የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዋስትና ታገዷል ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከእስር እንዲፈታ ወይም የማይፈታበትን ምክንያት ካለ ችሎት ቀርቦ እንዲያስረዳ ታዞ የነበረው አዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን ዛሬ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ፀረ ሽብር ችሎት ቀርቦ፣ የዋስትናው ብይን በፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የታገደ ስለሆነ ሊፈፅም ያለመቻሉን አስረድቷል። ችሎቱም ያልተፈታበትን ይሄን የጠቅላይ ፍ/ቤት ምክንያት ተቀብሎ አሰናብቶናል። በዚህ መሠረት ጠቅላይ ፍ/ቤት፣ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዋስትና ሊፈታ አይገባም ክርክር ላይ ይግባኙን ለማድመጥ ለሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ.ም ቀጠሮ ሰቷል። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ላይ መንግስት በምጥ ያዋለደው ወንጀል በፍርድ ቤት ዋሰትና ቢፈቀድም እንቢተኛው ፖሊስ አልፈታም ብሎ ሠንብቷል::ዛሬም አቃቤ ህግ ይግባኝ ብሏል በማለት የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዋስትናውን አግዷል:: የሁሌ አዲስ ሚዲያ ፈጣን መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፤ Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/ Telegram : https://t.me/Hulaadiss YouTube Channel https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media? 174 viewsEyasu zekariyas1, edited 16:02