Get Mystery Box with random crypto!

በአሁኑ ሰዓት በአለምገና ሰማይ ስር በ1ሽህ ሜትር ዙሪያ ገብ በምትሰማው የኦፍታና የማህበረሰብ ሬዲ | ኦፍቲ ቲዩብ-ልበ ጥሞና



በአሁኑ ሰዓት በአለምገና ሰማይ ስር በ1ሽህ ሜትር ዙሪያ ገብ በምትሰማው የኦፍታና የማህበረሰብ ሬዲዮዬ በድምጽ እና በማህበራዊ ሚዲያው ማከናወን የምችለው ሁለት ነገር ብቻ ይመስለኛል።
የማህበረሰቤን ሕጸጽ መጠቆምና በኔ የተጠቆመው ተደግሞ እንዳይኖር መተጋትን!

የእኔ እውነት ይሄን ይነግረኛል!
በየትኛውም የኢትዮጵያ ጥጎች የምንጋደለውም ሆነ የምንገደለው
ተመችቶን።
ወደን።
ፈቅደን
እና አምነንበት ነው እላለሁ።

"ምክክር" የሚል ሀገራዊ አጀንዳን ይዘናል። ግና ይህን አዝጋሚውን መንገዳችን ጥሩ ነው አልልም።

በኔ በኩል የምታዘበው አንድ መንፈሳዊ ድብቅ ምስጢር አለን አምኜ ተቀብያለሁ። የኢትዮጵያውያንን ደም እያፈሰሰና እያፋሰሰ ለጌታ ሉሲፈርና ነገደ አጋንንቱ የሚያጠጣ ስውር የግድድል ደጋሽ መኖሩንና፤ ሀገር ላይ ሁሉም ነገር በግዜው እንዳይከናወን እንደመርግና አዚም ህዝቡና አስፈፃሚዎቹ ላይ ተጭኖ የሚያሳንፍና ለውጥን የሚያዘገይ ስውርሽአካል እንዳለ!

መላ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን" ህገ አራዊት" ወዶትና ፈቅዶት የተቀበለው ህገ መንግስቱ ነው እላለሁ። አለቀ መቼም እንዳይቀየር የሚሳሳለት ውድ እንቁው!

ባይሆን ኖሮማ

በአዲስ የብዙሃን ፍላጎት ህገ-መንግስቱ እንዲሻሻል ለመትጋት እቅልፍም ሊኖረን አይገባም ከማለት ይልቅ ህገ መንግስቱ ባለበት የህግ አናቅጽታት ክፍተት የተነሳ ከጎኑ ወገኖቹ ሲጎድሉና ሲገደሉ አይኑ እያየ የምን ቀጠሮ ማንዛዛት ነው።

የምንስ ስራ ገብቶ መስራት ነው። የምንስ ፓርላማ ስብሰባ ነው ህሊና ጸሎት..ብሄራዊ ሀዘን ወዘተ እያሉ "መደናቆር" ነው።

መሆን ካለበትም!
ሞት ሰልችቶናል።
በቃን መጋደሉ።
ስራ በየትኛው ጥግ አቁሙ። እናቁም። ምከሩ እንምከር። የህገመንግስት ማሻሻያ ድምጸ ውሳኔ ህዝብ ባስቸኳይ ይሰጥ።

ከዚያም ቀጥሎ ለሰላሙ ሁሉም አንድ አፍ ተናጋሪ አንድ ልብ መስካሪ ሆኖ ይቁም።
ነው መባል የነበረበት

እኛ ማለት "ቅድሚያ የሚሰጠው" የሚለው ቃለ ሀረግ በመዝገበ ቃላታችን ውስጥ እንጅ በድርጊታችን ውስጥ የማይታወቅ ህዝብና ሀገር ነን። በሌላ ቋንቋ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በደመነፍስ እንደ እንስሳ ተኗኗሪ ህዝብ ነን ብዙ ገመናችን ያስብለናል


መርጦ አልቃሽነትንምም..ያንዱ ህመም ለሌላው አለመሰማትና አለመቆርቆር መንፈስንም በእግዚሃብሔር ስም አውግዣለሁ።

ከማማረር ማምረር።
በድንቁርና ላይ እናምጽ።
ማንበብ አለማወቅን ይገልጻል።
አንባቢ ትውልድ ለሀገር ግንባታ-የ2014 ሙሉ ዓመት ሀገር አቀፉ የንባብ ቀን መሪ ቃል።