Get Mystery Box with random crypto!

የጅ/ዩ/ቴ/ኢ/ግ/ግቢ ጉባኤ [Y/M/M/Y/I/T/Jimmaa]

የቴሌግራም ቻናል አርማ jitgibigubae — የጅ/ዩ/ቴ/ኢ/ግ/ግቢ ጉባኤ [Y/M/M/Y/I/T/Jimmaa]
የቴሌግራም ቻናል አርማ jitgibigubae — የጅ/ዩ/ቴ/ኢ/ግ/ግቢ ጉባኤ [Y/M/M/Y/I/T/Jimmaa]
የሰርጥ አድራሻ: @jitgibigubae
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.04K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ በጅማ መካነአዕምሮ ሥነመላ ተቋም ግቢ ጉባኤ የግቢ ጉባኤውን አገልግሎት መረጃ የምንለዋወጥበትና መንፈሳዊ ትምህቶችን የምንማማርበት አውታር ነው::Yaa'ii mooraa Yuunivarsitii Inistitiyuutii Teeknooloojii Jimmaatti fuula odeeffannoo tajaajila yaa'ii mooraa fi barnoota afuuraa! @jitgibigubae

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 09:33:00 + ለእግዚአብሔር ስጦታ +
.............................................................
ለአምላክህ ስጦታ ለመስጠት አስበህ ታውቃለህ? ለፈጠረህ፣ ፈጥሮም ለሚመግብህ፣ ቅዱስ መንፈሱን አሳድሮብህ ልጁ እንድትባል ላደለህ ለአባትህ ምን እንደምትሰጠው ጨንቆህ ያውቃል? እንደ አቤል አምላክህን የሚያስደስት መሥዋዕት ለማቅረብ ዓይንህ አማትሮብህ ያውቃል? "ሁሉን ለፈጠረ፣ ሁሉም በእርሱ ለሆነ፣ ያለእርሱም ምንም ምን የሆነ ለሌለ" አምላክ ስጦታ መስጠት ምንኛ ያስጨንቃል? የሁሉም ነገር ባለቤት ለሆነው ጌታ የእርሱ ያልሆነውን አዲስ ነገር ምን ልትሰጠው ትችላለህ? ከእርሱ ሳይሰጥህ ለእርሱ የምትሰጠውስ ምን አዲስ ነገር አለህ?

በእርግጥ እግዚአብሔር እኛን በየምክንያቱ ለመማርና ዋጋ ለመስጠት ስለሚቸኩል እያንዳንዷን ስለእርሱ ብለን የምናደርገውን ነገር ሁሉ ይቆጥራታል። "ያደረግነውን ስራ ስለስሙም ያሳየነውን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዐመጸኛ ያልሆነው እግዚአብሔር" ለእርሱ የምንሰጠውን ገንዘብ፣ ጉልበት፣ ጊዜና ሌላው ቀርቶ ተግባር ላይ ሳይውል በሃሳብ ብቻ የቀረብንን መልካም መሻታችንን እንደ በጎ መዓዛ ያለው መሥዋዕት በደስታ ይቀበለዋል። ከእነዚህ ሁሉ ግን ይበልጥ የትኛው ስጦታ ያስደስተው ይሆን? ዕብራ 6፥10

አንድ ወላጅ ከልብ የሚደሰተው ልጁ እርሱ ያሰበለት እጅግ መልካም ደረጃ ላይ ሲደርስ ነው። ለምን ቢባል ለልጁ እጅግ ብዙ ዋጋ ስለከፈለለት ነው። እጅግ ብዙ ዋጋና መሥዋዕትነት የከፈልንበት ጉዳይ ፍጻሜውን ሲያገኝ ወይም ሲሳካ ከማየት በላይ የሚያስደስት ነገር የለም። እግዚአብሔርም ልክ እንደዚህ ነው። ለእርሱ ብዙ ወርቅ ገዝተህ ከምትሰጠው ይልቅ አንተ ንስሐ ገብተህ ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን ብትቀበልለት ከምንም በላይ ይደሰታል። ምክንያቱም እግዚአብሔር ለወርቅ ከመፍጠር ውጪ የከፈለለት ዋጋ የለም። ለአንተ ግን መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሕይወቱን ከፍሎልሃል። ንጹሐ ባሕርይ ሲሆን የአንተን ኃጢአት ተሸክሞ በሞቱ ደምስሶልሃል። ዋጋ ከፍሎ የሰጠህን የራሱን ስጋና ደም ኃጢአትህን ትተህ ስትበላለትና ስትጠጣለት ከምንም በላይ ታስደስተዋለህ። ስለዚህ ለእግዚአብሔር የምትሰጠው የመጨረሻ ስጦታ እርሱ የሰጠህን ስጦታ መቀበል ነው። እርሱም ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙን ነው።

ወዳጄ ሆይ ለእግዚአብሔር እንደ አየር የምትፈልገውን ነገር እንዲሰጥህ ስዕለት ስትሳል ለእርሱም የሚፈልግህን ራስህን ለመስጠት ተዘጋጅ። "ይህን ካደረግክልኝ ይህን ያህል ብር፣ ይህን ያህል ጥላ አስገባለሁ" ሳይሆን "ይህን ብታደርግልኝ ንስሐ ገብቼ እቆርባለሁ" ብለህ ተሳል። ዋጋ ከከፈለልህ ከራስህ በላይ ለእግዚአብሔር ስጦታ ልትሰጠው አትችልምና።
.........................................
ዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ
ነሐሴ 20/2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ከአንድ አስተዋይ እህቴ የተማርኩት
@dnJohannes


@jitgibigubae
118 viewsWegene Demeke, 06:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:50:45 ቅዱስ ፓትርያርኩ ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን አሜሪካን የነበራቸውን የሕክምና ክትትል በማጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ጤናቸውንም በተመለከተ የተወሰነ መሻሻል ማሳየቱ ታውቋል።

በመሆኑም ቀደም ሲል በተያዘው የጉዞ መርሐ ግብር መሠረትም ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@jitgibigubae
193 viewsንዑስ አነ እም አኃውየ, edited  18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:36:22
በኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በግብፅ በሚገኘው የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በዓለ እረፍቱ ከዋዜማው ጀምሮ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

ነሐሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም

+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ!!!


ምንጭ:-ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
@jitgibigubae
257 viewsንዑስ አነ እም አኃውየ, 08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:19:39
በዕውቀት እና በምግባር ታንጸን የወጣንበትን ቤት መልሰን ለማወቅ ፣ በምርቃት ዕለታችን ቤተክርስቲያን የሠጠችንን አደራ ለመጠበቅ በመስከረም 8 ቀን 2015 ዓ.ም የግቢ ጉባኤያት ምሩቃን ኅብረት ማስጀመሪያ መርሐግብር ይካሄዳል።

በዕለቱም ትምህርተ ወንጌል፣ የልምድ ልውውጥ፣ የፕሮጀክት ዳሰሳ እና መዝሙራት ይቀርባሉ።

ቃላችንን ጠብቀን ለቤተክርስቲያን ዘብ ለመሆን ኑ በኅብረት እንቁም።
ቀን፦መስከረም 8 ቀን 2015 ዓ.ም
ቦታ፦ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ
304 viewsWegene Demeke, 18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 07:27:23
በማኅበረ ቅዱሳን ልማት ተቋማት በግዕዝ፣ በአማርኛና በኦሮምኛ ... ቋንቋዎች አዳዲስና ነባር 120 መጻሕፍት በ1.2 ሚሊየን በላይ ቅጂ አሳትሞ ማሰራጨቱ ተገለጸ፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት በግዕዝ፣ በአማርኛና በኦሮምኛ ... ቋንቋዎች አዳዲስና ነባር መጻሕፍትን በማኅበሩ ማተሚያ ቤት እና በሌሎች ማተሚያ ቤቶች 120 መጻሕፍት በ1,202,465 ቅጂ ያላቸው ታትመው ተሠራጭተዋል፡፡
ተቋሙ በአቡነ ጎርጎርዮስ የዜማና የዜማ መሣሪያዎች ሥልጠና ማእከሉ በ6 ቅርንጫፎች ያስተማራቸውን 738 ሰልጣኞችን አስመርቋል።

እንዲሁም 1,844 የዜማ መሣሪያዎችን /በገናዎችን/ እና 34,084 የተለያዩ አልባሳትን አምርቶ ለገበያ አቅርቧል። 1,114,124 ጧፍ አምርቶ፣ እንዲሁም 31,249 ኪሎ ግራም ዘቢብ እና 38,901 ኪሎ ግራም እጣን ለተጠቃሚ ቀርቧል።
ሐመር መጽሔት 77,900 ቅጂ ታትሞ ተሠራጭቷል፡፡ ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ በየ15 ቀኑ ተዘጋጅቶ በድረገጽ እየተሠራጨ ይገኛል በማለት የማኅበሩ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ቢሆነኝ በሪፖርቱ ገልጸዋል።
@ ማኅበረ ቅዱሳን
. ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
@jitgibigubae
149 viewsንዑስ አነ እም አኃውየ, 04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 22:16:44
15ኛው የማኅበረ ቅዱሳን ጠቅላላ ጉባኤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት እየተከናወነ ይገኛል፡፡

በጉባኤውም ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒዎርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህር ዳርና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የምዕራብ ሐረርጌ እና አፋር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትና የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች፣ ጥሪ ተደረገላቸው እንግዶችና የማእከላት ተወካዮች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በጉባኤው “ሃይማኖት እና ፍፁም ተጋድሎ” በሚል ርዕስ ትምህርት ሰጥተዋል፡፡ በዚህም ማኅበሩ በሚሰራው ሁለንተናዊ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎትን የሚፈጽምና የሚከውን ስለሆነ ሃይማኖቱን በፍጹም ተጋድሎ በአንድነት ሊጠብቅ ይገባዋል ብለዋል፡፡ በጉባኤው ያለፉትን ሁለት ዓመታት ሪፖርት እንደቀረበ ሁሉ ለሚቀጥለው ዓመት ደግሞ የተሻለ ሥራ ለመሥራት የሚታቀድበት ጉባኤ እንደሚሆን አምናለሁ ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

“ንቁ በሃይማኖት ጸንታችሁ ኑሩ” በሚል ርዕስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ ትምህርት የሰጡ ሲሆን በሃይማኖት መቆም ማለት ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ እስከ ምናልፍ ድረስ እንጂ ጊዜያዊ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ፍቅር፣ ጥንካሬና ብርታት ያስፈልጋል ሰማያዊ ክብር የሚገኝበት ነውና በማለት አባታዊ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡
@jitgibigubae
199 viewsንዑስ አነ እም አኃውየ, 19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 21:12:10
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የክብር ዶክትሬት ሊሰጣቸው እንደሆነ ተገለጸ፡፡

ለብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና ለኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ ነሐሴ ፳፩ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም የክብር ዶክትሬት ሊሰጣቸው እንደኾነ የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በፌስቡክ ገጹ አስነብቧል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በትናንትናው ዕለት በገለፀው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በሃይማኖት አባትነታቸው የተማሩትንና ያስተማሩትን በተግባር ለሚኖሩት፤ ሰውን በሰውነቱ ብቻ ላከበሩት ታላቁ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስና ለኅብረተሰብ ፍቅርና አንድነት መጎልበት ለምትተጋው ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ የዓመቱን የክብር ዶክትሬት እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡

++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት
የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውን እንመሰክራለን!

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s....

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
https://t.me/+SjwkW1oiAsZDLLX0

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://www.tiktok.com/@mk_broadcast_service1?lang=en

@jitgibigubae
297 viewsንዑስ አነ እም አኃውየ, edited  18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 07:02:03
492 viewsWegene Demeke, 04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 07:02:03 ‹‹ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም ተሻገረች››(ቅዱስ ያሬድ)
ቅድስት ድንግል ማርያም በምድር ላይ ለ፷፬  ዓመት በሕይወተ ሥጋ ከኖረች በኋላ ቅዱስ ያሬድ እንደተናገረው በጥር ፳፩ ቀን ከሚያልፈው ዓለም ወደ ማያልፈው ዓለም ተሻግራለች፡፡ «ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ፤ ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም፣ (ከምድር ሕይወት ወደ ሰማያዊ ሕይወት) ተሻገረች» እንዲል፤  (ዚቅ ዘቅዱስ ያሬድ ነሐሴ ፲፮)  
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙስና መቃብርን ድል እንዳደረገ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም የልጇ መለኮታዊ ኃይል ሞትን አሸንፋ እንድትነሣ አደረጋት፡፡ ነቢዩ ዳዊት ስለ እመቤታችን ትንሣኤ እንዲህ ሲል ተናግሯል፤ ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት…›› የታቦት መቅደስ የተባለችውም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፤ እርሷ ከፍጡራን ሁሉ ከፍ ከፍ ያለችና ከተለዩ የተለየች፣ ከተመረጡ የተመረጠች፣ ንጽሕተ ንጹሓን፣ ቅድስተ ቅዱሳን በመሆኗ የአምላክ ማደሪያ ለመሆን በቅታለች፡፡  እርሷም ‹‹ነፍሴ እግዚአብሔርን ታከብረዋለች፤ መንፈሴም በአምላኬ፣ በመድኃኒቴ ሐሤትን ታደርጋለች›› በማለት ተናግራለች፡፡ (መዝ. ፻፴፩፥፰፣ሉቃ.፩፥፵፯)
ቅዱሳን ሐዋርያትም እመቤታችንን በአጎበር አድርገው ወደጌቴሴማኒ ይዘዋት በሚሄዱበት ጊዜ አይሁድ በምቀኝነት ተነሡባት፤ ሥጋዋን ለማቃጠልም ተማከሩ፤ በዚያን ጊዜም ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ከሐዋርያት እጅ ለመንጠቅ ዘሎ በመሄድ የአልጋውን ሸንኮር ሲይዝ የእግዚአብሔር መልአክ በረቂቅ ሰይፉ እጆቹን ቆረጠው፤ እጆቹም በአልጋው ሸንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ፡፡ አዛኝቷ ድንግል ማርያም ግን የምሕረት አማላጅ ናትና ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስን እጆቹን ይመልስለት ዘንድ በጸሎቱ እንዲማጸንለት ነግራው እንደነበረ መልሶለታል፡፡
ከዚህም በኋላ ቅዱሳን መላእክት ክቡር ሥጋዋን በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አኖራት፤ ከጥር ፳፩ እስከ ነሐሴ ዐሥራ ስድስት ቀን ለሁለት መቶ አምስት ቀናት ቆይታለች፡፡ ነገር ግን ሥጋዋ ያለበትን ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ቢመለከትም ሌሎቹ ሐዋርያት ባለማየታቸው እመቤታችን ድንግል ማርያም ባረፈች በ፮ኛው ወር ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ፲፬ ቀን ድረስ ከጾሙ በኋላ በ፲፬ኛው ቀን ሥጋዋን ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተቀብለው በጌቴሴማኒ በሚገኘው መቃብር ቀብረዋታል፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያምም እንደ ተወደደ ልጇ  በ፫ኛው ቀን ተነሥታ መላእክት አጅበው እየዘመሩላት ወደ ሰማያት ስታርግ ሐዋርያው ቶማስ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ ዕርገቷን በማየቱ መላእክት «እመቤትህ እርሷ ናት፤ ስገድላት» አሉት፤ እርሱም «ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ ይላል፤ ከደመናው ሊወድቅ ወደደ፤» ይህም ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ፣ ዛሬ ደግሞ የእርሷን ትንሣኤ ሳላይ ቀርቼ ነበር በማለት ነው፡፡ እመቤታችንም «ትንሣኤየን ያየህ አንተ ነህ፤ ሌሎቹ አላዩም» ብላ ሐዋርያት ገንዘው የቀበሩበትን የሐር ግምጃ ሰጠችው፡፡
ኢየሩሳሌም በደረስ ጊዜ ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያትን ስለ እመቤታችን ጠየቃቸው፤ እነርሱም  እንደቀበሯት ነገሩት፤ እርሱም ያየውን ምሥጢር በልቡ ይዞ «ሞት በጥር፤ በነሐሴ መቃብር፤ ለሰሚውም አያምር፤ ይህ እንዴት ይሆናል?» ቢላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ «ድሮም አንተ ተጠራጣሪ ነህ፤ ማን ያርዳ የቀበረ፤ ማን ይናገር የነበረ እንዲሉ፤ ገንዘን የቀበረን እኛ እያለን እንዴት ትጠራጠራለህ» ብለው ሊያሳዩት ወደ መቃብሯ ሄደው መቃብሯን ቢከፍቱት ባዶ ሆኖ አገኙት፡፡ በዚህ ጊዜ ሁሉም ተደናግጠው ተያዩ፤ ቅዱስ ቶማስ ግን እንዲህ አላቸው፤ «አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችንስ ተነሣች፤ ዐረገች፤ ይኸው ምልክቱ» ብሎ ገንዘው የቀበሩበትን ሰበን አሳያቸው፤ እነርሱም አምነው ሰበኗን ለበረከት ተካፈሉት፡፡
ከአንድ ዓመት በኋላም ሐዋርያት በመንፈሳዊ ቅናት ተነሣስተው «ቶማስ ትንሣኤዋን አይቶ እኛ ሳናይ እንዴት ይቀርብናል» በማለት ከነሐሴ ፩ ቀን ሱባኤ ጀምሩ፡፡
ጌታም የሐዋርያትን ጾማቸውን፣ ጸሎታቸውን ሱባኤያቸውን በ፲፮ኛው ቀን እመቤታችንን መንበር ጴጥሮስን ተራዳኢ፣ ካህን እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ አቅርቧቸዋል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ከነሐሴ ፩ እስከ ፲፭ ቀን  ጾመ ፍልሰታ ሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ዘንድ ተጹሞ ትንሣኤዋና እርገቷ ይከበራል።
የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን
እንኳን አደረሳችሁ!
ምንጭ፡- መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ነሐሴ፣ ፲፮ ቀን፣ ገጽ ፮፻፺፭‐፮፻፺፰    
441 viewsWegene Demeke, 04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ