ድርሻ ክፍፍሉ ላይ 24 ሰዓት ንቁ ነው
እነማን
ነገደ አጋንንት
ውለው ይደሩለት እንጅ ሃይል ቀላቢዎቹ ክፉአን የሰው ልጆች ሁሉ ነን ነቅቶ ውሎ የማደራቸውና የ24 ሰዓት ቆይታ ፊልፕስነታቸው ምስጢር
የምቸከችከው ገብቷችኋል ወይ
#ለማስታወስ
አጋንንት እስከተባረሩበት የትምክህትና ትዕቢት ዋዜማቸው ዕለት ድረስ ሃይልን የሚሞሉት ከፈጣሪያቸው ነበር። ሲጣሉ..ከክብራቸው ሲጎድሉ ግን የሰው ልጆችን እና እንስሳት ደምን በመላስና በማፋሰስ የመሰንበቻ ሃይልን በመምጠጥ በዘለዓለማዊ ባላንጣነት ከአዳም ዘር ሁሉ ጋር ጥርስ ተናክሰው መኖርን ቀጠሉ።
ሃይልን የሚጎናጸፉት በልዩ ልዩ መልክ ነው። በንዴት በቁጣ በክፉ ሀሳብ እና ስራዎች እንዲሁም ቅንቀና በምቀኝነት....ወዘተ ድርጊያዎችን በኩል ሃይልን እያስወጡን በመመጥመጥ።
ሀይላችን ሲባክን ይረከቡንና ሌላ የክፋት/ማሳሳት ድርጊያቸው ታድሰው ይነሳሉ...ይዘምታሉም። መልካምነትን ስናበዛ በጾም በጸሎት ውስጥ ስንቆይ ሀይል ስለማንለቅላቸው 24 ሰዓት በትጋት ከሚከውኑት አሳስቶ ሀይል ጉንጸፋ ድርጊያቸው ተልፈስፍሰው ትቢያ ላይ ሲርመጠመጡ ይከርማሉ። ቢያንስ ጥለውን ወደ ሌላ ስፍራ ሀይል አባካኝ ህዝብ ሰፈር/ሀገር ይዘምታሉ።
አሁን ላይ እነ ሩሲያ ሰፈር በገፍ የደም ድግሱን እየበሉ ነው ኢትዮጵያችንም አንዳንድ ስፍራ ላይ የግድድላችን ድግስ ላይ ታድመው ከጥጋብ አልፈው ስካር ጥግ ደርሰው ደማችንን እየተራጩበት ነው።
ይህ እውነት ነው።
እያንዳንዳችን ጎን በሰባቱ ሻክራችን ከእግዚሃብሔር በየዕለቱ የምንሞላውን ሃይላችንን ለመጥለፍና
ሃይል ለመሞላት የቁጣው ክሹፈ መላክ ሳጥናኤል፤
የኩራትና ትዕቢት ጌታ ሉሲፈር
የንፉግነት ጌታ ማሞን
የሆዳምነትና እልጠግብ ባይነታችን አግበስባሽነት ጌታ ብሄልዜቡል
የጥሎ ማለፍና ምቀኝነት ጌታ ሌዋታን
እንዲሁም የስራ ጠልነትና ስንፍና ጌታ ቤልፋጎር
ለዝሙተኝነታችን ለስካራችን ለቁማራችን ለዘርፈ በዛው ሴሰኝነታችን በልበልን ሊመክሩን ጌታ እስማንድዮስ እና ጋሻ ጃግሬዎቻቸው ሊሰለቅጡን ከበውን አሉ
ካልነቃንና ካልተቃወምናቸው በእያንዳንዳችን ጎን የየነገዳኑ ተላላኪዎቻቸው ሰፍረው ሃይላችንን ለመቆያቸው ሊመጥጡ አስፍስፈው 24 ሰዓታት ያለመታከት ይዞሩናል። ለጥፋተ/ስህተተ- አይነታት ስንመቻችላቸው ሃይል ሰልበውብን ከልፍስፍስነታቸው ይበረቱበታል።
ሰይጣንና ሠራዊቱ ህልውናው ሁሉ በሰው ልጆች ማይምነትና ድንቁርና ላይ የተመሰረተ ነው።
ለማምለጥ
ከማማረር ማምረር።
በድንቁርና ላይ ማመጽ።
ማንበብ አለማወቃችንን እንዲገልጽልን መርጠን እናንብብ
ዘንድሮ ክረምትን ስንት መጽሃፍት ሊያንብቡ አቀዱ
መዳንም ፈውስም ከድህነት ማምለጥና ሰላማችንና ወፍቅራችን በመጽሓፍት ሆድቃ ውስጥ ተሸሽገውብናል።
ስናነብ ብቻ ከዘርፈ በዛው ደዌያችን እንድናለን።
ዘመኑን የሚዋጅ ትውልድ ከንባብ አምባ አሁን
32 viewsጌቱ በቀለ, 04:22