Get Mystery Box with random crypto!

(✍ GOSPEL TALK ✍)

የቴሌግራም ቻናል አርማ gospel_talk — (✍ GOSPEL TALK ✍)
የቴሌግራም ቻናል አርማ gospel_talk — (✍ GOSPEL TALK ✍)
የሰርጥ አድራሻ: @gospel_talk
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.73K
የሰርጥ መግለጫ

ክርስትና ማለት ክርስቶስ ነው ክርስትያን ነኝ ካሉ መኖር ነው ክርስቶስ ለኛ ሲል ከሞተ እኛ ለሱ ስንል መኖር ነው
አቤል ግዛው ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየቶች ካሏቹ በ @abel_gizaw አናግሩን

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-28 20:34:09 የሚሹህን አትተዋቸውም

ዛሬ ጧት በማለዳ ከማር ወለላ ይልቅ የሚጣፍጠውን የእግዚአብሔር ቃል አንድ አራት ምዕራፎች አነበብኩ፡፡ መርጬ ካነበብኳቸው ምዕራፎች መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 9 ይገኝበታል፡፡ ይህንን ምዕራፍ አንዴ አነበብኩና ደገምኩት፡፡ “የውዴ ቃል በተራሮች ላይ ሲዘልል በኮረብቶችም ላይ ሲወረወር ይመጣል፡፡” (መኃ.2፥8) እንደሚል፣ ዓይኔ ከተተከለበት ፊት ለፊት ገጽ ላይ አንዲት ክፍል ተወርውራ ልቤን በሐሤት ሞላችው፡፡ እጅግ ደስ አለኝ፡፡ ወዲያው አምላኬንም ስለ ላከልኝ ቃል በኃይል አመሰገንሁት፡፡ ለእናንተም ይህንኑ ላካፍላችሁ ወደድሁ፡፡ ብትችሉ ሙሉውን ምዕራፍ አንቡት፤ ልቤን የነካው መልእክት ግን የሚከተለው ነው፡-

“ስምህን የሚያውቁ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፤
አቤቱ፣ አንተ የሚሹህን አትተዋቸውምና፡፡” (ቁ.10)

በተለይ በተለይ፣ እጅግ የነካኝ “የሚሹህን አትተዋቸውምና” የሚለው አገላለጽ ነው፡፡ ይህ ሃሳብ መንፈሳዊ መሻት ያለው ሰው የሚያገኘውን በረከት ነው የሚጠቁመው፡፡ ቃሉ “እኔ የሚወድዱኝን እወድዳለሁ፤ ተግተው የሚሹኝ ያገኙኛል” (ምሳ.8፥17) ይላልና!

በመንፈሳዊው ዓለም መሻት፣ መፈለግ፣ ቅናት፣ ግለት(passion)፣ ማሰስ(craving)፣ ጥማት፣ ራብ፣ ጉጉት፣ ናፍቆት ወዘተ እጅግ የሚያስፈልጉ ነገሮች ናቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች ወደ ፊት እንድንዘረጋና በጨመረ ሁኔታ ጌታን እንድንፈልገው እንደ ሞተር ነው የሚሆኑልን፡፡ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት እነዚህ ነገሮች በውስጡ የሚንተከተኩበት ሰው ትጉነት መገለጫው ነው፡፡ ያንን የሚወድደውን ነገር በሚገባ እስኪያገኘው ድረስ አይተኛም፡፡ እረፍት አይኖረውም፡፡ ያነባል፣ ይጸልያል፣ ይመሰክራል፣ ይጽፋል፣ ሃሳቡን ለሰዎች ያካፍላል፣ ወይ ከሰዎች ጋር ስለ ውዱ ያወራል እንጂ ሥራ ፈትቶ መቀመጥ የሚባል ነገር አይታሰብም፡፡

የእግዚአብሔር ቃል “እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው” (መዝ.105፥3) ይል የለ? እንዲህ ዓይነት ሰው የሚፈልገውን ነገር ገና በቅጡ ሳያገኘው ተባርኳል፡፡ እንዴት? “ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው” (ማቴ.5፥6) ከተባሉት ውስጥ ይመደባልና፡፡ ታዲያ ይህ ምስጉን ሳያሰልስ ትኩረቱን አምላኩ ላይ አድርጐ፣ ፊቱን እየፈለገ ሲተጋ፣ የእግዚአብሔርን ክብር ናፍቆ እየተጠባበቀ፣ በጸጋው ዙፋን ፊት ሲያሳልፍ ምንድነው ነው የሚሆንለት? ይጠግባላ! ምክንያቱም ከሚለውምነውና ከሚያስበው በላይ ሊያደርግ የሚቻለው አምላኩ በሕይወቱ ይገለጣል ፡፡

ለእርሱ በቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ኢየሱስ እስከ ትውልዶች ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን ፤ አሜን(ኤፌ.3፥ 20)፡፡

@nazrawi_tube
694 viewsΒενιαμίν, 17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-23 16:30:18 በሕይወት ውስጥ ትልቁ ነጥብ
ሕይወትን ለምን ያህል ጊዜ
ኖርከው?ሳይሆን እንዴት
ኖርከው?ነው፡
-መኖር ከተባለማ ማቱሳላም ኖሯል ግን አንድ ደና ነገር አልሰራም እኔ እስክውማውቀው ልክ እንደሱም ደሞ ኢየሱስም, ጳውሎስ, ሙሴ,.... ኖረዋል ልዩነቱ ምን ያህል ዘመን ኖርክ ሳይሆን እንዴት ኖርከው ነው ስለዚህ ቆም ብለህ አስብ ተራ ሕይወት እየኖርክ እንዳልሆነ አረጋግጥ ለሌሎች መኖር ጀምር ከራስህ እና ከጌታ ቀጥሎ ያኔ ነው ተፅኖ መፍጠር ምችለው
-ትላንትናህን አትድገም አዲስ ነገር ለማድረግ ተፍቸርቸር ያኔ ጌታ ባንተ ሊሰራ ሲወድ ከልካይ አይኖርበትም ሁሌም የምታስበውን ሃሳብ ድጋሚ አስብበት ምናልባት አንድ ልክ ያልሆነ ነገር ታገኛለህ ስለዚህ ኢየሱስ ለኛ ሲል ኖሮ እንደሞተ አንተም አንተም ከራስህ በተጨማሪ ለሌሎች መኖርን ተማር ያኔ እመነኝ የሆነ ያህል ተፅኖ ትፈጥራለህ

ወዳቹሃለው
@gospel_talk
Am back
1.2K viewsAbelo Fisher, 13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-07 13:48:08
1.3K viewsKal Tekletsadik, 10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-07 13:47:53 Christmas is all about God giving us his everlasting gift which is Christ through Mary.."And she shall bring forth a son, and thou shalt call his name JESUS: for he shall save his people from their sins."
- Matthew 1:21 (KJV)
Merry Christmas
1.2K viewsKal Tekletsadik, 10:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-09 21:53:13
1.5K viewsTsi የኢየሱስ ልጅ, 18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-28 07:28:58 . ይፃፍልኝ - ህሊና ዳዊት
ʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ

▷ @gospel_talk◁
▷ @gospel_talk◁
▷ @gospel_talk◁

△Join Us△
What a song
1.5K views˙·٠•● Bar7k ●•٠·˙, 04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-28 07:17:13 ራእዩ የተወሰደበት አገልጋይ ማለት ልቡ ከውስጡ ተቆርጦ እንደ ወጣበት ሰው ነው።

ራእይ አገልጋይን እግዚአብሔር ወደ አየለት ግብ የሚያሰኬዶ ሞተር ነው። ተግባርን በውስጡ የሚፈጥርና ተከታዮችን የሚያቀጣጥል እሳት ነው ።

ዘመን በዘመን ሲተካ ያለመናወጥ በጽናት መሰዋእት እየሆነ በታማኝነት እንዲያገለግል ያደርገዋል።


" #ራእይ ባይኖር ሕዝብ መረን ይሆናል፤ ሕግን የሚጠብቅ ግን የተመሰገነ ነው። "
(መጽሐፈ ምሳሌ 29:18)

እወዳችዋለሁ

: @Bar7k

መልዕክቱን ከወደዳችሁት:-
Share and join
@gospel_talk
@gospel_talk
@gospel_talk
1.2K views˙·٠•● Bar7k ●•٠·˙, edited  04:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-26 09:19:14 . "ፀሎቴ ጋ"
ዘማሪት ህሊና ዳዊት
NEW GOSPEL SONG
sʜᴀʀᴇ ◈JOIN◈ sʜᴀʀᴇ
▷◈ @ZELALEMAWI ◈◁
── ❖ ── ✦ ── ❖ ──
1.0K views˙·٠•● Bar7k ●•٠·˙, 06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-26 09:19:01 አስረ ሁለተኛ የተፈተንን ሁላችንም 12ን ጨረስን እንጂ መኖር አላበቃም፣ መኖርን መኖር የሚያሰኘው ደግሞ የጌታ ህልውና ነውና campus ለሚኖረንም ሆነ ለሚቀጥለው ኑሮዋችን በሙሉ የሚጠቅመንን ነገር የምንሰንቅበት ምቹ ጊዜ ጌታ ሰቶናልና እንጠቀምበት፤ጊዜያችንን ሳንጠቀም እየቀለድን ሳናውቀው እራሳችንን ውሃ ለመቅዳት እንደሄደችሁ ጨዉ ሆነን እንዳናገኘው ትኩረታችንን ከሁኔታውም ሆነ ከራሳችን አንስተን ክርስቶስ ለይ እናድርግ!!!

ነገ መሆን የምትፈልገውን የመሆን ቀላሉ መንገድ ነገን መፍጠረ ነውና ንቃ።

#ይህን ወቅት የምናሳልፍበት ምርጥ እቅድ:-

#ለነፍስ:

1.የግል ጊዜ (የፀሎትና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት) በመውሰድ
2.መንፈሳዊ መጽሀፍትን በማጥናት
3.ከወንድሞች ጋር ህብረት በማድረግ
4.የተለያዩ አህምሮአችንን ልያሰፉልን የሚችሉና መግባት ለምንፈልገው field ግብአት የሚሆኑ ነገረሮችን በማንበብ

#ለስጋ:

1.ሰውነት ማጎልበቻ በመስራት
2.የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ
3.በቂ እረፍት በማድረግ

#ለመንፈሳችን:
=ምንም ማድረግ አይጠበቅብንም ሙሉና ፍጹም ነዉና፣ ይልቁን መንፈሳችን በክርስቶስ የሆነውን ሁሉ በማወቅ(ነፍሳችንን በመመገብ) በሀሴት መኖር ይጠበቅብናል።

ከፊታችሁ:-

1.የከፍተኛ ትምህርት
2.የስራ
3.የትዳር
4.ልጆችን የመውለድና የማሳደግ ትላልቅ ጊዜያት ይጠብቁናል።

እናስተውል:- ከ preparatory
ትምህርት የ Campus Challenge full ነው፣ ከcampus ስንወጣ ስራ፣ ደምወዝ፣ ቤት፣መኪና፣የትዳር/የራእይ አጋር ሁሉም በራሱ ሌሎች ጥያቄዎችን ይወልዳሉ። ምን ልላችሁ መሰላችሁ እኛ ከልሞላን እች አለም አትሞላም፣ እኛ ካልረካን እች አለም አታረካንም፣እኛ ካላረፍን እቺ አለም አታሳርፍም። ከዛሬ አረት አመት በፊት 8 ለመፈተን ጓጓን፣ ከዛም ማትሪክ፣ከዛም enterance...ከሚኒስቲሪ ማትሪክ ከማትሪክ enterance ጊዜና አቅም ይፈልጋል፣ሚኒስትሪ አሪፍ ውጤት በሰራንበት እውቀት ማትሪክና እንተራንስ አንፈተንም። ነገሩ አየገበደ ስለሚመጣ የ8ተኛ ሰንፍና ብቻ ሳይሆን ጉብዝናም ቢሆን ለዛሬ ሰለማይሆን ማጥናትና ከሚኒስትሪ እውቀት ማለፍ ግድ ነበር።

አሁን ከፊታች ብዙ እሩጫዎች አሉና እንንቃ።
ከምንም በላይ ከራሳችን፣ከሰውና ከሁኔታው ጋር ከማሳለፍ ይልቅ ከጌታ ጋር ለማሳለፍ ጊዜ እንስጥ።

ፀሎቴ ጋ የሚለውን ይህን ድንቅ መዝሙርን ጋብዤ ልሰናበታችሁ።

ብሩህ ቀን !!!


Join: @gospel_talk

@Bar7k
1.1K views˙·٠•● Bar7k ●•٠·˙, edited  06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-22 15:33:19
ለሀገሬ እፀልያለሁ

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከምንጊዜውም በላይ የእግዚአብሄርን ጣልቃ ገብነት አጥብቃ የምትፈልግበት ወቅት ላይ እንገኛለን። ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያም ላለፉት ወራት #ለሀገሬእፀልያለሁ በሚል ርዕስ ስለኢትዮጵያ ግድ የሚላቸውን ሁሉ ለፀሎት በማስተባበር እንደዚሁም በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የተለያዩ ድጋፎችን በማሰባሰብ ለማገዝ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል አሁንም በማድረግ ላይ ይገኛል ።

በመሆኑም ስለሀገራችን ኢትዮጵያ ሁላችንም ካለንበት ቦታ በአንድ ልብ እና በንፁህ ሃሳብ ወደእግዚአብሄር ፊት እንቀርብ ዘንድ ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከ ምሽቱ 12፡00 ጀምሮ
የ ኦንላይን የፀሎት መረሀግብር አዘጋጅቷል።

እርሶም ካሉብት ቦታ ሆነው ይህንን ፕሮግራም በፌስቡክ የቀጥታ ስርጭት አብረውን እንዲሳተፉ በጌታ ፍቅር ተጋብዘዋል።

ለሀገራችን ሳናቋርጥ እንፀልይ ሌሎችም እንዲፀልዩ እናበረታታ።

#ለሀገሬእፀልያለሁ #prayforEthiopia

የማህበራዊ ድረገፅ ፕሮፋይል ፒክቸራችንን በዚህ ፍሬም በመቀየር ብዙዎችን ለፀሎት እንዲነሳሱ እናግዝ።
የፌስቡክ ፕሮፋይሎን ለመቀየር https://bit.ly/prayethiopiaframe
የቴሌግራም ፕሮፋይሎን ለመቀየር https://t.me/add_frame_bot
ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ

የፌስቡክ ገፅ ፡https://facebook.com/gcmethiopia
920 viewsΒενιαμίν, 12:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ