Get Mystery Box with random crypto!

ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅና ማየት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች 1 የመሳሪያ ስርዓት (Operating syste | Information Science and Technology

ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅና ማየት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች
1 የመሳሪያ ስርዓት (Operating system)
2 የስክሪን መጠን (Screen Size)
3 ሲፒዩ(CPU)
4 ራም(RAM)
5 የሃርድ ድራይቭ አይነት (Hard Drive Type)
6 የምስል ጥራት (Image Quality)
7 የባትሪ ቆይታ (Battery Life)
8 ብራንድ (Brand)
ኮርi3 ፣ ኮርi5፣ ኮርi7 ምንድናቸው?
በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን በርከት ያሉ የላፕቶፕ እና የኮምፒውተር ሱቆች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ለገቢያም የተለያዩ የላፕቶፕ አይነቶች.በተለያየ ይዘት ይገኛሉ፡፡ እንዚህን
የተለያየ ይዘት ያላቸውን የላፕቶፕ አይነቶች ለመግዛት በዋናነት መታየት ያለበትን ከዚህ በታች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡
1. የመሳሪያ ስርዓት (platform) Windows, Mac and Linux ለአጠቃቀም ምቹ እንደሆነ የሚነገርለት Windows የብዙ ሰዎች ምርጫ ነው፡፡ ቀላል፣ ምቹ እና ተለዋዋጭ ነው፤ በዋጋም ደረጃ ጥሩ የሚባል ነው፡፡
ማክ( Mac) የአፕል ድርጅት ምርት ሲሆን ለዲዛይን ተመራጭ የሆነ ፕላትፎረም ነው፡፡ለደህንነትም ከWindows እንደሚሻል ይነገርለታል፡፡
2. የስክሪን መጠን
ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ ወደ ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደየስክሪን መጠናቸው የተከፋፈሉ ናቸው፡፡
• 11 to 12 inches(27.94cm-30.48cm) ፡በጣም ቀጭን እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡፡ ከ1.1ኪሎ እስከ1.5ኪሎ ይመዝናል፡፡
• 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ የስክርን ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability
ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
• 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን ሳይዝ ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ እንመክራለን ፡፡
• 17 to 18 inches (43.18cm- 45.72cm)፡ ላፕቶፖን ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ትልቅ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ
ይህንን ይግዙ፡፡ ለጌመሮች እና ትልልቅ የሶፈተዌር ዲዛይን ለሚያደርጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ የላፕቶፕ አይነት ነው፡፡
3. ሲፒዩ(CPU)
የኮምፒዉተር አይምሮ በመባል የሚታወቀው ሲፒዩ(CPU), ላፕቶፕ ለመግዛት ሁላችንም ማየት ያለብን ዝርዝር ነው፡፡
• AMD A series or Intel Core i3 / i5: በየቀኑ ለምንጠቀማቸው ስራዎች የሚሆኑ የሲፒዩ አይነቶች ሲሆኑ Core i5 ለሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት እና አነስተኛ የዲዛይን ስራዎችን
ለምሳሌ እንደ Photoshop, Archicad, AutoCadን የመሳሰሉ በጥሩ ሁኔታ እንድንሰራ ይጠቅሙናል፡፡ በተጨማሪም ግራፊክስ ካርድ ያለውና የሌለው በማለትም ይለያያሉ፡፡
ግራፊክስ ካርድ ያለቸው የተሻለ የዲዛይን እና አኒሜሽን ስራዎችን ያከናውኑልናል፡፡ በዋጋውም ተመጣጣኝ ነው፡፡
• Intel Core i7፡ በጣም አስደማሚ የጌም እና የዲዛይን እንዲሁም ልዩ የሆኑ የኮምፒውተር ስራችን ለምሳሌ አንደ ሜትሮሎጂ፤ ውስብስብ ስሌቶችን እንድንሰራ የሚረዳን የላፐቶፕ አይነት ነው፡፡
4 .ራም(RAM): ለፍጥነት 4ጂቢ እና ከዛ በላይ የሆነ RAM እንዲጠቀሙ እንመክሮታለን፡፡ ዋጋቸው አነስ ያሉ ላፕቶፖች
በ2ጂቢ ይመጣሉ፡፡ የዲዛይን ስራዎችን እና የሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት ስራዎችን ለመስራት 6ጂቢ ራም እና ከዚያ በላይ ያለው ላፕቶፕ ቢገዙ ይመረጣል፡፡
5.የሃርድ ድራይቭ አይነት፡ ሁለት አይነት የሃርድ ድራይቭ አይነቶች አሉ( HDDrive እና SSDrive)
ለሌሎች
#like
#share

ለተሻለ ዕውቀት፣ችግር ፈቺ፣ ወጪ ቆጣቢ እና የተለያዩ መረጃዎችን ከዚህ በፊት ዩትብ ላይ ከለቀቅናቸው ቪድዪዎች ብዙ ነገር ማግኘት ትችላላችሁ።
▬▬ Share ▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም ዩቲዩብ ቻናላችንን በመቀላቀል በምስል እና በቭድዮ የተዘጋጁ ከስራ እና ከቴክኖሎጂ ጋር ይተዋወቁ Subscribe በማድርግ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q