Get Mystery Box with random crypto!

ለሀገሬ እፀልያለሁ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከምንጊዜውም በላይ የእግዚአብሄርን ጣልቃ ገብነት አጥ | (✍ GOSPEL TALK ✍)

ለሀገሬ እፀልያለሁ

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከምንጊዜውም በላይ የእግዚአብሄርን ጣልቃ ገብነት አጥብቃ የምትፈልግበት ወቅት ላይ እንገኛለን። ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያም ላለፉት ወራት #ለሀገሬእፀልያለሁ በሚል ርዕስ ስለኢትዮጵያ ግድ የሚላቸውን ሁሉ ለፀሎት በማስተባበር እንደዚሁም በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የተለያዩ ድጋፎችን በማሰባሰብ ለማገዝ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል አሁንም በማድረግ ላይ ይገኛል ።

በመሆኑም ስለሀገራችን ኢትዮጵያ ሁላችንም ካለንበት ቦታ በአንድ ልብ እና በንፁህ ሃሳብ ወደእግዚአብሄር ፊት እንቀርብ ዘንድ ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከ ምሽቱ 12፡00 ጀምሮ
የ ኦንላይን የፀሎት መረሀግብር አዘጋጅቷል።

እርሶም ካሉብት ቦታ ሆነው ይህንን ፕሮግራም በፌስቡክ የቀጥታ ስርጭት አብረውን እንዲሳተፉ በጌታ ፍቅር ተጋብዘዋል።

ለሀገራችን ሳናቋርጥ እንፀልይ ሌሎችም እንዲፀልዩ እናበረታታ።

#ለሀገሬእፀልያለሁ #prayforEthiopia

የማህበራዊ ድረገፅ ፕሮፋይል ፒክቸራችንን በዚህ ፍሬም በመቀየር ብዙዎችን ለፀሎት እንዲነሳሱ እናግዝ።
የፌስቡክ ፕሮፋይሎን ለመቀየር https://bit.ly/prayethiopiaframe
የቴሌግራም ፕሮፋይሎን ለመቀየር https://t.me/add_frame_bot
ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ

የፌስቡክ ገፅ ፡https://facebook.com/gcmethiopia