Get Mystery Box with random crypto!

የሚሹህን አትተዋቸውም ዛሬ ጧት በማለዳ ከማር ወለላ ይልቅ የሚጣፍጠውን የእግዚአብሔር ቃል አንድ | (✍ GOSPEL TALK ✍)

የሚሹህን አትተዋቸውም

ዛሬ ጧት በማለዳ ከማር ወለላ ይልቅ የሚጣፍጠውን የእግዚአብሔር ቃል አንድ አራት ምዕራፎች አነበብኩ፡፡ መርጬ ካነበብኳቸው ምዕራፎች መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 9 ይገኝበታል፡፡ ይህንን ምዕራፍ አንዴ አነበብኩና ደገምኩት፡፡ “የውዴ ቃል በተራሮች ላይ ሲዘልል በኮረብቶችም ላይ ሲወረወር ይመጣል፡፡” (መኃ.2፥8) እንደሚል፣ ዓይኔ ከተተከለበት ፊት ለፊት ገጽ ላይ አንዲት ክፍል ተወርውራ ልቤን በሐሤት ሞላችው፡፡ እጅግ ደስ አለኝ፡፡ ወዲያው አምላኬንም ስለ ላከልኝ ቃል በኃይል አመሰገንሁት፡፡ ለእናንተም ይህንኑ ላካፍላችሁ ወደድሁ፡፡ ብትችሉ ሙሉውን ምዕራፍ አንቡት፤ ልቤን የነካው መልእክት ግን የሚከተለው ነው፡-

“ስምህን የሚያውቁ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፤
አቤቱ፣ አንተ የሚሹህን አትተዋቸውምና፡፡” (ቁ.10)

በተለይ በተለይ፣ እጅግ የነካኝ “የሚሹህን አትተዋቸውምና” የሚለው አገላለጽ ነው፡፡ ይህ ሃሳብ መንፈሳዊ መሻት ያለው ሰው የሚያገኘውን በረከት ነው የሚጠቁመው፡፡ ቃሉ “እኔ የሚወድዱኝን እወድዳለሁ፤ ተግተው የሚሹኝ ያገኙኛል” (ምሳ.8፥17) ይላልና!

በመንፈሳዊው ዓለም መሻት፣ መፈለግ፣ ቅናት፣ ግለት(passion)፣ ማሰስ(craving)፣ ጥማት፣ ራብ፣ ጉጉት፣ ናፍቆት ወዘተ እጅግ የሚያስፈልጉ ነገሮች ናቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች ወደ ፊት እንድንዘረጋና በጨመረ ሁኔታ ጌታን እንድንፈልገው እንደ ሞተር ነው የሚሆኑልን፡፡ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት እነዚህ ነገሮች በውስጡ የሚንተከተኩበት ሰው ትጉነት መገለጫው ነው፡፡ ያንን የሚወድደውን ነገር በሚገባ እስኪያገኘው ድረስ አይተኛም፡፡ እረፍት አይኖረውም፡፡ ያነባል፣ ይጸልያል፣ ይመሰክራል፣ ይጽፋል፣ ሃሳቡን ለሰዎች ያካፍላል፣ ወይ ከሰዎች ጋር ስለ ውዱ ያወራል እንጂ ሥራ ፈትቶ መቀመጥ የሚባል ነገር አይታሰብም፡፡

የእግዚአብሔር ቃል “እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው” (መዝ.105፥3) ይል የለ? እንዲህ ዓይነት ሰው የሚፈልገውን ነገር ገና በቅጡ ሳያገኘው ተባርኳል፡፡ እንዴት? “ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው” (ማቴ.5፥6) ከተባሉት ውስጥ ይመደባልና፡፡ ታዲያ ይህ ምስጉን ሳያሰልስ ትኩረቱን አምላኩ ላይ አድርጐ፣ ፊቱን እየፈለገ ሲተጋ፣ የእግዚአብሔርን ክብር ናፍቆ እየተጠባበቀ፣ በጸጋው ዙፋን ፊት ሲያሳልፍ ምንድነው ነው የሚሆንለት? ይጠግባላ! ምክንያቱም ከሚለውምነውና ከሚያስበው በላይ ሊያደርግ የሚቻለው አምላኩ በሕይወቱ ይገለጣል ፡፡

ለእርሱ በቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ኢየሱስ እስከ ትውልዶች ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን ፤ አሜን(ኤፌ.3፥ 20)፡፡

@nazrawi_tube