Get Mystery Box with random crypto!

በምዕራብ ኦሮሚያ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች በታጣቂዎች ሲገደሉ የኢትየጵያ መንግሥት ጥቃቱ | ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)

በምዕራብ ኦሮሚያ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች በታጣቂዎች ሲገደሉ የኢትየጵያ መንግሥት ጥቃቱን ለመከላከል በቂ ጥበቃ አላደረገም ተባለ

ሂዩማን ራይትስ ዎች ባለፈው ሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. በምዕራብ ኦሮሚያ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች በታጣቂዎች ሲገደሉ የኢትዮጵያ መንግስት ጸጥታ ኃይሎች ጥቃቱን ለመከላከል በቂ ጥበቃ አላደረጉም ነበር አለ።

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቅዳሜ ሰኔ 11/2014 ዓ.ም. በኃይል የታጠቁ ኃይሎች ስምንት ሰዓታት በፈጀ ጥቃት ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ 400 የሚጠጉ ሰላማዊ የአማራ ተወላጆችን ቶሌ እና ሰኔ ቀበሌዎች ውስጥ ገድለዋል ብሏል።

የሂዩማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ቀንድ ዳይሬክተር ላቲሺያ ባደር “የታጠቁ ኃይሎች መንደሮችን አንድ በአንድ አወድመዋል፤  መላ ቤተሰብን በጭካኔ ገድለዋል፤ ይህ ሁሉ ሲሆን በአቅራቢያው ያሉ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ምንም አላደረጉም" ብለዋል።

ማንነታቸው ያልታወቁ ያላቸው ታጣቂዎች ከጥቃቱ ባሻገር በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን ከማቃጠል ባለፈ ዝርፊያም ፈጽመዋል ብሏል ሂዩማን ራይትስ ዎች።
ከሳተላይት በተገኘ መረጃ መሠረት በአምስት የገጠር አካባቢዎች ቃጠሎ መድረሱን እና 480 የሚጠጉ ግንባታዎች መወደማቸውን በመግለጫው ጠቅሷል።

በጥቃቱ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ተዓማኒ እና ገለልተኛ ምርመራዎችን ማከናወን፣ ተጠያቂ የሆኑትን መለየት እና ጉዳት ለደረሰባቸው በቂ እርዳታ ማድረስ አለበት ብለዋል።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media