Get Mystery Box with random crypto!

ኮምፒውቴክ🤖Techtalk

የቴሌግራም ቻናል አርማ compu_te — ኮምፒውቴክ🤖Techtalk
የቴሌግራም ቻናል አርማ compu_te — ኮምፒውቴክ🤖Techtalk
የሰርጥ አድራሻ: @compu_te
ምድቦች: ቴክኖሎጂዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 155
የሰርጥ መግለጫ

የተለያዩ ቴክኖሎጂና የሶፍትዌሮች ጥቆማ Updates tech info🚮 👁‍🗨 🗨💬 እናም Grow Knowledge

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

3

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-03-05 01:39:34
~~~~~~~~~~~~
TronLink BTT (TRC20) Renomination Airdrop Event
No waiting, airdrop are sent immediately.
No waiting for distribution date
Claim immediate to wallet
We will never ask you for any fees!

Claim 50,000BTT immediately to your wallet
19 viewsM Merim, 22:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 22:14:23 ዋና ዋና የሳይበር ጥቃት አይነቶች

መረጃ ጠላፊዎች የግለሰቦችን ኮምፒውተር፣ የስልክ፣ የባንክ ካርድ እና ማንኛውንም በይነመረብ ላይ ያኖሩትን መረጃ በርብረው ሊመነትፉ ይችላሉ።

የሳይበር ጥቃት በግለሰብ ደረጃ ሲፈጸም ጉዳቱ እጅግ አስደንጋጭ ባይሆንም ችግሩ በአገር ደረጃ መዋቅራዊ ጉዳትን ያስከትላል ተብሏል።

የሳይበር ጥቃቶች በተለያዩ የማጥቂያ መንገዶች የሚፈጸሙ ሲሆን÷ በሳይበር ምህዳሩ በስፋት ከተለመዱ ከሳይበር ጥቃት አይነቶች ውስጥ የአገልግሎት መቋረጥ፣ የዲፌስምነት ጥቃት፣ የማልዌር ጥቃት፣ ስፓምናየፌሺንግ ጥቃቶች ናቸው፡፡

የአገልግሎት መቋረጥ ይህ የሳይበር ጥቃት አይነት የሲስተሞችን አቅም ባልተፈለገ ሁኔታ በማጨናነቅ ህጋዊ ተጠቃሚው አገልግሎት እንዳያገኝ ማድረግ ነው፡፡

የዲፌስምነት ጥቃት ( መልክን የመቀየር ጥቃት ) ሆን ተብሎ እና ሳይጠበቅ ጣልቃ በመግባት መደበኛ የኮምፒውተር ተግባርን የሚያውክ የጥቃት አይነት ነው።

የማልዌር ጥቃት የተጠቂውን ድረ- ገጽ በሀሰተኛ ሰነዶች በመቀየር የሚፈጸም የጥቃት አይነት ሲሆን÷ ስፓም (Spam): ደግሞ ብዛት ያለው እና የአጥፊነት ተልዕኮ ያላቸው ኢሜሎችን በመላክ የሚፈጸም የጥቃት አይነት ነው ተብሏል፡፡

የፊሺንግ ጥቃት የሚባለው የሳይበር ጥቃት የተለያዩ የማታለያ እና የማዘናጊያ ዘዴዎችን በመጠቀም አጭበርባሪዎች ከተጠቃሚዎች ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎችን ለመመዝበር የሚደረግ የማህበራዊ ምህንድስና ጥቃት ነው።
652 views●▬▬▬▬๑۩Jemal Ali۩๑▬▬▬▬▬●, 19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 22:13:00 የሞባይል ባንኪንግ ሲጠቀሙ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች

የሞባይል ባንኪንግ የባንክ አገልግሎቶችን ወደ ባንኮች ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልግ በተንቀሳቃሽ ስልኮች አማካኝነት ብቻ የባንክ አገልግሎቶችን ማለትም ገንዘብ መላክ እና መቀበል እንዲሁም የተለያዩ ክፍያዎችን ለመፈፀም የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡

የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት የተጠቃሚዎችን ድካም ከመቀነስ ጋር በተያያዘ አገልግሎቱን ተመራጭና ቀላል ያደርገዋል፤ ታዲያ ይህ አገልግሎት የቴክኖሎጂ ውጤት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተጓዳኝ የመረጃ መረብ ጥቃት ተጋላጭነት አያጣውም፡፡

ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን ሲጠቀሙ የሚከተሉትን ጉዳዮች ሊያውቋቸው እና ጥንቃቄ ሊያደርጉባቸው ይገባል ሲል የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ይመክራል፡፡

➊. የተረጋገጡና ትክክለኛ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎችን (application) ከተረጋገጡ ምንጮች አውርዶ መጠቀም፦ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎች ትክክለኛ በባንኩ እውቅና ያላቸው መሆኑንና የሚገኙትም በትክክለኛው የመተግበሪያ ቋት ማለትም ለአንድሮይድ የመተግበሪያ ቋት ወይም ለአይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማውረድ መጠቀም ተገቢ ነዉ፡፡

➋. በስልኮች ላይ ያሉ ሌሎች መተግበሪያዎች ፍቃዶችን ማጥናት፡- በስልክዎ ላይ የሚገኙ ሌሎች መተግበሪያዎች የሚጠይቋቸውን ግንኙነቶች (አክሰስ) ልብ ይበሉ፡፡
መተግበሪያዎች ለአገልግሎቶቻቸው ከሚያስፈልጋቸው የሞባይል መረጃ ዉጪ ሌሎች መረጃዎች እንዲዳረሱ እንዳይፈቅዱ፡፡

➌. አፕሊኬሽኖችን /መተግበሪያዎችን ማዘመን፡- በስልኮች ላይ የሚገኙ የባንኪንግ መጠቀሚያ መተግበሪያዎችን ወቅቱን ጠብቀዉ ያዘምኑ፡፡
መተግበሪያዎች ላይ ለስርቆት የሚዳርጋቸው ክፍተቶች ሲገኙ በየወቅቱ ማዘመኛ ስለሚለቀቅላቸው የደህንነት ክፍተቶቹን ለመድፈንና የባንክ ሂሳብዎን ደህንነት ለማስጠበቅ በየጊዜው ያዘምኗቸው፡፡

➍. የሞባይል ስልክ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን ማዘመን፡- የስልክዎን ደህንነት ክፍተት ለመሙላት በየጊዜው ክፍተት መሙያና ማሻሻያ እድሳቶች ስለሚለቀቁ በየወቅቱ እየተከታተሉ ያዘምኗቸው፡፡

➎. ከህዝብ መገልገያ ዋይፋይ ይልቅ የሞባይል ዳታ ይጠቀሙ፡- የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶችን በሞባይልዎ ለመጠቀም ለህዝብ መገልገያ የቀረቡ ነፃ ዋይፋዮችን ከመጠቀም ይልቅ የሞባይል ዳታዎችን ይጠቀሙ፡፡

➏. ዘርፈ-ብዙ የደህንነት ማስጠበቂያ የይለፍ-ቃሎችን ይጠቀሙ፦ ሞባይል ስልክዎን በአሻራ፣ ፊት ማንበብያ (ፌስ ሪኮግኒሽን)፣ ፓተርን፣ ፓስወርድ እና ፓስ ኮድ የመሳሰሉትን በመጠቀም ስልክዎን ይቆልፉ፡፡

➐. በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቋቸውን ግላዊ መረጃዎች ይገድቡ፡- በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚለቀቁ መረጃዎች የተገደቡ ሊሆኑ ይገባል፡፡

➑. ፀረ-ቫይረስ (ማልዌር) ይጠቀሙ

➒. የሞባይል ስልክዎን አካላዊ ደህንነት ያስጠብቁ

➓. የባንክ ሂሳብዎን ዘወትር ይከታተሉ፡- በተጨማሪ ተገቢውን ሁሉ ጥናቃቄ ካደረጉ በኋላም ስለ ባንክ አካውንትዎ የሚደርሱ ማንቂያዎችን (notifications) በአግባቡ መከታተል እንዲሁም በየጊዜው ስለ አካውንትዎ ሁናቴ (ስታተስ) መከታተል እና የማያውቁት የሂሳብ ለውጥ ካለ በአፋጣኝ ለባንክዎ ያሳውቁ፡፡
https://t.me/Compu_Te
https://t.me/Compu_Te
1.3K views●▬▬▬▬๑۩Jemal Ali۩๑▬▬▬▬▬●, 19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 11:38:44
I Phone 14
105 viewsJemal A Merim, 08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 23:12:36 ስልኮዎ በቫይረስ መጠቃቱን
እንዴት ማወቅ ይችላሉ?
ስልኮዎን ከቫይረስ እንዴት ነጻ
ማድረግ እንደሚችሉ የሚያሳይ ትምህርት ነው

1 በስልኮዎ ውሰጥ ያሉ ፐሮግራሞቸ አልከፍት ይላሉ

2፡በሚሞሪ ካርድዎ እና በስልክዎ ውስጥ ያሉ የራስዎ
ፋይሎች ራሳቸውን ይቀይራሉ።

በተለይ ደግሞ በቫይረስ
የተጠቃው ስልክዎ ከሆነ ፋይሎችን አልያ ሶፍትዌሮችን
ለመክፈት ሲሞክሩ application not supported or
file dasn’t exist የሚል ሜሴጅ ሊመጣ ይችላል

3፡የስልክዎ የባትሪ ጉልበት በጣም እየደከመ ለምሳሌ
ይሀ ምልክት ግነ በኖርማል ስልኮች ላይም ሊስተዋል
ይችላል።

ያ የሚሆነው ደግሞ የሚጠቀሙት ባትሪ ኦርጅናል
ባለመሆኑና በሌሎችም ችግሮች ሊሆን ይችላል ለምሳሌ
የስልክዎ ባትሪ ኮኔክተር ችግር ካለበት ባትሪዎን ቶሎ ቶሎ
ይጨርስቦታል

4:ምናልባት ስልክ ደውለው እያናገሩ እያለ አልያባጋጣሚ
ገና እየደወሉ እያለ ስልክዎ ይቋረጣል :

ይህም ሌላ
ምክነያትሊኖረው ይችላል ለምሳሌ የስልክዎ ስክሪን
ችግር ካለበትና ስልክዎ ባጋጣሚ የሚጠፋ
ከሆነ፣የባትሪዎ ችግርም ሊሆን ይችላል

5: በስልክዎ ላይ በጫኑት አፕልኬሽን እየተጠቀሙ እያሉ
ፕሮግራሙ በራሱ ጊዜ ሊዘጋቦ ይችላል

6: እንደ አጠቃላይ ልናየው የምንችለው ደግሞ የስልክዎ
ነገራቶችን በፍጥነት የመከወን ብቃት እጅጉን ይቀንሳል።

ተሰላችተ እስከመወርወር ድረስ ሊያናድድዎም ይችላል።

ስለምለክቶቹ ይህን ያክል ካልን እንዴት መከላከል
እንዳለብንና እንዴትስ ሁነቱ ከተከሰተ በኋላ ማስወገድ
እንደምንችል አንዳንድ ነገራቶችን እንጥቀስ

1፡ ኢንተርኔት እየተጠቀሙ እያለ ከሆነ ክስተቱ የተፈጠረው
ስልክዎን ወዲያውኑ አጥፍተው ያብሩት/ ያስነሱት ይህን
ማድረግዎ ኦንላይን የተለቀቁ ቫይረሶች በስልክዎ ላይ
ለውጥ ማምጣት እንዳይችሉ ይረዳወ ዘንድ ነው።

2:የተጠራጠሩትን ፕሮግራም ከሞባይልዎ ሾርትከት ላይ
ለማጥፋት ይሞክሩ። ይህ አልሆን ካለ

3:ከስልክዎ ውሰጥ setting የሚለውን በተን ተጭነው
app የሚለውን ጠቅ ሲያደርጉ ብዙ ፕሮግራሞች ይታያሉ
ከነኛ መካከልእርስዎ የተጠራጠሩትን ያጥፉት select
and then press uninstall

4: ከ setting ሳይወጡ ወደሆላ በመመለስ security
የሚለውን ይምረጡ።

ከዚክ ጋ device adminstartore
የሚለውን ይጫኑትና በ ቼክ ቦክስ cheekbox ቲክ
የተደረጉትን በሙሉ አጥፍተው ስልክዎን ሪስታርት
ያድርጉት።

ምናልባት ስልክዎ ቫይረስ ከሌለው ይህኛው
አማራጭ በ ቼክ ቦክስ cheekbox ቲክ የተደረጉነ
ፕሮግራሞችን ላያመጣይችላል

5.ስልኮን አጥፍተው የድምፅ መቀነሻው ይጫኑና
እሲከበራ አይልቀቁ በዚህን ጊዜ ስልኮ ሴፍ ሞድ የሚል
ፅሁፍ ያመጣልናል:

ይህ የሚጠቅመን አልጠፋም ያሉ
የቫይረስ አፕሊኬሽኖችን ከሴቲንግ መተግበሪያ ውስጥ
በቀላሉ ለማጥፋት ነው::

@Compu_Te
125 viewsJemal Merim, 20:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 23:11:12 ኤሎን መስክ የትዊተር ግዢያቸውን አጠናቀቁ

ኤሎን መስክ ትዊተር የተሰኘውን የማህበራዊ ትስስር ገጽ በ44 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የመግዛት ሂደትን አጠናቀቁ።

በዓለም ቁጥር አንድ ባለሃብት የሆኑት ኤለን መስክ የትዊተር ግዢ ሒደትን ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ የኩባንያውን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችን ከስራ አሰናብተዋል።

ኤሎን መስክ ጉዳዩን አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸውባሰፈሩት ጽሑፍም “ወፏ ነጻ ወጣች“ በማለት ትዊተርን የግላቸው እንዳደረጉ ጠቁመዋል፡፡

ይሁን እንጂ ኩባንያው የግዢ ሂደቱ መጠናቀቁን አስመልክቶ እስካሁን ያለው ነገር አለመኖሩ ቢቢሲ ዘግቧል።

@Compu_Te
78 viewsJemal Merim, 20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 23:09:29 Python programming language ምንድን ነው?
Python ታዋቂ የፕሮግራም ቋንቋ ነው።
የተፈጠረው በጊዶ ቫን ሮስም ነው፣ እና በ1991 ተለቀቀ።
ይህ open-source programming language በብዛት በሶፍትዌር ኢንጂነሮች ጥቅም ላይ የሚውል ስሆን የ #back-end Web developers በአሁኑ ግዜ ዕይታቸውን ወደ ፖይተን አዙረዋል። Python ለሳይንትፊክ ካልኩለሽን እንድሁም ሰው ሰራሽ ክህሎት artificial intelligent ዋነኛ ነው ። ከሌሎች አንፃር ለመልመድ ቀላል ነው ።
ከዚህም ውጭ እጅግ ብዙ ጥቅሞች ያሉት ፓይተን። ባላችሁበት ቦታ ሆናችሁ አስገራም ኮዶች መፃፍ እስክትችሉ ድረስ ተቃሎ በስልኮች ላይ መቷል።

ጥቅም ላይ የሚውለው ለ:
የድር ልማት(web development)(server side) ፣
የሶፍትዌር ልማት ፣
ለሂሳብ፣
የስርዓት ስክሪፕት.

ፓይቶን በጣም ቀላል ቋንቋ ነው ፣ እና በጣም ቀጥተኛ አገባብ አለው። የፕሮግራም አዘጋጆች ያለ ቦይፕሌት (ዝግጁ) ኮድ ፕሮግራም እንዲያወጡ ያበረታታል። በፓይቶን ውስጥ በጣም ቀላሉ መመሪያ የ “ህትመት” መመሪያ ነው - እሱ በቀላሉ መስመርን ያትማል (እንዲሁም ከ C በተለየ መልኩ አዲስ መስመርን ያጠቃልላል) ፡፡

ፓይቶን ለመማር ቀላል ፣ ኃይለኛ የፕሮግራም ቋንቋ ነው ፡፡ ቀልጣፋ የከፍተኛ ደረጃ የመረጃ አወቃቀሮች እና ለዕቃ-ተኮር መርሃግብር ቀላል ግን ውጤታማ አቀራረብ አለው ፡፡ የፒቶን የሚያምር አገባብ እና ተለዋዋጭ ትየባ ፣ ከተተረጎመው ተፈጥሮው ጋር ፣ በአብዛኛዎቹ መድረኮች ላይ በብዙ አካባቢዎች ለስክሪፕት እና ፈጣን የትግበራ ልማት ተስማሚ ቋንቋ ያደርጉታል ፡፡

ፓይዘን ተተርጉሟል - ፓይተን በአስተርጓሚው በሚሠራበት ጊዜ ይሠራል ፡፡ ፕሮግራምዎን ከመፈፀምዎ በፊት ማጠናቀር አያስፈልግዎትም ፡፡ ይህ ከ PERL እና ከ PHP ጋር ተመሳሳይ ነው።

ፓይቶን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፣ በተፈጥሮ ቋንቋ ትውልድ ፣ በነርቭ ኔትወርኮች እና በሌሎችም በኮምፕዩተር ሳይንስ የላቁ መስኮች በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል ፡፡ ፓይቶን በኮድ ተነባቢነት ላይ ከፍተኛ ትኩረት ነበረው እናም ይህ ክፍል ከመሰረታዊ ነገሮች ፓይቶን ያስተምራዎታል ፡፡ ስለዚህ AI ወይም ጥልቅ ትምህርት መማር መጀመር ከፈለጉ ፡፡ ፒቶን መማር ታላቅ ጅምር ነው!

Python ምን ማድረግ ይችላል?
ፓይተን የድር መተግበሪያዎችን ለመፍጠር በአገልጋይ ላይ መጠቀም ይችላል።
የስራ ፍሰቶችን ለመፍጠር Python ከሶፍትዌር ጋር አብሮ መጠቀም ይችላል።
Python ከመረጃ ቋት ስርዓቶች ጋር መገናኘት ይችላል። እንዲሁም ፋይሎችን ማንበብ እና ማሻሻል ይችላል።
Python ትልቅ መረጃን ለማስተናገድ እና ውስብስብ ሂሳብን ለመስራት ሊያገለግል ይችላል።
Python ለፈጣን ፕሮቶታይፕ፣ ወይም ለምርት ዝግጁ የሆነ ሶፍትዌር ልማት ሊያገለግል ይችላል።

ለምን Python?
ፓይትርን በተለያዩ መድረኮች (Windows፣ Mac፣ Linux፣ Raspberry Pi፣ ወዘተ) ላይ ይሰራል።
Python ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ቀላል አገባብ አለው።
ፓይተን ገንቢዎች ከሌሎች የፕሮግራም አወጣጥ ቋንቋዎች ባነሱ መስመሮች እንዲጽፉ የሚያስችል አገባብ አለው።
ፓይተን የሚሠራው በአስተርጓሚ ስርዓት ነው፣ ይህ ማለት ኮዱ ልክ እንደተጻፈ ሊተገበር ይችላል።
ይህ ማለት ፕሮቶታይፕ በጣም ፈጣን ሊሆን ይችላል.
ፓይትርን በሥርዓት፣ በነገር ተኮር መንገድ ወይም በተግባራዊ መንገድ ሊታከም ይችላል።

ማወቁ ጥሩ ነው
በጣም የቅርብ ጊዜ ዋናው የፓይዘን ስሪት Python 3 ነው፣ እሱም በዚህ አጋዥ ስልጠና ውስጥ የምንጠቀመው።
ሆኖም፣ Python 2፣ ምንም እንኳን ከደህንነት ዝመናዎች በስተቀር በሌላ ነገር ባይዘመንም አሁንም በጣም ተወዳጅ ነው።
በዚህ ማጠናከሪያ ትምህርት Python በጽሑፍ አርታኢ ውስጥ ይጻፋል።
እንደ ቶኒ፣ ፒቻርም፣ ኔትቤንስ ወይም ግርዶሽ ባሉ የተቀናጀ ልማት አካባቢ ፓይተንን መፃፍ ይቻላል በተለይ ትላልቅ የፓይተን ፋይሎችን ሲያቀናብሩ ጠቃሚ ናቸው።

ምሳሌ print("Hello, World!")
@Compu_Te
81 viewsJemal Merim, 20:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-28 22:20:36 እውነተኛውን የብር ኖት ከሀሰተኛውን እንዴት መለየት ይችላሉ ?

• የገንዘቡ ቁጥሮች በሚያጎላ ማሽን ሲታዩ ከጥቁር ወደ አረንጓዴ ፍሎረሰንት ቀለም ይለወጣሉ፡፡

• የብሩን ዋጋ የሚገልጽ፤ ማየት የተሳናቸው በእጅ ዳሰሳ ማወቅ የሚችሉበት የደህንነት መጠበቂያ አለው፡፡

• የብር ኖቱ ሲዳሰስ የመጎርበጥ ስሜት አለው፡፡

• ገንዘቡ ወደላይ ወይም ወደታች ሲዞር የሚንቀሳቀስ ደማቅ የቀለም ፍንጣቂ ይታያል፡፡

• የሚሽከረከር ደማቅ ቀለም ኮከብ አዲስ የደህንነት መጠበቂያ ክር፤ በክሩ ውስጥ NBE፣ ኢብባ እና የገንዘብ አይነት ተጽፎ ይገኛል፡፡

• ገንዘቡ ወደ ብርሃን አቅጣጫ ተደርጎ ሲታይ በላዩ ላይ ከሚገኘው ምስል ፊት ለፊት ተመሳሳይ ደብዛዛ የውሃ መልክ ያለው ምልክት ይታያል፡፡

• የብር ኖቶች ከብርሃን አቅጣጫ ሲታዩ ኳስ መሳይ ምልክት ከገንዘቡ በስተኋላ ካለው ተመሳሳይ ምልክት ጋር በፍጹም ትይዩ ሆነው በአንድ ላይ ያርፋሉ፡፡

https://t.me/Compu_Te
593 viewsJemal Ali, 19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-28 22:01:44 ሰላም ውድ  ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ በዛሬው ፕሮግራማችን ስለ ላፕቶፖቻችን እናያለን

ላፕቶፕ ከ ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ጋር ተመሳሳይ ሲሆኑ ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮችን ከ ቦታ ቦታ ይዘናቸው እየተንቀሳቀስን መጠቀም አንችልም ይህን ስል ተንቀሳቃሽ አይደሉም እያልኩ ሳይሆን በቀላሉ ይዘናቸው አንንቀሳቀስም ለማለት ነው ላፕቶፖችን ግን በቀላሉ በቦርሳዎችም ይሁን በጃችን ይዘን መንቀሳቀስ እንችላለን እንዲሁም በትንሽ ቦታ ላይ አስቀምጠን መጠቀም እንችላለን እንዲሁም እንደ ሞባይል ስልኮቻችን ቻርጅ እያደረግን ስለሆነ ምንጠቀመው የመብራት መቆራረጥ ስራችንን አስቸጋሪ አያደርገውም ማለት ነው ስለ ላፕቶፕ ብዙ ማለት ይቻላል ግን እዚህ ላይ ይብቃንን ስለ አጠቃቀማችን እና ጥንቃቄ አወሳሰዳችን እንይ

ላፕቶፖች ለመያዝ እና ለማንቀሳቀስ ቀላል ስለሆኑ አብዛኛዎቻችን በ እግራችን ላይ አስቀምጠን እንጠቀማለን ነገር ግን በእግራችላ ይ ማስቀመጥና መጠቀም እንደሌለብን ጥናቶች ያሳያሉ ላፕቶፖቾ ስራ በሚሰሩ ሰአት ሙቀት ይፈጠራል ያ ሙቀት እየበዛ በሚሄድ ሰአት ከሙቀቱ ጋር አብሮ የተለያዩ ጨረሮች ይለቀቃሉ ይህም በእግራችን ላይ ጉዳት ያደርሳል ነገሩ እየተደጋገመ ሲመጣ ደግሞ ለከፋ ጉዳት ይዳርገናል በተለይ ነብሰጡሮች በፅንሱ ላይ ከፍ ያለ ጉዳት ስለሚያደርስ ጥንቃቄ መውሰድ አስፈላጊ ነው፡፡
ስለሆነም ላፕቶፖችን ስንጠቀም ከሆዳችን 30cm ራቅ አርገን በጠረጴዛ ላይ አስቀምጠን እንድንጠቀም ይመከራል፡፡

ሌላው ደግሞ የባትሪያችንን እድሜ ማስረዘም ሲሆን የላፕቶፕ ባትሪዎች ከ 60 _ 70% ቻርጅ ከተደረጉ በቂ ነው በተለይ 99 98% ሲሉ ብንነቅላቸው እና ሲጨርሱ 1% እንደዚህ ሲቀራቸው ብንሰካቸው ይህን ሬንጅ በመጠበቅ ቻርጅ ብናረግ እድሜያቸውን ማስረዘም እንችላለን ማለት ነው፡፡

እንዲሁም ላፕቶፖችን በጨለማ ወይም በቂ ብርሀን በሌለበት ቦታ አለመጠቀም ከ ላፕቶፑ ብርሀን ጋር ተመጣጣኝ ብርሀን ያለበት ቦታ መጠቀም አይናችንን ከህመም መጠበቅ እንችላለን፡፡

ላፕቶፓችን አየር እንዲያገኝ ማድረግ እና አካባቢውን ሙቀት እንዳይበዛበት ለማድረግ መሞከር ፀሀይ ላይ አለመጠቀም በአካባቢው መፅሀፍት ምግቦች መጠጣች ወዘተ አለመደርደር ስስ የሆኑ ነገሮች ላይ አለማስቀመጥ ማለት ለምሳሌ አልጋ ላይ አርገን ይህም የላፕቶፑን አየር ማስገቢያውን ቀዳዳዎች ስለሚያፍኑት ለላፕቶፑ ጤንነት ጥሩ አይደለም፡፡

፡የላፕቶፑን ንፅህና መጠበቅ እና ማፅዳት ቢያንስ በቀላሉ ከላይ ያሉ አቧራዎችን ወዘተ ንፁህ በሆነ ጨርቅ ማፅዳት ከማፅዳታችን በፊት ላፕቶፑን ማጥፋታችንን አለመዘንጋት ከዚህ ባለፈ የላፕቶፑ ኪይቦርድ በምናፀዳበት ወይት በቀላሉ መነቀልና መሰካት ስለሚችል ነቅለን ማፅዳት፡፡ እንዲሁም የ ላፕቶፑ ፋን አየር ለማስገባት በሚስብብት ወቅት የተለያዩ አቧራዎች አብረው ይገባሉ ይህነንን ለማፅዳት ላፕቶተፑን በደንብ እምናውቀውና ፈተን የመግጠም ችሎታው ካለን ፈተን ማፅዳት እንችላለን ካልሆነ ደግሞ በላፕቶፑ አየር ማስገቢያ ቀዳዳዎች ውስጥ ከፍ ያለ አየር በማስገባት ማፅዳት እንችላለን ማለት ነው ፡፡ ያው ላፕቶፕ የራሱ ማፅጃ ያለው ቢሆንም መግዛት ካልቻልን በተቻለ መጠን በንፁህ ስስ ጨርቅ በጥንቃቄ ማፅዳት ተገቢ ነው፡፡ ከብዙ በጥቂቱ ለላፕቶፖቻችን መውሰድ ካሉብን ጥንቃቄዎች ውስጥ የተወሰኑት እነዚህ ናቸው፡፡

@Compu_Te
70 viewsJemal Ali, edited  19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-21 14:31:32
https://t.me/Compu_Te
561 viewsMirim Merim, 11:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ