Get Mystery Box with random crypto!

#ፍላሽ_ዲስክ_እንዴት_በፓስዎርድ_ማሰር_ይቻላል? በፍላሽ ዲስክ የተለያዪ ሚስጥራዊ ዳታዎች እንይዛለ | Information Science and Technology

#ፍላሽ_ዲስክ_እንዴት_በፓስዎርድ_ማሰር_ይቻላል?
በፍላሽ ዲስክ የተለያዪ ሚስጥራዊ ዳታዎች እንይዛለን! ከራሳችሁ ውጪ ሌላ ማንም ሰው እንዳያየው የምትፈልጉት ዳታ(ፋይል፣ቪድዮ፣ፎቶዎች ወዘተ) በፍላሽ ዲስክ ትይዛላችሁ።
ስለዚህ ሚስጥራዊ ዳታችሁን ከናንተ ውጪ ማንም ሰው እንዳያየው ወይም እንዳይጠቀምበት የግድ ፍላሽ ዲስኩን በፓስወርድ መቆለፍ ይኖርባችኋል።
እሺ windows 10 የምትጠቀሙ ሰዎች ፍላሽ ዲስካችሁን በፖስወርድ ለመቆለፍ የሚከተሉትን ስቴፖች በመከተል መቆለፍ ትችላላችሁ።
1-ፍላሽ ዲስኩን ኮምፒውተራችሁ ላይ ሰኩት እና"This PC" የሚለው አይከን ደብል ክሊክ አድርጉት
2- "This PC" የሚለው አይከን ደብል ክሊክ ስታደርጉት የሚመጣው ቦክስ ውስጥ ፍላሽ ዲስካችሁ ይመጣል
3- ፍላሽ ዲስኩን "right click" አድርጉ
4- ፍላሽ ዲስኩን "right click" አ.ስታደርጉ "Turn BitLocker on" የሚለውን ሴሌክት ማድረግ
5- ከዚያ ፓስወርድ አስገቡ ይላችኋል፣ የማትረሱት ፓስወርድ አስገቡና "next" በሉት
6- ከዚያ "Encrypt entire drive" የሚለውን ሴሌክት በማድረግ "next" ማለት። በቃ አለቀ።ፍላሽ ዲስኩ በፓስውርድ ተቆለፈ።
ከዚህ በኋላ ያለ እናንት ሌላ ማንም ሰው ፍላሹን መጠቀም አይችልም።
ፍላሽ ዲስኩን መጠቀም ስትፈልጉ ኮምፒውተራችሁ ላይ ፍላሹን ደብል ክሊክ ስታደርጉ ፓስወርድ አስገቡ ይላችኋል።ፓስወርድ በማስገባት መጠቀም ትችላላችሁ ::
subscribe to our loved ones and respected followers on Youtube, because we open new youtube channel.
የ"youtube" ቻናላችንን Subscribe አድርጉ።
Subscribe ያላደረገ video ሊደርሰው ወይም መከታተል አይችልም። click z link below to subscribe

https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q