Get Mystery Box with random crypto!

ድክም ብሎኝ ስለዋልኩ አልጋዬ ላይ እንደወደቁ እንቅልፍ ሸለብ አርጎኝ ሳላጠፋ ያደርኩት መብራት ጠዋ | (✍ GOSPEL TALK ✍)

ድክም ብሎኝ ስለዋልኩ አልጋዬ ላይ እንደወደቁ እንቅልፍ ሸለብ አርጎኝ ሳላጠፋ ያደርኩት መብራት ጠዋት ስነቃ አይኔን ሊያጠፋ የተዘጋጀ ይመስል አይኔን ጨለምለም አረገው እንደምንም አይኔን ገላለጥቁና ተነስቼ አልጋዬን ማነጣጠፍ ጀመረኩ በዚህ ሰዓት ነበር ጉዋደኛዬ ክንፍ ሲል እቤታችን ሳይነጋ የመጣው ክፍሌን አንኩአኩአና ገባ
'እንዴ በሰላም ነው ፓፒ '
'አው ቻ የሆነ ቦታ እንድትወስደኝ ፈልጌ ነበር አንተ ስለምታውቀው '
'እና ስልኬ ላይ አትደውልም ነበር' አልኩት ትንሽ እንደመቆታት እያረገኝ
'ይቅርታ ይደብርሃል ብዬ አላሰብኩም ነበር '
'እኔ እንኩአን አልደበረኝም እንዳትለፋ ብዬ እንጂ' ብቻ ስለቦታው ምናምን አወራንና ወጣን ::
ወደ ቦታው እየደረስን ስንመጣ ፓፒ ማይሆን ነገር ጀመረ ያገኘውን ሰው 'አባት /እናት /እህት /ወንድም እንትን የቱ ጋር እንደሆነ ታውቃለህ' እያለ መጠየቅ ሲጀምር በጣም ተናደድኩ
'ፓ ምንድነው ችግርህ በጠዋቱ መተህ ከቤት ያወጣኅኝ ሰው እየጠየክ ለመሄድ ነው?'
'ውይይይ ቻ በጣም ይቅርታ እየረሳሁት እኮ' ምናምን ብሎ አብላልቶ እንደምንም አስረሳኝ በሃሳቤ ሄድ አልኩና 'ለካ መንፈስ ቅዱስም እንደዚው ነው ሚሰማው እሱ ሊመራኝ ሲፈልግ በዓለም እየተመራው ወደ እውነት ሁሉ ሊነዳኝ ሲፈልግ እኔ ግን በዓለም በሰዎች, በጉአደኛ, በማህበረሰብ, እና በራሴ እየተመራው ነው የሳትኩት ወይኔ መንፈስ ቅዱስ ልያወራኝ ፈልጎ አላደምጥ እያልኩት ይሆን ብቻ ምሕረቱን ያብዛልን' እያልኩም ሳብሰለስል 'ቻ ወዴት ሄድክ? እ ቦታውን አልደረስንም እንዴ? 'አለኝ ፓፒ ጥያቄውን አከታትሎ ሲጠይቀኝ ከሃሳብ ባህሬ ወጣው ከዛም ዞር ዞር ብዬ ሳይ ለካ አልፈነው መተናል 'ውይይ ፓ አልፈነው ነው መጣን መሰለኝ ' አልኩት በጥፋቴ እንደማፈር ነገር እያረገኝ 'ለዚህ እኮ ነው ሰው ስጠይቅ የነበረው አለ' ለቅድሙ ጥፋት ማስተባበያ ያገኘ ይመስል ፈገግ እያለ ብቻ ወደ ኅላ ተመልሰን ደረስን ያሰማልንብንበት::

የእውነት መንፈስ ቅዱስ ሊመራን እየዳዳ እኛ በራሳችን መመራት አይሁንብን
fisher
@gospel_talk join our channel