2023-04-03 05:52:40
እባቡ አብሪ ትልን ያሳድዳታል
አብሪ ትሏ ለእባቡ ጠላትም ስጋትም አይደለችም
ምስኪን አብሪ ትል የህይወቷ ግብ ፍክት ማለት ነው - እባቡ ግን ያሳድዳታል
"ሶስት ጥያቄ ልጠይቅህ?" አለችው አብሪ ትል
"እሺ ጠይቂኝ" እባቡ መለሰላት
"ምግብ ልሆንህ እችላለሁ?"
"አትችዪም! ከማልበላቸው ፍጥረታት ነሽ" መለሰ እባቡ
"ያደረግኩህ ነገር አለ?" ጠየቀች አብሪ ትሏ
“ኧረ በጭራሽ! ደግሞ አንቺ ምን ልታደርጊኝ"
"እኔን በማሳደድህ የምትጠቀመው ነገር አለ?"
"በጭራሽ! ደግሞ ካንቺ ጥቅም" እባቡ መለሰላት
"ታዲያ ለምን ትሳድደኛለህ?"
"ምክንያቱም ፍክት እና ብርት ስትዪ አልወድም! እሱን ማየት መቋቋም አልችልም" ሲል መለሰላት
.
.
.
ብዙ ጊዜ እንደዚህ ነው
አንዳንድ ሰዎች አሉ በቃ - ስኬትህ እና ከፍታህ ማየት የሚያማቸው
ጠላታቸው አይደለህም
ምንም የዋልክባቸው ክፋት የለም
በመክፋታቸው አይጠቀሙም
ግን በቃ ስኬትህን አይፈልጉም! ደስታህን አይፈልጉም!
መራር ሃቅ !!
.
Zemelak Endrias
18 viewsጌቱ በቀለ, 02:52