Get Mystery Box with random crypto!

5G ቴክኖሎጂ እንዴት ይሰራል? ******* የ 5G ቴክኖሎጂ የ አምስተኛው ትውልድ የሞባይል ቴክኖ | Information Science and Technology

5G ቴክኖሎጂ እንዴት ይሰራል? *******
የ 5G ቴክኖሎጂ የ አምስተኛው ትውልድ የሞባይል ቴክኖሎጂ ሲሆን የዲጂታል ዓለሙ የሚፈልገውን ፈጣን ግንኙነት ለመፍጠር ትልቅ እርምጃ ያራመደ ቴክኖሎጂ ተደርጎም ይወሰዳል። የ 5G ቴክኖሎጂ የመረጃ መለዋወጫ ፍጥነትን አሁን ካለው የ4G ቴክኖሎጂ ከ10 እስከ 100 የተሻለ እጥፍ እንደሚልቅ ይገምታል። ይህም ማለት የሞባይል ኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን እስከዛሬ ከነበረው የm/s ፍጥነት ወደ g/s ያሳድገዋል ማለት ነው።
ኒዮርክ በሚገኘው የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ሃሪሽ ክሪሺናስዋሚ እንዳሉት “ የ 5G ቴክኖሎጂ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም አሁን ባለው የኔትዎርክ ፍጥነት መተግበር ያልቻልናቸውን ከፊተኛ የሆነ የኔትዎርክ አቅምን የሚጠይቁ መተግበሪያዎችን እንድንጠቀም ያስችለናል ለምሳሌ በ ጊጋ ባይት ደረጃ ያሉ ተንቀሳቃሽ መስሎችን በሰከንድ ከኢንተርኔት ማውረድ ያስችለናል እንድሁም እንደ ቨርችዋል ሪያሊቲ መተግበሪያና ሰው አልባ መኪኖችን ላይ ለፈጣን የመረጃ ዝውውር መጠቀም ያስችለናል”። በተጨማሪም ዘመኑ እየፈጠራቸው ያሉ ቴክኖሎጂዎች ማለትም እንደ አጉመንትድ ሪያሊቲ እና ሰው አልባ መኪኖች ከፍተኛ የሆነ የመረጃ ልውውጥ ፍጥነትን ይሻሉ ስለሆነም የ5G ቴክኖሎጂ የመረጃ የመዘግየት ሂደንት ወደ 1 ሚሊ ሴኮንድ ዝቅ ማድረን አላማ አድርጎ ተነስቷል ይህ ማለት ተንቀሳቃች መሳሪያዎች መረጃን የ1 ሴኮንድ 1/1000 ባነሰ መለዋወጥ ያስችላቸዋል።
ባለፉት ትውልዶች ቴክኖሎጂዎች የሚጠቀሙት የኤሌክትሮማግኔቲክ ጨረርን እንደ ሬድዮ ሞገድ ባሉ ቴክኖሎጂዎች በመሆኑ የእነዚህ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ በከፍተኛ ሁኔታ የኔትዎርክ መጨናነቅን ይፈጠርበታል፡፡ ስለሆነም ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከፍተኛ የሆነ የራድዮ ሞገድ ከመጠየቁም በላይ በ ሴንቲሜትር የሚለካውን ወደ ሚሊሜትር ሞገድ ዝቅ ማድረግ አስፈልጓል። እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ቀድመን ከምናውቀው ትልልቅ የሆኑ የኔትዎርክ ምሰሶዎች በላይ በማይፈልጉ የህንጻዎች አናት እና በመብራት አስተላላፊ ምሰሶዎች ላይ ሊገጠሙ የሚችሉ በመሆኑ ቴክኖሎጂዎቹ አዲስ የግንኙነት መንገድ የክፈቱ አስብሏቸዋል። ነገር ግን እነዚህ የሞገድ አይነቶች ሌሎች ተግዳሮቶች አጋጥሟቸዋል ከነዚህም መካከል ሞገዶቹ በዛፎችና በህንጻዎች ከመዋጥ አልዳኑም። ነገር ግን እነዚህ በመጠናቸው አንስተኛ የሆኑ የኔትዎክ አስተላላፊዎች ለአዳዲስ የምርምር ስራዎች መፈጠር ጉልህ አስተዋጾ ነበራቸው። የ አምስተኛው ትውልድ ኔትዎርክ የመፈጠር ምክንያትም ናቸው። የአምስተኛው ትውልድ ኔትዎርክ (5G) ቀድሞ በነበሩት የኔትዎርክ አስተላላፊዎች ላይ ቁጥራቸው በርከት ያሉ በመጠን አነስተኛ የሆኑ አንቴናዎችን በመጨመር እንዲሁም የማስተላለፍ አቅማቸውን በማሳደግ ከፍተኛ የሆነ የመረጃ መላላኪያ ፍጥነትን በመጨመር የተፈጠረ ሲሆን የመረጃ መዘግየትን በእጅጉ ቀንሷል። እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ከዚህ በተጨማሪም በፊት ከነበሩት የኔትዎርክ አስተላላፊዎች ያነሰ የኤሌክትሪክ ሃይል መጠቀማቸውም ልዩ ያደርጋቸዋል።
▬▬ Share ▬▬▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
▬▬ Share ▬▬▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe በማድርጉ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q