Get Mystery Box with random crypto!

Information Science and Technology

የቴሌግራም ቻናል አርማ information_science_technology — Information Science and Technology I
የቴሌግራም ቻናል አርማ information_science_technology — Information Science and Technology
የሰርጥ አድራሻ: @information_science_technology
ምድቦች: ቴክኖሎጂዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.16K
የሰርጥ መግለጫ

Information science is a field primarily concerned with the analysis, collection, classification, manipulation, storage, retrieval, movement, dissemination, and transfer of information.

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-05-31 22:57:48 Watch: ከሞባይላችን ወደ ኮምፒውተራችን xender በመጠቀም እንዴት ፋይል ማስተላለፍ እንችላለን?
ኢንተርኔት ኮኔክሽን ሳያስፈልግ በቀላሉ የፈለግነው ፋይል ከሞባይላችን ወደ ኮምፒውተራችንን በኤክሰንደር ማስተላለፍ የሚንችልበት ዘዴ ነው። ቪድዮውን በማየት ያከናውኑ።


556 views19:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 17:07:36 Watch "ምርጥ 5 የኮምፒተር አፖሊኬሽ ማውረጃ ዌብሳይት_ Top 5 app downloader website for pc" on YouTube


1.5K views14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 12:39:53 #ፍላሽ_ዲስክ_እንዴት_በፓስዎርድ_ማሰር_ይቻላል?
በፍላሽ ዲስክ የተለያዪ ሚስጥራዊ ዳታዎች እንይዛለን! ከራሳችሁ ውጪ ሌላ ማንም ሰው እንዳያየው የምትፈልጉት ዳታ(ፋይል፣ቪድዮ፣ፎቶዎች ወዘተ) በፍላሽ ዲስክ ትይዛላችሁ።
ስለዚህ ሚስጥራዊ ዳታችሁን ከናንተ ውጪ ማንም ሰው እንዳያየው ወይም እንዳይጠቀምበት የግድ ፍላሽ ዲስኩን በፓስወርድ መቆለፍ ይኖርባችኋል።
እሺ windows 10 የምትጠቀሙ ሰዎች ፍላሽ ዲስካችሁን በፖስወርድ ለመቆለፍ የሚከተሉትን ስቴፖች በመከተል መቆለፍ ትችላላችሁ።
1-ፍላሽ ዲስኩን ኮምፒውተራችሁ ላይ ሰኩት እና"This PC" የሚለው አይከን ደብል ክሊክ አድርጉት
2- "This PC" የሚለው አይከን ደብል ክሊክ ስታደርጉት የሚመጣው ቦክስ ውስጥ ፍላሽ ዲስካችሁ ይመጣል
3- ፍላሽ ዲስኩን "right click" አድርጉ
4- ፍላሽ ዲስኩን "right click" አ.ስታደርጉ "Turn BitLocker on" የሚለውን ሴሌክት ማድረግ
5- ከዚያ ፓስወርድ አስገቡ ይላችኋል፣ የማትረሱት ፓስወርድ አስገቡና "next" በሉት
6- ከዚያ "Encrypt entire drive" የሚለውን ሴሌክት በማድረግ "next" ማለት። በቃ አለቀ።ፍላሽ ዲስኩ በፓስውርድ ተቆለፈ።
ከዚህ በኋላ ያለ እናንት ሌላ ማንም ሰው ፍላሹን መጠቀም አይችልም።
ፍላሽ ዲስኩን መጠቀም ስትፈልጉ ኮምፒውተራችሁ ላይ ፍላሹን ደብል ክሊክ ስታደርጉ ፓስወርድ አስገቡ ይላችኋል።ፓስወርድ በማስገባት መጠቀም ትችላላችሁ ::
subscribe to our loved ones and respected followers on Youtube, because we open new youtube channel.
የ"youtube" ቻናላችንን Subscribe አድርጉ።
Subscribe ያላደረገ video ሊደርሰው ወይም መከታተል አይችልም። click z link below to subscribe

https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
2.1K views09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 12:26:42
1.5K views09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 12:24:01 ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅና ማየት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች
1 የመሳሪያ ስርዓት (Operating system)
2 የስክሪን መጠን (Screen Size)
3 ሲፒዩ(CPU)
4 ራም(RAM)
5 የሃርድ ድራይቭ አይነት (Hard Drive Type)
6 የምስል ጥራት (Image Quality)
7 የባትሪ ቆይታ (Battery Life)
8 ብራንድ (Brand)
ኮርi3 ፣ ኮርi5፣ ኮርi7 ምንድናቸው?
በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን በርከት ያሉ የላፕቶፕ እና የኮምፒውተር ሱቆች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ለገቢያም የተለያዩ የላፕቶፕ አይነቶች.በተለያየ ይዘት ይገኛሉ፡፡ እንዚህን
የተለያየ ይዘት ያላቸውን የላፕቶፕ አይነቶች ለመግዛት በዋናነት መታየት ያለበትን ከዚህ በታች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡
1. የመሳሪያ ስርዓት (platform) Windows, Mac and Linux ለአጠቃቀም ምቹ እንደሆነ የሚነገርለት Windows የብዙ ሰዎች ምርጫ ነው፡፡ ቀላል፣ ምቹ እና ተለዋዋጭ ነው፤ በዋጋም ደረጃ ጥሩ የሚባል ነው፡፡
ማክ( Mac) የአፕል ድርጅት ምርት ሲሆን ለዲዛይን ተመራጭ የሆነ ፕላትፎረም ነው፡፡ለደህንነትም ከWindows እንደሚሻል ይነገርለታል፡፡
2. የስክሪን መጠን
ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ ወደ ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደየስክሪን መጠናቸው የተከፋፈሉ ናቸው፡፡
• 11 to 12 inches(27.94cm-30.48cm) ፡በጣም ቀጭን እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡፡ ከ1.1ኪሎ እስከ1.5ኪሎ ይመዝናል፡፡
• 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ የስክርን ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability
ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
• 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን ሳይዝ ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ እንመክራለን ፡፡
• 17 to 18 inches (43.18cm- 45.72cm)፡ ላፕቶፖን ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ትልቅ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ
ይህንን ይግዙ፡፡ ለጌመሮች እና ትልልቅ የሶፈተዌር ዲዛይን ለሚያደርጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ የላፕቶፕ አይነት ነው፡፡
3. ሲፒዩ(CPU)
የኮምፒዉተር አይምሮ በመባል የሚታወቀው ሲፒዩ(CPU), ላፕቶፕ ለመግዛት ሁላችንም ማየት ያለብን ዝርዝር ነው፡፡
• AMD A series or Intel Core i3 / i5: በየቀኑ ለምንጠቀማቸው ስራዎች የሚሆኑ የሲፒዩ አይነቶች ሲሆኑ Core i5 ለሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት እና አነስተኛ የዲዛይን ስራዎችን
ለምሳሌ እንደ Photoshop, Archicad, AutoCadን የመሳሰሉ በጥሩ ሁኔታ እንድንሰራ ይጠቅሙናል፡፡ በተጨማሪም ግራፊክስ ካርድ ያለውና የሌለው በማለትም ይለያያሉ፡፡
ግራፊክስ ካርድ ያለቸው የተሻለ የዲዛይን እና አኒሜሽን ስራዎችን ያከናውኑልናል፡፡ በዋጋውም ተመጣጣኝ ነው፡፡
• Intel Core i7፡ በጣም አስደማሚ የጌም እና የዲዛይን እንዲሁም ልዩ የሆኑ የኮምፒውተር ስራችን ለምሳሌ አንደ ሜትሮሎጂ፤ ውስብስብ ስሌቶችን እንድንሰራ የሚረዳን የላፐቶፕ አይነት ነው፡፡
4 .ራም(RAM): ለፍጥነት 4ጂቢ እና ከዛ በላይ የሆነ RAM እንዲጠቀሙ እንመክሮታለን፡፡ ዋጋቸው አነስ ያሉ ላፕቶፖች
በ2ጂቢ ይመጣሉ፡፡ የዲዛይን ስራዎችን እና የሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት ስራዎችን ለመስራት 6ጂቢ ራም እና ከዚያ በላይ ያለው ላፕቶፕ ቢገዙ ይመረጣል፡፡
5.የሃርድ ድራይቭ አይነት፡ ሁለት አይነት የሃርድ ድራይቭ አይነቶች አሉ( HDDrive እና SSDrive)
ለሌሎች
#like
#share

ለተሻለ ዕውቀት፣ችግር ፈቺ፣ ወጪ ቆጣቢ እና የተለያዩ መረጃዎችን ከዚህ በፊት ዩትብ ላይ ከለቀቅናቸው ቪድዪዎች ብዙ ነገር ማግኘት ትችላላችሁ።
▬▬ Share ▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም ዩቲዩብ ቻናላችንን በመቀላቀል በምስል እና በቭድዮ የተዘጋጁ ከስራ እና ከቴክኖሎጂ ጋር ይተዋወቁ Subscribe በማድርግ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
1.5K views09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 12:20:41 የድህረገፅ ጥቆማዎች
☞በአለማችን ይኖራሉ ብለው የማይገምቷቸው አስገራሚ ድረ ገፆች
☞ በአሁኑ ወቅት መጠኑ ይለያይ እንጂ አንዳንዶቻችን በየቀኑ የኢንተርኔት መረቦችን መቃኘታችን የተለመደ ተግባር ሆኗል።
የምንቃኛቸው ድረ ገፆችም ብዙ ጊዜ የምናውቃቸውን አልያም በጣም ታዋቂዎቹን ነው።
አንዳንድ ጊዜም በፌስቡክ አማካኝነት ያገኘናቸው መረጃዎች አዳዲስ ድረ ገፆችን ያስተዋውቁናል።
እነዚህን አዳዲስ ድረ ገፆችም ጠቃሚ ሆነው ስናገኛቸው ለሌላ ጊዜ እንድንጠቀማቸው ቡክማርክ አድረገን እናስቀምጣቸዋለን።
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት 9 ድረ ገፆች ግን ምናልባትም አይተናቸው የማናውቃቸው እና የተለየ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው።
. 10Minutemail.com
ይህ ድረ ገፅ ለ10 ደቂቃ የሚቆይ የኢሜል አድራሻ ለመክፈት ያስችላል።
ድረ ገፁ የተላላክናቸውን መልዕክቶች እና የኢሜል አድራሻውን ከ10 ደቂቃዎች በኋላ ሙሉ በሙሉ ያጠፋዋል።
10Minutemail.com እንደከፈትነው ምንም ምዝገባ ሳያስፈልገን ራሱ የኢሜል አድራሻ ይሰጠናል።

በተጨማሪም Tempmail ለዚህ ይጠቅመናል አጠራጣሪ ድረገጾች ስንከፍት ኢሜል ሲጠይቁን በዚህ መጠቀም እንችላለን
. የሀሰት ስም እና አድራሻ ፈጣሪ - Fake Name Generator
በጣም አይነአፋር የሆኑ፣ የግል ጉዳያቸው የሚያስጨንቃቸው እና ትክክለኛ ስማቸውን ይፋ ማድረግ የማይፈልጉ ሰዎች በዚህ ድረ ገፅ አማካኝነት የሀሰት ስም እና ዝርዝር መረጃዎችን መፍጠር ይችላሉ።
Fakenamegenerator.com
. አንዳንድ ድረ ገፆች የማይከፍቱት እንዳልከፍታቸው ስለታገድኩ ነው ወይስ ስለማይሰሩ? - Down for Everyone or Just Me
አንዳንድ ጊዜ ኮምፒውተርዎ የተወሰኑ ድረ ገፆችን አልከፍት ሊልዎት ይችላል። እናም በዚህ ድረ ገፅ አማካኝነት እውን ይህ ድረ ገፅ አልከፍት ያለዎት ስለማይሰራ ነው አልያስ ሆን ተብሎ እንዳይከፍቱት ስለተደረገ ነው የሚለውን ማረጋገጥ ይችላሉ።
Downforeveryoneorjustme.com
. የቀናት ልዩነትን ለማስላት - Date and Time
በዚህ ድረ ገፅ ደግሞ በቀናት እና አመታት መካከል ያሉ ልዩነቶችን ለማስላት ይጠቅማል።
ለአብነትም እድሜያችን በቀናት ለማስላት የተወለድንበትን ቀን፣ ወር እና አመት እና የእለቱን ቀን ወር እና አመት በማስገባት በምድር ላይ ለስንት ቀናት ቆይታ እንዳደረግን ማስላት እንችላለን።
የምናሰላው ቀን በአላትን እና ቅዳሜ እና እሁድን አካቶ አልያም ሳያካትት ስንት እንደሆነም ማወቅ ያስችላል።
timeanddate.com
. የድረ ገፆችን የፊት ገፅ ምስል ለማስቀረት - Web Capture
የተለያዩ ድረ ገፆችን የፊት ገፅታ ምስል ለማስቀረት እና ወደ JPG/JPEG፣ PNG አልያም PDF ፎርማት ለመቀየር ይህን ድረ ገፅ ይጠቀሙ።
webcapture.net/
. ጎግልን ያለምንም የሀገር ገደብ ለመጠቀም - Google NCR
የጎግል ድረ ገፅን (google.com) ስንከፍት ጎግል ወደየሀገራችን ዶሜን ያስገባናል። ለምሳሌ ጎግልን በኢትዮጵያ ስንከፍት google.com.et ወደሚለው ያሸጋግረናል። ይህም የሚሆነው ጎግል እንደየሀገራቱ የሚከለክለው እና የሚፈቅደው ስላለው ነው።
እናም ጎግልን ያለምንም የሀገራት ገደብ ለመክፈት google.com/ncr ብለን መፈለግ በቂ ነው።
. የተላኩልን ፋይሎች በቫይረስ የተጠቁ መሆን አለመሆናቸውን ለማረጋገጥ - Virustotal.com
ከጓደኞቻችን አልያም ከማናውቀው ግለሰብ የሚያጠራጥር ፋይል ከተላከልን እና ከኢንተርነየት በቀጥታ ካወረድነው በዚህ ድረ ገፅ አማካኝነት የተላከልን ፋይል ቫይረስ መያዙን እና አለመያዙን ማወቅ እንችላለን።
ቪሩስቶታል ነፃ የኢንተርኔት የቫይረስ መመርመሪያ (ስካነር) ነው።
. በአለማችን እየተከናወኑ ያሉ ወቅታዊ የመረጃ ዘረፋዎችን የሚያሳይ ካርታ - IPviking
በአለም ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ የመረጃ ምንተፋዎች፣ የአይፒ አድራሻዎች፣ የመረጃ ዘራፊዎቹን አድራሻ እና የመሳሰሉ መረጃዎችን http://map.norsecorp.com/#/ በተባለው ድረ ገፅ ላይ መመልከት ይቻላል።
. Hackertyper
ይህን ድረ ገፅ ከፍተን የተለያዩ ፊደላትን እና ቁጥሮችን ስንጫን መረጃ ዘራፊዎች የሚጠቀሙበትን አይነት ገፅ ይከፍትልናል።
በዚህም ጓደኞቻችን እና ወዳጆቻችን የተለያዩ ድርጅቶችን መረጃዎችን እየሰረቅን ለማስመሰልና ለመሸወድ እንችላለን።
http://hackertyper.net/
. Password Generator
ጠንካራ እና በቀላሉ ብሬክ የማይደረግ የይለፍ ቃል ለፌስቡክ ለኢሜል ለሌሎች ፓስወርድ ለሚጠይቁ በሙሉ ጠንካራ የይለፍ ቃል (ፓስወርድ) ለመመስረት ይጠቅመናል።
https://strongpasswordgenerator.com/

Share , Like , Comment , ያድርጉ ?

ለተሻለ ዕውቀት፣ችግር ፈቺ፣ ወጪ ቆጣቢ እና የተለያዩ መረጃዎችን ከዚህ በፊት ዩትብ ላይ ከለቀቅናቸው ቪድዪዎች ብዙ ነገር ማግኘት ትችላላችሁ።
▬▬ Share ▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም ዩቲዩብ ቻናላችንን በመቀላቀል በምስል እና በቭድዮ የተዘጋጁ ከስራ እና ከቴክኖሎጂ ጋር ይተዋወቁ Subscribe በማድርግ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
1.3K views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 12:15:49 #ለተማሪዎች የሚሆኑ ምርጥ 4 የአንድሮይድ አፕሊኬሽኖች
ተማሪዎች የሃይ ስኩል እና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተደራራቢ አሳይመንቶች ሊሰጣችሁ ይችላል፡፡
ተደራራቢ የቤት ስራዎች፡የግሩፕ አሳይመንቶች፡ፕሮጀክቶች፡ ተደራራቢ ጥናቶች ተማሪዎች ላይ ጫና ሊያበዛ ይችላል፡፡ ይሄ ጫና ደሞ ጭንቀት ሊፈጥር ይችላል፡፡
በትምህርት ወቅት ጫና እንዳይፈጠርባችሁ ዋናውና ቁልፍ ነገር ለየአንዳንዱ ነገር ፕሮግራም ማዘጋጀት ነው፡፡
ቀጥሎ የምነግራችሁ 4 አፕሊኬሽኖች ተማሪዎች በትምህርት በሚቆየበት ዓመታት ጫና ሳይፈጠርባቸው ትምህርታቸውን ባግባቡ በመከታተል በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት እነነዲያመጡ የሚረዱ አፕሊኬሽኖች ናቸው፡፡ እውቅናም የተሰጣቸው አፕልኬሽኖች ናቸው።
1ኛ፡- School Planner Application
ይህ አፕሊኬሽን የቤት ስራዎችን፡ የግሩፕና የግል አሳይመንቶችን፡ፕሮጀክቶችን፡ የእያንዳንዱን ክላስ ሰዓትና ቀን…ማንኛውም ትምህርት ነክ አክቲቪቲዎቻችሁን ኦርጋኒዝ ያደርግላችሃል፡፡ ፕሮግራም ያወጣላችኋል።
oይህ አፕሊኬሽን በየቀኑ በፕሮግራማችሁ መመሰረት በየቀኑ መስራት ያለባችሁን ለምሳሌ ጥናት ወይም የቤት ስራ፡ወይም የግሩፕ አሳይመንት ወይም የላብራቶሪ ሙከራ ….ባጠቃላይ ጠዋት ምን ማድረግ እነዳለባችሁ፡፡፡፡፡፡ ከሰዓት ምን መስራት እንዳለባችሁ…….ማታ ምን መፃፍ እንዳለባችሁ ያስታውሳችሃል….
የምታስረክቡት አሳይመንት ወይም ፕሮጀክት ካለባችሁ የምታስረኩብበት ቀን በዚህ ቀን ነው፡፡፡፡ ቀኑ እየደረሰ ነው…እያለ ያስታውሳችሃል፡፡
2ኛ፡- Brilliant ይባላል
ይህ አፕሊኬሽን ደሞ በተለይ በሂሳብ፡ በሳይንስና በኮምፒውተር ሳይንስ ጥሩ ውጤት ለማምጣት በጣም የሚጠቅም አፕ ነው፡፡ o o ይህ አፕሊኬሽን እየሸመደዳችሁ እንዳታጠኑና በተለይ ረጃጅም ቃላት የሚበዙባቸው የትምህርት አይነቶችን ዘርዘር ያሉ ገለፃዎችን በመጠቀም ሳትሰለቹ ትምህርቶቹን በቀላሉ እንድታጠናቸውና እንዲገባችሁ ይረዳል
3ኛ፡- Grammarly ይባላል
o ይህ አፕሊኬሽን ደሞ በእንግሊዘኛ የመፃፍ ችሎታችሁን ያሳድጋል፡፡
o የተለያዩ ESSAY በእንግሊዘኛ ስትፅፉ  የግራመር ስህተታችሁን ያርማል፡  ትክክለኛ ቃላት እንድትመርጡ ይረዳል፡፡
 ረጃጅም አረፍተ ነገሮችን ስትፅፉ የሲንታክስ ስህተታችሁን ያርማል፡፡  በእንግሊዘኛ የመፃፍ ችሎታችሁን ቀስበቀስ ያሳድጋል፡፡
4ኛ፡- Mendeley ይባላል o Research በምትሰሩበት ግዜ ለሪሰርቻችሁ የሚሆኑ የተለያዩ ሪሶርሶች እንዴት እንደምታገኙ ይረዳችሃል፡፡
ለጥናታችሁ ወይም ለሪሰርቻችሁ የሚጠቅሙ መፅሃፎችን፡ጥናታዊ ፅሁፎችን፡ ምክረ ሃሳቦችን እንዴት ኦርጋኒዝ እንደምታደርጉ ያስተምራቸሃል፡፡
ለሪሰርቻችሁ የተጠቀማችሁባቸውን የተለያዩ የጥናታዊ ፁሁፎች ፃሃፊዎችን፡የመፅሃፎች ደራስያን ፡ምሁራንን ስማቸውን በመጥቀስ ጥናታችሁ ላይ በማካተት እንዴት እውቅና ወይም ክሬዲት እንደምትሰጡ ያስተምራችሃል፡፡
playstore ላይ በመግባት App አውርዷቸው

ለተሻለ ዕውቀት፣ችግር ፈቺ፣ ወጪ ቆጣቢ እና የተለያዩ መረጃዎችን ከዚህ በፊት ዩትብ ላይ ከለቀቅናቸው ቪድዪዎች ብዙ ነገር ማግኘት ትችላላችሁ።
▬▬ Share ▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም ዩቲዩብ ቻናላችንን በመቀላቀል በምስል እና በቭድዮ የተዘጋጁ ከስራ እና ከቴክኖሎጂ ጋር ይተዋወቁ Subscribe በማድርግ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
1.4K views09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 12:15:06
ለተሻለ ዕውቀት፣ችግር ፈቺ፣ ወጪ ቆጣቢ እና የተለያዩ መረጃዎችን ከዚህ በፊት ዩትብ ላይ ከለቀቅናቸው ቪድዪዎች ብዙ ነገር ማግኘት ትችላላችሁ።
▬▬ Share ▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም ዩቲዩብ ቻናላችንን በመቀላቀል በምስል እና በቭድዮ የተዘጋጁ ከስራ እና ከቴክኖሎጂ ጋር ይተዋወቁ Subscribe በማድርግ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
1.8K views09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 22:41:42 Watch:- በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከኮምፒውተራችን፣ከሲ ድራይቭ ፣ከዲ ድራይቭ፣ ከፍለሽ ዲስክ ወይም ከሃርድ ዲስክ ወዘተ የጠፋብን ፋይል እንዴት መልሰን ማግኘት እንችላለን?



742 views19:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 23:17:33

575 views20:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ