Get Mystery Box with random crypto!

ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)

የቴሌግራም ቻናል አርማ hulaadiss — ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)
የቴሌግራም ቻናል አርማ hulaadiss — ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)
የሰርጥ አድራሻ: @hulaadiss
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.80K
የሰርጥ መግለጫ

ትክክለኛዉ የሁሌ አዲስ ሚዲያ ገፆች
Facebook : bit.ly/42rUuKj
Telegram: bit.ly/3NBQbro
YouTube : bit.ly/3p7kj3N
Twitter : bit.ly/3NVMRrB
Website : bit.ly/3ntuxuZ
ለጥቆማ ና አስተያየት እንዲሁም ለማስታወቂያ ስራ ተከታዮን አድራሻ ይጠቀሙ
bit.ly/3VMy7x7 ወይም 251939758767

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 22:02:25 በአዲስ አበባ ከተማ አንዲት የቤት ሠራተኛ ሁለት ህጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደለች በኋላ በቁጥጥር ሥር መዋሏን ፖሊስ አስታወቀ።

በሕጻናቱ ላይ የተፈጸመው ይህ የግድያ ወንጀል ያጋጠመው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አራብሳ ኮንዶሚንየም ተብሎ በሚጠራው የጋራ መኖሪያ ቤት መንደር መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።

የግድያ ወንጀል ድርጊት የተፈጸመባቸው ሁለቱ ህጻናት የሁለት እና የሦስት ዓመት እድሜ ያላቸው ወንድ እና ሴት ወንድም እና አህት ናቸው።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቢቢሲ እንደተናገሩት “እጅግ በጣም አሳዛኝ እና ዘግናኝ” በተባለው በዚህ ወንጀል የተጠረጠረችው የቤት ሠራተኛ የ19 ዓመት ወጣት መሆኗን ገልጸዋል።

ኮማንደር ማርቆስ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 26/2014 ዓ.ም. ከረፋዱ ከ3፡30 እስከ 4 ሰዓት መሆኑን ገልጸው፤ ተጠርጣሪዋ ህጻናቱን አንቃ እና ስለት ተጠቅማ በአስቃቂ ሁኔታ መግድሏ የሚያመላክቱ መላምቶች አሉ ብለዋል።

የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን ለመፈጸም ምን እንዳነሳሳት ወይም የአእምሮ ጤና ችግር እንዳለበት ለማወቅ ምርመራዎች እየተካሄዱ ነው ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነዉ።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media
147 viewsEyasu Zekarias1, 19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 16:25:08
በቅርቡ ተመቶ ሰለወደቀው አዉሮፕላን የተነገረው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ

ከሰሞኑ ለህወሓት የጦር መሳሪያ ሊያቀርብ ሲል በኢትዮጵያ አየር ኃይል ተመትቶ ስለወደቀው የጦር አውሮፕላን በሱዳን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አምባሳደር የሆኑት ይበልጣል እምሮ ለጋዜጠኞች በሰጡት ምለሽ “አውሮፕላኑ ተመትቶ መውደቁ አረጋገጡ እንጂ የየትኛውንም ሀገር ስም ከአውሮፕላኑ መውደቅ ጋር አያይዘው አልጠቀሱም” ሲል ኤምባሲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ማብራሪያ ሰጥቷል።

ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ቦታ ትሰጣለች ያለው ኤምባሲው፤ ሆኖም ግን አንድ አንድ የመገናኛ ብዙሃን አምባሳደሩ የተናገሩትን ከአውድ ውጪ በተዛባ መልኩ መጠቀማቸው እንዳሳዘነው ጠቅሶ ሁለቱ እህትማማች ሀገሮች ግንነኙነታቸውን በየደረጃው ለማጠናከር ተቀራርበው እየሰሩ መሆኑን ኤምባሲው አስታውቋል።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media
384 viewsEyasu Zekarias1, edited  13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 16:24:47
የትግራይ ኃይሎች ከአማራ ክልል እንዲወጡ የብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጠየቁ

የትግራይ ኃይሎች በአማራ ክልል የጀመሩትን ውጊያ አቁመው ወደ ትግራይ ክልል እንዲመለሱና በትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ኃይሎችም ክልሉን ለቀቅው እንዲወጡ የብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ ጠይቀዋል።

ቪኪ ፎርድ ይህን ያሉት ህወሓትና የኢትዮጵያ መንግስት ዳግም ወደ ግጭት መመለሳቸውን ተከትሎ ዛሬ ሐሙስ ባወጡት መግለጫ ነው። በሁለቱ ኃይሎች እንደገና ወደ ግጭት መግባባት በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸውን የማጣት አደጋ እንደተጋረጠባቸው ሚኒስትሯ ገልጸዋል።(Ethiopian Insider)

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media
325 viewsEyasu Zekarias1, edited  13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 16:24:09
ቦሌ አራብሳ ኮንዶሚንየም ውስጥ አሳዛኝ ነገር ተከሰተ

በአዲስ አበባ ቦሌ አራብሳ ብሎክ 51 ላይ ሁለት ህፃናት በአንዲት ሰራተኛ ታርደው ተገኝተዋል። ህፃናቱ ወንድምና እህት ሲሆኑ ሰራተኛዋ አንዷን አርዳ፤ አንዱን በማነቅ የሁለቱም ህፃናት ህይወታቸው አልፏል። አሁን ላይ ሰራተኛዋ ለፖሊስ እጇን መስጠቷን ከ ጉርሻን ፔጅ ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል።

ወላድ ከስራ ስትመጣ ልጆቿ
ታርደዉ ነዉ ያገኘችዉ

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media
323 viewsEyasu Zekarias1, 13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 14:15:42
ህወሓት የኤርትራ መንግስት ጥቃት ከፍቶብኛል ሲል ከሰሰ

የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ የኤርትራው መሪ "ኢሳያስ አፈወርቂ ሀይሎች" ከኢትዮጵያ ጦር ጋር በመሆን በአራት አቅጣጫ በምእራብ በኩል በአድያቦ ጥቃት መክፈታቸውን በትዊተር ገጻቸው ጽፈዋል።

በተለያየ አቅጣጫ ጥቃት እንደተከፈተባቸው የገለጹት ቃል አቀባዩ ጥቃቱን እየመከቱት መሆኑን ገልጸዋል።

ኤርትራ በህወሓት ክስ ላይ እስካሁን በይፋ ያለችው ነገር የለም።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media
361 viewsEyasu Zekarias1, edited  11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 14:10:37
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሐረሪ ክልል መጠነ-ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ መጀመሩን አስታወቀ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መጠነ-ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በሐረሪ ክልል መጀመሩን በዛሬው ዕለት አሳውቋል።ይህ የደንበኞች የሙከራ ምዕራፍ ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለመስጠት ከሚዘጋጅበት ጊዜ አስቀድሞ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የኔትወርክ እና የአገልግሎት ጥራቱን በተጠናከረ ሁኔታ የሚፈትሽበት ወቅት መሆኑን ገልጿል።

በሐረሪ ክልል የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ፤ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች የሚካሔድ ሲሆን ደንበኞች በዐ7 በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮቻቸውን መርጠው ሲም ካርድ መግዛት እንደሚችሉም ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አስታውቋል።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media
350 viewsEyasu Zekarias1, edited  11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 00:16:43 በምዕራብ ኦሮሚያ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች በታጣቂዎች ሲገደሉ የኢትየጵያ መንግሥት ጥቃቱን ለመከላከል በቂ ጥበቃ አላደረገም ተባለ

ሂዩማን ራይትስ ዎች ባለፈው ሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. በምዕራብ ኦሮሚያ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች በታጣቂዎች ሲገደሉ የኢትዮጵያ መንግስት ጸጥታ ኃይሎች ጥቃቱን ለመከላከል በቂ ጥበቃ አላደረጉም ነበር አለ።

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቅዳሜ ሰኔ 11/2014 ዓ.ም. በኃይል የታጠቁ ኃይሎች ስምንት ሰዓታት በፈጀ ጥቃት ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ 400 የሚጠጉ ሰላማዊ የአማራ ተወላጆችን ቶሌ እና ሰኔ ቀበሌዎች ውስጥ ገድለዋል ብሏል።

የሂዩማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ቀንድ ዳይሬክተር ላቲሺያ ባደር “የታጠቁ ኃይሎች መንደሮችን አንድ በአንድ አወድመዋል፤  መላ ቤተሰብን በጭካኔ ገድለዋል፤ ይህ ሁሉ ሲሆን በአቅራቢያው ያሉ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ምንም አላደረጉም" ብለዋል።

ማንነታቸው ያልታወቁ ያላቸው ታጣቂዎች ከጥቃቱ ባሻገር በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን ከማቃጠል ባለፈ ዝርፊያም ፈጽመዋል ብሏል ሂዩማን ራይትስ ዎች።
ከሳተላይት በተገኘ መረጃ መሠረት በአምስት የገጠር አካባቢዎች ቃጠሎ መድረሱን እና 480 የሚጠጉ ግንባታዎች መወደማቸውን በመግለጫው ጠቅሷል።

በጥቃቱ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ተዓማኒ እና ገለልተኛ ምርመራዎችን ማከናወን፣ ተጠያቂ የሆኑትን መለየት እና ጉዳት ለደረሰባቸው በቂ እርዳታ ማድረስ አለበት ብለዋል።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media
476 viewsEyasu Zekarias1, edited  21:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 23:05:04 በርካታ ቁጥር ያላቸው የቻይና ወታደሮች ሩሲያ ገቡ

የቻይና ጦር በሩሲያ ግዛት ውስጥ በሚካሄደው ወታደራዊ ልምምድ ላይ ለመሳተፍ በትናትናው እለት ሞስኮ መድረሱ ተነግሯል።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ትናንት በለቀቀው የቪዲዮ ምስል ላይ የቻይና ጦር ለግዙፉ ወታደራዊ ልምምድ ዝግጅት ሩሲያ መድረሱን ያሳያል።

ቮስቶክ 2022 የሚል መጠሪያ የተሰጠው ወታደራዊ ልምምድ ከነገ ጀምሮ ለ7 ቀናት በሩቅ ምስራቅ ሩሲያ እና በጃፓን ባህር ላይ የሚካሄድ መሆኑ ተነግሯል።

ቻይና እና ሩሲያን ጨምሮ ስድስት ሀገራት የጦር ልምምድ ሊያደርጉ መሆኑን አስታወቁ
በዚህ ወታደራዊ ልምምድ ላይ አዘጋጇ ሩሲያን ጨምሮ ቻይና፣ ቤላሩስ፣ ታጃኪስታን፣ ህንድ፣ ሞንጎሊያ እና ሌሎችን ሀገራት ይሳተፋሉ ተብሏል።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media
464 viewsEyasu Zekarias1, 20:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:59:38 በኦሮሚያ ክልል ሆሮጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ አገምሳ ከተማ ትናንት ከማለዳ ጀምሮ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ ቢያንስ 55 ሰዎች መገደላቸው ተዘገበ

የአከባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ለአንድ ዓመት ያህል የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች የአከባቢውን ፀጥታ ሲያስከብሩ ነበር። ይሁንና ባለፈው ዕሁድ ነሐሴ 22 ቀን፣ 2014 የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከከተማዋ መነሳታቸውን ተከትሎ የተለያዩ ስያሜ ያላቸው ታጣቂዎች በከተማዋ መፈራረቃቸውን ነው የዐይን እማኞች የገለጹት።

የአይን እማኞቹ ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት «መንግስት ‘ሸኔ’ ያላቸው “የኦሮሞ ነጻነት ጦር” ሰኞ ጠዋቱን ገብተው ከተማዋን ተቆጣጠሩዋት» ብለዋል።ታጣቂዎቹ ከተማዋ ውስጥ ሙሉ በሙሉ መንቀሳቀስ ከጀመሩ በኋላ ወደ 59 መሳሪያ ከማህበረሰቡ አስፈትተው በዚያው ሰኞ ቀን ከተማዋን ለቀው ወጥተዋል፡፡ 

“ትናንት ማክሰኞ ጠዋት ደግሞ ፋኖ ነን ያሉ የታጠቁ አካላት ወደ ከተማዋ ገብተው ከኦነግ ጋር አብራችኋል በሚል በመደዳው ከተማዋ ላይ ተኩስ በመክፈታቸው ከ15 ሺህ የማያንሱ የከተማዋ ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል” ነው ያሉት፡፡

ከትናንት ማታ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የ55 ሲቪል ዜጎች አስከሬን መቅበራቸውንና የ32 ሰዎች አስከሬን በየጫካውና በየገደሉ እየፈለግን ነው” ሲሉም የችግሩን ስፋት አስረድተዋል፡፡(የጀርመን ድምፅ )
   
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media
461 viewsEyasu Zekarias1, edited  18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:55:42
የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የ8ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዛሬ ጀምሮ በኢንተርኔት ላይ ማየት እንደሚቻል አስታወቀ

ቢሮው የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት መውጣቱን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ በክልሉ 451 ሺሕ 21 ተማሪዎች ለፈተና የተመዘገቡ ሲሆን 98 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆኑት ፈተና መውሰዳቸውን ገልጿል።

በዚህም መሰረት የ9ኛ ክፍል የማለፊያ ውጤት
ለወንዶች 50 በመቶ እና
ለሴቶች 47 በመቶ ነው ብሏል።

በአርብቶ አደሩ አካባቢ የ9ኛ ክፍል ማለፊያ ውጤት በመቶኛ ለወንዶች 47% ለሴቶች 44% ሲሆን ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ደግሞ ለወንዶች 44% እና ለሴቶች 41% መሆኑም ተገልጿል። ማለፊያው ውጤት በአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ እና በትምህርት ጥራት ላይ ተመስርቶ መወሰኑን የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ግርማ ባይሳ ገልጸዋል::

ሴት ተማሪዎች የተሻለ የፈተና ውጤት በማምጣት ለውጥ አምጥተዋልም ነው ያሉት።

ተማሪዎች ውጤታቸውን በኢንተርኔት ላይ ‘https://oromia.ministry.et/#/home

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media
463 viewsEyasu Zekarias1, 17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ