Get Mystery Box with random crypto!

የስንኝ ቋጠሮ

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmv — የስንኝ ቋጠሮ
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmv — የስንኝ ቋጠሮ
የሰርጥ አድራሻ: @gitmv
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.02K
የሰርጥ መግለጫ

የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው።
ግጥሞችን ለመላክ @Abebekasu @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-18 12:54:20 የቀድሞው ህጋችን እንደተጠበቀ ነው።ቅድሚያ 60 ላይክ ለሚደርስ ተወዳዳሪ የ 25 ብር ካርድ፣ሁለተኛ 15 ብር እንዲሁም ለሶስተኛ 10 ብር ካርድ የምንሸልም ይሆናል።
ውድድሩን ምሽት 3:00 እንጀምራለን።እስከ 2 ሰዓት ድረስ ግጥሞቻችሁን ላኩልን።
@gitmv
430 views09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 08:52:05 ምሽት ላይ ለሚኖረን የግጥም ውድድር ግጥሞቻችሁን @mogea፣@Abebekasu ላኩልን።
ክረምቱ ስንኞቻችሁን ይሻል።በክረምት ያላችሁን የትዝታ፣የናፍቆት፣የፍቅር፣የልጅነት ስሜቶቻችሁን አጋሩን።
ሌሎች ወዳጆቻችሁንም ወደ ቻናሉ ጋብዙ።
@gitmv
456 views05:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 22:53:07 ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች የግጥም ውድድር ሀሙስ ምሽት ለማሰናዳት አስበናል።ስለዚህም ለዛ የሚሆን ግጥም ብትልኩልን እንደምንቀበል ለማሳወቅ እንወዳለን።
1.የግጥሙ ሀሳብ በክረምት ውስጥ ስለሚያልፍ ጊዜ የሚያትቱ ስንኞች ይሆኑ ዘንድ እንሻለን።
እስኪ ክረምትን በስንኞቻችሁ ግለፁልን።
ምናልባት "ክረምት እና ናፍቆት"፣"ክረምት እና ልጅነት"፣"ክረምት እና ትዝታ"፣"ክረምት እና ፍቅር" እና መሰል የግጥም ሀሳቦችን የያዙ ስንኞችን @mogea እና @Abebekasu ላይ ላኩልን።
846 views19:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 07:23:17 *አትምጪ*
አለመምጣትሽን ልቤ ይከጅለዋል
ጠብቄሽ መቅረትሽን ውስጤ ይሽተዋል
የመጣሽ እንደሆን 'መሄድሽ ነው' እያልኩ ሰዓቱን እያየሁ
ከመቅረትሽ ይባስ በሃሳብ እዋኛለሁ
ናፍቆት ያጎበጠው፤ድካም የተጫነው ልብ እና አካሌን
መምጣትሽ አይደለም እቅፍሽም እንዲሁ መዳኛ 'ሚሆነው
በዛው መቅረትሽ ነው ከደዌ 'ሚያርቀው።
Ab
17/11/2014
918 views04:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 22:56:10 ሆያ ሆዬ

ድቅን አለ ፊቴ ሳስበው በድንገት፣
ሆያ ሆዬ ስንል ያኔ በልጅነት፡፡
የሙልሙሉ ዳቦ የኩበቱ ሽታ፣
መቼም አይረሳም የቡሄ ትዝታ፡፡
ሆያ ሆዬ ሆ ሆያ ሆዬ፣
ሙልሙሊቷን ስጡኝ እባኮ ጌታዬ፡፡
እዛ ማዶ ሆ አንድ ስንደዶ፣
እዚ ማዶ ሆ አንድ ስንደዶ፣
የዚ ቤት ጌታ ጥርሰ በረዶ፣
"እንለው ነበረ"
ጥርሱ ግን ወላልቆ ቢሆንም ባዶ፡፡
ድቅን አለ ፊቴ ሳስበው በድንገት፣
ጆሮዬን ተሠማው የጅራፉ ጩኸት፣
ተሠማኝ ሙቀቱ የችቦውም እሳት፡፡
ሆያ ሆዬ ሆ ሆያ ሆዬ፣
ሙልሙሊቷን ስጡኝ እባኮ ጌታዬ፡
እዛ ማዶ ሆ አንድ እረኛ፣
እዚ ማዶ ሆ አንድ እረኛ፣
የዚ ቤት ጌታ የኢትዮጵያ አርበኛ፣
" እንለው ነበረ"
ለራሱም ቢያስፈልግ ጠባቂ ዘበኛ፡፡
ዳቦውም ይበላል ችቦው ይለኮሳል፣
ሆያ ሆዬ ተብሎ ቡሄ ይከበራል፡፡
እጅጉን ደነቀኝ ገረመኝ ሳስበው፣
ሆያ ሆዬ ማለት ራሡ ጥበብ ነው፡፡

Afe.Z.eth @gitmv
1.3K views19:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 20:47:03 የጥቅምት መስክ ነኝ !!
(በእውቀቱ ስዩም)

ሰው ለሰው ይፈርዳል
ልብን ዘልቆ ሳያይ
ላልቃሽ እያዘነ
በፈካ ገፅ ውስጥ ያደፈጠን ስቃይ
-ማነው የመዘነ?
የይስሙላም ይሁን: ከልብ ያለቀሰ
አያጣም አይዞህ ባይ
ካንጀት ይሁን ካንገት : እንባ ላፈሰሰ
አይጠፋም ከምንገድ : መሀረብ አቀባይ
ይብላኝ ላሳሳች ፊት: አፅናኝ ለማይጋብዝ
አንዳንድ ሀዘን አለ
ከላይ ተሰውሮ : ልብ የሚበዘብዝ
የጥቅምት ብሩህ መስክ: አደይ የለበሰ
ስንቱን ጉድ አዝሎታል: ስሩ ከተማሰ!!
የጥቅምት መስክ ነኝ : አደይ ያደመቀው
ፈገግታ ቢውጠው: ዘበት ቢደብቀው
የኔን ብቻ ህመም: እኔው ነኝ የማውቀው::
(ተከፍተው የተከፉ ለማይመስሉ)
1.3K views17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 09:01:35 *የማይድን...*
ምን ብንታገል ከሆድ የማናወጣው
በጊዜ ሂደት እንርሳው ብንል የማንረሳው
ስንት ህመም አለን
ሰርክ የሚያደማን
'እህህ' ብለን የማይወጣልን
በሚመሽ እድሜ የማይመሽልን
እልፍ ህመም አለን
ከቀን እስከሌት ከዘመን ዘመን
ከጉያችን ስር 'ሚበረታብን።
Ab
07/11/2014
1.7K views06:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 21:46:04 ልብህ ነው
እግርማ ታዛዢ ነዉ..ከላከዉ ሚደርስዉ
እግርህን ላሰርዉ.....ልብህን ጠይቀዉ
እንዳደርስ ላርገህ...... ተራራውን መስሎ
ሳትይዝ ያሳጣህ........ በፍራት ጠቅልሎ
le comment @Amen122119 @gitmv
2.0K views18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 21:40:21 አመሏን አውቃለሁ ሰው አልምዳ አታውቅም
ተረተረት እጂ ሀሳብ ህልም የላትም
ስለወደፊቷ ትንሽ ብትረዳ፣
ተስፋ ቢኖራትም
አላሚዋን ጥላ ህልመኛዋን ጥላ ፣
የትም አትሄድም @gitmv
@hashuya
1.8K views18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 21:07:10 ሆነ ሰበር ዜና
ፈጣሪ ፈልጎት : ዛፉማ ሲፈጠር
ሰው ሊጠቀምበት : ለግልጋሎት ነበር
የሰውን ሞት ረሳን : ዛሬ ያ ቀረና
ዛፍን መትከልና መቁረጥ : ሆነ ሰበር ዜና
@gitimv
1.6K views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ