2022-10-07 07:36:07
ስለ ረሱሉ {ሰ.ዓ.ወ} ይህን አልን…
በአሁኑ ጊዜ በቢሊዮኖች በሚቆጠሩ፣ በሁሉም ዖታ፣ በሁሉም ዕድሜ ወዘተ ላይ በሚገኙ ሙስሊሞች ልብ ውስጥ የሚገኙ ደግሞም እልፍ በነፍስ የሚፈቀሩ፣
የዘር መድሎን፣ ኢ-ፍትሐዊነትን፣ የአመራርንና የአስተዳደር በደልን፣ ወዘተ የሚጠየፉ፣ ፍቅርን፣ማካፈልን፣ሰላምን፣ ሰውነትን፣መታዘዝን፣አብሮነትንና አቃፊነትን ማስተማር ብቻ ሳይሆን የዓለም ህዝብ በዚህ መንገድ እንዲመራ በፈጣሪ በጥበብ ያስተማሩ፣
አላህ {ሱ.ወ} ስማቸውን ከስሙ ጎን የአድርጎ ያከበራቸው በአለም ከነበሩትም ከሚመጡትም ሰዎች መካከል የመረጣቸው፣ መርጦም ልባቸውን በመላኢካው ጅብሪል {አ.ሰ} በንፅህት ያጠበላቸው፣አጥቦም በምድርም ሆነ በመጭው አለም የአሁኑን ያለፈውንና የወደፊቱን ዕውቀት በልባቸው የሞላላቸውና ያሳወቃቸው፣
ለእርሳቸው የተወረደላቸ ቁርዓን ያ የኔ መመሪያ የአለም ብርሃንና የዕውቀት ምንጭ መሆኑን የዓለም ሊቃውንት በመረዳታቸው በ114 ቋንቋዎች የተረጎመ፣ ሐዲሳቸው የዓለም ሁሉ የዕውቀት ምንጭ የሆነ፣
ሰው እርሳቸውን በማፍቀሩ ብቻ በአላህ {ሱ.ወ} ዘንድ የሚፈቀር፣መመሪያቸውን በመከተሉ ብቻ የዘልዓለም ህይወትን የሚያስገኝ፣
ፍቅራቸው እልፍ የሚናፈቅ ፣ፍቅሩህ ልክ እንደዝናብ ዘንቦ ዘንቦ ማይጠገብ የልብ ማይደረስ የማያልቅ፣ስለሱ በሰሙ ቁጥር ይበልጥ ናፍቆትና ፍቅሩ የሚያጓጓ እንደ አዲስ ፍቅሩ የሚያገረሽ የሚ'ያም ' ያያ '...ያ 'ነው የኔ ነብይ ሰ.ዐ.ወ
አንቱ የአላህ መልክተኛ ፊዳ ልሁንልዎት!
መልካም ልደት!
እናንተስ?
መሃመድ ስራጅ {ጋዜጠኛና የማህበረሰብ ጥናት ባለሙያ}
መስከረም 2015 ዓ.ም
ላይክ ሼር ኮሜንት
https://www.facebook.com/moonews.et
telegram
https://t.me/AWSHfm
17 viewsጌቱ በቀለ, 04:36