Get Mystery Box with random crypto!

የፊንላንድ መንግስት በአማራ ክልል በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚውል ከ10 ነጥ | ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)

የፊንላንድ መንግስት በአማራ ክልል በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚውል ከ10 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳር ሚስ ኦቲ ሆሎፓይነን ድጋፉን ዛሬ ባስረከቡበት ወቅት እንዳስታወቁት፤ መንግስታቸው ከኢትዮጵያ ጋር ለዘመናት የዘለቀ የልማት  ትብብር በመመስረት እየሰራ ነው።

በግብርና፣ በትምህርትና ሌሎች የልማት ሥራዎች እንዲሁም በሴቶችና የአካል ጉዳት ያለባቸው ዜጎችን  እየደገፈ መሆኑንም ገልጸዋል።

ዛሬ ደግሞ በጦርነቱ ወቅት በአማራ ክልል  ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባትና ለማቋቋም የሚያስችል ከ10 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማምጣታቸውን አስታውቀዋል።

የገንዘብ ድጋፉ ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችና የማህበራዊ ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም እንደሚውልም አመልክተዋል።

የሁሌ አዲስ ሚዲያ ፈጣን መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፤
Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media?