Get Mystery Box with random crypto!

አስረ ሁለተኛ የተፈተንን ሁላችንም 12ን ጨረስን እንጂ መኖር አላበቃም፣ መኖርን መኖር የሚያሰኘው | (✍ GOSPEL TALK ✍)

አስረ ሁለተኛ የተፈተንን ሁላችንም 12ን ጨረስን እንጂ መኖር አላበቃም፣ መኖርን መኖር የሚያሰኘው ደግሞ የጌታ ህልውና ነውና campus ለሚኖረንም ሆነ ለሚቀጥለው ኑሮዋችን በሙሉ የሚጠቅመንን ነገር የምንሰንቅበት ምቹ ጊዜ ጌታ ሰቶናልና እንጠቀምበት፤ጊዜያችንን ሳንጠቀም እየቀለድን ሳናውቀው እራሳችንን ውሃ ለመቅዳት እንደሄደችሁ ጨዉ ሆነን እንዳናገኘው ትኩረታችንን ከሁኔታውም ሆነ ከራሳችን አንስተን ክርስቶስ ለይ እናድርግ!!!

ነገ መሆን የምትፈልገውን የመሆን ቀላሉ መንገድ ነገን መፍጠረ ነውና ንቃ።

#ይህን ወቅት የምናሳልፍበት ምርጥ እቅድ:-

#ለነፍስ:

1.የግል ጊዜ (የፀሎትና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት) በመውሰድ
2.መንፈሳዊ መጽሀፍትን በማጥናት
3.ከወንድሞች ጋር ህብረት በማድረግ
4.የተለያዩ አህምሮአችንን ልያሰፉልን የሚችሉና መግባት ለምንፈልገው field ግብአት የሚሆኑ ነገረሮችን በማንበብ

#ለስጋ:

1.ሰውነት ማጎልበቻ በመስራት
2.የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ
3.በቂ እረፍት በማድረግ

#ለመንፈሳችን:
=ምንም ማድረግ አይጠበቅብንም ሙሉና ፍጹም ነዉና፣ ይልቁን መንፈሳችን በክርስቶስ የሆነውን ሁሉ በማወቅ(ነፍሳችንን በመመገብ) በሀሴት መኖር ይጠበቅብናል።

ከፊታችሁ:-

1.የከፍተኛ ትምህርት
2.የስራ
3.የትዳር
4.ልጆችን የመውለድና የማሳደግ ትላልቅ ጊዜያት ይጠብቁናል።

እናስተውል:- ከ preparatory
ትምህርት የ Campus Challenge full ነው፣ ከcampus ስንወጣ ስራ፣ ደምወዝ፣ ቤት፣መኪና፣የትዳር/የራእይ አጋር ሁሉም በራሱ ሌሎች ጥያቄዎችን ይወልዳሉ። ምን ልላችሁ መሰላችሁ እኛ ከልሞላን እች አለም አትሞላም፣ እኛ ካልረካን እች አለም አታረካንም፣እኛ ካላረፍን እቺ አለም አታሳርፍም። ከዛሬ አረት አመት በፊት 8 ለመፈተን ጓጓን፣ ከዛም ማትሪክ፣ከዛም enterance...ከሚኒስቲሪ ማትሪክ ከማትሪክ enterance ጊዜና አቅም ይፈልጋል፣ሚኒስትሪ አሪፍ ውጤት በሰራንበት እውቀት ማትሪክና እንተራንስ አንፈተንም። ነገሩ አየገበደ ስለሚመጣ የ8ተኛ ሰንፍና ብቻ ሳይሆን ጉብዝናም ቢሆን ለዛሬ ሰለማይሆን ማጥናትና ከሚኒስትሪ እውቀት ማለፍ ግድ ነበር።

አሁን ከፊታች ብዙ እሩጫዎች አሉና እንንቃ።
ከምንም በላይ ከራሳችን፣ከሰውና ከሁኔታው ጋር ከማሳለፍ ይልቅ ከጌታ ጋር ለማሳለፍ ጊዜ እንስጥ።

ፀሎቴ ጋ የሚለውን ይህን ድንቅ መዝሙርን ጋብዤ ልሰናበታችሁ።

ብሩህ ቀን !!!


Join: @gospel_talk

@Bar7k