Get Mystery Box with random crypto!

#ቅድስና ቅድስና መምሰልና አለመምሰል ነው። መምሰል እግ/ርን ሲሆን አለመምሰል ደግሞ ዓለምን ነው | (✍ GOSPEL TALK ✍)

#ቅድስና

ቅድስና መምሰልና አለመምሰል ነው። መምሰል እግ/ርን ሲሆን አለመምሰል ደግሞ ዓለምን ነው።
ቅድስና ከዓለም ማለትም ከሥጋ ምኞት፣
ከዓይን አምሮትና ስለ ገንዘብ መመካት (1ዩሐ 2:15) በመለየት፣ የእየሱስ ክርስቶስን መልክ በመምሰል ማደግና የመለኮት ባሕርይ ተካፋይ መሆን ነው። (ዕብ 12:10)

ቤተ ክርስቲያን ሙሽራዋን እንደምትጠብቅ ሙሽሪት ያለ ነውር በቅድስና ልትኖር ተጠርታለች (ኤፌ 5:27)። ስለዚህ የእግ/ር ፍቃድ ለእኛ መቀደስን እንድንፈልግ እንድንቀደስና በመቀደስም እግ/ርን እንድንመስል ነው (1ጴጥ 1:15-16)
ቅድስና በዘሌዋውያን እንደተገለጸው መሥዋዕት በሚቀርብበት ሰዓት ወይም ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገባ ብቻ የመታጠብ ወይም የመንጻት ሕግ ሳይሆን፣ ቅድስና የኑሮ ዓይነት፣ የሕይወት ፍልስፍናና አኗኗር ነው።
ቅድስና ከሥጋዊ ምኞት መሸሽ ነው።
( ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤
ቲቶ 2 : 12-13)
እግ/ርም በልጁ የሚያምኑትን ሁሉ ልጁን እንዲመሰሉ አስቀድሞ ወስኗል( ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ ሮሜ 8 : 29)
ይህ ልጁን መምሰል የልጁን ባህርይ መያዝ ነው፣ ልጁን መምሰል በትንሳኤ ጊዜ የማይበሰብሰ አካል መልበስ ነው።


https://t.me/Tsegish011
Join us
@gospel_talk
@gospel_talk