2022-07-07 20:34:31
ፍየል አርቢው ሞሃመድ ሃሰን ናሬጆ ረጅም ጆሮ ያላትንና ሲምባ በመባል የምትታወቀውን ፍየሉን በኩራት ያሳያል። ፍየሏ ሲምባ በፓኪስታን ሚዲያዎች ከፍተኛ ትኩረትን ስባለች።
በካራቺ ትኩረትና ፍቅርን እያገኘ የሚኖረው ሲምባ ባለፈው ወር ሲወለድ ከተለመደው በላይ ረጅም ከሆነ ጆሮ ጋር ነበር። አሁን ጆሮው 54 ሴንቲሜትር ይለካል።
አርቢው ሞሃመድ ናሬጆ እንደሚለው ጊነስ ዎርልድ ሬከርድስ የተባለውና የተለዩና አስገራሚ ክስተቶችን የሚመዘግበው ድርጅት ሲምባን እንዲሚዘግብለት ጠይቋል። የድርጅቱ ድህረ ገጽ “ረጅም የፍየል ጆሮ” የሚል የመወዳደሪያ መደብ ለጊዜው አያሳይም።
“በተወለደ 10 እና 12 ቀናት ውስጥ በሃገሪቱና በዓለም አቀፍ መገናኛ ትኰረት ሲያገኝ የቁንጅና ውድድርም አሸንፏል” ይላል ናሬጆ በኩራት።
“ሌሎች ሰዎች ከ25 እስከ 30 ዓመት ሊወስድባቸው የሚችል ታዋቂነትን ሲምባ በ 30 ቀናት ውስጥ አግኝቷል” ሲል ያክላል ናሬጆ።
የሲምባ ጆሮ በጣም ረጅም ስለሆነ ናሬጆ አጥፎ ከኋላው ያደርገዋል። ይህም ሲምባ በእግሩ በቆመበት ቁጥር ሲያመው የሚያለቅሰውን ለቅሶ አስቁሟል።
ሲምባ አንገቱ ላይ በታሰረው ገመድ ረጅሞቹን ጆሮዎች እንዲሸከም ናጄሮ መላ ዘይዷል።ኤኤፍፒ ፣ ቪኦኤ)
______
የሁሌ አዲስ ሚዲያ ፈጣን መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፤
Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media?
156 viewsEyasu zekariyas1, 17:34