Get Mystery Box with random crypto!

ስልኬ ስታክ እያረገ አስቸገረኝ መፍትሄዉ ምንድነዉ? ----------------------------- | Information Science and Technology

ስልኬ ስታክ እያረገ አስቸገረኝ መፍትሄዉ ምንድነዉ?
-------------------------------------------------
ስልክዎ ስታክ እያደረገ ካስቸገሮት መነሻ ምክንያቱንና መፍትሄዉን እንደሚከተለዉ አቅርበናል፡፡
--------------------------------------------------------------------------------

ስልኮ ከተለመደዉ በላይ ይዘገያል ወይስ እንዲያ ከናካቴዉ አልሰራም ብሎ ቀጥ ብሎ ይቆማል፡፡ እንግዲህ ስልኮ በጣሙን የሚዘገይ አልያም አልታዘዝ ካሎት ስልኮ የሆነ ችግር ገጥሞታል ማለት ሲሆን ለዚህ አይነት ችግር መንስዔ የሚሆኑ መነሾዎችን ከነመፍትሄዎቻቸዉ ጋር እንደሚከተሉት አቅርበንሎታልና ይተግብሯቸዉ፡፡
 ከስልኮ ላይ የአላስፈላጊ አፕሊኬሽኖች መኖር
ከስልኮ ላይ አላስፈላጊ አፕሊኬሽኖችን ያጥፉ፡፡ ስልኮ ላይ ብዙ አላስፈላጊ አፕሊኬሽኖች ለምሳሌ ጌሞች ፣ የፎቶ እና ቪዲዮ ማሳመሪያ(ኤዲትኢንግ) ሶፍትዌሮች የተለያዩ የሙዚቃም ይሁን የቪዲዮ ማጫወቻ(ፕሌየሮች) ስልኮ ላይ ካለ በተቻለ መጠን የሚፈልጉትን አፕሊኬሽን ሶፍሮች ብቻ ትተዉ ሌላዉን በአብዛኛዉ የማይጠቀሙባቸዉን አፕሊኬሽኖች ያጥፉ፡፡

 የስልኮ ዳታ መያዣ(ስቶሬጅ) በፋይሎች መጨናነቅ
በስልኮ ሜሞሪ ላይ ብዛት ያላቸዉ ሙዚቃዎች፣ ቪዲዮች፣ያልጫኑት ሶፍትዌር አፕሊኬሽኖች አስቀምጠዉ ከሆነ በተቻለ መጠን የማይፈልጉትን ቢያጠፉ አልያም ከቆይታ በኋላ ብፈልጋቸዉ አላገኛቸዉም ካሉ በሌላ ተንቀሳቃሽ የመረጃ ቐት(ሜሞሪ) ያስቀምጡት፡፡

 የስልኮን ኦፕሬቲንግ ሲስተም እና ስልክዎ ላይ ያለን ሶፍትዌር አለማደስ
ስልኮ ያሉትን ሶፍተዌሮች እና ስልኮን ያለማደስ ስልኮን ለሌላ ቫይረስ አልያም ጎጂ ሶፍትዌር ያጋልጣል ይህም የስልኮን ፐሮግራሞች ሳይዘጉ ከኋላ እንዲነሳ(background play) ስለሚያደርገዉ ስልኮንና የሚጠቀሙበትን ሶፍትዌር ያደሱት፡፡

 ካች (Cache) ዳታን አለማፅዳት
ካች ዳታ የምንላዉ አብዛኛዉን ጊዜ የምንጠቀምባቸዉን ሶፍትዌሮችና ፋይሎች ስልካችን የሚያስቀምጥበት ቦታ ሲሆን ስልካችንን መረጃን በማመላለስ (loading data) ጊዜን እና ቦታ ተጣቦ ከመዘግየትና ከመቆም ያደናል ስለዚህ የስላካችንን ከች ማፀዳት ተቃሚ ያደርገናል፡፡

 Widgets መጠቀምን ማብዛት
አንድሮይድ ስልኮች ከሚሰጡን የተለየ ጥቅም አንዱ ዊጄትስ ቢሆንም ያን ያህልም የሚሰሩትን ካልገደብን ስልካችንን በማጨናነቅና እንዲቆም (ስታክ) እንዲያደርግ በማድረግ ረገድም ከፍ ያለ ድርሻ ያላቸዉ በመሆናቸዉ ዊጄትስን በመቀነስ ካልሆነም በማጥፋት ስልኮ በየጊዜዉ መቆሙን አላያም መንቀራፈፉን ማስቆም አማራጭ ነዉ፡፡

 ፋብሪካዉ ሲያመርተዉ ወደነበረበት ማሰተካከያ መመለስ(reset factory setting)
የስልኮ ማርጀት አልያም ለብዙ ጊዜያት መጠቀም ስልኮን እንዲቀራፈፍ አልያም በየማሃሉ እንዲቆም ለመሆኑ ምክንያት ላይሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ የማስተካከያ(ሴቲንግ) ለዉጦች ወይም አቅጣጫ መጠቆምያ ጂፒስ ኦን ማድረግ(ማብራት) ለስልኮ መንቀራፈፍ ምክንያት ሊሆኑ ስለሚችሉ የስልኮ በመሃል በመሃል መቆም(ስታክ) ሲያጋጥሙ ስልኩ ሲዘጋጅ ወደነበረበት መመለስ (reset factory setting) ችግሩን ሊቀርፍ ይችላል፡፡

 ዎልፔፐር (Wallpaper) መጠቀም
ስልኮ ለዓይን እንዲስብ አልያም በአንድ አንድ አቋራጭ ቴክኒኮች ምክንያት ስልኮ ላይ ላይቭ ዎልፔፐር (Live Wallpaper) መጠቀም አንዱ የአንድሮይድ ስልኮች ገፀ-በረከት ቢሆንም ለስልኮ መዘግየትም ይሁን መቆም(ስታክ ማድረግ) ምክንያት ሊሆን ስለሚችል ማጥፋቱ መንቀራፈፉን አልያም ሰታክ ማድረጉን ሊያስቆም ይችላልና ይሞክሩት፡፡

 ስልኮ አቧራ ከሞላዉ
የሚሰሩበት ቦታ አልያም የሚዉልበት አከባቢ አቧራማ ከሆነ ስልኮን ማፅዳትና ከተፀዳም በኋላ መልሶ በአቧራ እንዳይሞላ መከላከያ መጠቀም፡፡

ከተጠቀሱት አማራጮች ዉስጥ አንዱን ብቻ መርጦ በመተግበር ሳይሆን ሁሉንም አልያም አብዛዛኛዉን መፍቴዎች በአንድ ላይ በመተግበር ዉጤት ስለሚያስገኝ ከመፍቴዎች ዉስጥ በመምረጥ ሳይሆን ከቻሉ ሁሉንም መፍትሄዎች ስልኮ ላይ መተግበር ካልሆነም የተቻሉትን መከወን እንደመፍተሄ ይሆናል፡፡


ሌሎች መሰል ጥያቄዎች ካሎት በፌስቡክ ፔጃችን ኮመንት ያርጉልን አልያም ኢንቦክስ ያርጉልን፡፡ እርስዎን በመርዳትዎ ደስታ ይሰማናል፡፡

ይህን ፖስት ከወደዱት Like & Share