Get Mystery Box with random crypto!

15ኛው የማኅበረ ቅዱሳን ጠቅላላ ጉባኤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ | የጅ/ዩ/ቴ/ኢ/ግ/ግቢ ጉባኤ [Y/M/M/Y/I/T/Jimmaa]

15ኛው የማኅበረ ቅዱሳን ጠቅላላ ጉባኤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት እየተከናወነ ይገኛል፡፡

በጉባኤውም ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒዎርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህር ዳርና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የምዕራብ ሐረርጌ እና አፋር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትና የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች፣ ጥሪ ተደረገላቸው እንግዶችና የማእከላት ተወካዮች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በጉባኤው “ሃይማኖት እና ፍፁም ተጋድሎ” በሚል ርዕስ ትምህርት ሰጥተዋል፡፡ በዚህም ማኅበሩ በሚሰራው ሁለንተናዊ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎትን የሚፈጽምና የሚከውን ስለሆነ ሃይማኖቱን በፍጹም ተጋድሎ በአንድነት ሊጠብቅ ይገባዋል ብለዋል፡፡ በጉባኤው ያለፉትን ሁለት ዓመታት ሪፖርት እንደቀረበ ሁሉ ለሚቀጥለው ዓመት ደግሞ የተሻለ ሥራ ለመሥራት የሚታቀድበት ጉባኤ እንደሚሆን አምናለሁ ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

“ንቁ በሃይማኖት ጸንታችሁ ኑሩ” በሚል ርዕስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ ትምህርት የሰጡ ሲሆን በሃይማኖት መቆም ማለት ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ እስከ ምናልፍ ድረስ እንጂ ጊዜያዊ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ፍቅር፣ ጥንካሬና ብርታት ያስፈልጋል ሰማያዊ ክብር የሚገኝበት ነውና በማለት አባታዊ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡
@jitgibigubae