Get Mystery Box with random crypto!

Information Science and Technology

የቴሌግራም ቻናል አርማ information_science_technology — Information Science and Technology I
የቴሌግራም ቻናል አርማ information_science_technology — Information Science and Technology
የሰርጥ አድራሻ: @information_science_technology
ምድቦች: ቴክኖሎጂዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.16K
የሰርጥ መግለጫ

Information science is a field primarily concerned with the analysis, collection, classification, manipulation, storage, retrieval, movement, dissemination, and transfer of information.

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-06-19 12:22:39 የግድ ማወቅ የሚገባን የስልካችን ሴቲንግ ብቻ በማስተካከል በየሰዓቱ ሜባላችን ቻርጅ ከማድረግና ሞባይላችን እንዳይግልና ሙቀት እንዳይፈጥር ያደርጋል። ይህንን ቪድዮ አይተው አሁኑኑ ያስተካክሉ:-


1.9K views09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 20:06:18 የስልካችንን ሴቲንግ ወደ ዳርክ ሞድ በመቀየር የባትሪ ፍጆታችንን እጅጉን ይቀንሳል የዓይናችንን ጤነትም ከጨረር እንከላከላለን።
ይህ ዳርክ ሞድም የተዘጋጀው ለዚህ ጥቅም ሲባል ነው። change phone settings to dark mode and save battery life and and Reduce brightness to protect our eyes.


1.5K views17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 17:24:51 ስልካችን ቢጠፋ ወይም ቢሰረቅ ፣ በሲም ካርዳችን ሌላ ሰው እንዳይጠቀም ወይም በሲም ካርዳችን ወንጀል እንዳይሰራበት እንዴት ሎክ እናደርጋለን?

2.1K views14:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 18:24:00 የሳትላይት ዲሽ ረሲቨር ከዋይፋይ or ሞባይል ኔትወርክ ጋር ኮኔክት በማድረግ እንዴት ዩቱብ በ ቴሌቪዥን መጠቀም እንችላለን።


972 viewsedited  15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 06:34:08 የያዝነው ሞባይል ወደ 5G ኔትዎርክ እንዴት ማሳደግ እንችላለን?
5G ቴክኖሎጂ እንዴት ይሰራል? *******
የ 5G ቴክኖሎጂ የ አምስተኛው ትውልድ የሞባይል ቴክኖሎጂ ሲሆን የዲጂታል ዓለሙ የሚፈልገውን ፈጣን ግንኙነት ለመፍጠር ትልቅ እርምጃ ያራመደ ቴክኖሎጂ ተደርጎም ይወሰዳል። የ 5G ቴክኖሎጂ የመረጃ መለዋወጫ ፍጥነትን አሁን ካለው የ4G ቴክኖሎጂ ከ10 እስከ 100 የተሻለ እጥፍ እንደሚልቅ ይገምታል። ይህም ማለት የሞባይል ኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን እስከዛሬ ከነበረው የm/s ፍጥነት ወደ g/s ያሳድገዋል ማለት ነው።
?

2.6K viewsedited  03:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 20:00:20 ጎግል ፕሌይ ስቶር ብልሽት ለማስተካከል
Google Play Store በአብዛኛዎቹ የAndroid ዘመናዊ ስልኮች ላይ ተጭኖ የሚመጣ ሲሆን በሆነ ምክንያት በዲቫይሱ(ስልክ ወይም ታብሌት) ላይ መሥራት ሊያቆም ሊያጋጥም ይችላል፡፡ በዚህም ምክንያት በዲቫይሱ ላይ የተጫኑ ሶፍትዌሮችን የቅርብ ግዜ ማድረግ፣ ሶፍትዌሮችን ዳውንሎድ አድርገን መጫን እና አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን የቅርብ ግዜ ማድረግ አንችልም፡፡
Google Play መደብር በእርስዎ ዲቫይስ ላይ የማይሰራ ከሆነ ችግሩን ለመፍታት አንዳንድ መንገዶችን እጠቁማለሁ
1. የዲቫይሱን ቀን እና ሰዓት ቅንብር(ሴቲንግ) ያስተካክሉ
የተሳሳተ ቀን እና የጊዜ ገደብ ሲኖርዎት የGoogle አገልጋዮች ከአሳሽዎ ጋር ማመሳሰል ችግሮች ያጋጥማቸዋል ለማሰተካከል ወደ ሲስተም ሴቲንግ በመሄድ «ቀን እና ሰዓት» ማስተካከል ይጠበቅብዎታል፡፡
“Automatic date & time” and “Automatic time zone” እንዲሰራ ክፍት ያድርጉ ወይም ማኑዋሊ ቀን እና ሰዓት ያስተካክሉ፡፡
2. ጎግል ፕሌይ ስቶር ከዚህ በፊት ይዞት የነበረውን ዳታ ማጽዳት
በጎግል ፕሌይ ስቶር ላይ ከዚህ በፊት ተጠቅመናቸው የነበረው ሶፍትዌሮች ዝርዝ ይዞ ይቀመጣል(Cached data) ይሄ በምንፈልገው ጊዜ በፍጥነት ለመክፈት ኢንተርኔት ግንኙነቱ ፍጥነት ባይኖረውም ይረዳናል ነገር ግን Cached data አንዳንድ ጊዜ በPlay Store ላይ ችግር ይፈጥራል፡፡ በGoogle Play ላይ Cached data ለማጽዳት እነዚህን ደረጃዎች ይከተሉ:
ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ
ደረጃ # 2: አፕስ (Apps)
ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ
ደረጃ # 4: ስቶሬጂ በመክፈት “CLEAR CACHE“.
3. የቅርብ ግዜ የሆነ ጎግል ፕሌይ ስቶር መጫን
በየጊዜው ሶፍትዌሮችን የሚሰሩ ዴቨሎፐሮች ለሰሩት ሶፍትዌር የቅርብ ግዜ ማድረጊያ አብዴተር የሚለቁ ሲሆን በዚህ የቅር ማድረጊያ ላይ የተለያዩ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል ይካተታል፡፡.
በተመሳሳይ መልኩ Google የ Play ስቶር አብዴተር በየጊዜው የሚያወጣ ሲሆን እንደሚኖሩበት አገር የሚለቀቀው አብዴት ሊዘገይ ይችላል በቀጥታ የቅርብ ማድረጊያውን(APK ፋይል) ማግኘት ከቸኮሉ APKMirror በማለት ኢንተርኔት መጠቀሚያ ብሮውዘር ላይ ፈልገው ማውረድ ይችላሉ፡፡
4. ጎግል ፕሌይ ስቶር ወደነበረበት የመጀመሪያው ቨርዥን መመለስ
አንዳንዴ የቅርብ ጊዜየተደረገ የጎግል ፕሌይ ስቶር ስሪት በርካታ ችግሮችን ሊያመጣ ይችላል ስለሆንም አብዴት የተደረገው በማጥፋት ዲቫይሱን ስንገዛ የነበረውን(factory version ) ጊዜ መመለስ፡፡ እነዚህን ደረጃዎች በመከተል እናጥፋ:
ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ
ደረጃ # 2: አፕስ (Apps)
ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ
ደረጃ # 4: “Uninstall Updates”
5. ጎግል ፕሌይ ሰርቪስ መስራቱን ማረጋገጥ
Google Play Services ዋናው ተግባራት የGoogle አገልግሎቶች የሆኑትን Google Play ስቶር፣ ጎግል ማፕ፣ ጎግል ፕላስ ወዘተ አገልግሎቶች አውቶማቲካሊ ግንኙነት እንዲያደርጉ እና አብዴት የሚያደርግ የሚረዳ በመሆኑ እንደ ተጨማሪ መፍትሄ በመውሰድ Google Play Services መስራቱን ያረጋግጡ፡፡
6. ጎግል ፕሌይ ስቶርን ዘግቶ መክፈት
ይህ በአብዛኛው ተጠቃሚዎች የሚተገበሩበት የተለመደ ዘዴ ነው፡፡ ማድረግ ያለብዎት ነገር Google Play Storeን በመዝጋት እንደገና ማስጀመር( ለሌሎች አፕ ይሰራል) ችግሩን ሊፈታው ይችላል
ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ
ደረጃ # 2: አፕስ (Apps)
ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ
ደረጃ # 4: “Force Stop” የሚለውን በመጠቀም መዝጋት እና እንደገና ይክፈቱ
7. ዲቫይሱን አጥፍቶ ማብራት
ዲቫይሱን አጥፍቶ ማብራት ተመራጭ መፍትሄ ሲሆን ብዙውን ግዜ ይሰራል ምክንያቱም ስማርትፎን ስልኮች አጥፍተን ዳግም ማስጀመር በዲቫይሱ ላይ ያሉትን አፕ ያረጋጋል፡፡ በተቻለ መጠን አንድ አፕ ከወትሮው የተለየ ተግባር ካመጣ ዳግም አጥፍተን ስናስጀምር የተሻለ አፈጻጸም እና ችግሩን መፍታት ይችላል፡፡
8. ዲቫይሱን አንድሮድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ዳግም ማስጀመር
ከላይ በጠቀስኩት መፍትሄ ምንም የማይሰራ ከሆነ ዲቫይሱን ፋብሪካ ዳግም ማስጀመር (hard reset) ማድረግ በዚህ ሂደት በዲቫይሱ ላይ ያሉትን ዳታ፣ የተጫኑ አፕሊኬሽን ሶፍትዌር እንደዚሁም የተጠቃሚውን አካውንት የመሳሰሉትን ሁሉ ያጠፋል፡፡
በርካታ ችግሮች በዲቫይሱ ላይ ካልገጠመዎት በስተቀር የፋብሪካ ዳግም ማስጀመር (hard reset) ባትጠቀሙ እመርጣለሁ ዳግም ለማስጀመር ከወሰኑ ሚሞሪው ያውጡ መጠባበቂያ መውሰድዎን አይርሱ፡፡
ይሄን ችግር ለመፍታት ሊያግዝ የሚችል የተሻለ መፍትሄዎች ካለዎት አስተያየትዎን ይስጡን እንዲሁም ለ ጉዋደኞቹዎ ያካፍሉ።

ለተሻለ ዕውቀት፣ችግር ፈቺ፣ ወጪ ቆጣቢ እና የተለያዩ መረጃዎችን ከዚህ በፊት ዩትብ ላይ ከለቀቅናቸው ቪድዪዎች ብዙ ነገር ማግኘት ትችላላችሁ።
▬▬ Share ▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም ዩቲዩብ ቻናላችንን በመቀላቀል በምስል እና በቭድዮ የተዘጋጁ ከስራ እና ከቴክኖሎጂ ጋር ይተዋወቁ Subscribe በማድርግ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
1.3K views17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 19:57:42 #ኦርጅናሉን_ስልክ_ከፌኩ_በቀላሉ__እንዴት_መለየት_ይቻላል?እነዚን መንገዶች በመጠቀም ፌክ ሳምሰንግ ስልኮችን መለየት ይችላሉ።
የስልኩን ቀፎ አካላዊ ገጽታዎች በመገምገም
ፌክ ሳምሰንግ ስልክ
❶. የስክሪኑ መስታወት ጥራት የለዉም
❷. ስክሪኑ ከቀፎዉ ጠርዝ በጣም ይርቃል
❸. ስክሪኑ ድምቀት ይጎድለዋል
❹. የሳምሰንግ ሎጎ (ሳምሰንግ የሚለዉ ጽሁፍ) ሲነካ
ይሻክራል፣ በደንብ ከተጫኑት ይለቃል
❺. ከኦርጂናል ስልኮች ጋር ሲያስተያዩት፤ የባትሪ መክደኛዉን ሲከፍቱ የሚታዩ ትንንሽ አካሎች እና ባትሪዉ ላይ የሚገኙት መረጃዎች የተለያዩ መሆናቸዉን
ይመለከታሉ፡፡
የስልኩን ፍጥነት እና ትእዛዞችን አፈጻፀም በመገምገም
❶. በስልኩ ፎቶዎችን ለማንሳት ይሞክሩ፣ በፌክ ሳምሰንግ
ስልኮች የሚያነሱት ፎቶ ጥራት የወረደ ይሆናል
❷. በተመሳሳይ ጊዜ በርካታ ጌሞች እና አፕሊኬሽኖችን
ለመክፈት ይሞክሩ፣ ፌክ ስልኮች ስታክ(ቀጥ) የማለት ባህሪይ ያሳያሉ፡፡
❸. ስልኩን አጥፍተዉ ያብሩት፣ ፌክ ስልኮች ቶሎ አይከፍቱም
የስልኩን የምርት መረጃዎች በመገምገም
❶. ከአፕሊኬሽን ማዉጫዉ ላይ፣ Settings የሚለዉን ይጫኑ
❷. ከ Settings ላይ More የሚለዉን ይጫኑ እና #Storage የሚለዉን በመጫን ስልኩ ላይ መጫን ሚችሉትን የዳታ መጠን ይመልከቱ፤ ከኦርጂናሎቹ ስልኮች በጣም ያነሰ ከሆነ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡
እንዲሁም About device የሚለዉን ይጫኑ እና የስልኩን ሞዴል ቁጥር እና baseband, build number
ጉግል ላይ ይፈልጉት፣ የሚያገኙት መልስ ፌክ ወይም ኦርጅናል መሆኑን ይነግሮታል፡፡
የሳምሰንግ ኮዶችን በመጠቀም ወደ ስልክ መደወያዉ በመሄድ፣ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ኮዶች ያስገቡ እና Call የሚለዉን ይጫኑ፤ ስልኩ
ያስገቡትን ኮድ አዉቆ መልስ መስጠት ከቻለ ኦርጅናል
መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ ካልሆነ ግን ፌክ ስልክ ነዉ፡፡
*#0*# #አጠቃላይ መገምገሚያ
*#1234# or *#9999# ስልኩ የሚጠቀመዉን
#ሶፍትዌር እና #ሞደም ማወቂያ
*#12580*369# #ስለ ስልኩ #ሶፍትዌር እና #ሀርድዌር ማወቂያ
*#06# #የስልኩን ኢንተርናሽናል #መለያ ቁጥር
ማወቂያ
*#9998*246# #የስልኩን #የባትሪ እና ሚሞሪ መረጃዎች ማወቂያ
ሳምሰንግ ኪይ(Samsung Kies) ሶፍትዌርን በመጠቀም ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች ፌክ ሳምሰንግ ስልክን መለየት ካልቻሉ ይህን ሶፍትዌር ይጠቀሙት፡፡
❶. Samsung Kies ሶፍትዌርን ኮምፒዉተሮት ላይ
ይጫኑት
❷. ለማረጋገጥ የፈለጉትን ስልክ ከኮምፒዉተሮት ጋር ያገኛኙት
❸. ሶፍትዌሩ ስልኩን ያነበዉ እና የስልኩን ስም ፣ የሚጠቀመዉን ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ያሳያል፤
ሶፍትዌሩ ስልኩን ማንበብ ካልቻለ በድጋሚ ይሞክሩት በድጋሚ ማንበብ ካልቻለ ሰልኩ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡

መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ።
አስተያየትዎን በcomment ወይም በinbox ላይ ቢያደርሱን በደስታ እንቀበላለን።
*

ለተሻለ ዕውቀት፣ችግር ፈቺ፣ ወጪ ቆጣቢ እና የተለያዩ መረጃዎችን ከዚህ በፊት ዩትብ ላይ ከለቀቅናቸው ቪድዪዎች ብዙ ነገር ማግኘት ትችላላችሁ።
▬▬ Share ▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም ዩቲዩብ ቻናላችንን በመቀላቀል በምስል እና በቭድዮ የተዘጋጁ ከስራ እና ከቴክኖሎጂ ጋር ይተዋወቁ Subscribe በማድርግ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
1.1K views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 19:47:12 የስልካችን ሚሞሪ ምድነዉ የሞላዉ?
መፍትሄዉስ?
የአብዛኞቻችን የራስምታት የሆነብን በስልካችን ላይ ቪድዮ ሙዚቃ አፕልኬሽን ስንጭን ሙሞሪ ሞልቷል (Insufficient storage avaliable) የሚለዉን pop up dialog እንዴት ሚሞሪያችን #free አድርገን አንደምናስተካክል እናያለን።
ግን ለምን ይመጣል?
የ አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ስራ(አፕልኬሽን install ለማድረግ ፋይል ለማስቀመጥ ...) የመስራያ ቦታ ሲያጣ ይከንን #Notification ያሳየናል።
የአንድሮይድ አፕልኬሽኖች ማስቀመጫ storage አይነት ይጠቀማሉ።
ለ አፕሌክሽኖቹ ለራሳቸዉ የሚወስዱት #memory አለ።
ለራሳቸዉ ለ አፕልኬሽኑ #data ማስቀመጫ የሚጠቀሙበት #memory አለ።
ለአፕልኬሽኑ #catch ጊዜያዊ ፋይል ማስቀመጫ #memory አለ።
እነዚህ #Catch ላይ የተቀመጡ ፋይሎች ጣም ብዙ ቦታ ሊይዙ ይችላሉ።
መፍትሄ
ቆይ መጀመራያ እስቶሬጃችሁን ምን ምን እንደሞላዉ እዩት።
የስልካችሁ ለማየት #Internal storage ምን ምን እንደሞላዉ ለማየት ከታች ያሉትን ስፔፖች ይከተሉ ።
#Setting ዉስጥ ይግቡ
ከዛ #Storage የሚለዉ ዉስጥ ይግቡ ።
አዚህጋ የ RAM,Internal Storage,SD Card የያዙትን መጠን በ% ያሳያችሗል።
Internal Storage የሚለዉን ይጫኑት ።
Avaliable :አሁን ያላችሁ #free የሆነ የሚሞሪ መጠን ነወ።
System ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ለራሱ እና ከስልኩ ገር ለሚመጡ ለአንዳንድ አፕልኬሽኖች(እግደ Setting,Chrome,Phone,GMail,Google,Contacts,Photo. ..) ለማስቀመጥ የተጠቀመበት #memory ያሳየናል።
Owners እኛ የጫናቸዉን አፕሌኬሽኖች, ፎቶዎች,ያሳየናል።
አዉድዮ ፋይሎች እና Catch ሚሞሪ ላይ ያሉት ፋይሎች የያዙትን የሚሞሪ መጠን ያሳየናል።
አሁ ከላይ ካየሐችሁት ዉስጥ ብዉ ቦታ ይዞ ሚሞራያችሁን የሞላዉን ትመርጣላችሁ።
አፕልኬሽን ከሆነ ብዙ ጊዜ የማትጠቀሙበትን #uninstall ማድረግ።
uninstall ለማድረግ #Setting->Apps ከዛ uninstall ለማድረግ የፈለጋችሁትን አፕልኬሽን መርጣችሁ ስትጫኑት uninstall የሚል ሲመጣ አሱን ይጫኑት።
ፎቶ ከሆነ የማትፈልጉትን ፎቶ አየመረረጣችሁ ማጥፋት አለባችሁ።
Video ከሆነ የማትፈልጉትን #Video እየመረጣችሁ ማጥፋት።
Audio ከሆነም አሸዛዉ ምረጡና አጠያጥፉ
የሚለዉ ዉስጥ ይግቡ እና እንደ Other#Screenshot የመሣሠሉትን ፋይሎች ያጥፉ
Clear data የሚለዉን በመጫን #catch ሚሞሪ ላይ ያሉትን ፋይሎችያጥፉ
ሌላኛዉ አማራጭ ትላልቅ ፋይሎችን ከ Internal Memory ላይ #Cut አድርጎ ወደ SD card ላይ ፔስት ማድረግ ነዉ።
ሌላዉ አማራጭ SD Card የስልኩ defalu ፍይል (Apps,photo,video,audio በቂ ሁሉንም ነገር)
ማስቀመጫ ማድረግ ነዉ።
ይከን ለማድረግ

Setting-> Storage->default write disk የሚለዉጋ Phone Storage የሚለዉን ተመርጦ ታገኙታላችሁ አናተ SD card የሚለዉን ይምረጡ።
ስለተከታተላችሁን አናመግናለን
ስልኩ እየሞላበት የተቸገረ ጓደኛችሁ ስለሚኖር #Share አድርጉላቸዉ።

ለተሻለ ዕውቀት፣ችግር ፈቺ፣ ወጪ ቆጣቢ እና የተለያዩ መረጃዎችን ከዚህ በፊት ዩትብ ላይ ከለቀቅናቸው ቪድዪዎች ብዙ ነገር ማግኘት ትችላላችሁ።
▬▬ Share ▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም ዩቲዩብ ቻናላችንን በመቀላቀል በምስል እና በቭድዮ የተዘጋጁ ከስራ እና ከቴክኖሎጂ ጋር ይተዋወቁ Subscribe በማድርግ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
1.3K views16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 00:01:05 Watch "ፍላሽ ዲስክ እንዴት በፓስዎርድ ማሰር ይቻላል_How to lock your USB Flash for bitlock" on YouTube


345 views21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 19:01:46 Watch now:-Best app of 2022
=======================
የሙዚቃ ፍቅር ያላቹሁ በድጄ እና በ ሙዚቃ እዲቲንግ ስራ መስራት ለምትፈሉጉና እየሰራቹሁ ላላቹሁ ምርጥ አፕልኬሽን ይዘን መጥተናል ። ይህ አፕልኬሽን ሞሲስ ይባላል። ስራው ሙዚቃ ድምፅ ለብቻው ግጥም ለብቻው ምስል ካለውም ለብቻው ዘርዝሮ ቁጭ ያደርጋል ለበለጠ ይህንን ቪድዮ እዩት በጣም ቆንጆ አድርጎ ይተነትናል ሼር ማድረግ ይልመድባቹሁ መልካም ግዜ ተመኘን።



▬▬ Share ▬▬▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም ዩቲዩብ ቻናላችንን በመቀላቀል በምስል እና በቭድዮ የተዘጋጁ ከስራ እና ከቴክኖሎጂ ጋር ይተዋወቁ Subscribe በማድርግ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
1.5K views16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ