Get Mystery Box with random crypto!

Information Science and Technology

የቴሌግራም ቻናል አርማ information_science_technology — Information Science and Technology I
የቴሌግራም ቻናል አርማ information_science_technology — Information Science and Technology
የሰርጥ አድራሻ: @information_science_technology
ምድቦች: ቴክኖሎጂዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.16K
የሰርጥ መግለጫ

Information science is a field primarily concerned with the analysis, collection, classification, manipulation, storage, retrieval, movement, dissemination, and transfer of information.

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-05-13 23:09:35 ቡዙግዜ በብዙ ሰው የተጠየቀ ጥያቄ ነው
የጠፋብንን የፌስቡክ፣ የኢሜል ፣የቲክቶክ ፣የዩቱብ ፣የቴሌግራም እና ሌሎች ፓስዋርድ እንዴት ማግኘት እንችላለን?
▬▬ Share ▬▬



የጠፋብንን የፌስቡክ፣ የኢሜል ፣የቲክቶክ ፣የዩቱብ ፣የቴሌግራም እና ሌሎች ፓስዋርድ እንዴት ማግኘት እንችላለን?
388 views20:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 08:56:47
ለተሻለ ዕውቀት፣ችግር ፈቺ፣ ወጪ ቆጣቢ እና የተለያዩ መረጃዎችን ከዚህ በፊት ዩትብ ላይ ከለቀቅናቸው ቪድዪዎች ብዙ ነገር ማግኘት ትችላላችሁ።
▬▬ Share ▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም ዩቲዩብ ቻናላችንን በመቀላቀል በምስል እና በቭድዮ የተዘጋጁ ከስራ እና ከቴክኖሎጂ ጋር ይተዋወቁ Subscribe በማድርግ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
368 views05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 17:17:43 ኮምፒውተር ወይም ላፕቶፕ ከሞባይል ወይም ከታብሌት ጋር በማገናኘት መቆጣጠር ወይም እንተርኔት መጠቀም ፣ ኮምፒውተርዎ መዝጋት መልዕክት መለዋወጥ እንደሚችሉ ያቃሉ? በጣም ቀላል እና በጎጉል አማካኝነት በተሰራው ጎጉል ክሮም ዴስክቶፕ ኮንትሮል በሚባል ሶፍትዌር በመጠቀም አሁኑኑ በማጋናኘት ከፈለጉት ኮምፒውተር ጋር በማስተሳሰር ግዜዎ ይቆጥባል የኮምፒውተርዎ ድህንነት ይጠብቃል። ይህንን ቪድዮ በማየት በቀላሉ ይጠቀሙበት።


1.7K viewsedited  14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 16:31:23 5G ቴክኖሎጂ እንዴት ይሰራል? *******
የ 5G ቴክኖሎጂ የ አምስተኛው ትውልድ የሞባይል ቴክኖሎጂ ሲሆን የዲጂታል ዓለሙ የሚፈልገውን ፈጣን ግንኙነት ለመፍጠር ትልቅ እርምጃ ያራመደ ቴክኖሎጂ ተደርጎም ይወሰዳል። የ 5G ቴክኖሎጂ የመረጃ መለዋወጫ ፍጥነትን አሁን ካለው የ4G ቴክኖሎጂ ከ10 እስከ 100 የተሻለ እጥፍ እንደሚልቅ ይገምታል። ይህም ማለት የሞባይል ኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን እስከዛሬ ከነበረው የm/s ፍጥነት ወደ g/s ያሳድገዋል ማለት ነው።
ኒዮርክ በሚገኘው የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ሃሪሽ ክሪሺናስዋሚ እንዳሉት “ የ 5G ቴክኖሎጂ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም አሁን ባለው የኔትዎርክ ፍጥነት መተግበር ያልቻልናቸውን ከፊተኛ የሆነ የኔትዎርክ አቅምን የሚጠይቁ መተግበሪያዎችን እንድንጠቀም ያስችለናል ለምሳሌ በ ጊጋ ባይት ደረጃ ያሉ ተንቀሳቃሽ መስሎችን በሰከንድ ከኢንተርኔት ማውረድ ያስችለናል እንድሁም እንደ ቨርችዋል ሪያሊቲ መተግበሪያና ሰው አልባ መኪኖችን ላይ ለፈጣን የመረጃ ዝውውር መጠቀም ያስችለናል”። በተጨማሪም ዘመኑ እየፈጠራቸው ያሉ ቴክኖሎጂዎች ማለትም እንደ አጉመንትድ ሪያሊቲ እና ሰው አልባ መኪኖች ከፍተኛ የሆነ የመረጃ ልውውጥ ፍጥነትን ይሻሉ ስለሆነም የ5G ቴክኖሎጂ የመረጃ የመዘግየት ሂደንት ወደ 1 ሚሊ ሴኮንድ ዝቅ ማድረን አላማ አድርጎ ተነስቷል ይህ ማለት ተንቀሳቃች መሳሪያዎች መረጃን የ1 ሴኮንድ 1/1000 ባነሰ መለዋወጥ ያስችላቸዋል።
ባለፉት ትውልዶች ቴክኖሎጂዎች የሚጠቀሙት የኤሌክትሮማግኔቲክ ጨረርን እንደ ሬድዮ ሞገድ ባሉ ቴክኖሎጂዎች በመሆኑ የእነዚህ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ በከፍተኛ ሁኔታ የኔትዎርክ መጨናነቅን ይፈጠርበታል፡፡ ስለሆነም ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከፍተኛ የሆነ የራድዮ ሞገድ ከመጠየቁም በላይ በ ሴንቲሜትር የሚለካውን ወደ ሚሊሜትር ሞገድ ዝቅ ማድረግ አስፈልጓል። እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ቀድመን ከምናውቀው ትልልቅ የሆኑ የኔትዎርክ ምሰሶዎች በላይ በማይፈልጉ የህንጻዎች አናት እና በመብራት አስተላላፊ ምሰሶዎች ላይ ሊገጠሙ የሚችሉ በመሆኑ ቴክኖሎጂዎቹ አዲስ የግንኙነት መንገድ የክፈቱ አስብሏቸዋል። ነገር ግን እነዚህ የሞገድ አይነቶች ሌሎች ተግዳሮቶች አጋጥሟቸዋል ከነዚህም መካከል ሞገዶቹ በዛፎችና በህንጻዎች ከመዋጥ አልዳኑም። ነገር ግን እነዚህ በመጠናቸው አንስተኛ የሆኑ የኔትዎክ አስተላላፊዎች ለአዳዲስ የምርምር ስራዎች መፈጠር ጉልህ አስተዋጾ ነበራቸው። የ አምስተኛው ትውልድ ኔትዎርክ የመፈጠር ምክንያትም ናቸው። የአምስተኛው ትውልድ ኔትዎርክ (5G) ቀድሞ በነበሩት የኔትዎርክ አስተላላፊዎች ላይ ቁጥራቸው በርከት ያሉ በመጠን አነስተኛ የሆኑ አንቴናዎችን በመጨመር እንዲሁም የማስተላለፍ አቅማቸውን በማሳደግ ከፍተኛ የሆነ የመረጃ መላላኪያ ፍጥነትን በመጨመር የተፈጠረ ሲሆን የመረጃ መዘግየትን በእጅጉ ቀንሷል። እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ከዚህ በተጨማሪም በፊት ከነበሩት የኔትዎርክ አስተላላፊዎች ያነሰ የኤሌክትሪክ ሃይል መጠቀማቸውም ልዩ ያደርጋቸዋል።
▬▬ Share ▬▬▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
▬▬ Share ▬▬▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe በማድርጉ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
1.8K views13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 16:31:19
1.4K views13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 16:30:05 + ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባችው እንስሳ +
የኖኅ መርከብ ጉዳይ በጣም አስገራሚ ከሚሆኑብኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች አንዱ ነው:: በዓለማችን አሁን ያሉ እንስሳት ሁሉ "ከነ ባለቤትዎ" እንዲገኙልን እንደሚባልበት ሰርግ ጥንድ ጥንድ ሆነው የገቡባት ትልቅ መርከብ ታሪክ : ዳግም ለሰው ልጆች ወላጆች ለመሆን የተመረጡ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ብቻ የተሳፈሩባት ትልቅ መርከብ ሁኔታ ትኩር ብሎ ላየው አስገራሚ እውነቶችን ያዘለ ነው::
ከሁሉም በላይ ግን መርከቢቱ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ መሆንዋ ብዙ ነገር እንድናስብ ያግዘናል:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ወደ ኖኅ መርከብ ተኩላ ገብቶ ሲወጣም ተኩላ ሆኖ ይወጣል:: ወደ ቤተክርስቲያን ግን ተኩላ ሆነው ገብተው በግ ሆነው የወጡ ብዙዎች ናቸው" ብሎአል::
እውነትም ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን መለወጥ የምትችል መርከብ ናት:: ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጅብ ሆዳም ሆነው ገብተው ጾመኞች ሆነው የወጡ አሉ:: እንደ የሌሊት ወፍ በቀን መኖር አቅቶአቸው ሌሊቱን የልባቸው ዓይን ታውሮ በኃጢአት ጨለማ ሲደናበሩ የኖሩ ሰዎች ወደ መርከቢቱ ገብተው እንደ ንስር አርቀው አጥርተው ቀኑን የሚያዩ ሆነዋል:: ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን የምትለውጥ መርከብ ናት:: ውኃ ወደ እርስዋ ሲገባ ጠበል ይሆናል:: አፈር ወደ እርስዋ ሲገባ እምነት (እመት) ይሆናል:: ዘይት ወደ እርስዋ ሲገባ ቅዱስ ቅባት ይሆናል:: ኅብስትና ወይን ወደ እርስዋ ሲገባ ወደ ቅዱስ ቁርባን ይለወጣል::
ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ያልተለወጠ ሰው ግን ሲገባም ጅብ ሲወጣም ጅብ ሆኖአል:: ኖኅ ከመርከብ መልእክት ልኮት የቀረው የቁራ ነገርስ? ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ስንቶች በዚያው ቀርተዋል? ለዓለም ጨው እንዲሆኑ ተልከው በዚያው ሟሙተው የቀሩ ስንት አሉ:: ርግብ ግን ማረፊያ ስታጣ ተመልሳ ነበር:: ከመርከቢቱ የራቅን ሁላችን "ልባችን በእግዚአብሔር እስካላረፈ ድረስ ዕረፍት የለውም" እንዳለ ሊቁ ወደ መርከቢቱ ፈጥነን መመለስ አለብን::
ሰሞኑን ደግሞ አንድ ጥያቄ በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ:: "ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባው እንስሳ ማን ሊሆን ይችላል?" የሚል:: ይህን ጥያቄ በግልም በጉባኤ ላይም ሰዎችን ጠይቄ ነበር:: መቼም ለዚህ ጥቅስ አያስፈልገውም:: ኖኅ ቆሞ እንስሳቱ እስኪገቡ ድረስ እንደጠበቀና ማንንም እንስሳ ጥሎ እንዳልገባ የታወቀ ነው::
በዚህ ምክንያት እንስሳቱ ወደ መርከቢቱ የሚገቡት እንደደረሱበት ቅደም ተከተል ነው:: ክንፍ ያላቸው በርረው ቀድመው ይገባሉ:: እንደ ጥንቸል እንደ ካንጋሮ እንደ ሚዳቁዋ ያሉትም እየዘለሉ ፈጥነው ይገባሉ::
ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነፍሳቸውን ለማዳን ፈጥነው በርረው የገቡ እንደ ሚዳቋ ዘልለው የደረሱ ብርቱዎች አሉ:: እንደ ፒኮክ ያሉ ባለ ውብ ክንፎች : እንደ ቀጭኔ ያሉ ባለ ረዥም አንገቶች እንደ ጃርት ያሉ ሌላው ላይ የሚሰኩት እሾኽ የለበሱ እንስሳት ወደ መርከብዋ ገብተዋል:: በቤተክርስቲያን እንደ ፒኮክ አምሮ መታየት መዘባነን የሚወዱ ለታይታ የሚገዙ ብዙዎች ገብተዋል:: እንደ ቀጭኔ አንገታቸውን ከፍ አድርገው ሰውን ቁልቁል የሚመለከቱና "አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የዕብራውያን ሴቶች" ዓይነት ሕይወት ያላቸውም ገብተዋል:: እንደ ጃርት በክፉ ንግግር የሰው ልብ ላይ የሚሰኩት ጥላቻ የተላበሱ ሰዎችም ገብተዋል:: የኖኅ መርከብ ያልያዘችው እንስሳ እንደሌለ ቤተ ክርስቲያንም ያልተሸከመችው ዓይነት ሰው የለም::
ወደ ጥያቄው ስመለስ በእኔ ግምት ወደ መርከቡ በጣም ዘግይታ የገባችው ኤሊ ነበረች:: በላይዋ ድንጋይ የተጫናት እጅግ ቀርፋፋዋ ኤሊን የማይቀድም እንስሳ መቼም አይኖርም:: ምንም ብትዘገይም ኖኅ እስከመጨረሻው ጠብቆ አስገብቶ ለዘር አትርፎአታል:: የኤሊ ዘሮችም "ኖኅ ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ዳይኖሰር በጠፋን ነበር" ብለው ኖኅን ማመስገናቸው አይቀርም:: እግዚአብሔር ምንም ብትዘገይ ኤሊ ሳትገባ መርከቡን አልዘጋውም::
የኤሊ በመርከቡ መትረፍ በቤተ ክርስቲያን ልንተርፍ ተስፋ ለምናደርግ ለእኛ ትልቅ መጽናኛችን ነው::
ወዳጄ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት እንደ ወፍ ትበርራለህ? እንደ ሚዳቋ ትዘልላለህ? ወይንስ እንደ ኤሊ ትጎተታለህ? እግሮችህ ለመንፈሳዊ ነገር ሲሆን አቅም እያጡ አልተቸገርህም?
ልብህ ቢፈልግም እንደ ኤሊዋ የተጫነህ የኃጢአት ድንጋይ አላንቀሳቅስ ብሎህ አልዘገየህም?
እንዲህ ከሆነ አትጨነቅ መርከብዋ ቤተ ክርስቲያን አንተን ሳትይዝ ጥላህ ወዴትም አትሔድም:: ጉዞህን እስካላቆምህ ድረስ ትጠብቅሃለች:: እየተጎተትህም እየተሳብህም ቢሆን አንተ ብቻ ወደ ደጁ ገስግስ::
አንተ ብቻ መንገድ ጀምር እንጂ ፈጣሪ በሩን የሚዘጋው አንተ እስክትገባ ጠብቆ ነው::
ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር እንዲህ ብለህ ለምነው :-
"ብበድልህም እንኳን አሁንም በርህን እያንኳኳሁ ነው:: እየተጎተትሁም ቢሆን አሁንም የምጉዋዘው ወደ አንተ ለመምጣት ነው"
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 5 2013 ዓ ም
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
1.6K views13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 16:28:04

1.7K views13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 19:20:17

4.5K views16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 10:08:55 ስልኬ ስታክ እያረገ አስቸገረኝ መፍትሄዉ ምንድነዉ?
-------------------------------------------------
ስልክዎ ስታክ እያደረገ ካስቸገሮት መነሻ ምክንያቱንና መፍትሄዉን እንደሚከተለዉ አቅርበናል፡፡
--------------------------------------------------------------------------------

ስልኮ ከተለመደዉ በላይ ይዘገያል ወይስ እንዲያ ከናካቴዉ አልሰራም ብሎ ቀጥ ብሎ ይቆማል፡፡ እንግዲህ ስልኮ በጣሙን የሚዘገይ አልያም አልታዘዝ ካሎት ስልኮ የሆነ ችግር ገጥሞታል ማለት ሲሆን ለዚህ አይነት ችግር መንስዔ የሚሆኑ መነሾዎችን ከነመፍትሄዎቻቸዉ ጋር እንደሚከተሉት አቅርበንሎታልና ይተግብሯቸዉ፡፡
 ከስልኮ ላይ የአላስፈላጊ አፕሊኬሽኖች መኖር
ከስልኮ ላይ አላስፈላጊ አፕሊኬሽኖችን ያጥፉ፡፡ ስልኮ ላይ ብዙ አላስፈላጊ አፕሊኬሽኖች ለምሳሌ ጌሞች ፣ የፎቶ እና ቪዲዮ ማሳመሪያ(ኤዲትኢንግ) ሶፍትዌሮች የተለያዩ የሙዚቃም ይሁን የቪዲዮ ማጫወቻ(ፕሌየሮች) ስልኮ ላይ ካለ በተቻለ መጠን የሚፈልጉትን አፕሊኬሽን ሶፍሮች ብቻ ትተዉ ሌላዉን በአብዛኛዉ የማይጠቀሙባቸዉን አፕሊኬሽኖች ያጥፉ፡፡

 የስልኮ ዳታ መያዣ(ስቶሬጅ) በፋይሎች መጨናነቅ
በስልኮ ሜሞሪ ላይ ብዛት ያላቸዉ ሙዚቃዎች፣ ቪዲዮች፣ያልጫኑት ሶፍትዌር አፕሊኬሽኖች አስቀምጠዉ ከሆነ በተቻለ መጠን የማይፈልጉትን ቢያጠፉ አልያም ከቆይታ በኋላ ብፈልጋቸዉ አላገኛቸዉም ካሉ በሌላ ተንቀሳቃሽ የመረጃ ቐት(ሜሞሪ) ያስቀምጡት፡፡

 የስልኮን ኦፕሬቲንግ ሲስተም እና ስልክዎ ላይ ያለን ሶፍትዌር አለማደስ
ስልኮ ያሉትን ሶፍተዌሮች እና ስልኮን ያለማደስ ስልኮን ለሌላ ቫይረስ አልያም ጎጂ ሶፍትዌር ያጋልጣል ይህም የስልኮን ፐሮግራሞች ሳይዘጉ ከኋላ እንዲነሳ(background play) ስለሚያደርገዉ ስልኮንና የሚጠቀሙበትን ሶፍትዌር ያደሱት፡፡

 ካች (Cache) ዳታን አለማፅዳት
ካች ዳታ የምንላዉ አብዛኛዉን ጊዜ የምንጠቀምባቸዉን ሶፍትዌሮችና ፋይሎች ስልካችን የሚያስቀምጥበት ቦታ ሲሆን ስልካችንን መረጃን በማመላለስ (loading data) ጊዜን እና ቦታ ተጣቦ ከመዘግየትና ከመቆም ያደናል ስለዚህ የስላካችንን ከች ማፀዳት ተቃሚ ያደርገናል፡፡

 Widgets መጠቀምን ማብዛት
አንድሮይድ ስልኮች ከሚሰጡን የተለየ ጥቅም አንዱ ዊጄትስ ቢሆንም ያን ያህልም የሚሰሩትን ካልገደብን ስልካችንን በማጨናነቅና እንዲቆም (ስታክ) እንዲያደርግ በማድረግ ረገድም ከፍ ያለ ድርሻ ያላቸዉ በመሆናቸዉ ዊጄትስን በመቀነስ ካልሆነም በማጥፋት ስልኮ በየጊዜዉ መቆሙን አላያም መንቀራፈፉን ማስቆም አማራጭ ነዉ፡፡

 ፋብሪካዉ ሲያመርተዉ ወደነበረበት ማሰተካከያ መመለስ(reset factory setting)
የስልኮ ማርጀት አልያም ለብዙ ጊዜያት መጠቀም ስልኮን እንዲቀራፈፍ አልያም በየማሃሉ እንዲቆም ለመሆኑ ምክንያት ላይሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ የማስተካከያ(ሴቲንግ) ለዉጦች ወይም አቅጣጫ መጠቆምያ ጂፒስ ኦን ማድረግ(ማብራት) ለስልኮ መንቀራፈፍ ምክንያት ሊሆኑ ስለሚችሉ የስልኮ በመሃል በመሃል መቆም(ስታክ) ሲያጋጥሙ ስልኩ ሲዘጋጅ ወደነበረበት መመለስ (reset factory setting) ችግሩን ሊቀርፍ ይችላል፡፡

 ዎልፔፐር (Wallpaper) መጠቀም
ስልኮ ለዓይን እንዲስብ አልያም በአንድ አንድ አቋራጭ ቴክኒኮች ምክንያት ስልኮ ላይ ላይቭ ዎልፔፐር (Live Wallpaper) መጠቀም አንዱ የአንድሮይድ ስልኮች ገፀ-በረከት ቢሆንም ለስልኮ መዘግየትም ይሁን መቆም(ስታክ ማድረግ) ምክንያት ሊሆን ስለሚችል ማጥፋቱ መንቀራፈፉን አልያም ሰታክ ማድረጉን ሊያስቆም ይችላልና ይሞክሩት፡፡

 ስልኮ አቧራ ከሞላዉ
የሚሰሩበት ቦታ አልያም የሚዉልበት አከባቢ አቧራማ ከሆነ ስልኮን ማፅዳትና ከተፀዳም በኋላ መልሶ በአቧራ እንዳይሞላ መከላከያ መጠቀም፡፡

ከተጠቀሱት አማራጮች ዉስጥ አንዱን ብቻ መርጦ በመተግበር ሳይሆን ሁሉንም አልያም አብዛዛኛዉን መፍቴዎች በአንድ ላይ በመተግበር ዉጤት ስለሚያስገኝ ከመፍቴዎች ዉስጥ በመምረጥ ሳይሆን ከቻሉ ሁሉንም መፍትሄዎች ስልኮ ላይ መተግበር ካልሆነም የተቻሉትን መከወን እንደመፍተሄ ይሆናል፡፡


ሌሎች መሰል ጥያቄዎች ካሎት በፌስቡክ ፔጃችን ኮመንት ያርጉልን አልያም ኢንቦክስ ያርጉልን፡፡ እርስዎን በመርዳትዎ ደስታ ይሰማናል፡፡

ይህን ፖስት ከወደዱት Like & Share


4.5K views07:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 08:58:37 ስልክ ሲደውሉ ቁጥሩን እንዴት እንዳይታይ ማድረግ ወይም መደበቅ እንችላለን? ለሚያውቁት እና ለማያውቁት ሰው ስልክ መደወል አለብዎት? ችግር የለም ፣ በተቀባዩ ስልክ ላይ ቁጥር እንዳይታይ እና ስልክ ደውለው እንዳጠናቀቁ በስውር እንዴት ይደውላሉ ፡፡ እንዴት ነው የማደርገው ብለውስ? ቀድሞውኑ ስለራስዎ አስበው ያውቃሉን? ነገር ግን በስልክ ውስጥ ብዙ ልምድ ስለሌሉ ፣ እንዴት መቀጠል እንዳለብዎ አታውቁም? ገብቶኛል. ስለዚህ ይህንን እናድርግ ፣ ጥቂት ጊዜዎችን ነፃ ጊዜ ለራስዎ ወስደው ይህንን ቪድዮ በማየት ፣ የግል ቁጥር እንዴት እንደሚደረግ ቀላል ነው።


3.2K viewsedited  05:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ