Get Mystery Box with random crypto!

በማኅበረ ቅዱሳን ልማት ተቋማት በግዕዝ፣ በአማርኛና በኦሮምኛ ... ቋንቋዎች አዳዲስና ነባር 120 | የጅ/ዩ/ቴ/ኢ/ግ/ግቢ ጉባኤ [Y/M/M/Y/I/T/Jimmaa]

በማኅበረ ቅዱሳን ልማት ተቋማት በግዕዝ፣ በአማርኛና በኦሮምኛ ... ቋንቋዎች አዳዲስና ነባር 120 መጻሕፍት በ1.2 ሚሊየን በላይ ቅጂ አሳትሞ ማሰራጨቱ ተገለጸ፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት በግዕዝ፣ በአማርኛና በኦሮምኛ ... ቋንቋዎች አዳዲስና ነባር መጻሕፍትን በማኅበሩ ማተሚያ ቤት እና በሌሎች ማተሚያ ቤቶች 120 መጻሕፍት በ1,202,465 ቅጂ ያላቸው ታትመው ተሠራጭተዋል፡፡
ተቋሙ በአቡነ ጎርጎርዮስ የዜማና የዜማ መሣሪያዎች ሥልጠና ማእከሉ በ6 ቅርንጫፎች ያስተማራቸውን 738 ሰልጣኞችን አስመርቋል።

እንዲሁም 1,844 የዜማ መሣሪያዎችን /በገናዎችን/ እና 34,084 የተለያዩ አልባሳትን አምርቶ ለገበያ አቅርቧል። 1,114,124 ጧፍ አምርቶ፣ እንዲሁም 31,249 ኪሎ ግራም ዘቢብ እና 38,901 ኪሎ ግራም እጣን ለተጠቃሚ ቀርቧል።
ሐመር መጽሔት 77,900 ቅጂ ታትሞ ተሠራጭቷል፡፡ ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ በየ15 ቀኑ ተዘጋጅቶ በድረገጽ እየተሠራጨ ይገኛል በማለት የማኅበሩ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ቢሆነኝ በሪፖርቱ ገልጸዋል።
@ ማኅበረ ቅዱሳን
. ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
@jitgibigubae