Get Mystery Box with random crypto!

(✍ GOSPEL TALK ✍)

የቴሌግራም ቻናል አርማ gospel_talk — (✍ GOSPEL TALK ✍)
የቴሌግራም ቻናል አርማ gospel_talk — (✍ GOSPEL TALK ✍)
የሰርጥ አድራሻ: @gospel_talk
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.73K
የሰርጥ መግለጫ

ክርስትና ማለት ክርስቶስ ነው ክርስትያን ነኝ ካሉ መኖር ነው ክርስቶስ ለኛ ሲል ከሞተ እኛ ለሱ ስንል መኖር ነው
አቤል ግዛው ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየቶች ካሏቹ በ @abel_gizaw አናግሩን

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-23 20:40:46 ስለ ዮሃንስ ወንጌል እግዚአብሔር ይመስገን

የዮሃንስ ወንጌል ልክ እንደ ሌሎቹ ሦስት ወንጌሎች ኢየሱስን በአመዛኙ ከታሪክ ጋር አጋብቶ ብቻ ሳይሆን የሚነግረን “አሁን” በአማኝ ወይም በቤተክርስትያን ሕይወት ውስጥ ያለውን ፋይዳ በጥልቀት በማውሳትም ነው፡ በሌላ አባባል ታሪካዊ / historical ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን የሚያስተዋውቀን አሁናዊ / existential ክርስቶስንም ነው።

ዮሃንስ በወንጌሉ ከሚገልጻቸው አሁናዊ እውነቶች መካከል አንደኛው አንድነት / unity ነው፡ ይህንን የአንድነት ክቡር እውነት በዋነኛነት በምእራፍ 17 ላይ አጽንኦት በመስጠት ያቀርብልናል።

ክፍሉ የሚጀምረው፦

“ኢየሱስም . . . ወደ ሰማይ አይኖቹን አነሳና እንዲህ አለ”
ብሎ ነው።

ይሄም የሚያሳየን እውነት በዚህ ክፍል ውስጥ ጌታችን የሚናገረው ነገር በሙሉ በአብ ፊት እንደ ጸሎት የቀረበ ምልጃ መሆኑን ነው። በዚህ የምልጃ ምእራፍ ውስጥ ነው እንግዲህ ጌታችን በሚገርምና እጅግ ደስ በሚል መልኩ በአብ፣ በወልድና፣ በአማኞች መካከል ያለውን አንድነት ጸሎታዊ በሆነ ቅርጽ ለአባቱ የሚያቀርበው።

#አንድ
የአማኞች የእርስ በርስ አንድነት

ክርስቶስ በዚህ ምእራፍ ቁጥር አሥራ አንድ ላይ እንዲህ ብሎ ይጸልያል፦

“ቅዱስ አባት ሆይ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ ጠብቃቸው”

መቼም ይህን ቁጥር በጥድፊያ ካላነበብነው በስተቀር ወሳኝ የሆነውን አሳብ የምናልፈው አይመስለኝም፡ ክርስቶስ በዋነኛነት አማኞች እርስ በርስ በአንድ የሰመረ ሕብረት እንዲሆኑ ወይም ብዙዎች ቢሆኑም ነገር ግን አንድ እንዲሆኑ አባቱን ይለምንላቸዋል፡ ከሁሉ የሚገርመው ደግሞ አማኞች አንድ እንዲሆኑ ለማነጻጸሪያ የተጠቀመበት እውነት ነው፡ እንዲህ ይላል፦

“እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ”

የአንድነቱ ንጽረት አባትና ልጅ ናቸው፡ ታዲያ ይሄ አይገርምም!
በዚሁ ወንጌል ውስጥ ጌታችን “እኔና አብ አንድ ነን - We are in one accord” ብሎ እንደተናገረ እናነባለን፣ ይሄንኑ አንድነት ወይም የአሳብና የልብ ስምረት አማኞች እርስ በርሳቸው እንዲለማመዱት ይጸልይላቸዋል፡ እውነት ግን እስኪ አስቡት፣ አብና ወልድ አንድ እንደሆኑት እኛ አንድ እንድንሆን እኮ ነው የሚጸልየው፡ በምድር ላይ የአማኞችን አንድነት ለማነጻጸር የሚመጥን አንድ እውነት ያለው በአብና በኢየሱስ መካከል ያለው አንድነት ብቻ ነው፡ ይሄ አንድነት ደግሞ እኛ #የምንጀምረው ሳይሆን #የምንገባበት ነው፣ ምክንያቱም አስቀድሞ በአባትና በኢየሱስ መካከል የተመሰረተ ነው። አንድነታችን የዘር፣ የቋንቋ፣ የአጥቢያ ቤተክርስትያን፣ የጓደኝነት፣ ወይም የቲፎዞ ሳይሆን የእግዚአብሔርና የኢየሱስ ነው፡ ከዚህ ያነሰ አንድነት በሰው፣ ከሰውና፣ ለሰው የሆነ ነው።

#ሁለት
የአብ፣ የወልድና፣ የአማኞች አንድነት


አማኞች እርስ በርስ ሊኖራቸው ከሚገባቸው አንድነት ወይም ሕብረት በዘለለ መልኩ ጌታችን፣ እርሱ፣ አብና፣ አማኞች ደግሞ በአንድ አንድ እንዲሆኑ ሲጸልይ እናነባለን ቁጥር 21 - 22

“አባት ሆይ በእኔ እንዳለህ፣ እኔም በአንተ፣ እነርሱም ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ . . . እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ . . . “

ደቀመዛሙርት በአብና በወልድ መካከል ባለ አንድነት እርስ በርሳቸው አንድ እንዲሆኑ ብቻ ሳይሆን የተጸለየላቸው፣ እነርሱ ራሳቸው ከአብና ከወልድ ጋር በአንድ እንዲሰመሩም ጭምር ነው፡ አብ በወልድ ውስጥ፣ ወልድ ደግሞ በአብ ውስጥ፣ አማኞች ደግሞ በአብም በወልድም ውስጥ ሆነው በአንድ እንዲሆኑ፡ እውነት ከዚህ የሚበልጥ ጸሎት አለ? እውነት ከዚህ የሚበልጥ ክብር ወይም ሕይወት አለ? ከአብና ከወልድ ጋር አንድ መሆን!!

#ማሳረጊያ

የእርስ በርስ አንድነታችን ወይም ሕብረታችን በአብና በወልድ መካከል ባለው ሕብረት መቃኘቱ ሲገባን፣ እንዲሁም አንድነታችን የእርስ በእርስ ብቻ ሳይሆን ከአብና ከወልድም ጋር በአንድ መሆኑ ሲገባን፣ ለዚህ ክቡር እውነት ስንል የማንጥለው ነገር አይኖርም፡ ለዚህ ሕብረት ብለን የምንጥለው ነገር ሕብረቱ የገባንን ያህል ነው።

በዚህ አንድነት ውስጥ ያልተሰመረ ሁሉ፣ ፓስተር ይሁን ሐዋርያ፣ ወንጌላዊ ይሁን ነብይ፣ የሥነ-መለኮት ምሁር ይሁን ዓቃቤ-እምነት፣ ፈጽሞ የመለኮትን ሕይወት አይቋደስም - የመለኮት ሕይወት ከአብና ከወልድ ጋር እንዲሁም እርስ በርስ አንድ በመሆን ብቻ የሚገለጥ ነው።

ምን አይነት ክብር ነው!
ከአብም ከወልድም ጋር በአንድ መሰመር!


“ኅብረታችንም ከአባት ጋር ክልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው”

Yilu danu
@nazrawi_tube
@nazrawi_tube
609 viewsΒενιαμίν, 17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 07:59:35 Relation ship #1 share ከተቀማችሁ
አቤል ነኝ
Any comment or question @abelo_fisher

@gospel_talk
@gospel_talk
506 viewsAbelo Fisher, edited  04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 19:29:59 የተሠጠክ ምን ያክል #ትልቅ እንደሆነ ብታውቅ የጠየከው #ቀሊል እንደሆነ ይገባካል

በነፃ የተሠጠህ #ክርስቶስ_ታላቅ ነው

አንዳች ነገር አስፈልጎክ ወደ #ፀጋው_ዙፋን_ፊት ቀርበህ ስትጠይቅ፣ #በእምነት አድርገው እንጂ ላንተ ሠማይ የደመደልክ የጠየከው ያንተ እንዲሆን ያረጋገጠልክ #የኪዳን_ቋንቋ #እንዲያው የሚል ነው

"ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ #ሁሉን ነገር #እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?"
ሮሜ 8:32
         
ስለዚህ የሠማይ አባትክን #አምነክ ቅረበው፣በነፃ የሠጠክ #ልጁ ታላቅ #ከልኬትም_በላይ  በመሆኑ ሌላውን #ልጄ_ሆይ በነፃ ውሠድ ይልካል

ጌታን ከምጠይቀው ይልቅ እርሡ አስቦልኝ በነፃ የሠጠኝ ታላቅ ነውና ሌላውን ነገር #እንዲያው ይሠጠኛል የሚል ብቻ #አሜን ሲል መልክቱን ይቀበላል

Share share
Join join

@gospel_talk
649 viewsAbelo Fisher, 16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 11:55:08 -sexual purity with tseba ministry
ለድምፁ ጥራት sorry
እንደምትማሩበት ተስፋ አለኝ
661 viewsAbelo Fisher, edited  08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 10:40:34 የትኛውን እንጀምር በቅርቡ
-Relation ship
-sexual purity
-leader ship
-ወጣትነት እና ተግዳሮቱ
709 viewsAbelo Fisher, 07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 13:35:51 #የዋዜማ መልዕክት

በህይወቴ በጣም ከምገረምበት ነገር አንዱ በአል ሲመጣ በአል ነው ብለን ያመንበትን ምክንያት ከማሰብ ይልቅ ስለምንበላው ፣ ስለምንጠጣው ፣ ስለ ልብሳችን መጨነቃችን ነው ።

አዲስ አመት መጣ አዲስ ልብስ ልግዛ ፣
ገና ነውና ስጦታ ካልተሰጠኝ ፣ ፋሲካ ነው ዛሬ በጉን ዶሮውን ልግዛ ሆኖል የኛ ህይወት መብላቱ መጠጣቱ ክፋት ሆኖ ሳይሆን ከርሱ በላይ እግዚአብሔርን እንድናስበው ስለምፈልግ ነው

እንደሚታወቀው ነገ ፋሲካ ነው ዛሬ ዋዜማው ላይ ቆመናል ብዙዎቻችንን ያስጨነቀን ነገር ግን የሽንኩርት ፣ የዘይት ፣ የዶሮ መወደድ ነው እስቲ ስንቶቻችን ነን ከበአሉ ሽር ጉድ ውጪ በፅሞና ስለተደረገልን ስለተከፈለልን ዋጋ የምናስበው ?

ከምንበላው በግ በላይ የናዝሬቱ ኢየሱስ ለኛ እንደ በግ ታርዶልናል እሱ ነው ሊያሳስበን የሚገባው !!!
የተከፈለልኝ ዋጋ ዋጋቢስ አድርጌዋለሁ ወይስ ገብቶኛል ብሎመፈተሹ ተገቢ ነው ።በአል ወር ሲቀረው ጀምረን በወጪ ከምንጨናነቀው በላይ ስለነፍሳችን ፣ ስለመዳናችን እንጨነቅ ።

እንደ ፅጌረዳ ፈክተን ተሽሞንሙነን እየበላን እየጠጣን ብቻ ከምናሳልፈው ይልቅ ምንም ሳይኖረን የተደረገልንን እያሰብን ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት አድርገን ብናሳልፈው እሱ ለእግዚአብሔር ታላቅ ዋጋ አለው ። ይህን ስል መብላቱ መጠጣቱ አያስፈልግም ማለቴ ሳይሆን በምቾታችን ተታለን ቅድሚያ መሰጠት ያለበትን ነገር እየረሳነው ይመስለኛል ።
ከጎረቤት አላንስም ፣ ያስለመድኩት አይቀርም እያልን አጉል መጨናነቅ ውስጥ ከመግባት ባለን ተደስተን ከቻልን አካፍለን እግዚአብሔር እያመሠገንን ባዕሉን ማሳለፍ ነው ።
ቅድሚያ ትኩረታችን #ኢየሱስ ላይ ይሁን ሌላው ትርፍ ነው ። በሰበብ ባስባቡ አመት ባል በመጣ ቁጥር ልዝናና ፣ ልጨፍር ፣ ልብላ ከማለት ይልቅ ልክ እንደ ወርቃማ እድል ቆጥረነው የምንችል ቤተክርስቲያን ያልቻልን ቤታችን ወይም ባለንበት ቦታ እግዚአብሔርን ፣ የተደረገልንን ነገር እያሰብን እናክብረው ማሰብ ብቻ ሳይሆን በቀረም ዘመናችን የመስቀሉን ስራ እያሰብን በዋጋ ተገዝተናልና ስለዛ እንኑር ።
መልካም የፋሲካ በአል እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ ተመኘሁ

በያኔት ማስረሻ
#share
@yanet_literatures
1.0K viewsYanet Masresha, 10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-07 05:49:15 እሁድ እሁድ ከቤት ውጪ የመብላት ልማድ አለኝ እንደተለመደው ጆንን ጠራሁትና ልንበላ ስፖርት ሆቴል ገባን አስተናጋጁ በተደጋጋሚ ስለምንጠቀም ምርጫችንን ያውቀዋል ስንቀመጥ አየንና የተለመደው ይሁንላችሁ አለ ተያየንና አው ዛሬ ግን አንድ ጉአደኛችን ስለሚመጣ ፓስታ በሱጎውን 2 አርገው ብለነው ወደ ጨዋታችን ተመለስን በወሬያችን መሃል አንዲት ተባይ ነገር የተቀመትንበት ጠረጴዛ ላይ አረፈች ጆን አፍጥቶ እያያት 'ቻ በኔ እጅ ላይ ነዋ ሕይወቷ' አለ ፈገግ እያለ 'አይመስለኝም ታያለህ ታመልጥሃለች' አልኩት እንደማይሆንለት እያሰብኩ 'ምን አለ በለኝ ቻ እሺ መድባ ' አለኝ 'እሽ በልተን ከወጣን በኃላ ያኔ ያልከውን መፃፍ ገዛልሃለው አልኩት' ሌላ ሰው የሚለውን መፃፍ በጣም እየፈለገው እንደነበር ትዝ ብሎኝ መስማማቱን አንገቱን ነቅንቆ አሳወቀኝና ወደተውናት ተባይ ተመለስን ስንፈልጋት የለችም ወዲያው አንድ ነገር መጣልኝ 'ለካ አለመስማት አንዱ ለመቀጠል ወሳኙ ነገር ነው ብዙ ወጣቶች እኔንም ጨምሮ ሌሎችን በመስማታችን ብዙ ነገር አተናል እቺ ተባይ ብትሰማንስ ብዬ አሰብኩ ግን እሷ የራሷን ሕይወት ቀጥላለች እራሷን ብቻ ነበር ምታደምጠው ለካ አትችልም አቅም ያንስሃል ምናምን ሚሉ ሰዎችን እየመረጥኩ መስማት አለብኝ' ብዬ እያሰብኩ ጆን ' በል ባክህ እንታጠብና እንብላ እርቦኛል አለ ' ከረሀቡ የተነሳ እየጠበቅን ያለውን ጉአደኛችንን እረስቶ....


ይሄን ስል ግን ሁሉንም ነገር አንስማ ሳይሆን just ወደ አላማችን የማያቀርበን ከሆነ ብዙም ትኩረት አንስጠው እንጂ ምክሮችን አንስማ አይደለም ሕይወታችን የራሳችን ስለሆነች
fisher
1.0K viewsAbelo Fisher, 02:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 13:52:27 Having sex before marriage is like awakening abeast. Once awakened, it's almost impossible to put back to sleep and cause untold damage: sexually transmitted diseases, abortion, single motherhood, guilt, broken relationship with Christ. Speak truth to your teenagers. Teach them to FLEE like Joseph did.
@gospel_talk share
730 viewsAbelo Fisher, 10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-02 07:07:05 ድክም ብሎኝ ስለዋልኩ አልጋዬ ላይ እንደወደቁ እንቅልፍ ሸለብ አርጎኝ ሳላጠፋ ያደርኩት መብራት ጠዋት ስነቃ አይኔን ሊያጠፋ የተዘጋጀ ይመስል አይኔን ጨለምለም አረገው እንደምንም አይኔን ገላለጥቁና ተነስቼ አልጋዬን ማነጣጠፍ ጀመረኩ በዚህ ሰዓት ነበር ጉዋደኛዬ ክንፍ ሲል እቤታችን ሳይነጋ የመጣው ክፍሌን አንኩአኩአና ገባ
'እንዴ በሰላም ነው ፓፒ '
'አው ቻ የሆነ ቦታ እንድትወስደኝ ፈልጌ ነበር አንተ ስለምታውቀው '
'እና ስልኬ ላይ አትደውልም ነበር' አልኩት ትንሽ እንደመቆታት እያረገኝ
'ይቅርታ ይደብርሃል ብዬ አላሰብኩም ነበር '
'እኔ እንኩአን አልደበረኝም እንዳትለፋ ብዬ እንጂ' ብቻ ስለቦታው ምናምን አወራንና ወጣን ::
ወደ ቦታው እየደረስን ስንመጣ ፓፒ ማይሆን ነገር ጀመረ ያገኘውን ሰው 'አባት /እናት /እህት /ወንድም እንትን የቱ ጋር እንደሆነ ታውቃለህ' እያለ መጠየቅ ሲጀምር በጣም ተናደድኩ
'ፓ ምንድነው ችግርህ በጠዋቱ መተህ ከቤት ያወጣኅኝ ሰው እየጠየክ ለመሄድ ነው?'
'ውይይይ ቻ በጣም ይቅርታ እየረሳሁት እኮ' ምናምን ብሎ አብላልቶ እንደምንም አስረሳኝ በሃሳቤ ሄድ አልኩና 'ለካ መንፈስ ቅዱስም እንደዚው ነው ሚሰማው እሱ ሊመራኝ ሲፈልግ በዓለም እየተመራው ወደ እውነት ሁሉ ሊነዳኝ ሲፈልግ እኔ ግን በዓለም በሰዎች, በጉአደኛ, በማህበረሰብ, እና በራሴ እየተመራው ነው የሳትኩት ወይኔ መንፈስ ቅዱስ ልያወራኝ ፈልጎ አላደምጥ እያልኩት ይሆን ብቻ ምሕረቱን ያብዛልን' እያልኩም ሳብሰለስል 'ቻ ወዴት ሄድክ? እ ቦታውን አልደረስንም እንዴ? 'አለኝ ፓፒ ጥያቄውን አከታትሎ ሲጠይቀኝ ከሃሳብ ባህሬ ወጣው ከዛም ዞር ዞር ብዬ ሳይ ለካ አልፈነው መተናል 'ውይይ ፓ አልፈነው ነው መጣን መሰለኝ ' አልኩት በጥፋቴ እንደማፈር ነገር እያረገኝ 'ለዚህ እኮ ነው ሰው ስጠይቅ የነበረው አለ' ለቅድሙ ጥፋት ማስተባበያ ያገኘ ይመስል ፈገግ እያለ ብቻ ወደ ኅላ ተመልሰን ደረስን ያሰማልንብንበት::

የእውነት መንፈስ ቅዱስ ሊመራን እየዳዳ እኛ በራሳችን መመራት አይሁንብን
fisher
@gospel_talk join our channel
806 viewsAbelo Fisher, 04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-31 13:56:56 #ቅድስና

ቅድስና መምሰልና አለመምሰል ነው። መምሰል እግ/ርን ሲሆን አለመምሰል ደግሞ ዓለምን ነው።
ቅድስና ከዓለም ማለትም ከሥጋ ምኞት፣
ከዓይን አምሮትና ስለ ገንዘብ መመካት (1ዩሐ 2:15) በመለየት፣ የእየሱስ ክርስቶስን መልክ በመምሰል ማደግና የመለኮት ባሕርይ ተካፋይ መሆን ነው። (ዕብ 12:10)

ቤተ ክርስቲያን ሙሽራዋን እንደምትጠብቅ ሙሽሪት ያለ ነውር በቅድስና ልትኖር ተጠርታለች (ኤፌ 5:27)። ስለዚህ የእግ/ር ፍቃድ ለእኛ መቀደስን እንድንፈልግ እንድንቀደስና በመቀደስም እግ/ርን እንድንመስል ነው (1ጴጥ 1:15-16)
ቅድስና በዘሌዋውያን እንደተገለጸው መሥዋዕት በሚቀርብበት ሰዓት ወይም ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገባ ብቻ የመታጠብ ወይም የመንጻት ሕግ ሳይሆን፣ ቅድስና የኑሮ ዓይነት፣ የሕይወት ፍልስፍናና አኗኗር ነው።
ቅድስና ከሥጋዊ ምኞት መሸሽ ነው።
( ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤
ቲቶ 2 : 12-13)
እግ/ርም በልጁ የሚያምኑትን ሁሉ ልጁን እንዲመሰሉ አስቀድሞ ወስኗል( ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ ሮሜ 8 : 29)
ይህ ልጁን መምሰል የልጁን ባህርይ መያዝ ነው፣ ልጁን መምሰል በትንሳኤ ጊዜ የማይበሰብሰ አካል መልበስ ነው።


https://t.me/Tsegish011
Join us
@gospel_talk
@gospel_talk
666 viewsŤŚ€Ĝ@, 10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ